የሠራተኛ እና የአሠራር ሁኔታዎች የናሙና ክፍሎች

የሠራተኛ እና የአሠራር ሁኔታዎች. 1 በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ እና የሰብአዊ መብቶች የበጎ ፈቃደኝነት መርሆዎች መመሪያ ላይ በተብራራው መሠረት ሲኤፍኤም እና የሲአይኦ የተመደቡ ገንዘቦች ፈሰስ የሚደረጉባቸው ሁሉም ኢንቨስትመንቶች በአይኤፍሲ የአፈጻጸም መስፈርት 2 እና በአይኤልኦ ዓቢይ ኮንቬንሽን ላይ በተቀመጡት ሕጋዊ መስፈርቶች መሠረት የሠራተኛ እና የአሠራር ሁኔታዎችን የሚያስተካክሉባቸው ዘዴዎች በቦታው ይኖራቸዋል። እንዲህ ሲሆን፣ ሁሉም ፕሮጄክቶች የሚከተሉትን የሚያሟሉ ማስተካከያዎችን ተፈጻሚ ያደርጋሉ፦ • ከአካባቢ ለሚገኙ እንዲሁም ለውጭ አገር ሠራተኞች የቅጥር ምልመላ ስትራቴጂ፣ ፖሊሲ እና የአካሄድ መመሪያ፤ • በብሔራዊ የአሠሪና የሠራተኛ ሕጎች ተገዥነት፤ • ከሠራተኞች ጋር በጋራ እና ከየሠራተኛ ኅብረት ጋር መደራደር፣ እና የሠራተኛ የምክር አገልግሎት፣ መልእክት ማስተላለፍ ዘዴ እና ተሳትፎን ጨምሮ የሠራተኛ ግንኙነቶችን ለማስተዳደር የሚደረጉ ዝግጅቶች፤ • ግብረመልስ ለመስጠት፣ አቤቱታ እና ቅሬታን ለማቅረብ ለሠራተኞች የተዘጋጀ የሠራተኛ የአቤቱታ አቀራረብ ዘዴ፤ • ፍትሐዊ አያያዝ፣ በሥራ ቦታ ላይ የጾታ መድልዎ እንዳይፈጸም ጥንቅቄ ማድረግ ላይ እና በሥራ ቅጥር፣ ካሣ አከፋፈል፣ ሥራ ውልን ማቋረጥ፣ ደረጃን ከፍ ማድረግ፣ ሹመት እና ሌሎች ከሥራ ጋር የተገናኙ ሁኔታዎችን ወይም የሥራ ቅጥር ውሎችን በተመለከተ መድልዎ አለማድረግ እና ለሁሉም እኩል ዕድል መስጠት፤ • በአቅርቦት ሠንሠለት ውስጥ ያሉትን፣ ሕፃናትን፣ ስደተኛ ሠራተኞች እና በሦስተኛ ወገን የተቀጠሩ ሠራተኞችን ጨምሮ ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ ሠራተኞች ጥበቃ ማድረግ እና የጉልበት ብዝበዛ እንዳይፈጸም ለማድረግ እርምጃዎችን መውሰድ፤ እና • ለደኅንነት አስተማማኝ የሆነ እና ጤናማ የሥራ ድባብን መፍጠር።