ርዕሶች የናሙና ክፍሎች

ርዕሶች. የግጭት ዓይነቶች • የግጭት መንስኤዎች • ግጭት መከላከል • የውስጥ ግጭት መፍትሄ አሰጣጥ ሂደት • የውጭ ግጭት መፍትሄ አሰጣጥ ሂደት ስልልጠናው የሚያካትታቸው፡- የሚመለከታቸው አጋር አካላት ባለሙያዎች፣ የስልጠና መሳሪያዎች፡- ፊሊፐ ቻርት እና ማኑዋል፣ ስልጠናው የሚወስደው ጊዜ፡- 1፡30 /አንድ ሰዓት ተኩል/፣ 2.3.1 የግጭት ዓይነቶች‌ በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር የሚከተሉት ሁለት የግጭት ዓይነቶች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ • በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ውስጥ ያለ አለመግባባት /የውስጣዊ ግጭት/ እና • በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር እና በመንግስት አካላት ወይም ከሌሎች ድርጅቶች ጋር የሚፈጠር አለመግባባት /የውጫዊ ግጭት/ ናቸው፡፡ 2.3.2 የግጭት መንስኤዎች‌ ግጭት ሲባል ሁሉም የግጭት ዓይነቶች ማለትም በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ከመስኖ አውታሩ አሰራርና ጥገና /O&M/፣ ከአስተዳደርና ከገንዘብ አመራር በሚመለከት በመስኖ ልማቱ የአገልግሎት ክልል ያሉ ተጠቃሚዎች እርስ በእርሳቸው ወይም የውሃ ተጠቃሚ ቡድኖች እና በማኅበሩ፣ ወይም በማኅበሩና ከማኅበሩ ውጭ ካሉ ግለሰቦች ወይም ተቋማት ያሉ ግጭቶችን ያጠቃልላል፡፡ ? የስልጠናውን ተሳታፊዎች በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ሊከሰቱ የሚችሉ ውስጣዊና ውጫዊ አለመግባባቶች/የግጭት መንስኤዎች ምን ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ጥያቄ በመጠየቅ ሁሉም ተሳታፊ ያለገደብ ሃሳብ እንዲሰጥበት አድርግ፡፡ ተሳታፊዎች የሚሰጡትን መልስ በፊሊፕ ቻርት ወይም ነጭ ሰሌዳ ላይ ጻፍ፡፡ 2.3.2.1 ውጣዊ ግጭት‌ በአንድ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማህበር የውስጥ ግጭት መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ምክንያቶች፣ • የመስኖ ውሃ እኩል አለማከፋፈልና የውሃ ስርቆት፣ • የመስኖ ውሃ ተጠቃሚ ግለሰቦች ከማኅበሩ ፈቃድ ውጭ የመስኖ ውሃ መቆጣጠሪያዎችን መክፈት፣ • የመስኖ አሰራርና ጥገና ባለሙያዎች /O&M staff/ በመስኖ አውታሩ አሰራር ላይ ዝቅተኛ አፈጻፀም ሲኖር፣ • በመስኖ አውታሩና ቦዮች በቂ ጥገና አለመኖር፣ • በስራ አመራር ኮሚቴ፣ በቁጥጥር ኮሚቴ እና/ወይም ሌሎች ንኡሳን ኮሚቴዎች ምርጫ፣ • የመስኖ ውሃ አገልግሎት ክፍያ ዘግይቶ መክፈልና ምንም አለመክፈል፣ • የማኅበሩን ገንዘብና ንብረት አላግባብ ጥቅም ላይ ማዋል፣ • የማኅበሩን ህጎች እና ደንቦች የተወሰኑ ቡድኖችን ሊጠቅም በሚችል መንገድ መጠቀም /የመስኖ ውሃ ስርጭትን በሚመለከት/ እና • የንብረት መውደም ማለትም በማሳ ላይ ያለ ሰብል፣ መሬትና ቤቶች የጥገና ስራ በሚሰራበት ወቅት ወይም በአሰራር ችግር በጎርፍ መጎዳት፣ 2.3.2.2 ውጫዊ ግጭት‌ በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበርና ከማኅበሩ ውጭ ባሉ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች መካከል ውጫዊ ግጭቶች ወይም አለመግባባቶች በሚከተሉት ምክንያቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ • በማኅበሩና በሚመለከታቸው ተቋማት መካከል በመስኖ ልማቱ እና በግብዓት አቅርቦት በሚመለከት፣ • በማኅበሩ እና በወረዳ ውሃ ሀብት ተቆጣጣሪ አካል መካከል በመስኖ አውታሩ ስራና ጥገና ጋር በተያያዘ፣ • በማኅበሩ እና በተቆጣጣሪው አካል መካከል በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር አጠቃላይ አሰራር በተለይም ዓመታዊ በጀትና የሂሳብ መግለጫዎች ሲፀድቁ፣ እና • ተመሳሳይ የመስኖ ወንዝ በሚጠቀሙ በሁለት የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማህበራት መካከል፣ በተለይ አንዱ የውጭ ግጭት መነሻ ምክንያት በተፋሰሱ ውስጥ በላይኛውና በታችኛው አካባቢ ያሉ ተጠቃሚዎች • በወንዙ የታችኛው አካባቢ ያለ ማኅበርና በተፋሰሱ በላይኛው አካበቢ ያሉ ተጠቃሚዎች በመስኖ ውሃ ጠለፋው /divertion/ እና ሌሎች የውሃ ግንባታ ስራዎች፣ እና/ወይም • በታችኛው የወንዙ ተፋሰስ ያሉ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበርና እና በመንግስት መካከል በላይኛው ተፋሰስ ግድብ ሲሰራ እና/ወይም የመስኖ አውታር ሲገነባ ግጭቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ 2.3.3 ግጭት መከላከል‌ ? የስልጠናውን ተሳታፊዎች በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ከላይ የተዘረዘሩትን ግጭቶች እንዴት መከላከል ይቻላል የሚል ጥያቄ በመጠየቅ ሁሉም ተሳታፊ ያለገደብ ሃሳብ እንዲሰጡት ወይም በቡድን ተወያይተው ሀሳብ እንዲያቀርቡ አድርግ፡፡ ተሳታፊዎች የሚሰጡትን መልስ በፊሊፕ ቻርት ወይም ነጭ ሰሌዳ ላይ ጻፍ፣ ግጭትን መከላከል ለተከሰተ ግጭት መፍትሄ ከመሰጠት ይመረጣል፡፡ ሊከሰቱ የሚችሉ ግጭቶች ሊወገዱ የሚችሉት፤ • ሁሉም የመስኖ ተጠቃሚዎች በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ዓላማ፣ ስልጣንና ተግባራት እንዲሁም የራሳቸውን መብትና ግዴታቸውን ከተገነዘቡ፣ • አስተዳደረዊ ስራዎቸን ለመስራት፣ የፋይናንስና የቴክኒክ ስራዎቸን በውጤታማና በቅል...