አውቶሜትድ ኤሌክትሮኒክ ኬዝ ማኔጅመንት ሲስተም መተግበር የናሙና ክፍሎች

አውቶሜትድ ኤሌክትሮኒክ ኬዝ ማኔጅመንት ሲስተም መተግበር. ✓ ኮሚሽኑ የሚሰራውን የአቤቱታ አቀባበል ስርዓት ለማዘመን የሚረዳ አውቶሜትድ ኤሌክትሮኒክ ኬዝ ማኔጅመንት ሲስተም ልማት እና ሙከራ ሥራ ተጠናቋል። ✓ ሲስተሙ ላይ ለሚሰሩ የኮሚሽኑ የክትትል እና ምርምራ ባለሙያዎች እና የተቋሙ ኃላፊዎች በሁለት ዙር ሥልጠናዎች ተሰጥተዋል። ✓ ከመጨረሻ ዙር የሙከራ እና ፍተሻ ሥራ በኋላ በኮንትራት ስምምነቱ ላይ በተመለከተው እና በታቀደለት መሰረት ከሰኔ 13 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ወደ ትግበራ ይገባል። ጥናት በማድረግ ቁልፍ ባለድርሻ አካላትን በመለየት ውጤታማ የጉዳይ አመራር (ሪፈራል) ሥርዓት መዘርጋት ✓ በሪፖርት ወቅቱ በዋናው መስሪያ ቤት ውጤታማ የጉዳይ አመራር ስራ መስራት ይቻል ዘንድ በአዲስ አበባ የሚገኙ 48 መንግስታዊ አካላት፣ ዲሞክራሲያዊ ተቋማት የጸጥታና ፍትህ አካላት እንዲሁም የህግ፣ ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ አገልግሎት የሚሰጡ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የመለየትና መገኛ አድራሻ እንደ ስልክ፣ ኢ- ሜይልና መሰል መረጃዎችን የማጠናቀር ስራ ተከናውኗል፡፡ ✓ በቀጣይ አዲስ በጀት ዓመት በሁሉም የክልሎች የሚገኙ የሪፈራል አጋር ሊሆኑ የሚችሉ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን የመለየት ሥራ ለማከወን የሚያስችሉ ዝግጅቶች ተደርገዋል። አሁን ባለው አሰራር ምንም እንኳ በአሰራር ስርዓት እና በመግባቢያ ሰነዶች ላይ የተመረኮዘ ባይሆንም ሁሉም ፅ/ቤቶች ባለድርሻ አካላትን በመለየት የጉዳይ ቅብብሎሽ (ሪፈራል) ተግባራትን አከናውነዋል። ለአብነትም ✓ በ2ተኛው ሩብ አመት የጅማ 8 አቤቱታዎችን ጉዳዩ ለሚመለከተው አካላት ማለትም፡- ለጂማ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት፣ ለጂማ ዩኒቨርሲቲ ነፃ የሕግ አገልግሎት ማዕከል እና ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት በመምራት መፍትሔ እንዲያገኙ ተደርጓል። የሀዋሳ ም 10 አቤቱታዎች ጉዳዩ የበለጠ ለሚመለከታቸው አካላት ፍትሕ ተቋማት እና እምባ ጠባቂ ተቋም መርተዋል። ✓ በ3ተኛው ሩብ አመት ለአብነትም የባህርዳር 22 አቤቱታዎች ወደ ሚመለከታቸው የፍትህ ተቋማት፣ ወደ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም እና ወደ ክልሉ መንግስት የምግብ ዋስትና ተቋም የላከ ሲሆን፣ ጋምቤላ 2 አቤቱታዎች ለህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም እና ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የጅማ 15 አቤቱታዎችን ለጂማ ዩኒቨርሲቲ ነፃ የህግ አገልግሎት ማዕከል፣ ለጅማ ዞን ፖሊስ መምሪያ፣ ለጅማ ከተማ አስተዳደር፣ ለማና ወረዳ ዓቃቤ ህግ ጽ/ቤት እና ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት፣ ሰመራ 1 አቤቱታ ለእንባ ጠባቂ ተቋም መምራት ተችሏል፡፡ ✓ በ4ተኛው ሩብ አመት በጅማ ጽ/ቤት በኩል 58 አቤቱታዎች አግባብነት ላላቸው ተቋማት ተልከዋል፤ የባህርዳር 16 አቤቱታዎች ወደ ሚመለከታቸው የፍትህ ተቋማት እና ወደ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የላከ ሲሆን፣ በጅግጅጋ ጽ/ቤት በኩል በአጠቃላይ በሪፖርቱ ወቅት 38 ጉዳዮች ለሚመለከታቸው መንግስታዊ ተቋማት በመምራት መፍትሔ እንዲያገኙ ጥረት ተደርጓል፡፡ በግኝቶች እና በምክረ ሀሳቦቹ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ለመወያያት የምክክር መድረኮችን ማዘጋጀት፣ የአፈፃፀም ክትትል ማድረግ ✓ በሪፖርት ወቅቱ ክትትል እና ምርመራዎችን ተከትሎ ምክረ ሃሳቦች እንዲተገበሩ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ከሚካሄደው ኢመደበኛ ግንኙነት በተጨማሪ መደበኛ ውይይት ተደርጓል። በዚህም መሰረት ከሴቶችና ሕጻናት መብቶች የስራ ክፍል በመተባበር በጅግጅጋ በወንጅል ጉዳይ የተጠረጠሩ ሕፃናትን አያያዝ በተመለከተ የዳሰሳ ጥናት ከዋናዉ መስሪያ ቤት ጋር በመሆን በጂግጂጋና ጎዴ የተደረገ ሲሆን እንዲሁም በጥናቱ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ለተጨማሪ መረጃ የባለሞያዎች የምክክር መድረክ ተካሂዷል። በተጨማሪም ፅ/ቤቱ በሶማሌ ክልል በሚገኙ 3 ዞኖች በፋፈም፣ ጀረር እና ሲቲ ዞኖች በሚገኙ 7 ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ በተደረገ የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ክትትል መሰረት የተጠርጣሪዎች የሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ በተመለከተ በታዩ ክፍተቶች ላይ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በመወያየት በታዩት የሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ ክፍተቶች ላይ የመፍትሄ እርምጃ ለመውሰድ እንዲችሉ ተደርጓል። በጅማ እና በሀዋሳ በተለይም በቁጥጥር ስር ከዋሉ ሰዎች መብቶች ጋር በተገናኘ መድረኮች ተዘጋጅተው ክትትል ከተደረገባቸው ማረሚያ ተቋማት እና ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር ምክክር ተደርጎ ችግሮቹን ለመቅረፍ ከስምምነት ተደርሷል። ክስተተቶችን መሠረት ያደረገ የአደጋ ወቅት የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ክትትል ማድረግና የክትትል ግኝቶችንና ምክረ ሃሳቦችን ማውጣት ✓ የአደጋ ጊዜ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች ላይ ክ...