አስተዳደር /Governance or Social management/ የአባላትን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ዓላማ ማዘጋጀት የናሙና ክፍሎች

አስተዳደር /Governance or Social management/ የአባላትን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ዓላማ ማዘጋጀት. ዓላማዎቹን ለማሳካት ስልቶችን መቀየስ መተዳዳሪ ደንብ መቅረጽ፣ ማሻሻል የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ መቅረጽና ማሻሻል የጠቅላላ ጉባኤ አባላትንና የአስተዳደር አካላትን መምረጥ ዓመተዊና ወቅታዊ የተግባር ዕቅዶችን ከማስፈፀሚያ በጀት ጋር ማጽደቅ ዓመታዊ የተግባራትንና የበጀት አጠቃቀም ሪፖርቶችን ማጽደቅ የማኅበሩን የውስጥ ፋይናንስ ኦዲት ማድረግ በማህበሩ አባላት መካከል ያሉ አለመግባባቶችን መፍታት በማህበሩ አባለት መካከል በተፈጠሩ ግጭቶች ላይ መሸምገል ከውጭ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ጋር የሚያዙ ውሎችን ማጽደቅ የማኅበሩን የአገልግሎት ክልል ለውጥ ማጽደቅ የማኅበሩን እንደገና የመደራጀት ወይም መፍረስ ማጽደቅ ክፍል /Category ተግባራት አሰራርና ጥገና /Operation & maintenance/ የመስኖ አምታሮችንና መሳሪያዎችን በተከታታይነት በቋሚነት ቁጥጥር ማድረግ ዓመታዊና ወቅታዊ የመስኖ አምታርና መሳሪያዎች ጥገና የተግባር ዕቅድ ማዘጋጀት ለጥገና የሚውሉ የግንባታና መለዋወጫ መሰሪያዎች መቅረባቸውን ማረጋገጥ ጥቃቅን፣ ወቅታዊና የድንገተኛ ጥገና ስራዎችን ማካሄድ የጥገና ስራዎችን ክትትል ማድረግ እንደ አስፈላጊነቱ ስርነቀል ጥገና ወይም ያረጁ መሳሪያዎችን የመተካት አመታዊ/ወቅታዊ የውሃ ስርጨት ዕቅድ ማዘጋጀት አመታዊ/ወቅታዊ የውሃ ስርጭት ዕቅድ አተገባበር መከታተል የውሃ አጠቃቀሙን መለካትና መከታተል ዓመታዊ/ወቅታዊ የስራ ሪፖርቶችን ማዘጋጀት የአሰራሮችንና ጥገናን /O&M/ ተግባራት ለመከታተል አመላካቾችን /Indicators/ መለየትና መጠቀም በመስኖ አውታሩና መሳሪያዎች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎችን መለየትና ችግሮችን መከላከል/ማስወገድ በአፈር መሸርሸርና ጨዋማነት ሊደርስ የሚችለውን ችግር መለየትና መከላከል/ማስወገድ አባላትን በመስኖ አጠቃቀም ስልቶች ማሰልጠን ክፍል /Category ተግባራት ሥሥ ሥሥሥሥ /Management/‌ የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብና የአሰራር ህጎች ተግባራዊ እንዲሆኑ ማድረግ ዓመታዊ/ወቅታዊ በጀትና የመስኖ ውሃ አገልግሎት ክፍያ መጠን ማዘጋጀት በመጋዘን ያሉ ዕቃዎችን፣ መሳሪያዎችንና መለዋወጫ ዕቃዎችን በየጊዜው ቆጠራ ማካሄድ፣ የወጪና ገቢ ሂሳቦችን መመዝገብ፣ የመስኖ ውሃ አገልግሎት ክፍያ ማሰባሰብ፣ ጊዜ ባሳለፉ ወይም ባልከፈሉ አባላት እርምጃ መውሰድ፣ ቅጥር ሰራተኞች መቅጠር፣ አፈጻፀማቸውን መከታተልና ክፍያ መክፈል ከውጭ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ጋር የተያዙ ውሎች አፈጻፀም መከታተል በማህበሩ ውስጥ መልካም ግንኙነት እንዲኖር ማድረግ የማኅበሩን ሰነዶች መጠበቅ ሌሎች በጠቅላላ ጉባኤ ወይም በስራ አመራር ኮሚቴው የሚሰጡ ተግባራትን ማከናወን፣ 2.2 ውስጣዊና ውጫዊ ኮሙዩኒኬሽን /Internal and external communication/ ዓላማ በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራት አባላት መካከል፣ እንዲሁም በማኅበሩና በሌሎች ተቋማት እና ግለሰቦች መካከል ውጤታማ ግንኙነት መኖር ስላለው ጠቀሚታ የሰልጣኞችን ግንዛቤ ለማሳደግ፣ በዚህ ክፍል የሚተዩ ርዕሶች፣ • የኮሙኒኬሽን ዓይነቶች /types of communication/ • የኮሙኒኬሽን ዓላማዎች /purpose of communication/ • የኮሙኒኬሽን ጥራት /quality of communication/ • የኮሙኒኬሽን ስልቶች /means of communication/ ስልጠናው የሚያካትታቸው፡- የሚመለከታቸው አጋር አካላት ባለሙያዎች፣ የስልጠና መሳሪያዎች፡- ፊሊፐ ቻርት፣ ማኑዋል እና የክፍል/የቡድን ሥራ፣ ስልጠናው የሚወስደው ጊዜ፡- ሁለት ሰዓት፣ 2.2.1 የኮሙዩኒኬሽን ዓይነቶች /types of communication/‌ ? ሰልጣኞችን ኮሙዩኒኬሽን ምንድን ነው፣ በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ያሉ የኮሙዩኒኬሽን ዓይነቶች ምን ምን ናቸው? የሚል ጥያቄ ጠይቃቸው፡፡ በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራት ኮሙኒኬሽን ስንል ሁለት የኮሙኒኬሽን ዓይነቶችን ለያይተን ማየት ጠቃሚ ነው፡፡ • የውስጥ ኮሙዩኒኬሽን፡- በማኅበሩ ውስጥ በተለይም በአመራሩና በግለሰብ አባላት መካከል፣ በአባላትና በአባላት መካከል ያለው ግንኙነት ሲሆን፣ • ውጫዊ ኮሙዩኒኬሽን፡- በማኅበሩና በሌሎች ተቋማት እና ድርጅቶች መካከል ያለውን ግንኙነት የሚመለከት ሲሆን ማኅበሩ ከመንግስት ተቋማት፣ ከአካባቢው አስተዳደር አካላት፣ ከፋይናንስ ተቋማት እና/ወይም ከግል ካምፓኒዎች ጋር ያለውን ግንኙነት ያጠቃልላል፡፡ 2.2.2 የኮሙኒኬሽን ዋና ዓላማ‌ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራት ሥራቸውን ውጤታማ ሊያደርጉ የሚችሉት አብዛኛው የማኅበሩ አባላት በሁሉም የማኅበሩ አሰራሮች ግልጽ ሲሆኑና ሙሉ እምነት ሲኖ...