ባለ ድርሻ አካላት የናሙና ክፍሎች

ባለ ድርሻ አካላት. የቅሬታ አፈታት ስርዓቱን በመጠቀም ማንኛውንም አስተያየት፣ ሃሳብ እና ቅሬታን ያቀርባሉ፡፡ በጉዳዩ የተነካ ወገን(ኖች) - በአዎንታዊም ሆነ በአሉታዊ መልኩ በ CFM ተግባራት የተነኩ ባለድርሻ አካላት፡፡ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ሊነኩ ይችላሉ፡፡ ተግባቦት - በ CFM እና በተነኩ ወይም በሚመለከታቸው ወገኖች መካከል የሚደረግ ውይይት፡፡ ተግባቦት ማለት መረጃ መለዋወጥ (መስጠትና መቀበል) ማለት ነው፡፡ ተግባቦት CFM የተግባራቱን ገጽታዎች፣ ስጋቶችና መልካም አጋጣሚዎች ለማስተላለፍና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት መረጃ፣ አሳሳቢ ጉዳዮች፣ ጥያቄዎችና ሃሳቦችን ለመቀበል ያስችለዋል፡፡ ማህበረሰብ አቀፍ ድርጅቶች (CBOs) - ለትርፍ ያልተቋቋመና መደበኛ ወይም ኢ-መደበኛ ሊሆን የሚችል የአካባቢ ማህረሰብ ወይም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የሚንቀሳቀሱት በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ወይም የተለያዩ ማህበረሰቦች በሚገኙበት አነስተኛ መልክዓ ምድራዊ ክልል ውስጥ ነው፡፡