ክፍተኛ ፍርድ ቤት የናሙና ክፍሎች

ክፍተኛ ፍርድ ቤት. ማንኛውም ውስጣዊ ግጭት ያጋጠመውና በተሰጠው የግጭት አወጋገድ ውሳኔ ያልተስማማ ግለሰብ ጉዳዩን ለከፍተኛ ፍርድ ቤት የማቅረብ መብት አለው፡፡ 🗐 ከስልጠናው በኋላ ስለ ግጭት አወጋገድና እና እርቅ ዋና ዋና ጉዳዮችን በቀላል አቀራረብ የሚያብራራ ማኑዋል ለሁሉም ሰልጣኞች መሰጠት አለበት፡፡ 2.4 የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ አዘገጃጀት /Formulation of internal rules & regulations/‌ ዓላማ፣ • በማኅበሩ የውስጥ የግጭት ምንጭ የሆኑ ጉዳዮችን ለመከላከል እንዲቻል እና ማኅበሩ ጤናማ ስራ እንዲሰራ ለማድረግ አስፈላጊውን የቅጣት እርምጃዎች በሚያካትት መልኩ በውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ማዘጋጀትና ተግባረዊ ማድረግ ስላለው ጠቀሜታ የሰልጣኞችን ግንዛቤ ለማሳደግ ነው፣ ርዕሶች፣ • የህግ ማዕቀፍ o የመሰኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማህበር መርሆዎች • የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ዓላማ • በውስጥ መተዳደሪያ ደንብ መካተት ያለባቸው ጉዳዮች o የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ የማጽደቅና የማሻሻል ሂደት • ውጤታማ የቅጣት እርምጃዎች /effective sanction/ o የቅጣት እርምጃ ቅድመ ሁኔታዎች/Conditions for effective sanction/ ስልልጠናው የሚያካትታቸው፡- የሚመለከታቸው አጋር አካላት ባለሙያዎች፣ የስልጠና መሳሪያዎች፡- ፊሊፕ ቻርት፣ ማኑዋል እና የተግባር መልመጃዎች ስልጠናው የሚወስደው ጊዜ፡- 1፡30 /አንድ ሰዓት ተኩል/፣ 2.4.1 የመሰኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማህበር መርሆዎች፣‌ ? የስልጠናውን ተሳታፊዎች የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር መርሆች ስንል ምን ማለት ነው? እነዚህ መርሆዎች ምን ምን ናቸው? በምትሰሩበት ወረዳና ቀበሌ እንዴት ልትገልጿቸውና ተግባራዊ ልታደርጓቸው ትችላላችሁ? የሚሉ ጥያቄዎችን ጠይቅ፡፡ በውስጥ መተዳደሪያ ደንቡ ርዕሶች ውስጥ የሚከተሉት የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር መርሆዎች መካተት አለባቸው፡፡