መንግስት ፍትሃዊ የናሙና ክፍሎች

መንግስት ፍትሃዊ. በሆነ መንገድ ትምህርትን ለሁሉም ዜጎች ለማዳረስ ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት መረጃ ሥርዓት (EMIS) እንደሚያመለክተው በ1999 የመጀመሪያ ደረጃ የትም/ እድል ያገኙት ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ብዛት 33,300 የነበረ ሲሆን ይህ ቁጥር በ2007 ዓም 71,007 ደርሷል፡፡ በእነዚህ አመታት አንጻራዊ የቁጥር መጨመር ቢታይም ልዩ ፍላጎት ያላቸው በተለይም የአካል ጉዳተኛ ዜጎች የትምህርት ተደራሽነት አሁንም በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ ለአብነት ያህል ለመጥቀስ በ2007 ዓም በመጀመሪያ ደረጃ የትምህርት እድል ማግኘት ያለባቸው አካል ጉዳተኛ ህጻናት ብዛት ወደ 1.86 ሚሊዮን የሚገመት ሲሆን በትምህርት ገበታ ላይ የነበሩት ግን 71,007 (3.8%) ብቻ ናቸው፡፡ይህም ሁኔታ በአጠቃላይ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች የትምህርት አገልግሎቱ ተጠቃሚ አለመሆናቸውን ያመለክታል፡፡ 1.