ዓመታዊ የስራ ዕቅድና ሪፖርት አዘገጃጀት‌ የናሙና ክፍሎች

ዓመታዊ የስራ ዕቅድና ሪፖርት አዘገጃጀት‌. ዓላማ፣ • ሰልጣኞች በማኅበሩ የመስኖ አውታር አሰራርና ጥገና በዋናዋና ተግባራት እና በአመታዊ የስራ ዕቅድና ሪፖርት ጠቀሜታ ላይ ያላቸው ዕውቀት ለማሻሻላል፣ • ሰልጣኞች የራሳቸውን የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር አመታዊ የስራ ዕቅድ እና ሪፖርት ለማዘጋጀት ለማዘጋጀት ያላቸውን ክህሎት ለማጎልበት፡፡ ርዕሶች፣ • የመልካም አስተዳደር መርሆዎች፣ • የግልፀኝነትና ተጠያቂነት ጠቀሜታ፣ • የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ዓመታዊ የስራ ዑደት • ዓመታዊ የስራ ዕቅድ o አመታዊ የስራ ዕቅድ የማጽደቅ ሂደት • ዓመታዊ ሪፖርት ስልጠናው የሚያካትታቸው፡- የማኅበሩ ስራ አመራር ኮሚቴ አባላት፣ የስልጠና መሳሪያዎች፡- ፊሊፕ ቻርት፣ ማኑዋል፣ ምሳሌዎችና የተግባር መልመጃዎች፣ ስልጠናው የሚወስደው ጊዜ፡- 3፡00 /ሶስት ሰዓት/፣ 3.4.1 የመልካም አስተዳደር መርሆዎች፣‌ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር አባላት የማኅበሩን የስራ ዕቅድ የሚያዘጋጅ እና የሚፈጽም እንዲሁም ሌሎችን የማኅበሩን ተግበራት ኃለፊነት በመውሰድ ሊቆጣጠርና ሊሰራ የሚችል የስራ አመራር ኮሚቴ መምረጥ አለባቸው፡፡ የተመረጡ የስራ አመራር ኮሚቴ አባላት የተሰጣቸውን ተግባራት ቀልጣፋና ውጤታማ በሆነ መንገድ በሙሉ ኃለፊነት መፈፀም ይገባቸዋል፡፡ የመልካም አስተዳደር የማዕዘን ድጋይ መርሆዎች፣ • የኃላፊነት ስሜት፣ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር አመራር አባላት በማኅበሩ አገልግሎት ክልል ላሉ ለሁሉም የመስኖ ተጠቃሚዎች በእኩልነት እያገለገሉ መሆኑንና ተጠሪነታቸውም ለመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች አባላት መሆኑን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡ • ስራን ማወቅ፣ ምን ስራ መሰራትና መቸ መሰራት እንዳለበት ማወቅ፣ • ዕርምጃ የመውሰድ ተነሳሽነት፣ ስራዎችን ለመፈፀም ወይም ችግሮችን ለመፍታት መነሳሳት፣ • የስራ ክፍፍል፣ መሳተፍ፣ ሌሎቹ በስራው ተሳታፊ እንዲሆኑና እንዲያግዙ የማነሳሳት፣ የቡድን ስራ ማበረታታት፣ የተጠቃሚውን ክህሎት መጠቀም፣ • ትክክለኛ ውስኔ መወሰን፣ ማንኛውም ውሳኔ ሲወሰን ትክክለኛና ተቀባይነት ያለው ውሳኔ መወሰን፣ • ውጤታማነት፣ በፍጥነት ውጤት በሚገኝባቸው ተግባራት ማተኮር፣ ወጭን መቆጣጣር • ብልሀት፣ የችግር የማስወገድና ግጭቶችን የመፍታት ክህሎት፣ • አደረጃጀት፣ ጥሩ የሆነ አስተዳደራዊና የፋይናነስ አመራር ክህሎት መኖር፣ • ግልፀኝነት፣ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር አባላት /እና አባል ያልሆኑ ተጠቃሚዎች/ በአመራር አካላት ውሳኔዎች፣ በተግባራት አፈጻፀም እና የማኅበሩ የገንዘብ አጠቃቀም በወቅቱና ውጤታማ ለሆነ ጉዳይ ስራ ላይ መዋሉን ግልጽ ማድረግ፣ • የግንኙነት ክህሎት፣ በማኅበሩ አባላት እና አባል ባልሆኑ መካከል፣ አንዲሁም ማኅበሩ ከኅብረት ሥራ ማኅበራት ማስፋፊያ ኤጀንሲ፣ ከመስኖ እርሻ ልማት ፕሮግራም፣ ከወረዳ አስተዳደር፣ ከቀበሌ አስተዳደርና ከሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት ጋር መልካም ግንኙነት እንዲኖር ማድረግ፣ እነዚህ መሰረታዊ ነጥቦች አብዛኘዎቹ በራሳቸው ገላጭ በመሆናቸው በዚህ የስልጠና ማኑዋል ሌላ ተጨማሪ ዝርዝር ነገር አልተከተተም፡፡ የተወሰኑት የመልካም አስተዳደር መርሆዎች በሌሎች ማኑዋሎች የተካተቱ ናቸው፡፡ 3.4.2 ግልፀኝነት እና ተጠያቂነት፣‌ በአንድ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ውጤታማ ለመሆንና ዘላቂነት ያለው አሰራር ለማረጋገጥ፣ ለተጠቃሚዎች ተጠያቂ መሆን እና ግልጽ ውሳኔዎችን መወሰን ወሳኝና መሰረታዊ ጉዳዮች ናቸው፡፡ • ተጠያቂነት፡- ተጠያቂነት ማለት የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር የአመራር አባላት ሊቀመንበሩን ጨምሮ የሚሰሩትን ተግባራት አፈጻፀም ለማኅበሩ አባላት ግልጽ የማድረግና ባልፈፀሟቸው ተግባራትም ተጠያቂ የመሆን ግዴታ አለባቸው፡፡ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር የአመራር አባላት የሚመረጡት በማኅበሩ አባላት ሲሆን ጠቅላላ አባላትን በመወከል የዕለት ከዕለት ሥራዎችን ያከናውናሉ፡፡ • ግልፀኝነት፡- በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ከተጠያቂነት ተቀራራቢ የሆነው ጉዳይ ግልጽኝነት ያለው የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ነው፡፡ ግልፅኝነት ማለት የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ስራ አመራ ኮሚቴ ማንኛውንም የኮሚቴ ውሳኔዎችንና ተግባራትን ለአብነት የገንዘብ አጠቃቀምን ለሁሉም ተጠቃሚዎች ግልጽ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ☞ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ስራ አመራር ኮሚቴ አበላት ውጤታማ ስራ ለመስራት ቅድመ ሁኔታዎች በአባላትና አባል ባልሆኑ ተጠቃሚዎች ዘንድ እምነትንና ተቀባይነትን ለመገንባት ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ መሆንና የኮሚቴውን ባህሪ፣ እርምጃና እና ውሳኔዎችን በሚመለከት በግልጽ ለተጠቃሚዎች ማስገንዘብ ተቀዳሚ ተግበራቸው ነው፡፡ በሌ...