ለኢንቨስትመንት ኮሚቴው በሚቀርብ ሪፖርት ውስጥ የተካተተ አካባቢያዊና ማሕበራዊ መረጃ አጠቃላይ መግለጫ የናሙና ክፍሎች

ለኢንቨስትመንት ኮሚቴው በሚቀርብ ሪፖርት ውስጥ የተካተተ አካባቢያዊና ማሕበራዊ መረጃ አጠቃላይ መግለጫ. ለሶስቱም የ CIO ፈንዶች እያንዳንዳቸው አግባብነት ላላቸው የኢንቨስትመንት ኮሚቴ በሚቀርቡ ሪፖርቶች ውስጥ መካተት ያለባቸው አበይት ታሳቢ ጉዳዮች ማጠቃለያ ከዚህ በታች ቀርቧል፡፡ የልማት ፈንድ • በተገቢው ትጋት፣ በማስጠንቀቂያ ሪፖርት ወይም በሌሎች የ E&S ሪፖርቶች አማካይነት የተለዩ አበይት አካባቢያዊና ማሕበራዊ ስጋቶች ማጠቃለያ፡፡ • የፕሮጄክቱ ኩባንያ ለ E&S መስፈርቶች ያለው ቁርጠኝነት (የ E&S ተግባራትና ኃላፊነቶችን መግለጽ፣ የፖሊሲ መግለጫ፣ የስነ-ምግባር ደንብ፣ አግባብነት ያላቸው የሕግና ሌሎች መስፈርቶችን መረዳት የመሳሰሉ ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው የ E&S አስተዳደር አደረጃጀቶችን ጨምሮ)፡፡ የግባታ እኩልነት የገንዘብ ድጋፍ • በ ESIA፣ ESAP እና ሌሎች የ E&S ሪፖርቶች አማካይነት የተለዩ አበይት የአካባቢና ማሕበራዊ ስጋቶች ማጠቃለያና አበይት የ E&S ስጋቶችን ለማስተዳደር የሚያስችል/ሉ ዕቅድ/ዶች ስለመኖራቸው ማረጋገጫ፡፡ • ፕሮጄክቱ ሁሉንም አግባብነት ያላቸው IFC PS ስለመተግበሩ፣ የፕሮጄክት ደረጃ ESMS ስለመዘርጋቱና ግንባታ ከመጀመሩ በፊት አስፈላጊ የሆኑ ፈቃዶች በሙሉ ስለመገኘታቸው ማረጋገጫ፡፡ እንደገና መልሶ በገንዘብ ራሱን መደገፍ • በ ESIA፣ ESAP፣ ESMS እና ሌሎች የ E&S ሪፖርቶች አማካይነት የተለዩ አበይት የአካባቢና ማሕበራዊ ስጋቶች ማጠቃለያና አበይት የ E&S ስጋቶችን ለማስተዳደር የሚያስችል/ሉ ዕቅድ/ዶች ስለመኖራቸው ማረጋገጫ፡፡ • ፕሮጄክቱ ለ E&S ስጋት አመራር ያለው ቀጣይ ቁርጠኝነት ማረጋገጫ፣ ብቃት ያለው የ E&S ፖሊሲ እና ESMS በስራ ላይ ስለመዋሉ ማረጋጫ እና የሕግና ሌሎች መስፈርቶች ስለመከበራቸው ማረጋገጫ፡፡