የቅሬታ ምዘና - የቅሬታ ብቁነትና አመዳደብ - ደረጃ 5 የናሙና ክፍሎች

የቅሬታ ምዘና - የቅሬታ ብቁነትና አመዳደብ - ደረጃ 5. ምድባቸው ዝቅተኛ የሆኑ አሳሳቢ ጉዳዮችን በቀጥታ የሚያስተናግደው የቅሬታ አፈታት ኃላፊው ሲሆን በ7 ቀናት ውስጥ ቅሬታውን/ጥያቄውን/ሃሳቦችን መርምሮ የመፍትሔ ሃሳብ ያስቀምጣል፡፡ ክብደታቸው መካከለኛ ወይም ከፍተኛ ተደርገው የተመደቡ አሳሳቢ ጉዳዮች፣ አቤቱታዎች/ቅሬታዎችን በተመለከተ መወሰድ ያለበትን አግባብነት ያለው የእርምት እርምጃ ለመለየት ተጨማሪ የሥራ አመራር ቡድን አባላት መሳተፍ ሊኖርባቸው ይችላል፡፡ የሚመለከታቸው አካላት የእርምት እርምጃውን አንዴ ከወሰኑ፣ እንዳስፈላጊነቱ በቅሬታ አፈታት መኮንኑ ጸድቆ የሚፈረም ይሆናል፡፡