መግቢያ እና ዳራ - የፕሮጄክት መግለጫ የናሙና ክፍሎች

መግቢያ እና ዳራ - የፕሮጄክት መግለጫ. እስካሁን ምን ዓይነት የተጽእኖ ግምገማ ስራ እንደተሰራና ምን ዓይነት የሃገር በቀል ሕዝቦች ጉዳዮች እንደተለዩ የሚያሳይ መግለጫ፡፡ የመጨረሻ ESIA ከተዘጋጀ፣ ይኸው መቅረብ አለበት፡፡ የተሟላ ESIA ዝግጁ ካልሆነ፣ በጉዳዩ የተነኩ ማህበረሰቦችን ግልጽ መገለጫ፣ መተዳደሪያቸውንና ሁኔታዎቻቸውን በተመለከተ በቂ ዝርዝር መቅረብ ያለበት ሲሆን በሃገር በቀል ህዝቦች ላይ ጥገኛ የሆኑ የተፈጥሮ ሐብቶችን እንደዚሁም ሊያስከትሉ የሚችሏቸውን ተጽእኖዎች መግለጽና በቁጥር ማስቀመጥ ይገባል፡፡ የ IPP መለኪያዎች - በዚህ ውስጥ መካተት ያለባቸው የ IFC የአፈጻጸም መለኪያዎች 7 እና የመምሪያ ማስታወሻ 7፣ እንደዚሁም የአካባቢ ፖሊሲና ሕግ ናቸው፡፡ ቀደም ሲል የተገኘ ካልሆነ፣ የማነጻጸሪያ ነጥቦች በ IFC የአፈጻጸም መለኪያዎችና በአካባቢ መለኪያዎች መካከል ባለው ልዩነት ላይ የክፍተት ትንተና የማካሄድን አስፈላጊነት ያካትታል፡፡ ከመስፈርቶቹ ሁሉ ጥብቅ የሆነው በ IPP ላይ ተግባራዊ ይሆናል፡፡ CFM እና የጋራ አልሚው ፕሮጄክቱ ከ IFC የአፈጻጸም መለኪያ 7 ወይም የአካባቢ መለኪያዎች ባሻገር እንዲሄድ በሚጠይቁበት ወቅት፣ ይኸው በግልጽ መመልከት አለበት፡፡