አሰራርና ጥገና /operation and maintenance/ የናሙና ክፍሎች

አሰራርና ጥገና /operation and maintenance/. ይህ ተግባር የውሃ ስርጭትና ጥገና፣ የአፈር ጥበቃ እና ለአባላት በመስኖ አጠቃቀም ስልጠና ለመስጠት ማቀድን፣ ዕቅድን ተግባራዊ ማድረግን እና ክተትልን ያካትታል፡፡ 3. አመራር የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበርን ከማስተዳደርና ፋናንስን ከመምራት ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ በአስተዳደርና በሥራ አመራር መካከል ያለው የልዩነት መደበላለቅ መወገድ አለበት፡፡ ለምሳሌ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ጠቅላላ ጉባኤ በጀት ያፀድቃል /አስተዳደር/ የፀደቀው በጀትም በስራ አመራር ኮሚቴው አማካኝነት ተግባራዊ ይደረጋል /ሥራ አመራር/፡፡ በርካታ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ተግባራት ቀጥሎ ባለው ሰንጠረዥ ተዘርዝረዋል፡፡ በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራት ለማቀድ፣ ተግባረዊ ለማድረግና ለመከታተል ዋና መሳሪያዎች (1) የጥገና ዕቅድ (2) የውሃ ስርጭት ዕቅድ እና (3) በጀት ናቸው፡፡