ዓመታዊ የመስኖ አውታር ጥገና የናሙና ክፍሎች

ዓመታዊ የመስኖ አውታር ጥገና. በአመታዊ የጥገና ቁጥጥር ስራ መሳተፍ፣ • ዓመታዊ የጥገና እና የበጀት እቅድ አዘገጃጀት ላይ ድጋፍ ማድረግ፣ • ማንኛውንም የዕድሳትና አነስተኛ ጥገና ስራዎች በፀደቀው የጥገና ዕቅድ መሰረት ከመስኖ ስራ ወቅት በፊት እንዲሰሩ ዝግጅት ማድረግ፣ማስተባበር እና መቆጣጠር፣ • የዕድሳትና የጥገና ስራዎችን ለመስራት የጉልበት ስራ የሚሰሩ አባላትን ወይም ተቀጣሪ የቀን ሰራተኞችን እና ሙያ ያላቸው የሰለጠኑ የጉልበት ሰራተኞቸን በማነሳሳት ድጋፍ ማድረግ፣ • የእድሳትና ጥገና ስራ ለመስራት አስፈላጊ የሆኑ የእጅ መሳሪያዎችን /ማለትም የርዝመት መኪያ/ሜትር፣ ገመድ፣ ባልዲ፣ መዶሻ፣ መሮ ወዘተ…/ እና ሌሎች መሳሪያወች/ የሲሚቶና አሸዋ ማደባለቂያ/ማቡኪያ/ የመሳሰሉትን የሚቀርቡበትንና በአጠቃቀማቸው የቁጥጥር ስራ በመስራት መደገፍ፣ የጉልበት ሰራተኛ ማንኛውንም ጥቃቅን የዕድሳት እና አነስተኛ የጥገና ስራዎች የመስኖ ስራ ከመጀመሩ አስቀድሞ በወቅቱ እንዲፈፀሙ ለማስተባበር ማኅበሩ በርካታ ቁጥር ያላቸው የቀን ሰራተኞች በየዓመቱ ከአንድ እስከ ሁለት ወር የቆይታ ጊዜ ሊቀጥር ይችላል፡፡ የቀን ሰራተኞች ተግባራት የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል፡፡ • የመስኖ ቦዮችን ለማጽዳት /የሚፀዳ ካለ/ • በካናሉ ዙሪያ ያሉ ቁጥቋጦዎች እና ሳር ለማጽዳት /ካለ/ • የውሃ መቆጣጠሪዎችን ግሪስ እና ቀለም ለመቀባት /ካለ/ እና • ጥቃቅን የጥገና ስራዎች ለመስራት ለምሳሌ ስንጥቆችን በኮንክሪት መሙላት፣ እና/ወይም የጎርፍ መከላከያዎችን በጋቢዎን መስራት /ካለ/ የሂሳብ ሰራተኛ የገንዘብ አስተዳደሩን በሚመለከት በከፍተኛ ሁኔታ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ለማድረግ የማኅበሩ የገንዘብ አስተዳደር ውጤታማና ትክክለኛ በሆነ አሰራር መመራት አለበት፡፡ ማኅበሩ ለዚህ ተግባር ልምድ ያለው የማኅበሩን ገንዘብ ያዥ ሊያግዝ የሚችል ቢያንስ የሚከተሉትን ተግባራት ሊያከናውን የሚችል ሂሳብ ሰራተኛ መቅጠር አለበት፡፡ • የማኅበሩን ዓመታዊ በጀት ማዘጋጀት • በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች የሚከፈሉ የመስኖ ውሃ አገልግሎት እና ሌሎች ክፍያዎች ደረሰኝ ማዘጋጀት • የተሰበሰበ የመስኖ ውሃ አገልግሎት ክፍያ በመስኖ ውሃ አገልግሎት ክፍያ መዝገብ መመዝገብ • የማህበሩን ዓመታዊ የሂሳብ ሪፖርት ማዘጋጀት • በተጨማሪም ሂሳብ ሰራተኛው የሚከተሉት ኃላፊነቶች ሊኖሩት ይችላሉ • ማንኛውንም የሂሳብ መዛግብትና ሰነዶች መጠበቅ • የመስኖ ውሃ አገልግሎትና ሌሎች ክፍያዎች የሚከፈሉበትን ሁኔታ የማመቻቸት • በወቅቱ ክፍያ ያልከፈሉ ተጠቃሚዎችን ዝርዝር የማዘጋጀት • ወቅቱን አሳልፈው በሚከፍሉ ተጠቃሚዎች መክፈል የሚገባቸውን ቅጣት ጨምሮ ሂሳቡን መስራትና ክፍያውን መከታተል፣ • ማህበሩ ክፍያ ለፈፀመባቸው ማንኛውም ክፍያዎች ደረሰኞቸን ማሰራጨት • ወርሃዊ/የሩብ ዓመት ሪፖርት በማዘጋጀት ለስራ አመራር ኮሚቴው ማቅረብ እና • የማኅበሩን ተንቀሳቀሽና ተንቀሳቃሽ ያልሆኑ ንብረቶች ቆጠራ መከታተል/መያዝ የሂሳብ ሰራተኛው የመጀመሪያዎችን አራት ተግባራት ብቻ ለማከናወን ኃላፊነት ከተሰጠው በየዓመቱ ከ3 እስከ 4 ወራት ብቻ መቅጠር በቂ ሊሆን ይችላል፡፡ ማኅበሩ ማንኛውንም የፋይናስ ጉዳይ እንዲሰራ ከፈለገ ሙያ ያለው ሂሳብ ሰራተኛ ቢያንስ ከ6 እስከ 9 ወራት ቆይታ መቅጠር አለበት፡፡ 3.5.2 ፈጻሚ ቅጥር ሰራተኞችን እና የቀን ሰራተኛ የአቀጣጠርና የቁጥጥር ሂደት በዋናነት ፈጻሚ ቅጥር ሰራተኞችንና የቀን ሰተኞችን የመቅጠርና የማሰናበት እንዲሁም የቅጥሩን ሁኔታ ማለትም የደመወዙንና ማትጊዎችን የመወሰን የማኅበሩ ሊቀመንበር ኃላፊነት ነው፡፡‌ ፈጻሚ ቅጥር ሰራተኞችንና የቀን ሰራተኞችን የቅጥርና የቁጥጥር ተግባር ለማከናውን መከተል ያለብን ሂደቶች፣ • የማህበሩ ሊቀመንበር የቅጥር መነሻ ዕቅድ ማለትም ምን ያህል ሰራተኛ ሊቀጠር እንደሚገባና ስለ ቅጥሩ ሁኔታ/ ደመወዙን፣ ቅጥሩ ለምን ያህል ወራት እንደሆና ማበረታቻዎችን በሚመለከት በጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ወቅት ለጠቅላላ ጉባኤው ያቀርባል፣ • የጠቅላላ ጉባኤው የቀረበውን የፈጻሚ ቅጥር ሰራተኛና የቀን ሰራተኞች ረቂቅ የቅጥር ዕቅድ የቅጥሩን ሁኔታ ጨምሮ ማጽደቅ አለበት፣ • የማኅበሩ ጠቅላላ ጉባኤ በህጋዊ መንገድ የቅጥር ዕቅዱን ካፀደቀው በኋላ የማኅበሩ ሊቀመንበር የተማረ የሰው ሃይል በፀደቀው የስራ መደብ ላይ በግልጽና ተጠያቂነት ባለው ሁኔታ እንዲቀጠር ማድረግ አለበት፣ • የማኅበሩ ሊቀመንበር በፀደቀው የስራ መደብ ለመቅጠር የተመረጡትን ፈጻሚ ቅጥር ሰራተኛ አስመልክቶ ሪፖርት ለስራ አመራር ኮሚቴው በወርሃዊ ስብሰባ ወቀት ያቀርባል፣ • የስራ አመራር ኮሚቴም በተለያዩ...