የ CIO Funds እና የትኛውም ተጓዳኝ ፈንድ የሚከተሉትን ጉዳዮች የሚያካትት ማንኛውንም ተግባር፣ ምርት፣ ጥቅማ ላይ መዋል፣ መነገድ፣ ማሰራጨትን ፋይናንስ አያደርግም፡ የናሙና ክፍሎች

የ CIO Funds እና የትኛውም ተጓዳኝ ፈንድ የሚከተሉትን ጉዳዮች የሚያካትት ማንኛውንም ተግባር፣ ምርት፣ ጥቅማ ላይ መዋል፣ መነገድ፣ ማሰራጨትን ፋይናንስ አያደርግም፡. የግዳጅ ሥራ 1 ወይም የሕጻናት ጉልበት ብዝበዛ2 በአስተናጋጅ ሃገር ሕጎች ወይም ደንቦች ወይም በዓለም አቀፍ ኮንቬንሽኖችና ስምምነቶች ሕገ-ወጥ ተደርገው የተፈረጁ ወይም ዓለም አቀፍ የቀነ ገደብ ማለፍ ወይም እገዳ የተጣለባቸው ተግባራት ወይም ቁሳቁስ፣ ለምሳሌ፡ ኦዞን የሚጎዱ ንጥረ ነገሮች፣ (ፖሊክሎሪኔትድ ባይፌኒልስ) እና ሌሎች የተለዩ አደገኛ መድኃኒቶች፣ ፀረ-ተባይ/ፀረ-አረም መድኃኒቶች ወይም ኬሚካሎች፤ የዱር ሐብቶች ወይም በዓለም አቀፍ ለአደጋ የተጋለጡ ዝርያዎች በዱር እንስሳ እና ተክሎች መነገድ ኮንቬንሽን (CITES) ስር ቁጥጥር የሚደረግባቸው የምርት ውጤቶች፤ ወይም ዘላቂነት የሌላቸው የዓሳ ማጥመጃ ዘዴዎች (ለምሳሌ፡ ከ2.5 ኪሜ በላይ እርዝመት ያላቸውን መረቦች በመጠቀም በባሕር አካባቢ ላይ ፈንጂን በመጠቀም ዓሳን መሰብሰብ እና መረብን ወደታች በጥልቀት በመላክ የማጥመድ ስራ)፡፡ የባዝል ኮንቬንሽን እና መሰረታዊ ደንቦቹን ባከበረ ሁኔታ ካልሆነ በስተቀር በዝቃጭና የዝቃጭ ውጤተች ድንበር ተሻጋሪ ንግድ ማካሄድ 3 ከፍተኛ የአካባቢ ጥበቃ ዋጋ ያላቸውን አካባቢዎች ማውደም4 ራዲዮ አክቲቭ ቁሳቁስ 5 እና ያልተገደቡ የአዝቤስቶስ ፋይበሮች ፖርኖግራፊ እና/ወይም ሴተኛ አዳሪነት፡፡ ዘረኛ እና/ወይም ጸረ ዴሞክራሲ ሚዲያ ከእነዚህ ተከታይ ምርቶች ውስጥ የትኛቸውም ቢሆኑ የአንድ ፕሮጄክትን በተቀዳሚነት ፋይናንስ የሚደረጉ የቢዝነስ ተግባራት አብዛኛውን ድርሻ ከያዙ፡6 የአልኮል መጠጦች (ከቢራ እና ወይን በስተቀር) ትምባሆ የጦር መሳሪያዎች እና ጥይቶች፤ ወይም የቁማር፣ የካሲኖ እና ተመሳሳይ ድርጅቶች ፡፡ የተ.መ.ድ. ወይም የአውሮፓ ሕብረት ማዕቀብ የተጣለባቸው ድርጅቶች፣ ተግባራት ወይም ግለሰቦች፡፡ ከዚህ በፊት ወይም አሁን በሙስና፣ በመሰረታዊ የስነ-ምግባር ልማዶች ወይም ሌሎች ስነ-ምግባራዊ የቢዝነስ መርሆዎች ላይ ከባድ ጥሰት መፈጸማቸው የተረጋገጠ ወይም የተጠረጠረ ድርጅቶች፡፡ 1 የግዳጅ ሥራ ማለት በፈቃደኝነት ላይ ተመስርቶ ያልተሰራና አንድን ግለሰብ በጉልበት ወይም በቅጣት በማስፈራራት የተሰራ ስራ ወይም አገልግሎት እንደሆነ በዓለም አቀፍ የስራ ድርጅት ኮንቬንሽኖች ላይ ተቀምጧል፡፡ 2 በዓለም አቀፍ የስራ ድርጅትሰ መሰረታዊ የሰብዓዊ መብቶች ኮንቬንሽን (የአነስተኛው ዕድሜ ኮንቬንሽን C138፣ አንቀጽ 2) መሰረት ሰዎች ለስራ ሊቀጠሩ የሚችሉት ዕድሜያቸው ቢያንስ 15 ዓመት ከሞላው ሲሆን ይህም የአካባቢው ሕግ በትምህርት ገበታ ላይ መገኘት ወይም ስራ ለመስራት መሟላት ያለበትን አነስተኛ ዕድሜ ካልደነገገ በስተቀር ነው፡፡ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ትልቁ ዕድሜ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ 3