የዓላማዎች ክለሳ. የሰፈራ እና/ወይም ኑሮን ወደ ቀድሞ ሁኔታ የመመለስ ዕቅድን ዋነኛ ዓላማዎች እና የሰፈራ ትግበራና ኑሮን ወደ ቀድሞ ሁኔታ የመመለስ (ለምሳሌ፡ የመጀመሪያ ደረጃና ቀጣይነት ያለው ምክከር፣ የባለድርሻ ልየታና የሕዝብ ቆጠራ ዳሰሳ ጥናቶች፣ ማሕበረ-ኢኮኖሚያዊ የመነሻ ጥናቶች፣ አሳታፊ የዕቅድ ማውጫ ስብሰባዎች፣ የሳይት መረጣ ጥናቶች፣ ለትግበራ የሚሆኑ ድርጅታዊ መዋቅሮች) እና የሒደቱ ምዘና እና የውጤት ግምገማ (ማናቸውንም ጥቅም ላይ የዋሉ አሳታፊ የክትትልና የግምገማ ስነ-ዘዴዎችን ጨምሮ) አጠቃላይ መግለጫ ማስቀመጥ፡፡