የስጋት ግምገማ የናሙና ክፍሎች

የስጋት ግምገማ. ሲኤፍኤም ሁሉም ፕሮጄክቶች ከነፍስ ወከፍ ፕሮጄክቶች ጋር ተያያዥነት ያላቸውን አካባቢያዊ እና ማኅበራዊ ስጋቶች ግምገማ እና ቁጥጥርን ተፈጻሚ ለማድረግ አስፈላጊ ዝግጅቶችን እንዲያደርጉ ይጠይቃል። በተቻለ መጠን ስጋቶችን ለማስወገድ የሚያስችሉ ዕድሎችን ለመፈለግ ትኩረት ያደረገ የማስተካከያ ቀጣይ እርከን ይህን ተከትሎ የሚመጣ ይሆናል። ይህ እርከን ተገቢነት ያላቸውን የማስተካከያ እና የቁጥጥር ስትራቴጂዎች እና እርምጃዎችን በሚያዘጋጁበት ጊዜ በሁሉም ወገኖች የሚከበር ይሆናል። የስጋት መመዝገቢያ (ሬጂስተር) ከግንባታው ደረጃ (ፌዝ) ጋር ግንኙነት ያላቸው የኢኤስአይኤ እና ሌሎች የኢ እና ኤስ ጥናቶችን ለማንፀባረቅ ሲባል የሚዘጋጅ ይሆናል። እንደ የፕሮጄክቱ የስጋት መመዝገቢያን ማጠናከር ሥራ አንድ አካል፣ የፕሮጄክት ቡድኑ ኢኤችኤስ እና ማኅበራዊ ስጋቶች አስቀድሞ መከላከል በሚያስችል ሁኔታ እና በዘዴ ተለይተው መታወቃቸውን፣ መገምገማቸውን፣ መተንተናቸውን እና ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ያረጋግጣል። ጥቅም ላይ የዋሉ ዘዴዎች አደጋ ከተፈጠረ በኋላ ማስተካከያ መፍትሔ ሰጪ ከመሆን ይልቅ አስቀድሞ መከላከል ላይ ያተኮሩ መሆናቸውን፣ ስጋቶችን ለይቶ ለማወቅ፣ እንደ ክብደታቸው ደረጃ ለመስጠት እና ለመሰነድ እንዲሁም መቆጣጠሪያዎችን ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ስጋቶችን ለይቶ ለማወቅ፣ ለመገምገም እና ለመተንተን ጥቅም ላይ የዋሉት ዘዴዎች በአፈጻጸም ምህዳራቸው፣ ተፈጥሮዋቸው እና ጊዜ አጠቃቀማቸው አኳያ የሚብራሩ ይሆናሉ። ጥቅም ላይ የሚውሉት ዘዴዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ካለው የአሠራት ልማድ ለምሳሌ ISO 31000 የተስማሙ ይሆናሉ። ሲኤፍኤም በአንድ ፕሮጄክት ውስጥ እንዲሠሩ የሚደረጉ ሁሉም ሠራተኞች ቁልፍ የአካባቢ፣ የጤና፣ የደኅንነት እና ማኅበራዊ ስጋቶችን እንደ የስጋት ግምገማ ሂደቱ አንድ አካል ለይተው እንዲያውቋቸው እና ምን እርምጃዎችን እንዲወስዱ እንደሚጠበቅባቸው እንዲያውቁ እንዲደረጉ ይጠይቃል። የስጋት መመዝገቢያው (ሬጂስተር)፣ የስጋት መቆጣጠሪያ አካሄድ ሥርዓቶች፣ እና የስጋት ግምገማዎች እንደ አስፈላጊነቱ ለሲኤፍኤም የሚቀርቡ እና ሊገኙ የሚችሉ ይሆናሉ።