ተጋላጭ ቡድኖች የናሙና ክፍሎች

ተጋላጭ ቡድኖች. ፕሮጄክቱ በሚተገበርበት አካባቢ የሚገኙና በተጋላጭነት ወይም በተጎጂነት ሁኔታቸው ምክንያት ከሌሎች የበለጠ የከፋ ተጽእኖ ሊደርስባቸው የሚችሉ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች፡፡ ይህ ተጋላጭነት በአንድ ግለሰብ ወይም ቡድን ዘር፣ ጾታ፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት፣ ፖለቲካዊ አስተያየት፣ ብሄራዊ ወይም ማህበራዊ ማንነት፣ ነብረት፣ ውልደት ወይም ሌላ ሁኔታ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ጾታዊ ማንነት፣ ብሔር፣ ባህል፣ ሕመም፣ አካላዊ ወይም አእምሯዊ ጉዳት፣ ድህነት ወይም ኢኮኖሚያዊ ጥቅም መነፈግና በልዩ ተፈጥሯዊ ሐብቶች ላይ የሚኖር ጥገኝነትን ጨምሮ ሌሎች ነጥቦችም ታሳቢ መደረግ አለባቸው፡፡