Placement Agreement
DEPARTMENT OF CHILDREN, YOUTH, AND FAMILIES
የምደባ ስምምነት
Placement Agreement
የተመደበው ልጅ(ጆች)/ወጣት | የትውልድ ቀን |
የሚከተለው ጋር ተመድቧል፡ | |
ከቤት-ውጪ እንክብካቤ ለሚያስፈልገው ልጅ/ወጣት ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ጥራት ያለው ምደባ ለማግኘት እንክብካቤ ሰጪዎች ከልጆች፣ ወጣቶች እና ቤተሰቦች መምሪያ (DCYF) እንዲሁም ከልጁ ቤተሰቦች ጋር ጠቃሚ ሸሪኮች ናቸው፡፡ ከቤት-ውጪ እንክብካቤ የሚያገኝ ልጅ/ወጣት ደህንነት የሚጠበቀው በእንክብካቤ ሰጪው፣ ወላጆች እና DCYF መካከል ግልጽ መግባባት እና አዎንታዊ የስራ ግንኙነት ሲኖር ነው፡፡ ይህ የምደባ ስምምነት ቤትዎ ውስጥ የሚመደበውን ልጅ ደህንነት የሚያረጋግጥ አስፈላጊ እና ጠቃሚ መረጃ ይሰጣል፡፡ የልጆች/ ወጣቶች ወይም ቤተሰቦቻቸው መረጃ ሚስጥራዊ ነው፤ መረጃው የሚሰጠው በጉዳዩ እቅድ ላይ ለሚሳፉ ሰዎች ብቻ ነው፡፡ ለሌሎች ሰዎች መረጃ ስለመስጠት እገዛ ለማግኘት የተመደበልዎትን የጉዳይ ሰራተኛ ያማክሩ፡፡ የልጁን ፍላጎት ለማሟላት፣ ከDCYF፣ የተመደበው ሰራተኛ እና ፍርድ ቤት ጋር ለመስራት ያለዎትን ሚና ለመረዳት ይህ ስምምነት ያግዝዎታል፡፡ በቤትዎ ውስጥ ለልጅ/ወጣት እንክብካቤ በሚሰጡበት ወቅት መጠቀም የሚችሉትን ግብአቶች እና ድጋፎች ይለያል፡፡ አስፈላጊ የአድራሻ መረጃ፡ የተመደበልዎት የጉዳይ ሰራተኛ በመደበኛ የስራ ሰአታት በ ስለልጁ የሚኖሩ ጥያቄዎችን ለመርዳት ይገኛል፡፡ • የጠረጠሩትን የልጅ ጥቃት እና ቸል መባል ለማሳወቅ ከመደበኛ የስራ ሰአታ በኋላ 1-866-END HARM ላይ ይደውሉ፡፡ ይህ ቁጥር በተጨማሪ ከ DCYF የአደጋ ጊዜ ከስራ ሰአት በኋላ ሰራኞች ጋር ያገናኝዎታል፡፡ • የጉዲፈቻ ወላጅ እና እንክብካቤ ሰጪ የድጋፍ መስምር 0-000-000-0000 አስቸጋሪ የጉዲፈቻ ሁኔታዎችን ለመፍታት ከስራ ሰአታት በኋላ ድጋፍ ይሰጣል፡፡ ከቤት እንክብካቤ-ውጪ የሚኖረውን ልጅ/ወጣት ደህንነት ለማሻሻል ከ DCYF ጋር መስራት እና የፍርድቤት ትዕዛዞችን ዝርዝር ማለትም የሚከተሉትን ጨምሮ ነገር ግን በዘህ ሳያበቃ ማክበር አስፈላጊ ነው፡ የመጀመሪያ ምደባ (የመጀመሪያው ከቤት-ውጪ ምደባ)፡ 1. ልጁ በተመደበ በመጀመሪያዎቹ 30 ቀናት ውስጥ የሚከተሉትን ማግኘቱን ማረጋገጥ፡ • በተቻለ ፍጥነት ነገር ግን ከምደባው ከአምስት ቀናት ሳያልፍ የመጀመሪያ የጤና ምርመራ፡፡ • ቀደም-ያለ ወቅታዊ በሽታ የማወቅ ምርመራ እና ህክምና (EPSDT) የሚባለውን የጤናማ-ልጅ ምርመራ አስቀድሞ ካልተደረገ በልጁ የመጀመሪያ ምደባ የመጀመሪያዎቹ 30 ቀናት ውስጥ ማድረግ፡፡ (የመጀመሪያ የጤና ምርመራ እና የ(EPSDT) ምርመራው በተመሳሳይ ጊዜ ሊቀጠር ይችላል፤ ለበለጠ መረጃ የልጁን ህክምና ሰጪ ያነጋግሩ፡፡) • ልጁ አንድ ጥርስ ካለው የጥርስ ምርመራ፡፡ ልጁ ባለፉት 6 ወራት ውስጥ የጥርስ ምርመራ ካደረገ አያስፈልገውም፡፡ 2. በተጨማሪ በተመደቡ በመጀመሪያዎቹ 30 ቀናት ውስጥ የልጅ ጤና እና ትምህርት ተቆጣጣሪ (XXXX) መርማሪው ስለልጁ የህክምና፣ እድገት እና የባህሪይ ፍላጎቶችን በተመለከተ ቀጠሮ ለማስያዝ ያነጋግርዎታል፡፡ እባክዎ በቀጠሮው ቀን እርስዎ እና ልጁ መገኘታችሁን ያረጋግጡ፡፡ |
እንክብካቤ ሰጪዎች፡
1. የ ProviderOne ካርድ ካልተገኘ ለጉዲፈቻ ልጆች ጊዜያዊ የፋርማሲ እና የህክመና አገልግሎቶች ደረሰኝ ለማግኘት የተመደበልዎትን የጉዳይ ሰራተኛ ያነጋግሩ፡፡
2. ምደባው ልጁ የቀድሞው ት/ቤቱን እንዲለቅ ካደረገ ልጁን ወዲያው አዲስ ት/ቤት ያስገቡ፡፡ የተመደበውን የጉዳይ ሰራተኛን እንደልጁ አንድ አድራሻ ይጥቀሱት፡፡ ልጁን ት/ቤት ለማስገባት ችግሮች ካሉ የተመደበውን የጉዳይ ሰራተኛ ያሳውቁ፡፡
3. ልጁ/ወጣቱ ከወላጆች፣ ወንድምና እህቶች እና/ወይም የቤተሰብ አባላት ጋር እንዲገናኝ የጉብኝት እቅድ በማዘጋጀት ይሳተፉ፤ የሚከለክል የፍርድቤት ትዕዛዝ ከሌለ በስተቀር፡፡ ለተቀጠሩ ጉብኝቶች ልጁን/ወጣቱን ያዘጋጁ፡፡
4. ማንኛውንም ያልታቀደ የወላጅ/ልጅ/ወጣት ግንኙነት ለምሳ የስልክ ጥሪ፣ ያልተጠበቀ ጉብኝት ወዘተ ለተመደበው የጉዳይ ሰራተኛ ያሳውቁ፡፡
5. የጋራ የማቀድ ስብሰባዎች ላይ ይሳተፉ፡፡ የጋራ የማቀድ ስብሰባ ስለልጁ ደህንነት እና ቋሚነት ግብአት እና እውቀት የሚሰጥ እድል ነው፡፡
6. ስለልጁ/ወጣቱ ማንኛውንም ስጋት ለምሳሌ የጥቃት፣ ቸልተኝነት፣ ህክምና፣ ባህሪይ፣ እድገት ወይም የትምህርት ጉዳዮች ለተመደበው የጉዳይ ሰራተኛ ያማክሩ፡፡
7. ከተመደበው የጉዳይ ሰራተኛ ጋር ይወያዩ እና በእርስዎ እንክብካቤ ስር ለተመደበው ልጅ/ወጣት የሚመቸውን ተገቢ የስነ-ምግባር ስልቶችን ወይም አማራጮችን ይተግብሩ፡፡ አካላዊ ቅጣት አይፈቀድም፡፡
8. የኢንዲያ ልጅ ደህንነት ህግ መስፈርቶችን ለማሟላት ተግባራዊ መደረግ ሲኖርበት ከልጁ/ወጣቱ የተመደበ የጉዳይ ሰራተኛ የሚሰጥ ማንኛውንም መመሪያ እንዲሁም ሌላ የልጁ/ወጣቱ የባህል ፍላጎቶችን ይከተሉ፡፡
9. ልጁ ቀጣይነት ያለው የህክምና፣ ጥርስ እና አዕምሮ የጤና አገልግሎቶች ማለትም በፌደራል ደረጃ በሚመከረው የምርመራዎች ቀጠሮ መሰረት እድሜ-ተኮር የ EPSDT ምርመራን ጨምሮ ማግኘቱን ያረጋግጡ፡፡ (በመጀመሪያው የህይወት አመት 5 ምርመራዎች፤ በ12 ወራት እና 2 አመት እድሜ መካከል 3 ምርመራዎች፣ በ3 እና 20 አመት እድሜ መካከል አመታዊ ምርመራዎች)፡፡
10. የህክምና/የጥርስ አገልገሎት ሰጪ ለማግኘት እገዛ ከፈለጉ የ Medicaid የባለጉዳይ አገልግሎት መስመር በ0-000-000-0000 የውስጥ መስመር 15480፣ ከሰኞ እስከ አርብ ፣ ከ7:30 AM እስከ 5:00 PM (ፓስፊክ ሰአት) ያነጋግሩ ወይም የ ProviderOne ድህረ-ገጽ xxxx://xxxx.xxxx.xx.xxx/xxxxxxxxxxx/xxxxxxxxx.xxx ይጎብኙ፡፡
11. ወደልጁ የህክምና/የጥርስ ቀጠሮዎች ለመሄድ የሚወጡ ወርሀዊ የርቀት ጉዞ ወጪዎች ይተካሉ፡፡ የእንክብካቤ ሰጪ ወርሀዊ የርቀት ጉዞ ቅጽ ከ
xxxx://xxx.xxxx.xx.xxx/xx/xxxxxxxxxxxxx/xxxxx-xxxxxxxx.xxx ላይ ማውረድ ይቻላል፡፡
12. ህክምና በሚያገኙበት ወቅት ለጤና ሰጪው የልጁን የ ProviderOne ካርድ ይስጡ፡፡
13. የህክምና/የጥርስ እንክብካቤ ቀጠሮዎች፣ አድራሻች እና የቀጠሮዎቹን ውጤቶች/ምክሮች ለመዘገብ የህክመና ሎጎ ይጠቀሙ፡፡ የልጁ/ወጣቱን ደህንነት በይበልጥ ለማረጋገጥ እንክብካቤ ሰጪው በሚከተሉት መንገዶች ለመተባበር ተስማምቷል፡
1. ለልጁ ቁጥጥር የማይደረግበት ተደራሽነት ያለው የ16 አመት እና ከዛ በላይ እድሜ ሰው ሁሉ ላይ የወንጀል የኋላ ታሪክ ምርመራ እንዲሁም የልጅ ጥናት እና የቸልተኛነት ምርመራ ያድርጉ፣
2. ቤት ውስጥ የሚኖር ሰው ከተለወጠ ለተመደበው የጉዳይ ሰራተኛ ያሳውቁ እንዲሁም ሰውየው ከላይ በ#1 ላይ የተገለጸውን መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ የወንጀል የኋላ ታሪክ ምርመራ እንዲሁም የልጅ ጥናት እና የቸልተኛነት ምርመራ ያድርጉ፣
3. ለልጁ/ወጣቱ እንክብካቤ የመስጠት ችሎታዎ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር የሚችል ማንኛውንም ጉዳይ ለተመደበው የጉዳይ ሰራተኛ ያሳውቁ፡፡ ይህ ማለት ልጁ/ወጣቱ ቤትዎ ውስጥ መቆየት እንደማይችል ካወቁ አዲስ ምደባ ለማቀድ ከተመደበው የጉዳይ ሰራተኛ ጋር በትብብር መስራትን ያካትታል፡፡
4. ልጅ ከቤትዎ እንዲወጣ ከጠየቁ አደጋ ከሌለ በስተቀር ተገቢ የሆነ እቅድ መኖሩን ለማረጋገጥ ቢያንስ የ14 ቀናት ማስታወቂያ ለተመደበው የጉዳይ ሰራተኛ መስጠት አለብዎት፡፡
5. ሁሉም እንክብካቤ ሰጪዎች የጣት አሻራ ምርመራ ማድረግ አለባቸው፡፡ ከላይ የተገለጸው ልጅ/ወጣት ላይ ከምደባ በፊት የ NCIC ወይም BCCU ምርመራ ማድረግ ያለባቸው የዘመድ እንክብካቤ ሰጪዎች ወይም ተመራጭ ሰዎች የጣት አሻራ ምርመራ ማድረግ እና ለተመደበው የጉዳይ ሰራተኛ መመለስ ያለባቸው የ NCIC ወይም BCCU ምርመራ በተደረገ በ10 ቀናት ውስጥ ነው፡፡
6. የተጠየቀውን መረጃ በሙሉ በተቻለ ፍጥነት በቶሎ ይመልሱ፡፡
7. ከተወለዱ እስከ አንድ አመት ድረስ ላሉ ልጆች የጨቅላ ደህንነቱ የተጠበቀ አተኛኘት መመሪያዎችን ለመከተል ተስማቼያለሁ፡፡
DCYF የሚከተለውን ያደርጋል፡ 1. የልጁ/ወጣቱን የህክምና፣ ትምህርት፣ ስነ-ልቦናዊ እና የባህሪ ፍላጎቶች በተመለከተ የሚታወቅ እና የሚገኝ መረጃ ይሰጥዎታል፡፡ 2. የጤና ችግር ላለባቸው ልጆች እንክብካቤ ከሚሰጡ ጋር የእንክብካቤ ሰጪ የድጋፍ እቅድ (DCYF 10-428) ያዘጋጃል፡፡ 3. የፍርድቤት አቤቱታ መስሚያ፣ የጋራ የማቀድ ስብሰባዎች ወዘተ ማስታወቂያ በወቅቱ ማግኘትዎን ያረጋግጣል፡፡ 4. በሚከተሉት ላይ መረጃ ይሰጥዎታል፡ ሀ. የጉዲፈቻ እንክብካቤ ፈቃድ መስጫ እና መገኛ አድራሻ ለ. የስልጠና እድሎች ሐ. የ TANF የገንዘብ ጥቅሞች መ. የህክምና / Medicaid ሽፋን ሠ. ሌሎች የሚገኙ አገልግሎቶችን 5. የቤተሰብ ቤቱ ላይ ጥናት ማድረግ፡፡ ልጁ/ወጣቱ በ DCYF አያያዝ ስር ስለሆነ የሚከተሉት ከሆኑ ፍርድቤቱ ሊያስወግደው ይችላል፡ • ምደባው የልጁ/ወጣቱን ጥቅም/ፍላጎት የማያስከብር መሆኑ ከተወሰነ፣ • የዚህ ስምምነት ማንኛውም አካል ከተጣሰ፣ • የልጁ/ወጣቱ የድንገተኛ ጊዜ ምደባ መቀጠል እንደማይችል ከተወሰነ ወይም • የዘመድ ወይም ምቹ የሆነው ሰው ቤት ለምደባ ተቀባይነት ካላገኘ፡፡ የልጁን መረጃ/የምደባ ጥቆማ ቅጽ (DCYF 15-300) ቅጂ ተቀብያለሁ፡፡ አዎ አይ የጨቅላ ደህንነቱ ተጠብቆ አተኛኘት መመሪያዎች ላይ ውይይት አድርገናል እንዲሁም የጨቅላ ደህንነቱ ተጠብቆ አተኛኘት መመሪያዎች ቅጽ DCYF 22-1577 ቅጂ ተሰጥቶኛል፡፡ አዎ አይ ተገቢነት የለውም | ||
እንክብካቤ ሰጪ ቀን | እንክብካቤ ሰጪ ቀን | የተመደበ የጉዳይ ሰራተኛ ቀን |
ስርጭት፡ የእንክብካቤ ሰጪ ግብዐት የቤተሰብ፣ የልጅ መዝገብ