Contract
በቪኤፍኤስ ግሎባል ለነዋሪዎች የካናዳ ቪዛ ማመልከቻ ማእከል (ካቪማማ) አገልግሎቶች የስምምነት ቅጽ እና የአጠቃቀም ውሎች
1. ካቪማማ ወደ ካናዳ ለመግባት ማመልከቻ ለሚያቀርቡ ደንበኞች በርካታአገልግሎቶች የአስተዳደር ድጋፍ አገልግሎቶችን እና የባዮሜትሪክ ስብሰባ አገልግሎት ይሰጣል።
በካቪማማ ለሚቀርቡ አገልግሎቶች የሚከፈሉ የአገልግሎት ክፍያዎች (በተገለጸው መሰረት) የካናዳ መንግሥት ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል ።
2. ተጠያቂነት
ቪኤፍኤስ ግሎባል ካቪማማን ጨምሮ የካናዳ መንግሥት ወኪሎች አይደሉም። ካቪማማ ሙሉ በሙሉ ራሱን የቻለ አካል ሲሆን ከካናዳ መንግስት ጋር በገባዉ ኮንትራት መሰረት እየተዳደረ አገልግሎቱን በሚሰጥበት ሃገር ህግጋት በመገዛት በራሱ አገልግሎቶች ላይ ብቻ ሃላፊነት ይወስዳል፡፡
ቪኤፍኤስ ግሎባል ፣ ካቪማማን ጨምሮ ፣ በቁጥጥሩ ስር ያሉትን ሁሉንም የግል መረጃዎች ለመሰብሰብ ፣ ለመጠቀም ፣ ለማከማቸት ፣ ለማቆየት እና ለመጠበቅ ሃላፊነት አለበት፡፡
3. የአገልግሎት ቋንቋ -
ካቪማማ አገልግሎቶችን እና ሁሉንም የግንኙነት ሰርጦች በእንግሊዝኛ እና/ ወይም ፈረንሳይኛ እና በዋናው የአከባቢ ቋንቋ (ዎች) ይሰጣል፡፡
4. የግል መረጃን በተመለከተ ማሳሰቢያ -
የካቪማማ አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንደመሆኔ ፣ እንደሚከተለዉ ተረድቻለሁ እና ተስማምቻለሁ-
ይህንን ሰነድ ሙሉ በሙሉ አንብቤዋለሁ። ካቪማማ ማመልከቻዎችን ለአይአርሲሲ በማቅረብ ዙሪያ አስተዳደራዊ ድጋፍ እንደሚሰጥ እና አገልግሎቱ በዚህ ሰነድ ውስጥም እንደተገለጸዉ በቪኤፍኤስ ግሎባል እና የካናዳ መንግስት መሀል በተደረገዉ ውል ላይ በተቀመጡት ውሎች እና ሁኔታዎች መሠረት ብቻ የቀረበ መሆኑን ተረድቻለሁ፡፡ ቪኤፍኤስ ግሎባል በቪዛ ማመልከቻዎች ላይ የውሳኔ አሰጣጥ ኃይል ወይም ተጽዕኖ የለውም።
በካቪማማ የሚሰበሰበዉ የግል መረጃ በቪኤፍኤስ ግሎባል አገልግሎቶች እና በካናዳ መንግስት መካከል በተገባ የዉል ሥልጣን መሠረት ሲሆን ይህም የካናዳ የግላዊነት ህጎችን ማክበር ያጠቃልላል። የውሉ ስልጣኑ ማንኛውንም የተፈቀደለት ንዑስ ተቋራጭ ያጠቃልላል፡፡
የካናዳ ቪዛ ፣ ፈቃድ ወይም የጉዞ ሰነድ ማመልከቻዬን ሂደት ለመደገፍ እንዲሁም እንደዚህ ያሉ ሰነዶችን እና መረጃን ወደ እና ከካናዳ መንግስት ለማስተላለፍ ሲባል ብቻ ካቪማማ ሰነዶችን ከእኔ እንደሚቀበል እና ከእኔ ጋር የተዛመደ የግል መረጃ ይሰበስባል፡፡
በተጨማሪም “በተዘዋዋሪ ለማስረከብ እና/ወይም ለመሰብሰብ ፍቃድ መስጫ” ውስጥ ከታች ተመልክቶ ከሆነ፤ ሰነዶቼን እና የግል መረጃዬን ለመቀበል/ለመስጠት ለካቪማማ ፈቃዴን ከ/ወደ “በተዘዋዋሪ ለማስረከብ እና/ወይም ለመሰብሰብ ፍቃድ መስጫ” ውስጥ ለተጠቀሰው ሰው ፈቃዴን ሰጥቻለሁ፡፡
የእኔ የግል መረጃ የማመልከቻ ቅጼን ፣ ደጋፊ ሰነዶችን ፣ የጣት አሻራዎች እና ፎቶግራፎች እና ሌሎች የባዮሜትሪክ መረጃዎች ፣ ለካናዳ መንግስት እንዳስፈለገ፤ ሊያካትት ይችላል። እንዲሁም የግል መረጃዬ ተዛማጅ የማመልከቻ ፣ ማንነት ፣ የሕይወት ታሪክ እና የማዉቃቸዉ ሰዎች ዝርዝር ፣ የኤሌክትሮኒክ መዝገቦችን ጨምሮ ወይም ከማመልከቻዬ ጋር የተዛመደ መረጃን ሊያካትት ይችላል።
ካቪማማ በቪኤፍኤስ ግሎባል እና በካናዳ መንግሥት መካከል ባለው ውል መሠረት በተለያዩ የካናዳ ህጎች የተጠቀሱ የግል መረጃ ፣ ምስጢራዊነትን እና የጥበቃ መርሆዎች ማክበር አለበት። በካቪማማ በሚደረገዉ የእኔ የግል መረጃ አያያዝ ላይ ስጋቶች ካለኝ ካቪማማ በሚሰጠኝ የማግኛ መረጃ በመጠቀም ለካናዳ የግላዊነት ኮሚሽነር አቤቱታ የማቅረብ መብት እንዳለኝ ተረድቻለሁ፡፡
ካቪማማ የእኔን የግል መረጃ የሚሰበስበዉ ፣ የሚጠቀመው ፣ የሚገልጠዉ ከካናዳ መንግስት ጋር ያለው ውል እንደሚያዘው እና ለእኔ የአስተዳደር ድጋፍ አገልግሎቶችን እና እንዳስፈላጊነቱ የባዮሜትሪክ አሰባሰብ አገልግሎቶችን ለማቅረብ ብቻ እንደሆነ አዉቃለሁ፡፡
ካቪማማ ያለአይ.ሲ.ሲ.ሲ ፈቃድ የግል መረጃዬን ለሌላ አገልግሎት እንዳይጠቀም ወይም እንዳይገልጥ የካናዳ መንግስት ከልክሏል፤ ስለዚህም እንደዚህ ዓይነቱ ይፋ የማድረግ ሁኔታ ሊፈጸም የሚችለዉ በሕግ ከተጠየቀ እና በተጠየቀዉ ልክ ብቻ ይሆናል።
ስም አድራሻ ስልክ ቁጥር ኢሜል አድራሻ ፊርማ ቀን የተፈረመበት ቦታ (ከተማ፣ ሀገር)
በተዘዋዋሪ ለማስረከብ እና/ወይም ለመሰብሰብ ፍቃድ መስጫ (የቪዛ ማመልከቻ ለማስገባት ወይም መልስ ለመዉሰድ አመልካቹ ከራሱ ዉጭ የጉዞ ወኪል ወይም ተወካይ ከተጠቀመ ብቻ የሚሞላ) |
በ (ከተማ፣ ሃገር) የሚገኘው የካናዳ ቪዛ ማመልከቻ ማእከል ከ/ለ ሰነዶችን እንዲቀበል/እንዲሰጥ ተስማምቻለሁ። በእኔ ስም ማመልከቻ የሚያስገባዉ ወይም መልስ የሚቀበለዉ ግለሰብ ስም፡ ከአመልካች ጋር ያለው ዝምድና፡ የአመልካች ፊርማ፡ ቀን፡ |
በኤሌክትሮኒክ ማመልከቻ ቅፅ ላይ በካቪማማ ሰራተኞች እገዛ ባገኙ አመልካቾች ብቻ የሚፈረም ማሳወቂያ |
የማመልከቻ መረጃዬን ለማስገባት ከካቪማማ ሰራተኞች እገዛ አግኝቻለሁ። ለማመልከቻው አስፈላጊ የሆኑ መረጃና መልሶችን በሙሉ ሰጥቻለሁ። የተጠናቀቀውንና የታተመውን የማመልከቻ ቅፅ አንብቤዋለሁ፣ የቀረበው መረጃ እውነት እንደሆነና ፣ ለማመልከቻዬ የሚረዱ ያቀረብኳቸው ሰነዶችም እውነተኛና በምንም መንገድ ያልተለወጡ መሆናቸውን አረጋግጫለሁ። የአመልካች ስም፡ የአመልካች ፊርማ፡ _ ቀን |
ባዮሜትሪክስ መስጠት የሚሹ አመልካቾች
የካናዳ መንግስት ድረገጽ ላይ የቀረበዉን የባዮሜትሪክስ አገልግሎት ግዜ እና አስፈላጊነት መገምገሚያ እንደገመገምኩ እና በየካናዳ መንግስት ድረገጽ ላይ በተሰጠው መረጃ መሠረት የባዮሜትሪክስ ምዝገባዬን እንደምሰጥ አረጋግጣለሁ፡፡ ይህን ውሳኔ የወሰንኩት በራሴ ፈቃድ እና ያለ ካቪማማ ሰራተኞች ተጽዕኖ ወይም አስተያየት ነው።
ስም፡
ፊርማ፡
ቀን፡
ባዮሜትሪክስ መስጠት የማይፈልጉ አመልካቾች
የካናዳ መንግስት ድረገጽ ላይ የቀረበዉን የባዮሜትሪክስ አገልግሎት ግዜ እና አስፈላጊነት መገምገሚያ አንብቤ የባዮሜትሪክስ ምዝገባዬን ላለመስጠት ወስኛለሁ፡፡ ይህን ውሳኔ የወሰንኩት በራሴ ፈቃድ እና ያለ ካቪማማ ሰራተኞች ተጽዕኖ ወይም አስተያየት ነው። ይህ ዉሳኔየ ተጨማሪ ግንኙነት ከአይአርሲሲ ሳይደረግ ማመልከቻየ ሊከለከል እንደሚችል አዉቃለሁ፡፡
ስም፡
ፊርማ፡
ቀን፡