ውጤታማ የመድረክ መሪ‌ የናሙና ክፍሎች

ውጤታማ የመድረክ መሪ‌. ስብሰባውን በተዳረጀና ቅደም ተከተሉን በጠበቀ ሁኔታ ለመምራት የሚከተሉት ኃለፊነቶች ያሉት የስብሰባ መሪ ያስፈልጋል፡፡ • ስብሰባው በታሰበው ሰዓት እንዲጀምርና እንዲጠናቀቅ ማድረግ • ስብሰባው እንዳይበላሽ ወይም በስርዓት እንዲመራ እና አጀንዳዎችን መሰረት በማድረግ እንዲካሄድ ማድረግ፣ • ቅደም ተከተል መጠበቅ/ማስጠበቅ፣ • ስብሰባው በዋና ዋና ጉደዮች ላይ እንዲያተኩር ማድረግ፣ • ስብሰባው ነጻና ሁሉንም ተሰብሳቢ የነቃ ተሳትፎ ሊያደርጉና የበኩላቸውን ሀሳብ ሊያቀርቡ በሚችልበት አግባብ መምራት፣ • ግልጽና የማያሻማ ውሳኔ እንዲወሰን በማድረግ ስብሰባውን ውጤታማ ማድረግ፣እና • የድምጽ አሰጣጥ ሰርዓትን በአግባቡ ተግባራዊ በማድረግ ሁሉም ውሳኔዎች በግልፀኝነት እንዲወሰኑ ማድረግ፣ ? የስልጠናው ተሳታፊዎችን የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር የስብሰባ መሪ እንዴት ውጤታማና ፍሬያማ ስብሰባዎችን ማካሄድ ይችላል የሚል ጥያቄ በመጠየቅ ሁሉም ተሳታፊዎች ሀሳብ እንዲሰጡበት በማድረግ የሚሰጡትን መልስ በፊሊፕ ቻርት ወይም በነጭ ሰሌዳ ጻፍ፡፡ በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ስብሰባ ወቅት ስብሰባውን የሚመራው የሰብሰባ መሪ ሰብሰባውን በይፋ በሚከፍትበት ጊዜ የሚከተሉትን ህጎች ማየት አለበት፡፡ • በስብሰባ ጥሪ ማስታወቂያው ላይ በተገለፀው ሰዓት ወይም ጊዜ መሰረት ስብሰባው እንዲጀመር ማድረግ፣ በዚህም ምክንያት አበላት በቀጣይ ስብሰባው ዘግይቶ ይጀመራል በሚል እንደልምድ ወስደው የመዘግየት ዕድላቸውን ያጠባል፣ • የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር የስብሰባ መሪ/ሊቀመንበር ስብሰባውን ለመጀመር ወይም ላለመጀመር አስቸጋሪ ሁኔታ አለመኖራቸውን በማረጋገጥ ስብሰባው አንዲቀጥል ማድረግ፣ • የስብሰባው መሪ ሁሉንም የስብሰባው ተሳታፊዎች እንኳን ደህና መጣችሁ የማለትና ተሰብሳቢወች የሚተላለፈውን መልዕክት ሊሰሙና ሙሉ በሙሉ ሊረዱት በሚችሉበት ሁኔታላይ መሆናቸውን ማረጋገጥ አለበት፣ • የስብሰባው መሪ በመተዳደሪያ ደንቡ በተገለፀው መሰረት ምልዓተ ጉባኤው መሟላቱን ማረጋገጥና ስለ ስብሰባው መቀጠል አለመቀጠል ለተሰብሳቢው መግለጽ አለበት፣ ስለሆነም ስብሰባው ሙሉ የመወሰን አቅም በመያዝ የሚቀጥልበት ወይም በማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ በተደነገገው መሰረት ለሌላ የስብሰባ ቀንና ሰዓት የሚተላለፍበት ሁኔታ ይፈጠራል፣ • በመጨረሻም የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር የስብሰባ መሪ የስብሰባውን አጀንዳወች ለተሰብሳቢዎች በጥቁር ሰሌዳ ላይ በመጻፍ ወይም በሌላ አቀራረብ ያቀርባል፣ ተሳብሳቢዎችን ሌላ ተጨማሪ መያዝ ያለበት አጀንዳ ካለ ይጠይቃል፣ 3.1.3.7 የተሰብሳቢወች መልካም ስነምግባር፣‌ ስብሰባው በቅደም ተከተልና በሰዓቱ እንዲካሄድ ለማድረግ ሁሉም ተሰብሳቢዎች የሚከተሉትን ህጎች የሚያከብሩ መሆን አለባቸው፣ • በአንድ ጊዜ አንድ ሰው ብቻ በስብሰባው መሪ ሲፈቀድለት መናገርና ሌሎች በፀጥታ የማዳመጥ፣ • መናገር/ሀሳብ ማቅረብ የሚፈልግ ተሰብሳቢ እጁን በማንሳት ለስብሳባ መሪው ምልክት ማሳየትና ሰብሳቢው የመናገር መብት እስኪሰጠው ድረስ መጠበቅ፣ • ማንኛውም ለውይይት በቀረበ ጽሁፍ/ሰነድ እና የውይይት ሀሳብ ስምምነት ላይ መድረስ፣ ገላጭና ዋናው ነጥብ ላይ ማተኮር ያስፈልጋል፣ • አላስፈላጊ ንግግር ማስወገድ • በአአባለት መካከል የሚደረግ ውይይት ወደ ግለሰባዊ ጥቃት ወይም በተወሰኑ ግለሰቦች መካከል የተካሄደ ውይይት አድርጎ መውሰድ አይፈቀድም፣ • ውይይቶች ሁሉም ተሳታፊ ነጻ፣ በንቃት፣ ምክንያታዊ ሁነው የሚናገሩበት እና ለሁሉም ክፍት መሆን አለበት፣ • በስብሰባው ወቅት የስብሰባው መሪ ውይይቱ ላይ ትኩረት እንዲኖር ማድረግ አለበት፣ • ባለፈ ጉዳይ ላይ ተደጋገሚ ውይይት ማድረግ ውጤታማ አያደርግም ወደ ተሻለ ደረጃም አያሸጋግርም፣ • ጥያቄዎችና ውይይቶች ሁልጊዜም መበረታታት ይኖርባቸዋል፣ ነገር ግን በወቅቱ ከተነሳው ጉዳይ ጋር መዛመድ ይኖርበታል፣ • አንድን እየቀረበ ያለ ጉዳይ ወይም ውይይት እንዲቋረጥ የማድረግ መብት ያለው የስብሰባው መሪ ብቻ ነው፣ 3.1.3.8 ውሳኔዎችን ለማጽደቅ ድምጽ መስጠት፣‌ በሁሉም የማኅበሩ እንቅስቃሴዎች የሁሉም የማኅበሩ አባላት የባለቤትነት ስሜት መኖር ጠቃሚ ነው፡፡ በማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ በተደነገገው መሰረት የማኅበሩን ሁሉንም ጠቃሚ ጉዳዮች ለማጽደቅ እና ውሳኔዎች ከመወሰናቸው በፊት አባላት እንዲመክሩበት ለማድረግ የስራ አመራር ኮሚቴው የማኅበሩን አባላት ይሁንታ ይፈልጋል፡፡ በጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ወቅትና በስራ አመራር ኮሚቴው ወርሀዊ ስብሰባ ወቅት ውሳኔዎች እንዲፀድቁ ለማድረግ መከተል ያለብን ሂደት፤ • አባላ...