የስያትል የስራ መስፈርት ቁጥጥር ቢሮ)- ለስደተኛ እና ለጥገኛ ለማገልገል ያለን ዝግጁነት OLS የጥገኛንና የስደተኛን መብት ይጠብቃል
የስያትል የስራ መስፈርት ቁጥጥር ቢሮ)- ለስደተኛ እና ለጥገኛ ለማገልገል ያለን ዝግጁነት OLS የጥገኛንና የስደተኛን መብት ይጠብቃል
የሲያትል Office of Labor Standards (OLS) በሲያትል ከተማ ውስጥ የስራ መስፈርትን ለማሻሻል ሁሉንም የሲያትል ሰራተኞችና ነጋዴዎችን ለማገልገል ዝግጁ ነው፡፡ በስደተኞችና በጥገኞች ላይ የሚያጋጥም የደሞዝ ስርቆት ሰፋ ያለና በብዛት የማይዘገብ ነው፡፡ OLS የስደተኝነት ሁኔታዎችን ሳያይ ለሁሉም ሰዎች በነጻ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ እነዚህ አገልግሎቶች የተፈጠሩ የስራ መደብ መተላለፎችን መመርመር፣ ሰራተኞችንና ነጋዴዎችን እየወጡ ማግኘት፣ መረጃዎችን እና እርዳታ ወደሚገኝበት መምራትን ማቅረብ ያጠቃልላል፡፡
ለሲያትል ስደተኛ እና ጥገኛ ማህበረሰቦች ጠቃሚ መረጃዎች፡
❖ OLS በፍጹም ስለ ስደተኝነት ሁኔታ እና የስደተኝነት ሁኔታ ሰነዶችን አይጠይቅም እናም የስደተኝነት ሁኔታ ማህደር አይዝም፡፡
❖ OLS የነጻ የቋንቋ ማስተርጎምና የጽfhፍ ትርጉም አገልግሎት ይሰጣል፡፡
❖ OLS በሲያትል ከተማ ውስጥ የሚገኝ ከፌደራል መንግስት ጋር የማይገናኝዲፓርትመንት ነው፡፡
ሲያትል እንግዳ ተቀባይ ከተማ የሆነበት ምክንያት ሁሉንም በማጠቃለልና በእኩልነት ስለምናምን ነው፡፡ የከተማው ሰራተኞች ስለዜግነት ሁኔታ የማይጠይቁና ሁሉንም ነዋሪዎች የስደተኝነት ሁኔታ ሳይጠይቁ በእኩል የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ ስደተኞችና ጥገኞች እዚህ ተቀባይነት አላቸው፡፡
OLS የሰራተኞችን መብት ያስጠብቃል
የትም ይኑሩ የትም፣ በሲያትል ውስጥ የሚሰሩ ከሆነ፣ የስራ መስፈርት መብትዎ የሚያጠቃልሉት፡
• ቢያንስ በሲያትል ውስጥ ያለውን ዝቅተኛ የደሞዝ ክፍያ እንዲያገኙ ፤
• ለሰሩበት እያንዳንዱ ሰዓት ክፍያ እንዲያገኙ፤
• እርስዎ ወይም የቤተሰብዎ አባል ታሞ ከሆነ እና ስራ መሄድ ካልቻሉ የታማሚ ጊዜ ክፍያ የማግኘት መብት፤
• አሰሪዎ መበቴን ጥሷል ብለው ካመኑ ለ OLS የማመልት መብት፤ እና
• ለ OLS ካመለከቱ ወይም በምርመራ ውስጥ የሚሳተፉ ከሆነ ስምዎንና መረጃዎን ሚስጥራዊ የማድረግ መብት፡፡
OLS ሰራተኞች ላይ ከሚደረግ የበቀል ድርጊት ይጠብቃል
የሲያትል ህግ የስራ መስፈርያ ጥሰት ዘገባ ያቀረበ ሰራተኛ ላይ የሚደርስን የበቀል ድርጊት ይከላከላል፡፡ አሰሪዎች በሰራተኞቻቸው ላይ የበቀል ድርጊት በሚከተሉት መንገድ የሚያደርጉ ከሆነ ህገወጥ ነው፡
• ለኢሚግረሽን ባለስልጣን አንድ ሰራተኛ ወይም የቤተሰብ አባላቱ ህጋዊ ሰነድ እንደሌላቸው ማሳወቅ ወይም ማስፈራራት፤
• ከመንግስት ኤጀንሲ ጋር የውሸት ሪፖርት ማቅረብ፤ እና
• ከስራ ሓላፊነት ደረጃ መቀነስ ወይም ማባረር፡፡
ምንም እንኳን ለእኛ የስራ መስፈርት ቅሬታ በማቅረብዎ ምክንያት የበቀል ድርጊት እንደማይደርስብዎ ባናረጋግጥም፣ በሰራተኞች ላይ የበቀል ድርጊት በሚያደርጉ አሰሪዎች ላይ ግን ተገቢውን ቅጣት እንዲቀበሉ እናደርጋለን፡፡ የበቀል ድርጊት እንደ ደረሰብዎ ወይም የስራ መስፈርት ጥሰት እንደደረሰብዎ የሚያስቡ ከሆነ ወይም ስለ መብትዎ ጥያቄ ካለዎት OLS ን በ ሚቀጥለው አድራሻ ያግኙ፡ 000-000-0000, xxxxxxx.xxxxxxxxxxxxx@xxxxxxx.xxx፣ ወይም xxxx://xxx.xxxxxxx.xxx/xxxxxxxxxxxxxx/xxxxxxx#xxxxxxx::
ንግድ ኖሮት ስለ ስራ
መስፈርት ጥያቄ ካለዎት OLS ን በሚቀጥለው አድራሻ ያግኙ፡ 000-000-0000 ወይም xxxxxxxx.xxxxxxxxxxxxxx@xxxxxxx.xxx.
OLS ከማህበረሰቡ እና ከንግድ ድርጅቶች ጋር የስራ መስፈርትን በተመለከተ እና የውጪ ግንኙነቶችን በተመለከተ የውል ስምምነት ያደርጋል፡፡ በቀጥታ OLS ን ማግኘት ምቾት የማይሰጥዎት ከሆነ፣ ስለ መብትና ግዴታዎት ያለዎትን ጥያቄዎች አንዱን አጋራችንን በማግኘት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ተጨማሪ መረጃዎች
በስራ ቦታ ላይ ለ ስደተኝነት ተፈፃሚነት ድርጊት እየተዘጋጁ ላሉ ሰራኞች እና ነጋዴዎች፡
• What to Do If Immigration Comes to your Workplace (ኢሚግሬሽን ወደ ስራ ቦታዎ ቢመጣ ምን ማድረግ እንዳለብዎ) (በእንግሊዘኛ፣ ስፓሽኒሽ፣ ታይ፣ ኮሪያን፣እና ቻይንኛ ማግኘት የሚቻል)፣ የቀረበው በ National Immigration Law Center (ብሄራዊ የኢሚግረሽን ህግ ማእከል) እና National Employment Law Project (ብሄራዊ የቅጥር ህግ ፕሮጀክት)፣ እና
• የኢሚግሬሽን ተፈጻሚነትን በመተመለከተ እገዛ, በዋሺንግተን ዋና ኣቃቤ ህግ የቀረበ፡፡
ለ ህጻን ሆነው በመጡ ላይ እርምጃ ማዘግየት ተቀባዮች
• የሲያትል ከተማ Office of Immigrant and Refugee Affairs (የስደተኞችና የጥገኞች ጉዳዮች ቢሮ) DACA ድረ ገጽ፣ መሰረታዊመረጃ እና ነጻ DACA (Deferred Action for Childhood Arrivals፣ ለመጡ ህጻናት የዘገየ ምላሽ) በሲያትል አካባቢ እና ዙሪያ በከተማው ማህበረሰብ እና በአጋሮች የሚዘጋጁ የእገዛ ኩነቶች፡፡
• Northwest Immigrant Rights Project (ኖርዝ ዌስት የስደተኛ መብቶች ፕሮጀክት) DACA መረጃ ገጽ፤ እና
• ብሄራዊ ድርጅት Here to Stay ጠቃሚ ድረ ገጽ፣ የአእምሮ ጤና አያያዝ ምክሮችን ጨምሮ፡፡
የህግ አገልግሎቶች
• የሲያትል-ኪንግ ካውንቲ የስደተኛ የህግ ጠበቃ ትስስር የነጻ የህግ አገልግሎትን ይሰጣል፡፡ ብቁ ለመሆን ዝቅተኛ ገቢ ያለዎትና በሲያትል ከተማ ውስጥ መስራት ይኖርብዎታል፡፡
ስለ ሲያትል የስራ መስፈርት እና ስለመብትዎ ጥያቄ ካለዎት OLS ን በሚከተለው ማግኘት ይችላሉ xxxxxxx.xxxxxxxxxxxxxx@xxxxxxx.xxx፣ ወይም 000-000-0000 ይደውሉ፡፡