ሰብአዊ መብቶች የናሙና ክፍሎች

ሰብአዊ መብቶች. ሰብአዊ መብቶች የሁሉም የድርድር ፍተሻ አንደ አካል ተደርጎ ይቆጠራል (በአባሪ 2 የተካተተውን ማረጋገጫ ዝርዝር ይመልከቱ) እና በእያንዳንዱ ፕሮጄክት መከናወን ያለባቸው አካባቢያዊ እና ማኅበራዊ ግምገማዎች ውስጥ መካተት አለበት። አንደ አጠቃላይ መርህ ሲኤፍኤም እና ሁሉም የሲአይኦ ኢንቨስትመንቶች በማናቸውም የሰዎች ቡድኖች ላይ በጾታቸው፣ በዕድሜ፣ በዘር፣ በአካል ጉዳት፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አቋም እና/ወይም ሌላ የግል ባሕሪ በመመርኮዝ እኩልነትን የሚያዛቡ ተጽእኖዎች የሚያሳድሩ ሁኔታዎችን ጨምሮ አካባቢያዊ እና ማኅበራዊ ተጻብዖዎችን ሊያስከትሉ የሚችሉ ማናቸውንም ለውጦች ከማድረግ ለመቆጠብ አስፈላጊውን ሁሉ እርምጃ ለመውሰድ፣ ለመገምገም፣ ለማስቀረት፣ ለመቀነስ ወይም እንዳይፈጠሩ ለማድረግ ቁርጠኛ አቋም አላቸው። ለሰብአዊ መብቶች መከበር የሚወሰዱ ማስተካከያ እርምጃዎች የፕሮጄክት ሠራተኞችን እና ንብረትን ለመጠበቅ ለእያንዳንዱ ፕሮጄክት በተዘጋጀው የኢ እና ኤስ የቁጥጥር ሥርዓት ላይ በተጨማሪ መካተት አለባቸው። እንዲህ ያሉት ማስተካከያ እርምጃዎች አግባብነት ባላቸው የሰብአዊ መብቶች መርሆዎች መሠረት የሚዘጋጅ እና ተፈጻሚ የሚሆን ይሆናል1 እንዲሁም ተጽእኖ በሚያሳርፍባቸው ማኅበረሰቦች ላይ ሊፈጠሩ የሚችሉ ስጋቶችን ለማስቀረት ወይም መጠኑን ለመቀነስ በሚያስችል መልኩ መዘጋጀት አለበት (ከዚህ በታች ያለውን ክፍል xii ይመልከቱ)።