ኃላፊነቶች የናሙና ክፍሎች

ኃላፊነቶች. የቅሬታ አፈታት ስርዓቱ ውጤታማ ትግበራ የሚከተሉት የስራ ድርሻዎችና ኃላፊነቶች እንዲሟሉ ይጠይቃል፡ ሚና ኃላፊነት/ተጠያቂነት የ ESG ሥራ አስኪያጅ - ሁሉም ሠራተኞች በዚህ የአሰራር ሒደት ውስጥ የተቀመጡ አስፈላጊ ሁኔታዎችን መከተላቸውን ያረጋግጣል፡፡ - ለጥልቅ ምርመራና የእርምት እርምጃ በቂ ትኩረትና ወሳኝነት እንደተሰጠው ያረጋግጣል፡፡ - መካከለኛ ወይም ከፍተኛ ደረጃ ለተሰጣቸው ቅሬታዎች እና የቅሬታ አፈታት ኃላፊው ቅሬታውን በተቀበለ በ5 ቀናት ውስጥ መፍትሔ መጠቆም ካልቻለ በቅሬታ አፈታት ሒደት ውስጥ ይሳተፋል፡፡ የቅሬታ ተቀባይ - ቅሬታ ወይም አቤቱታ የሚቀበል ሰው - ቅሬታ ተቀባዩ ጊዜን በጠበቀ መንገድ (ቅሬታ በተቀበለ በ24 ሰዓት ውስጥ) ጉዳዩን ለቅሬታ አፈታት ኃላፊው የማሳወቅ ኃላፊነት አለበት፡፡