ነባር (ቀደምት ተወላጅ) ሕዝቦች የናሙና ክፍሎች

ነባር (ቀደምት ተወላጅ) ሕዝቦች. ሲኤፍኤም ነባር (ቀደምት ተወላጅ) የሆኑ ተጋላጭና ተጎጂ ሕዝቦች ሊኖሩ በሚችሉበት ቦታ ፕሮጀክቱ ተጽእኖ በሚያደርስባቸው ቦታዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ የሚገነዘብና ይህም ነባር ሕዝቦችን እንደሚያካትት ይገነዘባል። ስለዚህ በአይኤፍሲ ፒኤስ መሠረት ከስምሪት፤ ምክክር፤ መሬት የሚያገኙበት መንገድና የፕሮጀክቱ ተፈጥሯዊ አካባቢ ላይ ማለትም ለእቃዎችና አገልግሎቶች የሚጠበቅባቸው ላይ የሚደርሱ ተጽእኖዎችን በተመለከተ ተጨማሪ የመፍትሄ እርምጃዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የተለየ ትኩረት ይሰጣል። በዚህም መሠረት ሁሉም ሊተገበሩ የሚችሉ ኢንቨስትመንቶች በተቻለ መጠን ቀደም ብሎ ነባር ሕዝቦች መኖራቸውን ማረጋገጥና መኖራቸው ከተረጋገጠ በአይኤፍሲ ፒኤስ7 ሥር የተቀመጡትን መስፈርቶችና ሂደቶች ማሟላት። በአይኤፍሲ ፒኤስ7 ዓላማዎች መሠረት ሲኤፍኤም የሲይኦ ፈንድ ፈሰስ የተደረገባው ሁሉም ፕሮጀክቶች የሚከተሉትን እንዲያደርጉ ያስገድዳል፦ • በሁሉም የልማት ተግባራት ውስጥ በተሟላ መልኩ የነባር ሕዝቦችን ሰብአዊ መብቶች፣ ክብር፣ ፍላጎቶች፣ ባሕልና በተፈጥሮ ሀብት ላይ የተመሠረተ አኗኗርን ማክበር፤ • ነባር ሕዝብ ባለበት ማኅበረሰብ ሊከተሉ የሚችሉ የፕሮጀክት ተፅእኖዎችን መተንበይና ማስወገድ ነገር ግን ማስወገድ በማይቻልበት ጊዜ መቀነስና እና/ወይም ለእንዲህ ዓይነቶቹ ተፅእኖዎች ካሳ መስጠት፤ • ለነባር ሕዝቦች በባሕላቸው መሠረት አግባብነት ያለው የዘላቂ ልማት ጥቅማጥቅሞችና እድሎችን መስጠት፤ • ከነባር ሕዝብ ጋር በመረጃ ላይ የተመሠረተ ምክክርና ተሳትፎ ፕሮጀክቱ ከሚነካቸው ሰዎች ጋር በፕሮጀክት ቆይታ ጊዜ በማድረግ ቀጣይነት ያለው መቀራረብ መፍጠርና ማስቀጠል። • በአይሲፒ ሂደት መሰማራትና በተለይ አስፈላጊ ሲሆን ፕሮጀክቱ የሚነካቸው ነባር ሕዝቦች በነፃነት እና በቅድሚያ በተገኘ መረጃ መሠረት በፍቃደኝነት ላይ የተመሠረተ አይሲፒ ማካሄድ፤ እና • የነባር ሕዝቦችን ባህል፤ እውቀትና ልማድ ማክበርና መጠበቅ። በጥንቃቄ ሂደቱ ወቅት አንድ ኢንቨስትመንት በነባር ሕዝቦች ላይ የሚኖረው መጥፎ ተፅእኖ በተቻለ ፍጥነት ምልክት ይደረግበት እና እንዲህ ዓይነቱ ኢንቨስትመንትም ውጤቱ ቢያንስ “ለ+” እንዲሆን ያስደርገዋል።በጥንቃቄ ሂደቱ የተነሳ፣ ኢንቨስትመንት እነደዚህ ዓይነቱ ኢንቨስትመንት ውጤትም ቢያንስ “ለ+” ነው። በሁኔታው ላይ ኤፍፒአይሲ የሚያስፈልግበት ሆኖ ሲገኝ፣ ፕሮጀክቱም “ሀ” የስጋት ደረጃ አሰጣጥን ያገኛል (ክፍል 5 ይመልከቱ)። አይፒዎች እንደ ኢኤስአይኤ በሚኖረው ውጤት ላይ በሚደረግ ግምገማ ተፅእኖ ሲኖረው፣ ከፕሮጀክቱ ጽንሰ ሐሳብ ላይ የሚኖረውን ተፅእኖ አያስቀረውም በመሆኑም IPP ከአበልጻጊዎች ጋር በመጣመር መዘጋጀት ይኖርበታል። የ IPP ዓላማ ከባሕል አንጻር አግባብነት ባለው መንገድ በሃገር በቀል ሕዝቦች ላይ የሚደርሱ አሉታዊ ተጽእኖዎችን ለመቀነስ እና/ወይም ለመካስ የሚያስችሉ እርምጃዎችን መግለጽ ነው፡፡ ቅጥያ 10 ለ IPP ማጣቀሻ የሚሆን ዝቅተኛውን መስፈርት የያዘ ውልና በ IFC PS7 ማስታወሻ ላይ የሰፈረው ቅጥያ 1 መመሪያን መሠረት ያደርጋል።