የስብሰባ ቃለጉባኤ አዘገጃጀት፣ የናሙና ክፍሎች

የስብሰባ ቃለጉባኤ አዘገጃጀት፣. 38 3.2.1 የሰብሰባ ቃለ ጉባኤ ይዘት፣ 38 3.3 ገንዘብ ነክ ያልሆኑ ሰነዶች አያያዝና አጠባበቅ 43 3.3.1 የአስተዳደራዊ አመራር አጠቃላይ መርሆዎች፣ 44 3.3.2 የአስተዳደራዊ አመራር ዓላማ 44 3.3.3 ገንዘብ ነክ ያልሆኑ ሰነዶች 45 3.3.3.1 የመሬት ይዞታ መዝገብ፣ 46 3.3.3.2 ውሎች፣ 47 3.4 ዓመታዊ የስራ ዕቅድና ሪፖርት አዘገጃጀት 59 3.4.1 የመልካም አስተዳደር መርሆዎች፣ 59 3.4.2 ግልፀኝነት እና ተጠያቂነት፣ 60 3.4.3 በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር የስራ ዑደት፣ 62 3.4.4 አመታዊ የስራ ዕቅድ 63 3.4.5 ዓመታዊ ሪፖርት 66 3.5 ቅጥር ሰራተኞች እና አገልግሎቶች፣ 69 3.5.1 የፈጻሚ ቅጥር ሰራተኞችና የጉልበት ሰራተኞች ውል አያያዝ 69 3.5.1.1 የመስኖ ቴክኒሻን 70 3.5.2 ፈጻሚ ቅጥር ሰራተኞችን እና የቀን ሰራተኛ የአቀጣጠርና የቁጥጥር ሂደት 72 3.5.3 የአገልግሎት ውል መዋዋል 73 3.6 ቢሮ፣ የቢሮ ሰራተኞች እና የንብረት አመራር፣ 76 3.6.1 የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ቢሮ አመራር 76 3.6.2 የቅጥር ሰራተኞች አመራር፣ 78 3.6.3 የንብረት አስተዳደር 79 ማገናዘቢያ /Referaces/ 80 የስልጠና ሰነድ 2፣ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራት አስተዳደር‌ 2.1 የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ምንነት‌ ዓላማ የስልጠናው ተሳታፊዎች በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር አስተዳደር፣ በአሰራር እና ጥገና አመራር እንዲሁም በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራት እና በመስኖ ኅብረት ሥራ ማኅበራት መካከል ያለውን ልዩነት ለማስገንዘብ ነው፡፡ በዚህ ክፍል የሚተዩ ርዕሶች፣ • የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ምንነት፣ • የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ኃላፊነት እና ተያያዥ ተግባራት፣ እና • የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር የህግ ማዕቀፍ፣ ስልልጠናው የሚያካትታቸው፡- የሚመለከታቸው አጋር አካላት ባለሙያዎች፣ የስልጠና መሳሪያዎች፡- ፊሊፐ ቻርት፣ ማኑዋል እና የክፍል/የቡድን ሥራ፣ ስልጠናው የሚወስደው ጊዜ፡- አንድ ሰዓት፣ ? ሰልጣኞችን የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር እና የመስኖ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ልዩነት ምንድን ነው የሚል ጥያቄ በመጠየቅ ሁሉም ተሳታፊዎች ሃሳብ እንዲሰጡበት አድርግ፡፡ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራትን ለማቋቋምና ለማስተዳደር የወጣው አዋጅ ቁጥር 239/2008፣ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራትን ለማቋቋም እና የመስኖና ድሬኔጅ አውታርን ለመስራትና ለመጠገን /Operation & maintenance/ የሚያስችል የተለየ የሕግ መሰረት ተጥሏል፡፡ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ የነበረው የሕግ ማዕቀፍ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበርን በሕጋዊ መንገድ ለማቋቋም የሚያስችል አልነበረም፡፡ በዚህም መሰረት፡- • የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራት በመንግስት አዋጅ የሚቋቋሙና ኃላፊነታቸውም ከመንግስት ፍላጎት ጋር የሚሄድ መሆኑ፣ • በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራት አባልነት ግዴታ መሆኑ፣ • የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራት አትራፊ ባልሆኑ ተግበራት ወይም ንግድ ነክ ባልሆኑ ተግበራት ላይ የተሰማሩ ቢሆንም ለአባሎቻቸው ከሚሰጡት አገልግሎት ለምሳሌ የመስኖ ውኃ አገልግሎት ክፍያ ያሰባስባሉ፡፡ • የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራት ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩና በአባላት የሚመሩ ራስገዝ ድርጅቶች ቢሆኑም ተግባሮቻቸውን ሲያከናውኑ ለህዝብ ጥቅም ሲባል በተወሰነ መልኩ የመንግስት ቁጥጥር ይደረጋል፡፡ መንግስት በሚያወጣው አዋጅ የሚቋቋሙ ድርጅቶች ኃላፊነት ባህሪ የመንግስትን ትኩረትም ጭምር የሚያንፀባርቁ ናቸው፡፡ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራት ኃለፊነት ለግብርና ስራ የሚውል የመስኖ ውሃ ለአበሎቻቸው መስጠት ነው፡፡ ይህ ተግባር በባህሪው የመንግስት ትኩረትም አለበት፡፡ ምክንያቱም፣ 1) የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራት የመስኖ ውሃ የሚሰጡት ከፍተኛ ቁጥር ላለው ህዝብ/ማህበረሰብ በመሆኑ እና፣ 2) ማኅበራቱ በአብዛኛው በመንግስት ድጋፍ በተገነቡ የመስኖ አውታሮች የሚጠቀሙ በመሆኑ፤ ማለትም መሰረተ ልማቱ በመንግስት የተገነባና ባለቤትነቱም የመንግስት በመሆኑ መንግስት ትኩረት ይሰጠዋል፡፡ የመንግስት አዋጆች ከህ-ገመንግስቱ የሚቀዱ ናቸው፡፡ የመንግስት አካላት ማለትም የማዕከላዊ መንግስት፣ የክልል እንዲሁም የተለየ የመንግስት ተግባር የሚያከናውኑ ተቋማት ለምሳሌ የመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ሆስፒታሎች ወዘተ…. አሰራራቸውን የሚወስኑ የተለዩ አዋጆች ይዘጋጁላቸዋል፡፡ ስለሆነም የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራት በመንግ...