ሰብአዊ መብት ቅሬታ አቀራረብ እና ስነስርአት መመሪያን መከለስ፣ አቅም ግንባታ ተግባራትን ማከናወን (የህፃናት፣ ስነፆታና አካልጉዳተኝነት አካታችነትን ጨምሮ) የናሙና ክፍሎች

ሰብአዊ መብት ቅሬታ አቀራረብ እና ስነስርአት መመሪያን መከለስ፣ አቅም ግንባታ ተግባራትን ማከናወን (የህፃናት፣ ስነፆታና አካልጉዳተኝነት አካታችነትን ጨምሮ). ✓ የሰብአዊ መብቶች ቅሬታ አቀራረብ እና ሥነ ሥርዓት መመሪያን የህፃናት፣ ስነፆታና አካልጉዳተኝነት አካታችነትን ባረጋገጠ መልኩ ተዘጋጅቶ የተጠናቀቀ ሲሆን በዚህም መሰረት በሰነዱ ላይ ከዋናው መስሪያ ቤት እና ከ ፅ/ቤቶች ከተውጣጡ የምርመራ ባለሙያዎች ግብዓት ለመሰብሰብ የ2 ቀናት ውይይት ተደርጎ አማካሪ ባለሙያዎች መመሪያውን አጠናቀው የመጨረሻውን ረቂቅ አስረክበዋል። በ3ኛው ሩብ አመት ከዋናው መስሪያ ቤት እና ከ ፅ/ቤቶች ለተውጣጡ የምርመራ ባለሙያዎች በመመሪያው ላይ ስልጠና ለመስጠት ተችሏል፡፡ የቅሬታ አቀራረብ መመሪያው በኮሚሽኑ በመበልጸግ ላይ ከሚገኘው የኤሌክትሮኒክ የአቤቱታ ቅበላ ስርዓት ጋር የተናበበ መሆን እንዲችል በኮሚሽነሮች ጉባኤ ፀድቆ ወደሥራ የሚገባበት ጊዜ በበጀት ዓመቱ የመጨረሻ ሩብ ዓመት ላይ እንዲሆን ተደርጓል። የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በሚመለከት የሚቀርቡ ቅሬታዎችን መቀበል፣ በራስ ተነሳሽነት መመርመር (ማማከር፣ ማስማማት ጉዳዩን ወደ ሌላ አካል መምራት እና ጉዳዩን መመርመር) ✓ ኮሚሽኑ ሰብአዊ መብቶችን የሚመለከቱ አቤቱታዎችን ተቀብሎ አስተናግዷል፡፡ በአጠቃላይ ኮሚሽኑ ባለፉት 11 ወራት በጠቅላላ 1593 አቤቱታዎችን የተቀበለ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 1130 ሚሆኑት በኮሚሽኑ ስልጣን ስር የማይወድቁ በመሆናቸው በምክር እና ወደሚመለከታቸው ተቋማት በመሸኘት የተቋጩ ሲሆን 463 የሚሆኑት ደግሞ የመጀመሪያ ደረጃ መፍትሔ የተሰጣቸው፣ በምርመራ ሂደት ላይ ያሉ፣ ተመርምረው ምክረ ሀሳብ የተሰጠባቸው እና በማስማማት የተፈቱትን ያጠቃልላሉ፡፡ ✓ ከዚህ በተጨማሪ በኮሚሽኑ የነፃ የስልክ መስመር በሪፖርት ወቅቱ 176 ጥሪዎች የተስተናገዱ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ጥቆማ እና አቤቱታ በማቅረብ ኮሚሽኑ ምክር የሰጠባቸው እና ለክትትልና ምርመራ ግብዓት የተወሰደባቸው ይገኙባቸዋል። ✓ በጥቅምት ወር 2014 ዓ.ም. መጨረሻ አካባቢ በታወጀው የጦርነት ጊዜ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት በእስር የቆዩና በእስር ለቆዩበት ጊዜ የፖሊስ ማስረጃ ለማቅረብ ባለመቻላቸው ወደ ስራ እና ትምህርታቸው ለመመለስ ሳይችሉ የቆዩ ግለሰቦች ወደ ስራ እና ትምህርታቸው እንዲመለሱ ምክረ-ሀሳብ በመስጠት የክትትል ስራ የተከናወነ ሲሆን በዚህም ለኮሚሽኑ ቅሬታቸውን ካቀረቡ 10 ሰዎች መካከል 8 ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ተችሏል፡፡