በእቅድ ሳይካተቱ የተከናወኑ ተግባራት የናሙና ክፍሎች

በእቅድ ሳይካተቱ የተከናወኑ ተግባራት. በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ጥያቄ መሰረት 'በኢትዮጵያ የአስተዳደር፣ የሰላም እና የጸጥታ ጥናት” ለማከናወን በተዘጋጁ የጥናት መሳሪያዎች ዙሪያ ተጨባጭ አስተያየቶችና ምክረ ሃሳቦች ተሰጥቷል። • የኢፌዲሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር ለኮሚሽኑ ባቀረበው ጥሪ መሰረት አሳታፊና የተቀናጀ የመሬት አጠቃቀም እቅድና ልማት አውደ ጥናት ላይ በመሳተፍ ሰብአዊ መብትን መሰረት ባደረገ አቀራረብ (human right based approach) ዙሪያ ምክረ ሃሳቦች ተሰጥቷል:: • በአቻ ለአቻ ግምገማ (Universal Periodic Review) ወቅት በተሰጡት ምክረ ሀሳቦች (Recommendation) ላይ ለስርጭት እና ክትትል እንዲውል በተዘጋጀው የአማርኛ ቅጅ ላይ አስተያየት ተሰጥቷል፡፡ • በብሄራዊ የፍልሰተኞች ፖሊሲ (National Migration Policy) በተመለከተ የተዘጋጀው ሰነድ በአጠቃላይ ከሰብአዊ መብቶች ጋር የማይቃረንና አካታች መሆኑን ለመገምገም ፤ እንዲሁም የፍልሰተኞችን እና ቤተሰቦቻቸው ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ መብቶችን በሚመለከቱ ጉዳዮች በተዘጋጀው ሰነድ ላይም ሙያዊ አስተያየት እና ምክረ ሀሳብ ተሰጥቷል፡፡ • የአፍሪካ የሰብአዊ መብቶች ተቋማት ጥምረት የአፍሪካ አህጉር ነጻ የንግድ ቀጠና ማዕቀፍ ውስጥ ሰብአዊ መብቶች ማካተትን በሚመለከት ለሚያካሂደው ጥናቱ ግብአት ተሰጥቷል።