የማኅበረሰብ ጤና፣ ደኅንነት እና ጸጥታ የናሙና ክፍሎች

የማኅበረሰብ ጤና፣ ደኅንነት እና ጸጥታ. ሲኤፍኤም ማኅበረሰቦች በሳይት እና ከሳይት ውጭ በሁለቱም ላይ በሚኖሩ ከፕሮጄክት ጋር በተገናኙ እንቅስቃሴዎች በከባድ ሁኔታ ተፅእኖ ሊያርፍባቸው እንደሚችል ያውቃል። በአይኤፍሲ ፒኤስ4 መሠረት እና እንዲሁም የዓለም ባንክ ኢኤችኤስ መመሪያዎችን ከግምት በማስገባት፣ ሲኤፍኤም ሁሉም ፕሮጄክት ኩባንያዎች የሚከተሉትን እንዲያደርጉ ይጠይቃል፦ • ከመደበኛ እና መደበኛ ካልሆኑ ሁኔታዎች በሁለቱም በኢንቨስትመንት ክፍለ ጊዜው ዕድሜ ላይ ተፅእኖ የሚያርፍባቸው ማኅበረሰቦችን መገመት እና ከባድ ተፅእኖ እንዳያርፍባቸው መከላከል፤ እና • ተገቢነት ባላቸው ሰብአዊ መብቶች መርሆዎች መሠረት የፕሮጄክት ሠራተኞች እና ንብረትን ጥበቃ ማድረግ1 እንዲሁም ተፅእኖ በሚያርፍባቸው ማኅበረሰቦች ላይ ያሉ ስጋቶችን ማስወገድ ወይም መቀነስ በሚያስችል አገባብ። በፕሮጄክት ተፅእኖ የሚያርፍባቸው ማኅበረሰቦች ጤና፣ ደኅንነት እና ጸጥታን በተመለከተ ሊከሰቱ የሚችሉ ስጋቶችን እና ተጨባጭ ስጋቶችን ለይቶ ማወቅ በኢንቨስትመንት ሂደቱ መባቻ ላይ በተቻለ መጠን መጀመሪያ ላይ እንዲሁም ቢያንስ በጥንቃቄ ማድረጊያ ሂደት ላይ ከግምት የሚገባ ይሆናል። ማናቸውም ሊከሰቱ የሚችሉ ግምት የሚሰጣቸው ገጽታዎች ለተጨማሪ ሐተታና ትንታኔ ቀይ ባንዴራ መጥቁም የሚደረግባቸው ሲሆን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እንደ ኢኤስአይኤ አንድ አካል ተጨማሪ ምርምር ይደረግባቸዋል። የማኅበረሰብ ጤና፣ ደኅንነት እና ጸጥታን በተመለከተ ለየት ያለ አንድ የተወሰነ የሚያሳስብ ነገር ካለ፣ የጤና ተፅእኖ ግምገማ እና/ወይም የሰብአዊ ስጋት ግምገማን እንደአስፈላጊነቱ እንዲያካትት ይህ መደበኛ የሆነው የኢኤስአይኤ ምህዳር እንዲሰፋ ሊያስገድድ (አባሪ 8ን ይመልከቱ) ይችላል። ለእያንዳንዱ ፕሮጄክት እንደ ዝቅተኛ መስፈርት መከናወን ካለባቸው ከሚከተሉት ግዴታዎች በተጨማሪ ሁሉም ፕሮጄክቶች በኢኤስአይኤ የተገለጹትን የቁጥጥር ዕቅዶች እንዲያዘጋጁ እና እንደ አስፈላጊነቱ የሚጣጣም እንዲያደርጉ ይጠየቃሉ፦ • የማኅበረሰብ ጤና እና ዋስትና ስጋቶችን ከግመት የሚያስገባ ተገቢነት ያለው የፕሮጄክት መሠረተ ልማት ዲዛይን እና ግንባታ፤ • የተሽከርካሪ እና የአሽከርካሪ ደኅንነት እና በሕዝብ መንገዶች ላይ ጤናማ ያልሆኑ ጭነቶች እንቅስቃሴን ጨምሮ የትራፊክ ቁጥጥር፤ 1 በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ እና የሰብአዊ መብቶች የበጎ ፈቃደኝነት መርሆዎች መመሪያ ላይ በተብራራው መሠረት • ማኅበረሰብ አቀፍ የስጋት መላ ምቶችን ከግምት የሚያስገባ የድንገተኛ አደጋ ሁኔታዎች ቁጥጥር ዕቅድ አወጣጥ፤ • የተጋላጭነት ስጋትን በሚቀንስ መልኩ አደገኛ ነገሮችንና ቆሻሻዎችን ማጓጓዝ ማከማቸትና ማስወገድ፤ • ለብዝሐ ሕይወት ቅድሚያ በመስጠት ተፅእኖዎችን ማስወገድ/ማስተካከል፤ • ለተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታ አምጪዎች ተጋላጭነትን መቆጣጠር፣ እና • በተመጣጣኝነት መርሆዎች እና በዓለምአቀፍ መመሪያ 1 መሠረት የደኅንነት ሠራተኞችን መምረጥና መቆጣጠር።