የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች የናሙና ክፍሎች

የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች. በአስራ አንድ ወራት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-8 o በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን ሀገር አቀፍ የሕዝብ አቤቱታ የሚቀርብበት ብሄራዊ ምርመራ (National Inquiry) ለማካሄድ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተከናውነዋል። ለብሄራዊ ምርመራው የቴክኒክ ድጋፍ የሚያከናውን የአለም አቀፍ አማካሪ ቅጥር ተከናውኗል፡፡ ብሄራዊ ምርመራ (National Inquiry) የማስጀመሪያ ሃገራዊ የምክክር አውደ ጥናት የካቲት 10፤ 2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡ የፌዴራልና የክልል የህግ አስከባሪ አካላት ክፍተኛ አመራሮች፤ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አመራሮችና የሚዲያ ተወካዮች በአውደ ጥናቱ የተሳተፉ ሲሆን መጠይቆች በማዘጋጀት ለምርመራው ግብአት የሚሆኑ ሃሳቦች ለመሰብሰብ ተችሏል፡፡ ከተሳታፊዎች የተሰበሰበውን ግብአት በመተንተን የአውደ ጥናት ሪፖርት ተዘጋጅቷል፡፡ o የብሄራዊ ምርመራው ቅድመ ዝግጅት አካል የሆነ ስልጠና ሰኔ 3 ቀን 2014 ዓ.ም. በቴክኒክ አማካሪዋ ለስራ ክፍሉ ባለሙያዎች እና ለሌሎች የስራ ክፍሎች ተሰጥቷል፤ስልጠናው ስለ ብሄራዊ ምርመራ ምንነትና አካሄድ የባለሙያዎችን አቅም ለማሳደግ ያለመ ነው፡፡ የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች የስራ ክፍል በዋናው መ/ቤትና በክልል ቅርንጫፎች የሚሰሩ ባለሙያዎች በስልጠናው የተሳተፉ ሲሆን በብሄራዊ ምርመራ የትኩረት አቅጣጫዎች እና ሂደቶች ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ተችሏል፡፡ o በሀዋሳና አዳማ የብሄራዊ ምርመራ ስብሰባዎች ለማከናወን የዝግጅት ስራዎች ተሰርተዋል፤የብሄራዊ ምርመራውን የሚመራ ሴክሬታሪያት ተቋቁሟል፡፡ ሴክሬታሪያቱ የብሄራዊ ምርመራ ኮሚሽነሮችን፤ ሰራተኞች፤የአስተዳደርና ሎጂስቲክስ ቡድን፤የህዝብ ግንኙነት ቡድን፤ የምርመራና ምርምር ቡድን፤ የሚዲያ አገናኝ ቡድን፤ የምስክሮች ደህንነት ጥበቃ ቡድን እና የውስጥ ክትትልና ግምገማ ቡድንን ያካተተ ነው፡፡ o ከብሄራዊ ምርመራው ቅድመ ዝግጅት ጋር በተያያዘ በዘፈቀደ እስራት ላይ ያተኮረ የዳሰሳ ጥናት በስራ ክፍሉ ባለሙያ ተዘጋጅቷል፡፤ o በሚዲያ አጠቃላይ ሁኔታ (የሚዲያ ነፃነት፣ ሃሳብን በነፃነት ከመግለፅ አንፃር) እና የመደራጀት መብቶችን እንዲሁም ነጻነታቸውን የተነፈጉ ሰዎች ፍትህ የማግኘት መብት አስመልክቶ ጥናቶች ለማከናወን ቢጋር የተዘጋጀ ሲሆን አማካሪ ለመቅጠር የዝግጅት ስራዎች ተከናውነዋል፡፡ የአማካሪ ቅጥር ማስታወቂያው በ USAID Feteh-Justice Activity በኩል ወጥቶ የቅጥር ሂደቱ ተጀምሯል፡፡ o የሰብአዊ መብት ጥሰት ለደረሰባቸው ተጐጂዎች ሊደረግ ስለሚችል ድጋፍ የተመለከተ የፅንሰ ሃሳብ ጥናት ተዘጋጅቷል፤ ጥናቱ ከዋና ኮሚሽነር ፅ/ቤትና ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች የስራ ክፍል ጋር የሚሰራ በመሆኑ ጥናቱን ለማጠናቀቅ በስራ ጫና ምክንያት ወደሚቀጥለው ዓመት ተላልፏል፡፡ o በሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች ላይ የሚሰሩ ቁልፍ ባለድርሻ አካላትን ልየታና ምክክሮች ተከናውኗል፡፡ የባለድርሻ አካላትን ልየታ ሰነድን ለማዳበር የልየታ ሰነዱን ለማዳበር ከፕሮግራምና አጋርነት የስራ ክፍል ጋር በመተባበር ቢጋር ተዘጋጅቷል፤ አማካሪ ድርጅት ተቀጥሮ የጅማሮ ሪፖርት (Inception report) ያቀረበ ሲሆን የስራ ክፍሉ ግብረ መልስ ከሰጠ በኋላ አማካሪው የዳት ማሰባሰብ ስራ እያከናወነ ነው፡፡ o ምርጫ ባልተካሄደባቸው ቦታዎች ከቅድመ ምርጫ እስከ ድህረ ምርጫ ጊዜ ክትትል ለማካሄድ 5 የክትትል ቡድኖች ተዋቅረው ስራቸውን ጨርሰው ረቂቅ የክትትል ሪፖርት ተዘጋጅቷል፡፡ እንዲሁም ረቂቅ የምርጫ ሪፖርት ተዘጋጅቷል፡፡ o ከክትትልና ምርመራ የስራ ክፍል ጋር በመተባበር ከትግራይ ግጭት ጋር በተያያዘ በአፋርና አማራ ክልሎች የተከሰቱ የመብት ጥሰቶች ምርመራ ለማካሄድ የ3 የምርመራ ቡድኖች ስልጠናና ስምሪት ተከናውኗል። ሪፖርቱም ይፋ ተደርጓል። የምርመራ ሪፖርቱ ይፋ መሆኑን ለማስተዋወቅ ጋዜጣዊ መግለጫ ተዘጋጅቷል፡፡ በኮሚሽኑና በስራ ክፍሉ ሃላፊዎች ስለምርመራው ግኝቶችና በግጭቱ ወቅት ስለተፈፀሙ የመብት ጥሰቶች ለሚዲያዎች ገለፃና ማብራሪያ በመስጠት ሪፖርቱን የማስተዋወቅ ስራ ተሰርቷል፡፡ o የሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች እና የዘላቂ ልማት ግቦች አፈጻጸም በተመለከተ የወቅታዊ ሁኔታ ሪፖርት ለማዘጋጀት ከተ.መ.ድ. ሰብአዊ መብቶች ድርጅት ጋር የቴክኒክ ድጋፍን የተመለከተ ምክክር ተካሂዷል እንዲሁም ቢጋር ተዘጋጅቷል፡፡ o የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸምን በተመለከተ የተያዙ ሰዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ እንዲሻሻል በተለያዩ ስፍራዎች ላይ ክትትል ተደርጓል፤ከሚመለከታቸው ባለድርሻዎች ጋር ምክክሮች ተካሂደዋል፤ እንዲሁም መ...