ማfhሌት ብዙነህ
83ኛ ዓመት ቁጥር 079 ኅዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም ዋጋ 10.00
ብዕራችን ለኢትዮጵያ ህዳሴ ይተጋል!
ኢትዮጵያና ቼክ ሪፐብሊክ
ትብብራቸውን ለማጠናከር ስምምነት አደረጉ
ሳሙኤል ወንደሰን
አዲስ አበባ፦ ኢትዮጵያና ቼክ ሪፐብሊክ ትብብራቸውን ለማጠናከር ስምምነት አደረጉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ትናንትና በቼክ ሪፐብሊክ መንግሥት ጽሕፈት ቤትና በጠቅላይ ሚኒስትር ፔትር ፊያላ ይፋዊ የአቀባበል ሥነ ሥርዓት ተደርጎላቸዋል::
ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ ውይይታቸው በመከላከያ ዘርፍ የቆየ ትብብራቸውን በማስፋት በግብርና፣ በማዕድን ልማት እና ቱሪዝም ትብብራቸውን ለማጠናከር ወስነዋል።
የቼኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ባለፉት ቅርብ ሳምንታት ኢትዮጵያን በመጎብኘት ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር ውይይት አድርገው እንደነበር ይታወሳል።
በተያያዘም በ20ኛው የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ጉባኤ ኢትዮጵያ ልዩ ተምሳሌት ሆና ለአዳጊ ሀገሮች ተሞክሮዋን ማቅረቧን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሠ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ልዑካን ቡድናቸው በ20ኛው የተባበሩት
መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ጉባኤ
ኢትዮጵያና ቼክ ... ወደ ገጽ 4 ዞሯል
በመዲናዋ
ከ11 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ሆነዋል
ገጽ 4
“ጠንካራ ርምጃ ካልተወሰደ ሙስና የሀገሪቱ የሕልውና ፈተና ሆኖ ይቀጥላል”
- አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ
አምባሳደር ደግፌ ቡላ
ወደ ፍርድ ቤት ከሚቀርቡ ጉዳዮች እልባት የሚያገኙት ከ30 በመቶ በታች ናቸው
ክፍለዮሐንስ አንበርብር
አዲስ አበባ - በኢትዮጵያ በአማካይ በየዓመቱ ወደ ፍርድ ቤት ከሚቀርቡ 7ነጥብ4 ሚሊዮን ጉዳዮች መካከል እልባት የሚሰጣቸው 2 ነጥብ2 ሚሊዮን ጉዳዮች(29.7 በመቶ) ብቻ መሆናቸው ተገለፀ::
ዋቅሹም ፍቃዱ
አዲስ አበባ፡- ሀገሪቱን እየተፈታተነ ባለው ሙስና ላይ ጠንካራ ርምጃ ካልተወሰደ የሕልውና አደጋ ሆኖ መቀጠሉ አይቀሬ ነው ሲሉ የኢትዮ-ኢንጂነሪግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ አስታወቁ::
አምባሳደር ሱሌይማን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፣ ባለፉት ሦስት አስርተ ዓመታት የተዘረጋው የሙስና ሰንሰለት ውስበስብ ከመሆኑም በላይ በአመለካከትም ሆነ በተግባር በትውልዱ ዘንድ በአጅጉ ሰርጿል::
ያለ ጥናት ፈተና ማለፍ፣ ያለ ውድድር ሥራ መቀጠር፣ ያለ ብቃት ማገልገል እና የመሳሰሉት ችግሮች ጠንካራ እርምጃ የሚሹ የሙስና መገለጫዎች ናቸው ያሉት አምባሳር ሱሌይማን፤ የቀድሞው የኢትዮጵያ ብረታብረት ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሽን/ሜቴክ የዛሬው የኢትዮ-ኢንጂነሪግ ግሩፕ 65 ቢሊዮን ብር የት እንደ
ገባ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም ብለዋል::
አምባሳር ሱሌይማን እንደገለጹት፤ ብሩ በግለሰቦች የተመዘበረ በመሆኑ በወቅቱ የነበሩ የተቋሙ አመራሮች ግማሾቹ ታስረዋል፤ ግማሾቹ ወደ ውጭ
ሀገር ሸሽተዋል:: ግለሰቦቹ በገንዘቡ በሀገር ውስጥ ያፈሩት ሀብት ስለሌላቸው በረቀቀ
መንገድ ከሀገር እንዳሸሹ ይታመናል ብለዋል:: ገንዘቡን ወደ መንግሥት ካዝና የመመለስ እድል
ወደ ፍርድ ቤት... ወደ ገጽ4 ዞሯል "ጠንካራ ርምጃ... ወደ ገጽ4 ዞሯል
አዲስ ዘመን
ረቡዕ ኅዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም
ዜና
ባለፉት አራት ወራት ከ193 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ
ፋንታነሽ ክንዴ
አዲስ አበባ፡- ባለፉት አራት ወራት 193 ነጥብ
98 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።
የገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ አይናለም ንጉሤ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ ሚኒስቴሩ የሚሰበስበው አጠቃላይ ገቢ ከዓመት ዓመት እያደገ መጥቷል። በዚህም ከሐምሌ 2015 እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2016 ባሉት አራት ወራት 193 ነጥብ 98 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ ተችሏል። ይህም አፈጻጸሙ የዕቅዱን 98 ነጥብ 78 በመቶ የሚሸፍን ነው ::
ከገቢው 129 ነጥብ 18 ቢሊዮን ብሩ ከሀገር ውስጥ ታክስ የተገኘ መሆኑን ጠቅሰው፤ 64 ነጥብ 79 ቢሊዮን ብር ከቀረጥና ታክስ የተሰበሰበ መሆኑን ተናግረዋል:: ገቢው ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ22 ነጥብ 74 በመቶ ብልጫ እንዳለው አመላክተዋል።
በተጠቀሰው ጊዜ 164 ነጥብ 22 ቢሊዮን ብር ወደ ገንዘብ ሚኒስቴር ፈሰስ ለማድረግ ታቅዶ 165 ነጥብ 11 ቢሊዮን ብር ማስተላለፍ ተችሏል ያሉት ወይዘሮ አይናለም፤ 14 ነጥብ 85 ቢሊዮን ብር ደግሞ ወደ ክልሎች ተላልፏል ብለዋል::
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አገልግሎትን ሥራ ላይ በማዋል ግብር ከፋዮች የተቀላጠፈ
ወይዘሮ አይናለም ንጉሤ
አገልግሎት እንዲያገኙ ሲሠራ መቆየቱን ጠቅሰው፤ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 18 ሺህ 652 ግብር ከፋዮች በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ሥርዓት ክፍያ ፈጽመዋል:: 19 ባንኮችም ወደ ሥርዓቱ እንዲገቡ ተደርጓል ነው ያሉት::
በተጨማሪም ሁለት ሺህ 143 ግብር ከፋዮች ሰባት ነጥብ 21 ቢሊዮን ብር በቴሌ ብር አማካኝነት የግብር ክፍያ መፈጸማቸውን ገልጸዋል::
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የኮንትሮባንድ ንግድን ለመከላከል የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል ያሉት ሚኒስትሯ፤ ባለፉት አራት ወራት ከገቢ ኮንትሮባንድ ሦስት ነጥብ አራት ቢሊዮን ብር፣ ከወጪ ኮንትሮባንድ አንድ ነጥብ
ሦስት ቢሊዮን ብር በድምሩ አራት ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የተለያዩ ዕቃዎችንና ሕገወጥ ገንዘቦች መያዛቸውን ገልጸዋል::
የታክስ አስተዳደሩን ኮንትሮባንድ፣ ደረሰኝና ሕገ-ወጥ ንግድ እየፈተኑት መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሯ፣ በአራት ወራት በኮንትሮባድና ሕገ-ወጥ ንግድ ተጠርጥርው ከተያዙ 312 ተጠርጣሪዎች ውስጥ በ258ቱ ላይ አስተማሪ እርምጃ መወሰዱን አመልክተዋል::
በገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ የተያዘው ዕቃ ግምት ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ32 ነጥብ 94 በመቶ ብልጫ አለው ብለዋል::
ኮንትሮባድና ሕገ-ወጥ ንግድ ለኅብረተሰቡ አስከፊነቱን የማስገንዘብ ሥራዎች ትኩረት የሚሰጣቸው መሆኑን ገልጸው፤ ለሕግ ተገዥ የማይሆኑትን ግን የታክስ ሕጉ በሚፈቅደው ልክ እርምጃ እንደሚወሰድም አመልክተዋል:: ለአፈፃጸም ውጤታማነት በገቢዎች ሚኒስቴር እና በጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮች እና ሠራተኞች እየዳበረ የመጣው ጠንካራ የሥራ ባሕልና ቅንጅታዊ አሠራር ጉልህ ድርሻ እንደነበረው ገልጸው፤ ለውጤቱ መገኘት ድርሻ
ለነበራቸው ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል::
ገቢዎች ሚኒስቴር በ2016 በጀት ዓመት 529 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ ወደ ሥራ መግባቱን መግለጹ ይታወሳል::
ፋይዛ መሐመድ
ሴቶች ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት ጉልህ ድርሻ ማበርከት ይጠበቅባቸዋል
ልጅዓለም ፍቅሬ
ለሀገር ዕድገት እንቅፋት የሆነውን ሙስና ለማጥፋት የተቀናጀ ጥረት ያስፈልጋል
ሚኒስትር ዴኤታ ግልጽነትና ተጠያቂነት በማስፈን ጥራት ያለው አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አመላክተዋል።
መስከረም ሰይፉ
አዲስ አበባ፡- ሴቶች የተዛባ ትርክትን በማረቅና የተጀመረውን የምክክር ሂደት ስኬታማ በማድረግ ረገድ ጉልህ ድርሻ ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ሕጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለጸ::
አዲስ አበባ፡- ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ዋነኛ እንቅፋት የሆነውን ሙስና ለማጥፋት ሁሉም ዜጋ የተቀናጀ ጥረት ሊያደርግ እንደሚገባ የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማ ገለጹ፡፡
የቱሪዝም ሚኒስትር ከተጠሪ ተቋማት ጋር ‹‹ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፤በኅብረት እንታገል›› በሚል መሪ ሃሳብ የፀረ-ሙስና ቀንን ትናንት አክብሯል፡፡
በዕለቱ በተደረገው የፓናል ውይይት የተገኙት የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማ እንደገለጹት፤ ሙስና ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ዋነኛ እንቅፋት በመሆኑ ሁሉም አካላት በጋራ ሊከላከሉት ይገባል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ ሙስናን ለመዋጋት እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች አበረታች ናቸው ያሉት አቶ ስለሺ፤ ነገር ግን ሙስና በመንግሥት በሚወሰዱ ርምጃዎች ብቻ መቀነስ ስለማይቻል የሁሉም ተቋማትና የእያንዳንዱ ዜጋ ድርሻ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
አሁን ላይ በሀገሪቱ ላለው የኑሮ ውድነትና ውስብስብ ችግር ሙስና ከፍተኛ ድርሻ እንደሚወስድ አቶ ስለሺ ጠቁመው፤ በኢኮኖሚው፣ በማኅበራዊውና በፖለቲካው
አቶ ስለሺ ግርማ
ዘርፍ ብቁ ትውልድ እንዳይፈጠር እንዲሁም በሁሉም ዘርፍ ሀብትን ለመፍጠር ሙስና እክል ፈጥሮ መቆየቱን አስረድተዋል።
እንደ አቶ ስለሺ ገለጻ፤ እንደ ሀገር ሙስናን ለመዋጋት በተሠሩ ሥራዎች ሕገ-ወጥ የቅርስ ዝውውር፣ የብሔራዊ ፓርኮች የመሬት ወረራ እንዲሁም ሕገ-ወጥ የዱር እንስሳት ዝውውር እንዲቀንስ ተደርጓል ያሉ ሲሆን፤ የቱሪዝም
የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው (ረ/ፕ)፤ በበኩላቸው ሙስና ለመቀነስ ለአንድ ለተወሰነ ተቋም ብቻ የሚሰጥ ተግባር ባለመሆኑ የሃይማኖት ተቋማት፤ ሚዲያዎች፣ ኅብረተሰቡ እንዲሁም ሁሉም የመንግሥት ተቋማት ሙስናን በጋራ መከላከል እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
ሙስና ሀገሪቱ ከሚፈትኗት ጉዳዮች አንዱ ነው መሆኑን አንስተው፤ የሰላም እጦት እንዲከሰትና አለመግባባቶች እንዲካረሩ ሙስና ጉልህ ተፅዕኖ እንዳለው በመረዳት ችግሩን ለመቅረፍ መሥራት ይገባል ሲሉ አስረድተዋል።
አሁን ላይ ሙስና ፖለቲካዊ ጫና እያሳደረ መሆኑን ጠቁመው፤ ሙስናን ለመከላከል የጋራ ጥረት ወሳኝ ነው ብለዋል።
በፓናል ውይይቱ የሙስና ምንነት፣ አጋላጭ ተግባራትና በሀገርና በሕዝቦች ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖ ዙሪያ ሰነድ ቀርቦ ወይይት ተደርጎበታል።
የዘንድሮ የፀረ-ሙስና ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ “ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፤ በኅብረት እንታገል” በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ
የሴቶች አደረጃጀቶች በክፍለ ከተማና በወረዳ ደረጃ ሲያከብሩት የቆዩት የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን የንቅናቄ ፕሮግራም በከተማ አቀፍ ደረጃ የማጠቃለያ ፕሮግራም በትናንትናው ዕለት አካሂዷል::
የአዲስ አበባ ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ፋይዛ መሐመድ እንደገለጹት፤ የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት የፀደቀበት፣ የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ኅዳር 29 ሲከበር የሴቶች መብት ከሕገ መንግሥት ጀምሮ በተለያዩ ሕግ ማዕቀፎች ውስጥ እውቅና የተሰጠበት መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ነው ።
በተለይ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 9/4 መሠረት ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች በሀገሪቱ የሕግ አካል ይሆናሉ ብሎ የደነገገ በመሆኑ በስምምነቱ የተዘረዘሩትን የሴቶች መብት ማክበርና የማስከበር ኃላፊነት የመንግሥት የትኩረት አቅጣጫ ሆኖ እየተተገበረ ይገኛል ብለዋል::
በኅብረ ብሔራዊ የፌደራል ሥርዓት የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ለማሳደግና ስለ ሴቶች ያሉ ጎጂ ልማዳዊ አመለካከቶችን ለመቀየር ብዙ መሥራት ይገባል ያሉት ምክትል አፈጉባኤዋ፤ የፖለቲካ ምሕዳሩ ሴቶችን
መመሪያው ማኅበራቱ ስጋት ሳይሆን የፀጥታ ዘብ
የሚሆኑበትን ሥርዓት የሚፈጥር ነው
የሚያካትትና የውሳኔ ሰጪነት አቅም የሚያጎለብት መሆን እንደሚኖርበት አመልክተዋል::
በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ብዝኃነት መገለጫቸው በሆኑ ሀገራት ለሁሉም ማንነቶች እውቅና በመስጠት
ማfhሌት ብዙነህ
አዲስ አበባ፡- አዲሱ የጫኝና አውራጅ መመሪያ ማኅበራቱ ለማኅበረሰቡ ስጋት ሳይሆን የፀጥታ ዘብ የሚሆኑበትን ሥርዓት የሚፈጥር መሆኑን አዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ::
አዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የጫኝና አውራጅ ማኅበራት የአገልግሎት አሰጣጥን ለመከታተልና ለመቆጣጠር በወጣው አዲሱ መመሪያ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ትናንት ውይይት ተካሂዷል::
በውይይት መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ እንደገለፁት፤ የከተማው ነዋሪ ከጫኝና አውራጆች አሠራር ጋር በተያያዘ የተለያዩ ቅሬታዎች ሲያቀርብ ይደመጣል:: ይህም ለፀጥታ መደፍረስ እና መጉላላት ምክንያት ሆኖ ቆይቷል:: ከዚህ መነሻነት አዲሱ መመሪያ የጫኝና አውራጅ ማኅበራት የአገልግሎት አሰጣጥ ለመከታተልና ለመቆጣጠር የሚያስችልና ከዚህ በፊት ሲነሱ የነበሩ ችግሮችን የሚፈታ ነው::
ቢሮው ጫኝ እና አውራጅ ማኅበራትን መልሶ
በማደራጀት እና ሕገወጦችን ወደ ሕጋዊነት በማምጣት በሕግና ሥርዓት እንዲተዳደሩ ለማድረግ ሲሠራ መቆየቱን ኃላፊዋ አመልክተው፤ የተዘጋጀው አዲሱ የመተዳደሪያ መመሪያ በጫኝ እና አውራጅ ሥራ ላይ ይነሳ የነበረውን ችግር በመፍታት ማኅበረሰቡ ሰላማዊና የንብረት ደህንነት የተረጋገጠ አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል ::
ማኅበራቱም በመመሪያው መሠረት በተደራጁበት ዓላማ ብቻ በመሥራት ለማኅበረሰቡ ስጋት ሳይሆን የሰላማዊ አገልግሎት እንዲሰጡ እንደሚያስችል ገልጸው፤ ማኅበራቱ ሥራቸውን ሕግና ሥርዓት በተከተለ መልኩ ስለሚሠሩም ከኅብረተሰቡ ጋር የሥራ አጋርነት ለመፍጠር የሚረዳ መሆኑን አስታውቀዋል::
መመሪያው ማኅበራትን ከማደራጀት ጀምሮ ከአገልግሎቱ ላይ የሚያጋጥሙ ቅሬታዎችን የሚፈታ፣ የሕግ ተጠያቂ የሚያሰፍን መሆኑን ጠቁመው፣ ያለአግባብ ክፍያንና አስገዳጅ አሠራርን የሚያስቀር እንደሆነም ጠቅሰዋል:: ከዚህ አኳያ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የመመሪያውን ጽንሰ ሀሳብ በመረዳት መተግበር ይኖርባቸዋል ብለዋል::
በመድረኩ ላይ በመመሪያው ዙሪያ ማብራሪያ የሰጡት የቢሮው ቴክኒካል አማካሪ አቶ ማስረሻ ሀብቴ በበኩላቸው
መመሪያው ከመዘጋጀቱ በፊት በመዲናዋ አንድ ሺህ 078 በሕጋዊ መንገድ እና 550 ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ የተደራጁ ማኅበራት የነበሩ መሆኑን አስታውቀው፤ መመሪያው ማኅበራቱን ለመከታተል እና ለመቆጣጠር ተዘጋጅቷል ብለዋል::
መመሪያው በጫኝና አውራጅ የተደራጁ ማኅበራት በባለንብረቱ ሙሉ ፍቃድ አገልግሎት ማግኘት የሚችል መሆኑን የሚፈቅድ መሆኑን አመልክተው፤ በየአካባቢው በተደረገ የገበያ ጥናት መሠረት በተቀመጠ አማካይ ዋጋ መሠረት አገልግሎቱን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ ያስችላል ነው ያሉት::
የጫኝና አውራጅ ማኅበራት ከአስር እስከ 12 አባላትን በማካተት በሚኖሩበት አካባቢ መደራጀት የሚችሉ መሆኑን ጠቁመው፤ በተሰጣቸው ሕጋዊ ፍቃድ ለሁለት ዓመታት ያህል አገልግሎት መስጠት የሚችሉ መሆኑንም አስታውቀዋል::
በመድረኩ ላይ በከተማው በተመረጡ አራት ክፍለ ከተሞች ላይ በተካሄደ የጫኝ እና አውራጅ ምልከታ የተስተዋሉ ክፍተቶች እና ጥንካሬዎች ላይ ውይይት ተደርጎ ወደፊት የተሻለ ልምድ የሚወሰድበት እንደሚሆን ተመልክቷል::
አካባቢያቸውን የማልማት አቅም መሠረት በማድረግ የማደግ እድል በመፍጠር ቋንቋቸውን፣ ባሕላቸውንና ታሪካቸውን በፆታ እኩልነት የሚገለጹበትን የፖለቲካ ምሕዳር ማስፈን አስፈላጊ መሆኑ አጽንዖት ሰጥተዋል::
ኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ያለ ፆታ ልዩነት በገዛ ፈቃዳቸው የገነቧት የጋራ ቤታቸው መሆኗን ፋይዛ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ሕጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ኃላፊ ወይዘሮ ወይንሸት ዘሪሁን በበኩላቸው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን መከበሩ ብዝኃነት ባለባት ኢትዮጵያ ልዩነታችን ውበታችን አንድነታችን መጋመጃችን ሆኖ ለማስቀጠል ወሳኝ ነው ብለዋል።
ወይዘሮ ወይንሸት ሰላምና መረጋጋት በሌለበት ሀገር ውስጥ ዋነኛ ተጎጂ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን በመግለጽ፣ ሀገሪቱ የጀመረችው የሰላም መንገድና የብልጽግና ጉዞ አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል:: ሴቶች ከዋና ሥራቸው ጎን ለጎንም አንድነትን በመስበክ፣ ሀገሪቱ የጀመረችውን የምክክር ሂደት ስኬታማ እንዲሆንና የተዛባ ትርክትን በማረቅ ረገድ ጉልህ
አስተዋፅዖ ማበርከት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
አዲስ ዘመን ረቡዕ ኅዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም
ገጽ 3
ዜና
አብርኆት በቀን እስከ 15 ሺህ አንባቢያን እያስተናገደ ነው
- ከኅዳር 17 ጀምሮ የ24 ሰዓት አገልግሎት መስጠት ጀምሯል
ዳግማዊት አበበ
አዲስ አበባ ፡- አብርኆት ቤተ-መጽሐፍት የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት በቀን እስከ 15 ሺህ አንባቢያን እያስተናገደ መሆኑን አስታወቀ:: ቤተ- መጽሐፍቱ ከኅዳር 17 ጀምሮ የ24 ሰዓት አገልግሎት መስጠት መጀመሩም ተገልጿል::
የአብርኆት ቤተ-መጽሐፍት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ውብአየሁ ማሞ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት፤ አብርኆት ቤተ-መጽሐፍት የአገልግሎት አድማሱን እያሰፋ ዛሬ በቀን እስከ 15 ሺ አንባቢያን የሚስተናገዱበት ተቋም ሆኗል::
ቤተ-መጽሐፍቱ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ከታኅሣሥ 24 ቀን 2014 ዓ.ም ጊዜ ጀምሮ እስከ ኅዳር 17 ቀን 2016 ዓ.ም ከ10 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ የንባብ ተጠቃሚ ሆኗል ያሉት ዳይሬክተሩ፤ የንባብ አገልግሎት መስጠት በጀመረበት ጊዜ ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት 12 ሰዓት ድረስ ለንባብ ክፍት ሆኖ ሲያገለግል ቆይቷል ብለዋል::
ነገር ግን በተደጋጋሚ ጊዜ ተጠቃሚው
በሚያቀርበው ጥያቄ መሠረት ከኅዳር 17 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለ24 ሰዓት ያልተቋረጠ አገልግሎት መስጠት እንዲጀመር ተደርጓል ሲሉ አስታውቀው፤
ይህ የሚያሳየው በሃገራችን ምን ያህል የአብያተ- መጽሐፍት እጥረት እንዳለ እንጂ አንባቢ እንዳልጠፋ ነው ሲሉ ገልጸዋል::
እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፤ በብዙ ቦታዎችና ጉባኤዎች፣ በመደበኛም ሆነ በኢ-መደበኛ ውይይቶች “አንባቢ ጠፋ፣ የንባብ ባህል ወደቀ” ሲባል ተደጋግሞ ይሰማል:: ይሁን እንጂ ትልቁ ችግር የሚያነብ ሰው እጥረት ሳይሆን የሚያነቡበት ቦታ መጥፋት ነው::
አብርኆት ቤተ-መጽሐፍት እጅግ የተመረጡ የተፈጥሮ ሳይንስና የማኅበራዊ ሳይንስ፣ የቋንቋና የሥነ-ጥበብ መጽሐፍትን በመያዙ የተለያዩ አንባቢዎችን ፍላጎት ለማርካት እየጣረ ይገኛል ያሉት ዳይሬክተሩ፤ በእድሜ ደረጃም ለሕጻናት፣ ለታዳጊዎች፣ ለወጣቶች፣ ለጎልማሶችና ለሽማግሌዎች የሚሆኑ ይዘቶች ያሏቸው መጽሐፍት ክምችት አለ ብለዋል ::
አክለውም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይህንን ለንባብ የሚተመውን ሕዝብ ይረዳው ዘንድ ቁጥር 2 የአብርኆት ቤተመጽሐፍት ለመገንባት ሙሉ ሥራውን አጠናቆ በዝግጅት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።
“የማዕድን ኤክስፖው ምርቶቻችንን በስፋት በማስተዋወቅ የገበያ ትስስር
እንድንፈጥር አስችሎናል”
- የማዕድን አምራችና አከፋፋዮች
በጅግጅጋ ለሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል
ሄለን ወንድምነው
አዲስ አበባ፡- ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የማዕድንና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ምርቶቻችንን በስፋት በማስተዋወቅ የተሻለ የገበያ ትስስር እንድንፈጥር አስችሎናል ሲሉ የማዕድን አምራችና አከፋፋዮች ገለጹ::
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተከፈተው ሁለተኛው የማዕድንና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ትናንትና ተጠናቋል::
ከዋርካዬ የኦፓል አምራች ማኅበር የመጡት አቶ ፍቃዱ መልካሙ እንዲሁም የሥራ ለዕድገት ማኅበር የኦፓል ማዕድን አምራችን ወክለው በኤክስፖው
ተጠቃሚዎችና ከዘርፉ ተዋንያን ጋር አስተዋውቆናል ያሉት ወይዘሮ ኤልሳቤት፤ በዚህም የዘርፉን ተሞክሮ መቅሰም ችለናል ሲሉ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ያላትን የማዕድን ሀብት በመለየት በአግባቡ የመጠቀም ችግር መኖሩን ገልጸው፤ በሀገሪቱ በርካታ ማዕድናት ቢኖሩም በብዛት የምንጠቀመው ከውጭ ሀገር በማስገባት ነው፤ ይህ ደግሞ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ፣ የማዕድን አምራቹንና አከፋፋዩን በእጅጉ እየጎዳ ይገኛል ሲሉ አስረድተዋል።
በሀገሪቱ ያለውን የማዕድን ሀብት በሚገባ በማስተዋወቅና የገበያ ትስስር በመፈጠር ሀብቱን በአግባቡ ለመጠቀም የሀገር ውስጥ ፍላጎታችንን
ማርቆስ በላይ
አዲስ አበባ፡- በሀገር አቀፍ ደረጃ በጅግጅጋ ለሚከበረው 18ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የከተማዋ ከንቲባ ኢንጂነር ዚያድ አብዲ አስታወቁ።
ኢንጂነር ዚያድ አብዲ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ “ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሃሳብ ኅዳር 29 ቀን 2016 ዓ.ም በጅግጅጋ ከተማ ለሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል፡፡
ጅግጅጋ የተለያዩ ብሔሮች በአብሮነትና በወንድማማችነት ተቻችለው የሚኖሩባት ከተማ ናት ያሉት ከንቲባው፤ የከተማው ሕዝብ ለ18ኛ ጊዜ ለሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል እንግዶቹን ለመቀበል ዝግጅት ማድረጉን ተናግረዋል።
የከተማውን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ከነዋሪዎች ጋር ውጤታማ ሥራ መሠራቱን የገለጹት ከንቲባው፤ በዚህም የኢንቨስትመንት ተመራጭ ከተማ እንድትሆን ማስቻሉን ገልጸዋል።
ቀደም ሲል ጅግጅጋ የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን አስተናግዳ እንደነበር የሚናገሩት ከንቲባው፤ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ለማክበር የባሕል አምባሳደር ሆነው ወደ ከተማዋ የሚመጡ ዜጎችን በበቂ ሁኔታ ለማስተናገድ የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን አንስተዋል።
ለከተማው የሆቴል ባለቤቶች ጋር ውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ መካሄዱን ጠቅሰው፤ ሁሉም ሆቴሎች እንግዶችን ለመቀበል የሚያስችል ዝግጅት
ማድረጋቸውን እንዳሳወቁ አስረድተዋል።
በከተማዋ ለሚከበረው ሀገር አቀፍ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል ለመታደም የሚመጡ እንግዶችን ከኅዳር 29 ቀን አምስት ቀን በፊት ጀምሮ ባሉት ቀናት ለመቀበል የሚያስችል መርሐ ግብር መዘጋጀቱንም አስታውቀዋል።
ከበዓሉ ጎን ለጎን የከተማዋን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ለማሳየት ጥረት እንደሚደረግ አመላክተው፤ በአሁኑ ጊዜ የከተማዋ መሠረተ ልማት በተሻለ ሁኔታ ላይ የሚገኝ የሰላምና ፀጥታ ሥራዎችን ተጠናክረው የቀጠሉ በመሆኑ ከተማዋ ውጤታማ የኢንቨስትመንትና ቱሪዝም መዳረሻ እንደምትሆን ይጠበቃል ብለዋል።
ከለውጡ ወዲህ በጅግጅጋ እየተከናወኑ በሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች የከተማዋን ገጽታ በመቀየር ላይ መሆናቸውን ጠቁመው፤ ከአምስት ዓመት በፊት 14 ኪሎ ሜትር ብቻ የነበረውን የከተማዋ የመንገድ ሽፋን በማሳደግ ተጨማሪ 40 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ መገንባቱን ገልጸዋል።
ከለውጡ በፊት በነበረው አለመረጋጋት በርካታ ነዋሪዎች ከከተማው ወጥተው በሌሎች አካባቢዎች መቆየታቸውን አስረድተው፤ በርካታ ነዋሪዎች ወደከተማዋ በመግባት የተረጋጋ ሕይወት እየመሩ መሆኑንና በርካታ ኢንቨስተሮች ወደ ከተማዋ በመምጣት ላይ መሆናቸውን አብራርተዋል።
የከተማዋ ልማት በማደጉ የመሬት ይዞታዋ እያደገ መሆኑን ገልጸው፤ በአሁኑ ወቅት የከተማዋ ማስተር ፕላን የሚሸፍነው መሬት 25 ሺህ ሄክታር መድረሱን ከንቲባው አስታውቀዋል።
የተካፈሉትና አቶ ማስሬ ሐሰን ለኢፕድ እንደተናገሩት፤
ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የማዕድንና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ምርታችንን በማስተዋወቅና የተሻለ የገበያ ትስስር ለመፍጠር ያስችላል።
በኤክስፖው የማዕድን አምራቾች፣ ላኪዎች፣ የማዕድን ተጠቃሚዎች፣ የቴክኖሎጂ አምራችና አቅራቢዎች በአንድ ላይ በመገናኘታቸው ምርትና አገልግሎታችንን በማስተዋወቅ የገበያ ትስስር መፍጠር ችለናል ሲሉ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።
በኤክስፖው ለተሳተፉ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ዜጎች ምርታችንን በስፋት ለማስተዋወቅ ዕድል አግኝተናል ያሉት አምራቾቹ፤ የኦፓል ምርትን በባሕላዊ መንገድ አውጥን በዝቅተኛ ገቢ የምንሸጥ በመሆኑ በቀጣይ እሴት የተጨመረበት የኦፓል ምርት ለሀገር ውስጥ ተጠቃሚዎች መሸጥ የሚያስችል የገበያ አማራጭና ልምድ አግኝተናል ብለዋል::
የማዕድን ሀብቶችን በደንብ ማስተዋወቅ እንደሚገባ ገልጸው፤ በየዓመቱ ለሚዘጋጀው የማዕድን ኤክስፖ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ትኩረት ሰጥተውት ረዘም ላለ ጊዜ ማዘጋጀት ከቻሉ ከዘርፉ ይበልጥ ተጠቃሚ መሆን እንችላለን ሲሉ አስረድተዋል።
የማርብል፣ ግራናይትና ላይምስቶን አምራችና አከፋፋይ የሆኑት ኤልሳቤት ወርቁ በበኩላቸው እንዳስረዱት፤ ኤክስፖው ምርቶችን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር የማዕድን ተጠቃሚዎች በስፋት በማቅረብ ተጠቃሚ የምንሆንበትን ምቹ ሥነ-ምሕዳር የፈጠረ ነው።
ኤክስፖው ከአስመጪና ላኪዎች፣ ከውጪ ኩባንያዎች፣ ከቴክኖሎጂ አቅራቢዎች፣ ከማዕድን
ማሟላትና ከውጭ የሚገቡትን ምርቶች በሀገር ውስጥ መተካት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል::
የማዕድን ሀብቱን ለማስተዋወቅ የተጀመረው ዓለም አቀፍ ኤክስፖ ገዢ ደንበኞችን እንድናፈራ፣ ከሌሎች መሰል ድርጅቶች ጋር ተጨማሪ ልምድ እንድንቀስምና ዕድል ፈጥሮልናል ብለዋል::
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሁለተኛውን ዓለም አቀፍ የማዕድንና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ሲከፍቱ ኢትዮጵያ የወርቅ፣ የከበሩ ድንጋዩችና የበርካታ ውድ ማዕድናት መገኛ እንደሆነች ኤክስፖው አመላካች ነው:: በመሆኑም ተማሪዎች፣ ተመራማሪዎች፣ ነጋዴዎች፣ ኢንቨስተሮችና ሌሎችም በለድርሻ አካላት በዘርፉ ምን እንዳለና ምን እየተሠራ እንደሆነ በመማር ኢኮኖሚውን ሊደግፍ እንደሚገባ ማስገንዘባቸው የሚታወስ ነው::
ከ90 በላይ ኩባንያዎች በኤክስፖው የተሳተፉ ሲሆን የወርቅ፣ የድንጋይ ከሰል፣ የከበሩ ማዕድናት ጌጣጌጦች እንዲሁም የኢንዱስትሪ ማዕድን ቴክኖሎጂ ሲሚንቶና ብረት ይዘው ቀርበዋል:: ከኤክስፖ ጎን ለጎን በዘርፉ ልምድና ተሞክሮዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል:: ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የማዕድንና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ትናንት የተጠናቀቀ ሲሆን፤ የማዕድን አምራቾች፣ ላኪዎች ፣ የማዕድን ተጠቃሚዎች፣ የቴክኖሎጂ አምራችና አቅራቢዎች ተገናኝተው ምርትና አገልግሎታቸውን ማስተዋወቅ እና የገበያ ትስስር
መፍጠር አስችሏቸዋል::
በሚሊኒየም አዳራሽ ከኅዳር 14-18 ቀን 2016 ዓ.ም ክፍት ሆኖ የቆየው ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የማዕድንና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ውጤታማ እንደነበር የማዕድን ሚኒስቴር አስታውቋል።
አዲስ ዘመን ረቡዕ ኅዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም
ፎቶ፡- እዮብ ተፈሪ
ዜና
በመዲናዋ ከ11 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ሆነዋል
ገበየሁ ሊካሳ (ዶ/ር)
ከ1ኛው ገጽ የዞረ
ሄለን ወንድምነው
አዲስ አበባ፡- በመዲናዋ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አራት ወራት ከ11 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ
አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡ በበጀት ዓመቱ ለ78 ሺህ ቤቶች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለማዳረስ እየተሠራ
ነው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ገበየሁ
ሊካሳ (ዶ/ር)
ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በተያዘው የ2016
በጀት ዓመት አገልግሎቱ 78 ሺህ ደንበኞችን ተ ጠ ቃ ሚ ለማድረግ አቅዶ፤ በአራት ወሩ 11
ኢትዮጵያና ቼክ ሪፐብሊክ...
ሺህ አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል፡፡
አገልግሎቱ ከኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭም 11 ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ በአራት ወራት ሦስት ነጥብ አራት ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ሥራ አስፈጻሚው አስታውቀዋል፡፡
በተሰበሰበው ገቢ የቅዱን 90 በመቶ ማሳካት እንደተቻለ ጠቁመው፤ የመንግሥት ተቋማት በወቅቱ ክፍያ መፈጸም ባለመቻላቸው ዕቅዱን ሙሉ ለሙሉ ማሳካት ባይቻልም አፈፃፀሙ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የተሻለ መሆኑን አንስተዋል።
በመዲናዋ በአጠቃላይ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ደንበኞች አሉ ያሉት ዶክተር ገበየሁ፤ ከዚህም ውስጥ ግማሽ ያህሉ የቅድመ ክፍያ ቆጣሪ ተጠቃሚዎች በመሆናቸው የስማርት ቆጣሪ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን አመላክተዋል።
አዲሶቹ የስማርት ቆጣሪዎች ለደንበኞች ከሚያስገኙት ጠቀሜታዎች መካከል የደንበኞችን ፍጆታ ሒሳብ መረጃ በየወሩ በተንቀሳቃሽ የእጅ ስልካቸው አማካኝነት በመላክ የሚያሳውቁ ሲሆን፤ ከቆጣሪ ንባብ ስህተትና በወቅቱ ካለመነበብ ችግር ጋር ተያያዞ የሚከሰቱ
ቅሬታዎችን ያስቀራሉ ብለዋል።
የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሲቋረጥም ያለደንበኛ ጥቆማ ቆጣሪው በራሱ ሲስተም በማሳወቅ የደንበኞችን የደህንነት ስጋት ከመቅረፍ ባለፈም ወቅቱን የጠበቀና ከስህተት ነፃ የሆነ ቢል እንዲዘጋጅ በማድረግ፣ የቢል እርማትን በማስቀረት፣ የኃይል ብክነትን በመቀነስና የቢል ዝግጅት ሂደትን በማሳጠር ተቋሙ ወጪውን በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያበረክታሉ ሲሉ አብራርተዋል፡፡
በ2015 በጀት ዓመት በተለያዩ ምክንያቶች የኃይል መቆራረጥ ችግር እንደነበር አስታውሰው፤ የኃይል መቆራረጡ ያጋጠመው ለረዥም ዓመታት የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ መስመሮችና ኔትዎርኮች ባለመሻሻላቸው እንዲሁም ከመሬት ጋር ግራውንድ በማድረግና በተለያዩ ዛፎችና በነፋስ አማካኝነት በሚደርስ የኤሌክትሪክ ብልሽት መሆኑን አመላክተዋል፡፡
በተያዘው በጀት ዓመት ችግሩን ለማቃለል በተቀናጁ አሠራሮች የተለያዩ የማሻሻያ ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን ገልጸው፤ የኮንክሪት ምሰሶ፣ የማከፋፈያ ትራንስፎርመር፣ የኤሌክትሪክ ሽቦ፣ ቆጣሪና የተለያዩ ግብዓቶችን በማሟላት ላይ በአራት ወሩ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።
“ጠንካራ ርምጃ...
ላይ የነበራቸውን ተሳትፎ በተመለከተ ለገሠ ቱሉ (ዶ/ር) እና ቢልለኔ ሥዩም ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ/ር) በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ20ኛው የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ጉባኤ በልዩ የክብር እንግድነት በመገኘት በዘርፉ የኢትዮጵያን ተሞክሮ አቅርበዋል።
በዚህም ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የሥራ አጥነት ችግሮችን ለመቅረፍ፣ በአረንጓዴ ልማት ላይ የተመሠረተ አማራጭ የኢነርጂ አቅርቦት ለማሻሻል፣ ግብርናን ማዕከል ያደረገና የተቀናጀ የኢንዱስትሪ ልማትን በማረጋገጥ ረገድ የተሠራውን ሥራ ለአዳጊ ሀገራት ተሞክሮዋን ማቅረቧን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራና ግብርናን ማዕከል ያደረገ የተቀናጀ ኢንዱስትሪ ልማት በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ ሥራ በመሥራቷ የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት
ድርጅት ለኢትዮጵያ እውቅና ሰጥቷል ያሉት ዶክተር ለገሠ፤ በጉባኤው ኢትዮጵያ ልዩ ተምሳሌት ሆና ለአዳጊ
ሀገሮች ተሞክሮዋን አቅርባለች ብለዋል።
ጉባኤው በኢንዱስትሪ የበለጸጉና ያደጉ ሀገሮች ቀደም ብለው የገቧቸውን ቃሎች የሚያከብሩበትና ለአዳጊ ሀገራት ከድህነት የሚላቀቁበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ(ዶ/ር) የአዳጊ ሀገሮችን የመሠረተ ልማት አቅርቦትን እና የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች የበለጸጉ ሀገራት በፋይናንስ፣ በቴክኖሎጂና በእውቀት ሽግግር እንዲደግፉ ጥሪ ማቅረባቸውንም ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የተደረጉ የማሻሻያ ሃሳቦች፣ በትግበራ ላይ የተገኙ ውጤቶች እና እየታዩ ያሉ ለውጦችን በሚመለከት ተጨባጭ ማብራሪያ ለጉባኤው ማቅረባቸውንም ተናግረዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ሥዩም በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት
ዓመታት በፖሊሲ ደረጃ፣ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በአይሲቲ እና በቱሪዝም ዘርፍ ከፍተኛ ለውጦችን እያመጣች መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለጉባኤው ማካፈላቸውን ጠቁመው፤ ይህም ኢትዮጵያ በለውጥ ተምሳሌትነት እንድትታይ ያስቻለ ነው ብለዋል።
የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጀነራል ገርድ ሙለር ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት ያከናወነቻቸውን የለውጥ ሥራዎች እንደ ተምሳሌትነት መጥቀሳቸውን የገለጹት ቢልለኔ ስዩም፤ ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሦስት እጥፍ የምርት እድገት ማሳየቷንና ይህም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ተጨባጭ ርምጃ እንደሆነ መመስከራቸውን ገልጸዋል።
በኢንዱስትሪው ዘርፍ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግና ተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ ማግኘት የሚያስችሉ ተግባራት ማከናወን እንደሚገባም በጉባኤው መነሳቱን ቢልለኔ ሥዩም ተናግረዋል።
ከ1ኛው ገጽ የዞረ
እንደሌለም ገልጸዋል::
ገንዘቡ በወረቀት ላይ ብቻ በመሆኑ ድርጅቱ አሁን ባለው አቋም እዳውን ለመንግሥት በማቅረብ እንዲሰረዝ መደረጉን ያነሱት አምባሳደር ሱሌይማን፤ ሆኖም ግን የተመዘበረው ገንዘብ ከተለያዩ ድርጅቶች የተሰበሰበ በመሆኑ ድርጅቶች ክስ እያቀረቡ ይገኛሉ:: እንደ ድርጅታቸውም ሆነ እንደ ሀገር ጥቂት ሙሰኞች በመዘበሩት ገንዘብ መንግሥት ያላጠፋና ያልተበደረውን እዳ ለመክፈል እየተገደደ ነው ሲሉ ተናግረዋል:: ከፍተኛ የሀብት ምዝበራ የተፈጸመበትና ሀገር ላይ ትልቅ ኪሳራ ያደረሰው ይህ ተቋም በለውጡ አመራር ተገቢ ትኩረት ማግኘቱን አውስተው፤ አሁን ላይ በዘጠኝ ግዙፍ ኢንዱስትሪዎችና ከ30
ከ1ኛው ገጽ የዞረ
ወደ ፍርድ ቤት ከሚቀርቡ...
በላይ ፋብሪካዎች ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት የራሱን አስተዋፅዖ ማበርከት ላይ መሆኑን ተናግረዋል::
በሀገሪቱ የሚስተዋሉት ግጭቶች በአንድም ሆነ በሌላ ለዘመናት
የፌደራል የፍትሕና የሕግ ምርምርና ሥልጠና
ኢንስቲትዪት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ደግፌ ቡላ በተለይም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ በኢትዮጵያ በአማካይ በየዓመቱ ወደ ፍርድ ቤት ከሚቀርቡ 7ነጥብ4 ሚሊዮን ጉዳዮች መካከል እልባት የሚሰጣቸው 2ነጥብ2 ሚሊዮን ጉዳዮች ብቻ ናቸው:: አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ጉዳዮችን ወደ ፍርድ ቤት አለመውሰድና በሽምግልና የመጨረስ ሁኔታ መኖሩን በመጠቆም ወደ ፍርድ ቤት የሚመጣው ጉዳይ በጣም አነስተኛ መሆኑን አብራርተዋል:: ከ 7ነጥብ4 ሚሊዮን ጉዳዮች መካከል እልባት የሚሰጣቸው 2ነጥብ2 ሚሊዮን ጉዳዮች ብቻ እልባት እንዲያገኙ መደረጉ ብዙ ጉዳዮች ላይ መሥራት እንደሚያስፈልግ ይጠቁማል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ በፍትሕ ሥርዓቱ መዘመንና ተደራሽነት ላይ በሰፊው መሥራት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል::
ዋናው ችግር ተቋሙ የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት በሚችልበት ደረጃ ላይ ያለመሆኑ ነው
ያሉት አቶ ደግፌ፤ ለዚህም በምክንያትነት ከሚጠቀሱት
መካከል በቂ ባለሙያ ለመሳብና ለማቆየት አለመቻል፣ የሚጠኑ ጥናቶች በተግባር ላይ ያለመዋል፣ የምርምርና የማሠልጠን አቅም ያለመዳበር፣ የዘመናዊ ቴክኖሎጂና ሌሎች መሠረተ ልማቶች ያለመሟላት ዋነኞቹ መሆናቸውን ጠቁመዋል::
በመሆኑም ተቋሙን ለማጠናከር በቅርቡ በአዲስ መልክ እንዲደራጅ መደረጉ የመፍትሔው አንዱ አካል መሆኑን አስገንዝበዋል::
ከባለሙያዎች ብቃት አኳያም ብዙ ጉድለቶች መኖራቸውን ጠቁመው፤ ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር መሄድ አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል:: ተቋሙ ሙሉ ለሙሉ የተሟላ ባለሙያ የሌለው ቢሆንም ከሌሎች ተቋማት ጋር በመናበብ እየሠራ መሆኑንም ገልጸዋል::
ከማስረጃ አቀራረብ አንጻር ቀደም ሲል ከነበረው አሠራር እየተሻሻለ መሆኑን የገለጹት አቶ ደግፌ፤ በቀጣይ የሚስተካከሉ ጉዳዮች መኖራቸውን አመልክተዋል::
በተለይም ቴክኖሎጂው የፍትሕ ሥርዓት አሰጣጡን
ጥሎ እንዳይሄድና በቴክኖሎጂ ተደግፈው የሚሠሩ ወንጀሎችን በብቃት ለመመርመርና ፍትሕ ለመስጠት የሚያስችሉ ሥራዎች በትኩረት እየተከናወኑ መሆኑን አስገንዝበዋል::
ይህን ለማሻሻል ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር የተናበበ ግንኙነት መፈጠሩን ጠቁመው፤ ከሀገር ውጭ ከሚገኙ አቻ ተቋማት ጋርም በተመሳሳይ መልኩ የሚከናወኑ አበረታች ተግባራት መኖራቸውን ገልጸዋል::
‹‹የኢፌዴሪ የፍትሕና የሕግ ምርምር ኢንስቲትዩት›› በመባል ይታወቅ የነበረው ተቋም በ2010 ዓ.ም ከ‹‹ፌደራል ፍትሕ አካላት ባለሙያዎች ሥልጠና ማዕከል›› ጋር ተዋሕዶ፣ ‹‹የፌደራል የፍትሕና የሕግ ምርምር እና ሥልጠና ኢንስቲትዩት›› የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን ‹‹የፌደራል የፍትሕና የሕግ ምርምር እና ሥልጠና ኢንስቲትዩት›› ሁለቱን ተቋማት አዋሕዶ የተደራጀው በአዋጅ ቁጥር 1071/2010 ዓ.ም ነው::
ከተዘረጋው የሌብነትና የዝርፊያ ሥርዓት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው ያሉት አምባሳደሩ፤ አመጽ የሚያቀጣጥሉ አካላት ዓላማቸው በኃይል ሥልጣን በመያዝ ሀገር ለመዝረፍ ከማለም ውጭ የረባ ምክንያታዊ አጀንዳ እንደሌላቸውም አመልክተዋል::
ባለፉት አምስት ዓመታት የለውጡ መንግሥት በይደር የመጡ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት አብዛኛውን ጊዜ ማሳለፉን ያወሱት አምባሳደር ሱሌይማን፤ አሁንም ሙስና ተገቢውን ትኩረት አላገኘም ብለዋል:: በመሆኑም ችግሩን ለመቅረፍ ኅብረተሰቡን ያሳተፈ ትግል ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል::
አዲስ ዘመን ረቡዕ ኅዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም
ገጽ 5
ርዕሰ አንቀፅ
ይህ አምድ በተለያዩ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዜጎች ነፃ ሀሳባቸውን የሚሰጡበት ነው።በዓምዱ ላይ የሚወጡ ጽሁፎች የዝግጅት ክፍሉን አቋም አያመለክቱም።
ነፃ ሃሳብ
የልማታችንና የሰላማችን ጠንቅ የሆነውን ሙስና በጋራ እንከላከል!
ሙስና እና ብልሹ አሠራር የሀገራችንን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እድገት የሚገታ ተግባር መሆኑን በመገንዘብ የሕግ ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በኢትዮጵያ የሥነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን በአዋጅ ተቋቁሞ ላለፉት ሃያ ዓመታት በሥራ ላይ ይገኛል። በዚህም ተቋሙ ከግንዛቤ ማስጨበጥ ጀምሮ የሙስናን ችግሮች መፍታትና መግታት የሚያስችሉ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል።
ይሁን እንጂ በተለያዩ ምክንያቶች የሙስና ችግር ከዕለት ዕለት ስር እየሰደደ እና ለሀገር ማኅበራዊ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እንዲሁም የሰላምና ደህንነት ስጋት እስከመሆን መድረሱ ተደጋግሞ ተነግሯል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) በአንድ ወቅት በፓርላማ ንግግራቸውም ለሙስና የተሰመረው ቀይ መስመር ቀይ ምንጣፍ ሆኗቸው የሚመላለሱበት ሙሰኞች ስለመኖራቸው እና ችግሩም ትልቅ ሀገራዊ በሽታ ስለመሆኑ ገልጸው ነበር።
ይሄን ችግር ከግምት ባስገባ መልኩም በተለይም ሀገራችን የተጀመረውን የልማት፣ የሰላም እና የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ቀጣይነት ያለው እንዲሆን፤ ሙስና እና ብልሹ አሠራርን መከላከል በመልካም ሥነ-ምግባር የተገነባ፣ ሙስናን የሚፀየፍ በፅናት የሚታገል ኅብረተሰብ መፍጠር በማስፈለጉ የፌዴራል የሥነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅን አዋጅ ቁጥር 1236/2013 እንደገና እንዲሻሻል ተደረገ።
ከዚህ በኋላም ተቋሙ የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት በርካታ ተግባራትን ያከናወነ ሲሆን፤ ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረትም፤ ባለፉት 20 ዓመታት ጉዞው ከ20 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ግንዛቤ እንዲያገኙ አድርጓል። ከዚህ ባለፈም ሕግን ለማስከበር ባደረገው እንቅስቃሴ 11 ሺህ 350 የሙስና ወንጀል የክስ መዝገቦች ላይ ውሳኔ በማሰጠት ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ማስመለስ ችሏል። በዚህ ረገድ ባለፉት ሦስትና አራት ዓመታት የተሻለ ሥራን ማከናወን እንደቻለ ያስታወቀው ኮሚሽኑ ታዲያ፤ በተለይም ባለፉት አራት ዓመታት በኢትዮጵያ ሙስናን ለመከላከል በተሠራ የቅድመ መከላከል ሥራ ከዘጠኝ ቢሊዮን ብር በላይ፤ እንዲሁም ከአራት ሚሊዮን ካሬ ሜትር በላይ መሬት ከምዝበራ ማዳን ችሏል። ከ829 ሚሊዮን ብር በላይ በሙስና የተገኘ ገንዘብም ተመላሽ እንዲሆን
አድርጓል።
ከዚህ በተጓዳኝ ባለፉት ሦስት ዓመታት የፍርድ ውሳኔ ያረፈባቸው ንብረቶች ወደ መንግሥት እንዲገቡ አድርጓል። ከእነዚህ ውስጥም 12 ቀላል ተሽከርካሪዎች፣ 179 ከባድ ተሽከርካሪዎች እና 17 ኮንቴይነሮች እንዲሁም 10 ቤቶች ወደ መንግሥት ገቢ ከሆኑት መካከል ይገኙበታል። በተመሳሳይ አንድ ነጥብ 09 ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ መንግሥት ካዝና እንዲገባ ተደርጓል።
ይሄን እና መሰል ጅምር ውጤቶች ሊገኙ የቻሉት ደግሞ፣ በአንድ በኩል መንግሥት ግልፅነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት አሠራርን ለመፍጠር የፖለቲካ ቁርጠኝነት የታየባቸው ርምጃዎችን በመውሰዱ ሲሆን፤ በሌላ በኩል የፀረ ሙስና ትግሉን ተቋማዊ እና ሀገራዊ በሆነ አደረጃጀት እንዲመራ በመደረጉ ነው።
ይሁን እንጂ በጅምር ደረጃ ሊታይ የሚችለው ይሄን መሰል ተግባርና እርምጃ፣ ከችግሩ ግዝፈትና ስፋት አንጻር ገና ብዙ መስራት የሚገባን፤ ሥራውም በጥብቅ ዲስፕሊን ሊመራ እና በጠንካራ መናበብ በታገዘ ትብብርና ቅንጅት ሊከወን የሚገባው ነው። ምክንያቱም ሙስና የሀገር ኢኮኖሚን የሚያናጋ፤ የማኅበራዊ እሴትና መሠረትን ሸርሽሮ የሚንድ፤ የፖለቲካ ስብራትን የሚፈጥር፤ እንዲሁም ከፍ ያለ ሀገራዊ ሰላምና ደህንነት ላይ አደጋን የሚጋርጥ ክፉ ደዌ ነውና።
ይሄንን ደዌ በወቅቱ የችግሩን ምክንያት መለየት፤ ችግር የተከሰተበትን ቦታ ማከም፤ በሽታው ላይድን የተጠናወተውን ቦታም ቆርጦ መጣልና በተሻለ አካል በመተካት ሕመሙን ማስታገስ፤ በሂደትም መፈወስ ይገባል። ይሄ የሚሆነው ደግሞ የችግሩን ግዝፈት በመረዳት፤ ሥራውም የአንድ አካል ብቻ አለመሆኑን አውቆ ሁሉም ከልብ በመነጨ ኃላፊነትና ትጋት የበኩሉን ማበርከት ሲችል ነው!
ዛሬ ላይ ፈተና የሆኑ ያደሩ ዕዳዎችን ለመክፈል
እስማኤል አረቦ
የበለጸጉ ሀገራት ዛሬ የደረሱበት የዕድገት እና የብልጽግና ማማ ላይ የደረሱት አባት አያቶቻቸው ባቆዩላቸው ወረትና ባሰፈኑላቸው ሰላም፤ ፍቅርና አንድነትነ ነው። ትናንት የተሠሩት በጎ ሥራዎች ለዛሬ ብልጽግናቸው እርሾ ናቸው። በተቃራኒው ደግሞ ከትናንት ያደሩ ቁርሾዎች ለዛሬ ዕድገት እንቅፋቶች ናቸው።
የዛሬዪቱ ኢትዮጵያ የትንናት እና የትናንት በስቲያ ቀጣይ እንጂ ዛሬ እንደጅብ ጥላ በቅላ ያደረች አይደለችም። የዛሬዪቱ ኢትዮጵያ የትናንት ደስታዎች፤ መከራና ችግሮች ወራሽ ነች። መጥፎና በጎ ትርክቶች ባለቤት ነች። ከዚህ ውጪ የሚያደርጋት የሀገረ መንግሥት ሆነ የማኅበረሰብ ታሪክ የለም።
በየትኛውም የዓለም ክፍል ያለ ትውልድ በታሪክ በአንደኛው ምዕራፍ፤ የወረሰው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ዕዳ አለው። ለዚያ ዕዳ ዋጋ ከፍሏል፤ ተመሳሳይ ዕዳ ውስጥ እንዳይገባም ካለፈው ተምሮ ዛሬዎቹን ሆነ ነገዎቹን የተሻሉ ለማድረግ ተንቀሳቅሷል፤ በዚህ ሂደት የተሳካለትም ያልተሳካለትም ማኅበረሰብ/ሀገር አለ።
ይህ እውነታ በእኛም ሀገር የተለየ አይደለም። እንደ ሀገር በተለያዩ ዘመናት ከገባንባቸው እና ብዙ ዋጋ ከሚያስከፍሉን ዕዳዎቻችን መውጣት አለመቻላችን ዛሬዎቻችንን እንድናጣ እየተገደድን ነው። በዚህም ስለነገዎቻችን ተስፈኞች እንዳንሆን ከመሆን ባለፈ፤ የሀገረ መንግሥት ግንባታችን ተግዳሮት ውስጥ እንዲወድቅ እየሆነ ነው።
እንደ ሀገር ከትናንት ተምረን መሻገር ካልቻልናቸው ዕዳዎቻችን / ችግሮቻችን መካከል የትናንት የፖለቲካ ዕዳ አንዱ ነው። ታሪካችንን ላገላበጠ፤ በአግባቡ ለመረመረ አብዛኞቹ ችግሮቻችን ከትናንት ከወረስናቸው የፖለቲካ ዕዳዎች የሚመነጩ ናቸው። ይህ ትውልድ ሆነ የፖለቲካ ሥርዓቱ የሚከሰሱበት አይደለም።
ኢትዮጵያውያን የአኩሪ ማኅበራዊ ባህላዊና መንፈሳዊ ዕሴቶች ባለቤት ናቸው። መከባበር፤ መደማመጥ፤ መቻቻልና መተዛዘን ከእነዚህ ዕሴቶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። እነዚህ እሴቶች ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ከፍ ያለ አቅም እንደሆኑ ይታመናል።
ይህም ሆኖ ግን፤ የትናንት የፖለቲካ ዕዳዎቻችንን እንዴት አድርግን እንክፈልና ዛሬዎቻችንን ከትናንት ጥላ እናውጣ ከማለት ይልቅ፤ ትናንት ላይ ቆመው በሚያላዝኑ፤ ቆሞ ቀር ፖለቲከኞች ምክንያት እንደ ሀገር ብዙ ትውልዶች ያልተገቡ ዋጋዎችን ለመክፈል ተገድደዋል።
የትናንት ባለዕዳ የሆነውን ትውልድና መንግሥት መውቀስን ዋነኛ የፖለቲካ አጀንዳ ያደረጉት እነዚህ ቆሞቀር ፖለቲከኞች፤ ትናንትን በትናንት መነፅር፤ የየዘመኑንም ትውልድ በራሱ ዘመን የአስተሳሰብ እሴቶች/ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እሴቶች/ከመገምገም ይልቅ በአሁነኛ ጥራዝ ነጠቅ እሳቤ በመክሰስና በመኮነን ለሀገራዊ ሰላም ሆነ ለሀገረ መንግሥቱ ፈተና ሆነዋል።
አዲስ ዘመን
ግንቦት 30 ቀን 1933 ዓ.ም ተቋቋመ
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ ስልክ ቁጥር - 000-000-00-00 ኢሜል ፡- xxx@xxxxx.xx
ዋና አዘጋጅ
አንተነህ ኃ/ብርሃን ወ/መድህን
አድራሻ
ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ
ወረዳ 06
የቤት ቁጥር 319 ኢሜይል - xxxxxxx.xxxxxxxxxxx@xxxxx.xx ስልክ ቁጥር - 011-1-26-42-40
የአዲስ ዘመን ማኔጂንግ ኤዲተር ወንድወሰን ሽመልስ ታደሰ ስልክ፡- 011 126 4200
Email:- xxxxxxxxx.xxxxxxxx@xxxxx.xx
የገበያ ልማትና ፕሮሞሽን ዘርፍ
ኢሜይል - xxxxxxxxxxxxxxxx@xxxxx.xxx
ስልክ - 000-000-00-00
ፋክስ - 000-000-00-00
የዝግጅት ክፍል ፋክስ - 251-011-1-56-98-62
የአዲስ ዘመን ምክትል ዋና አዘጋጆች
• ወርቁ ማሩ
• ኃይሉ ሣህለድንግል
• እስማኤል አረቦ
• ቦጋለ አበበ
የማስታወቂያ መቀበያ ክፍል ስልክ ቁጥር - 000-000-00-00 ፋክስ - 000-000-00-00
ቴሌግራም - 000- 000-00-00 - Press
የማስታወቂያ ሽያጭ ማስተባበሪያ
ስልክ - 011-1-26-43-39
ማከፋፈያ :- ስልክ ቁጥር - 000-000-00-00
የትናንት ችግሮች እንዴት እንደሚቀረፉና ሕዝብም ለዘመናት ይዞ የተጓዛቸው መልካም ዕሴቶችን እንዴት ማስቀጠል እንደሚገባው ከመምከር ይልቅ መልካም ዕሴቶች ቀሰበቀስ እንዲናዱ በማድረግ ወንድም በወንድሙ ላይ መታመን እንዲያጣ፤ ልዩነቶችን ጌጦቹ አድርጎ ሳያፍር ለዘመናት አብሮ በኖረ ሕዝብ መካከል ጥላቻ እንዲፈጠር፣ የዘመኑን ትውልድ ባልኖረበት ዘመን ትርክት በመወንጀል ለማሸማቀቅ፤ በዚህም የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ረጅም ርቅት እየሄዱ ነው። ንጹሃን ባልዋሉበት ሜዳ እንዲፈረጁ፤ እንዲሰደዱ፤ እንዲፈናቀሉና እንዲገደሉ አድርገዋል።
ከሁሉም የሚያሳፍረውና የሚያሳዝነው ደግሞ፤ በ1960ዎቹ በነበረው አሳዳጅና ተሳዳጅ፤ ገዳይና አስገዳይ ፖለቲካ ጭምር ተዋናይ የሆኑ አካላት ዓይናቸውን በጨው አጥበው ትናንት ለተፈጸመው ችግር የዛሬውን ትውልድ በአደባባይ ሲወቅሱ የመታየታቸው እውነታ ነው ።
እነዚህ ሰዎች ያደፈ ታሪካቸውን ይዘው ተሸፋፍነው መተኛት ሲገባቸው፤ እኔ ያላቦካሁት አይጋገርም በሚል ፈሊጥ በየቦታው ያዙኝ ልቀቁኝ ሲሉ ይደመጣሉ። ኅብረተሰቡ ተረጋግቶ እንዳይኖር የተለያዩ ሰሞነኛ አጀንዳዎችን በመፍጠር ውዥንብር መፍጠር ሥራቸው ሆኗል። እነዚህ የደም ፖለቲከኞች ዛሬም ለመጡበት በደም የተጨማለቀ መንገዳቸው ወጣቱን ለማማለል ሲጥሩ ይታያሉ።
ቆሞ ቀር በሆነው የፖለቲካ አስተሳሰብ ላይ የተቸነከሩት እነዚሁ ፖለቲከኞች ኢትዮጵያን የምታክል ታላቅ ሀገር ወደ ጎጥና መንደር አውርደው አንሰው ሊያሳንሷት ይሞክራሉ። ከ13 የአፍሪካ ሀገራት በላይ በአርማነት የወሰዱትን ሰንደቅ ዓላማ በመጸየፍ ጭምር የቅኝ ገዢዎችን ሃሳብ ሲደግሙ ይስተዋላሉ።
ለእነዚህ ወገኖች ዕሴት፣ ታሪክ፣ ባህል፣ ወግ የሚሏቸው ኢትዮጵያዊ ዕሴቶች ይጎረብጣቸዋል። እኩልነት የሚሉት ነገር
ደግሞ ያማቸዋል። እነዚህ ቆሞ ቀር ፖለቲከኞች መገኛቸው ብዙ ነው። እዚህም እዚም አሉ። በየትኛውም ብሔር፤ በየትኛውም ሃይማኖት ውስጥ አሉ። ሆኖም ለብሔራቸውም ሆነ ለሃይማኖታቸው የማይቆረቆሩና ይልቁንም በብሔርና በሃይማኖት ጭምብል ውስጥ የራሳቸውን ጥቅም የሚያሳድዱ ነጋዴዎች ናቸው።
ጥቅማቸውን ለማጋበስ ሲሉም የተፋቀረን ያጣላሉ፤ አብሮ የኖረን ያቃቅራሉ፤ ወንድማማቾችን ያለያያሉ። ወሬያቸው በሙሉ ክፋትና ጥላቻ ብቻ ነው። በእነዚህ ሰዎች መዝገበ ቃላት ውስጥ ፍቅር፣ሰላም፣አብሮ መኖር የሚሉት ቃላት ታስሰው አይገኙም።
በኋላቀሩ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል ውስጥ የሃሳብ ልዩነት ክብር የለውም፣ ዕውቅናም አይሰጠውም። በሃሳብ የተለየን እንደ ደመኛ ጠላት ማሳደድ፣ ማሰር፣ መግደል ወይም ማሰናከል የተለመደ ድርጊት ነው። ከአብሮነት ይልቅ ነጠላ ሆኖ በመቆም በአሸናፊነትና ተሸናፊነት መንፈስ ሀገርን ለመምራት መዳዳት ያረጀው የኢትዮጵያ ፖለቲካ አካሄድ ነው።
የዛሬው ትውልድ ለዘመናት የታኘከን ማስቲካ ለማላመጥ ፍቃደኛ አይደለም። የመጠፋፋትና የመገፋፋት ፖለቲካ ሰልችቶታል። ከልዩነት ይልቅ አንድነትን፤ ከመለያየት ይልቅ አብሮነትን፤ ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርን፤ ከመበታተን ይልቅ አብሮ መኖርን፤ ይሻል። ይህንን እውነታ መረዳት ሆነ ለእውነታው ታምኖ መኖር ለነዚህ ፖለቲከኞች የሚዋጥ አይደለም።
በ1960ዎቹ ያላዋጣው የመጠፋፋትና የመገፋፋት ፖለቲካ ዛሬ ሕይወት አይኖረውም። ትናንት የመከነ ዘር ዛሬ ፍሬ ሊያፈራ አይችልም፤ ዘመን ያለፈበት ፖቲካችሁን በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ሆነ በዚህ ትውልድ ስፍራ አይኖረውም። ለእናንተም ቢሆን መቼም ሊያተርፋችሁ የሚችል የፖለቲካ ስትራቴጂ አይደለም፤ ዘመኑን የሚዋጅ አቅም የለውም።
ዛሬ «የአክሱም ሐውልት ለወላይታው ምኑ ነው» የሚለው ከፋፋይና አግላይ አመለካከት ተቀይሮ ‹‹ሁሉም የኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያ የሁሉም›› በሚለው ተቀይሯል። ኢትዮጵያን ወደ ቁልቁለት ይዟት ሲንደረደር የነበረው የከፋፋይነትና የአግላይነት ማርሽ ተቀይሮ ወንድማማችነት፤ እህትማማችነት፤ አንድነት፤ አብሮነት፤ በሚሉ ምርጥ ማርሾች ተቀይሯል።
ዛሬ ሥልጣን ለመያዝ ብረት ማንሳት ሳይሆን ቁጭ ብሎ በጠረጴዛ ዙሪያ መወያየት ብቻ በቂ ነው። በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረጉ ውይይቶች ችግሮችን የመፍታት ባህል ባለማዳበራችን ምክንያት ችግሮቻችን ከአንድ ትውልድ ወደ ሌላው እየተሻገሩ ለሴራ ፖለቲካ አቅም ሆነው ቆይተዋል።
መነጋገር፣ መደማመጥ በሌለበት መተማመን ስለማይኖር ችግሮች የመፍትሔ ያለህ እያሉ ዓመታት ማስቆጠራቸው የማይቀር ነው። በዚህም፣ የችግሮቹ ባለቤት የሚጠበቅ ሆነ የማይጠበቅ ዋጋ ከመክፈል ሊታደግ የሚችል አይኖርም። xx በ1960ዎቹ እንደነበረው ከ50 አመትም በኋላ አሀዳዊና ፌዴራሊስት እየተባባሉ መካሰስ የዛሬም ትውልድ ዕዳ ከመሆን የሚያልፍ አይሆንም።
በቀደሙት ዘመናት ከመጣንበት ኋላቀር የፖለቲካ አስተሳሰብ አንጻር፣ ፖለቲካችንን በዕውቀት እና ሞግቶ ከማሸነፍ ላይ ከመመስረት ይልቅ ዛሬም ደምና አጥንትን እየቆጠሩ ሥልጣን ለመቆናጠጥ በሚደረጉ ሙከራዎች ጥላ ውስጥ ስለመኖሩ ያለፉት ሦስት አመታት ተጨባጭ ማሳያ ናቸው ።
ይህ ትውልድ እንደ ትውልድ /ሀገርም እንደሀገር ካለፈው ትውልዶች የወረሰቻቸው ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ዕዳዎችን ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ዕዳም ጭምር ነው። ይህን ዕዳ መክፈል በዚህ ትውልድ ጫንቃ ላይ ወድቋል።
የአስተዳደር ወሰን ጥያቄ፣ የማንነት ጥያቄ፣ የብሔር ጥያቄ፣ የቋንቋ ጥያቄ፣ የሃይማኖት ጥያቄ ወዘተ እየተባለ ለሚቀርቡ ትናንት ላልተመለሱ ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ መስጠት የዚህ ትውልድ የቤት ሥራ ሆኗል።
እነዚህ ያደሩ የቤት ሥራዎች ደግሞ በአንድ ጀንበር ተመልሰው የሚያልቁ አይደሉም። ጊዜ ያስፈልጋቸዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ የብሔር ጥያቄ በይፋ ለውይይት ከቀረበ ከሃምሳ ዓመታት በኋላ፣ ጥያቄው በአግባቡ መልስ ባለማግኘቱ ዛሬም ድረስ የብሔር ነፃ አውጪዎች ነፍጥ አንስተው ጫካ መግባት ፋሽን ከመሆን አላለፈም።
ከሁሉ የከፋው ደግሞ የብሔር ጥያቄና የነፃ አውጪነት መንፈስ ዛሬ የተፈጠረ በማስመሰል በዛሬው ትውልድ ላይ ክስ የሚያሰሙ ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች መብዛታቸው ነገሩን የበለጠ አስገራሚ ያደርገዋል።
ቢያንስ የዛሬው ትውልድ የወረሰውን ዕዳ እንዲከፍል ጊዜ መስጠትና መደገፍ አንድ ነገር ሲሆን፣ ካልተቻለም ተበዳዩን በዳይ ከሚያደርግ ፍረጃ መውጣት ኅሊና ካለው አንድ ዜጋ የሚጠበቅ ተግባር መሆን አለበት።
Website - xxx.xxxxx.xx Email - xxxxxxxxxx@xxxxx.xx Facebook - Ethiopian Press Agency
አዲስ ዘመን
ረቡዕ ኅዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም
ተጠየቅ
«የኤሌክትሮኒክስ የግዥ ሥርዓት አድሎና ማጭበርበርን
በማስቀረት ለተጫራቾች እኩል ዕድል ይሰጣል»
- አቶ ሐጂ ኢብሳ፣
የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር
ሞገስ ተስፋ
መንግሥት ለአንድ ዓመት ከሚበጅተው በጀት ውስጥ 65 ከመቶ በላይ የሚሆነው ገንዘብ ለግዥ ይውላል። ይሁን እንጂ ይህን በጀት በአግባቡ ከመጠቀም አንጻር ውስንነት እንዳለ ይጠቀሳል። ከመንግሥት ግዥ አፈጻጸም ጋር በተያያዘ የሚስተዋለውን ከሕግ አግባብ ውጪ ግዥ መፈጸም እና ሌብነት፤ በተለይም በፌዴራል ተቋማት የሚስተዋለው በውስብስብ አሠራር የሚፈጸም ሌብነትና ብልሹ አሠራር መኖሩን ከዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ሪፖርቶች መስማት የተለመደ ሆኗል።
ይህ ተግባር ደግሞ ምግባረ ብልሹ የሆኑ ግለሰቦችና ቡድኖች ባልተገባ መንገድ እንዲበለጽጉ፤ መንግሥት የሚበጅተው የሀገር ሀብት ለታለመለት ዓላማ እና ለሀገር ልማት እንዳይውል የሚያደርግ መሆኑ እሙን ነው። ይህንን ችግር ከመከላከል አኳያም በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ አሠራሮች የተሞከሩ ሲሆን፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ሥር የሰደደውን ችግር ለመቅረፍ ያስችላል የተባለለት የኤሌክትሮኒክስ የግዥ ሥርዓት ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል።
ይህ እንደ ሀገር የተጀመረው የኤሌክትሮኒክስ የግዥ ሥርዓት ታዲያ በሁሉም የባለበጀት ተቋማት እንዲተገበር እየተሠራ መሆኑም ይታወቃል። እኛም በዛሬው የተጠየቅ ዓምድ ዕትማችን በዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በማተኮር፤ በተለይም አሠራሩ እየተስተዋለ ያለውን ስር የሰደደ ችግር በምን ያህል ደረጃ ያቃልለዋል? የሚለውን ነጥብ ማዕከል በማድረግ፤ የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት አቶ ሐጂ ኢብሳ ጋር ቆይታ አድርገናል። መልካም ንባብ!
አዲስ ዘመን፡- እንደ ሀገር የመንግሥት የግዥ ሥርዓት ምን ደረጃ ላይ ይገኛል?
አቶ ሐጂ፡- የኤሌክትሮኒክስ የግዥ ሥርዓትን ለመተግበር ለሁለት ዓመታት ጥናት ተካሂዷል፤ የ14 ሀገራት ተሞክሮ ተቀምሯል። ይሄን መነሻ በማድረግም በ2014 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በዘጠኝ ተቋማት ላይ ተተግብሯል። በወቅቱ ከዘጠኙ ተቋማት ስድስቱ ግዥ ፈጽመውበታል። ቀሪዎቹ ያልተገበሩትም ወደ ሲስተሙ ያለመግባት በነበራቸው ፍላጎት ነበር። እናም በ2015 ዓ.ም ሥራውን በማጠናከር በ74 የፌዴራል ተቋማት እንዲተገበር ተደረገ። ሆኖም አራቱ ተቋማት አዳዲስ የተዋቀሩ ስለነበሩ መሠረተ ልማት ብዙም ስላልነበራቸው ግዥ ሳይፈጽሙ ሲቀሩ፤ 70ዎቹ ተቋማት ግን ግዢአቸውን በኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓት አከናውነዋል። ይህ ጅማሮ እንደ ሀገር ለሚፈለገው ዘመናዊ የግዥ ሥርዓት ትልቅ መሠረት የጣለ፤ ሥራውም በጥሩ ደረጃ ላይ መሆኑን ያሳየ ነው። አዲስ ዘመን፡- በ2015 በጀት ዓመት ለኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓት ዋና ፈተና የነበረው
ምንድን ነው?
አቶ ሐጂ፡- የ2015 በጀት ዓመት ዋና ተግዳሮት የነበረው ከ169 የፌዴራል ተቋማት 70ዎቹ በኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሲፈጽሙ፤ 100 የሚጠጋ የፌዴራል ተቋም ደግሞ በማንዋል ግዥ ይፈጽሙ ነበር። በዚህም ነጋዴው ሁለት ቦታ ላይ የመቆም፤ ፌዴራል ተቋማትም አንዱን በኤሌክትሮኒክስ ግዥ እፈጽማለሁ ሌላው በማንዋል እንድገዛ ይፈቀድልን የማለት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ ነበር። ይህም የሆነው ወጥ የሆነ የግዥ ሥርዓት ባለመኖሩ ነው።
ከዚህ በተጓዳኝ የንግዱ ማኅበረሰብም ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓት ውስጥ አለመግባት፤ እንዲሁም በኤሌክትሮኒክስ ግዥ እስኪለማመድ በማንዋል የመግዛትና የመሸጥ ፍላጎቶች ነበሩ። ስለዚህ ትልቁ ተግዳሮት የነበረው በኤሌክትሮኒክስ ግዥ የሚፈጽሙና በማንዋል ግዥ የሚፈጽሙ የፌዴራል ተቋማት መኖራቸው ሲሆን፤ ይሄም ለእኛ ከፍተኛ ማነቆ ነበር።
አዲስ ዘመን፡- ባለሥልጣኑ በቀጣይ በኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓት ያለውን ችግር ለመቅረፍ ምን አስቧል?
አቶ ሐጂ፡- ዋናው እቅዳችን፣ በተያዘው 2016 በጀት ዓመት 169 የሚሆኑ የፌዴራል ተቋማትን ከተጠሪ ተቋማቱ ውጪ ሙሉ ለሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓት እንዲገቡ ማድረግ ነው። ይህ በተገቢው ሁኔታ ተከናውኗል። በፌዴራል ደረጃ የቀሩት ተጠሪ ተቋማት ብቻ ናቸው። እስካሁን ያለው መረጃ በዕቅዳችን መሠረት 163 የሚሆኑት በግዥ ሥርዓቱ ውስጥ ገብተዋል።
አዲስ ዘመን፡- ቀሪዎቹ የትኞቹ ተቋማት ናቸው? ምን ደረጃ ላይ ይገኛሉ?
አቶ ሐጂ፡- የቀሩት ስድስት የሚሆኑ ተቋማት ሲሆኑ፤ እነዚህም ዩኒቨርሲቲዎች ናቸው። አራቱ የትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች ናቸው። ይህም የሆነው በተፈጠረው ግጭት ምክንያት በዩኒቨርሲቲዎቹ ያሉ መሠረተ ልማቶች በደረሰባቸው ጉዳት የግዥ ሥርዓቱን ማስጀመር አልተቻለም። አሁን ላይ መሠረተ ልማቱ እየተሠራ ነው። ለባለሙያዎችም ሥልጠና እየተሰጠ ነው። ከሁለት ወር በኋላ ወደ ግዥ ሥርዓቱ የሚገቡበት ሁኔታ ይፈጠራል።
ቀሪዎቹ ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ በአማራ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፤ እንጅባራና ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ሲስተሙ ለመግባት ሥራ ላይ ናቸው። ስለዚህ አሁን ባለው መረጃ ከስድስቱ ተቋማት ውጪ ሁሉም የፌዴራል ተቋማት በኤሌክትሮኒክስ የግዥ ሥርዓት ገብተው ግዢአቸውን እየፈጸሙ ነው።
አዲስ ዘመን፡- በእርግጥ ሁሉም ተቋም ከማንዋል ወጥተው ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ግዥ እየፈጸሙ ነው? ከሆነስ ምን ያህል የንግዱ ማኅበረሰብስ በሥርዓቱ ተሳትፎ እያደረገ ነው?
አቶ ሐጂ፡- አዎ፤ እስሁን አንድም ተቋም በማንዋል ግዥ እንዲፈጽም ፈቃድ አልሰጠንም። የንግዱን ማኅበረሰብም በ2015 ሐምሌ ወር ላይ ሥራ ሲጀመር መቶ የሚሆኑ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች ነበር የተመዘገቡት። አሁን ላይ በትላልቅ ደረጃ ከሦስት እስከ 20 የተለያየ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ከ15 ሺህ በላይ የሆኑ ነጋዴዎች ተመዝግበዋል።
በእያንዳንዱ ፈቃድ ሲታይ 38 ሺህ የሚሆን የንግዱ ማኅበረሰብ ተመዝግቧል። ሐምሌ 2015 መቶ ነበር፤ አሁን ላይ ግን ከ38 ሺ በላይ የንግዱ ማኅበረሰብ ተሳትፎ እያደረገ ነው። ስለዚህ በማንኛውም አገልግሎትና ሥራ ውስጥ በቂ ተወዳዳሪ አለ። በመሆኑም እስካሁን ባለው ሥራና ሂደት ውስጥ የገጠመን ምንም ችግር የለም።
አዲስ ዘመን፡- ምንም ችግር አልገጠመንም ሲሉ፤ ሁሉም ሥራዎች እንከን አልባ በሆነ መንገድ እየተሠሩ ነው ማለት ነው?
አቶ ሐጂ፡- ይህ ሲባል ጥቃቅን ችግሮች የሉም ማለትም አይደለም። ለምሳሌ፣ የኤ.ቲ.ኤም አገልግሎት ከተጀመረ ቆይቷል። ነገር ግን ኤሌክትሮኒክስ ቢሆን በኔትወርክ የሚሠራ በመሆኑ አልፎ አልፎ ‹‹ስታክ›› ወይም ከአገልግሎት ውጪ ሲሆን ይታያል። ሞባይልም ቢሆን እንዲሁ ነው። ስለዚህ ከጥቃቅን ችግሮች ውጪ በሚፈለገው ሁኔታ ወደ ሥራ ተገብቷል።
አዲስ ዘመን፡- የ2016 በጀት ዓመት ሩብ ዓመት ላይ እንደመገኘታችን መጠን፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ የግዥ ሥርዓቱ ምን ያህል ውጤታማ ሆኗል? አቶ ሐጂ፡- በሩብ ዓመቱ የተገኘው የአሠራር ለውጥ ባለፈው በጀት አመት ከነበረው የበለጠ ነው። ባለፈው አመት ሙሉ 70 ተቋማት ብቻ ነበሩ፤ አሁን ላይ 163 ተቋማት በሩብ ዓመቱ በኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓት ውስጥ ገብተዋል። በዚህም በሩብ ዓመቱ ብቻ ከ728 በላይ የሚሆኑ ጨረታዎች አየር ላይ አሉ። በ2015 ዓመቱን በሙሉ 20 የሚሆኑ ጨረታዎች ናቸው
አየር ላይ ውለው የነበሩት።
በግዥ ሂደት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የዝግጅት፤ ሁለተኛና ሦስተኛው ሩብ ዓመት የግዥ ነው። አራተኛ ሩብ ዓመት ደግሞ በጣም ጥቃቅን ግዥዎች ካልሆኑ በስተቀር ከግንቦት በኋላ ሙሉ በሙሉ ይዘጋል። ስለሆነም ያለው ሂደት ሲገመገም መልካም ውጤት ላይ ነው ያለው።
ፎቶ፡ እዮብ ተፈሪ
አንዱ የዚህ የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓት ጠቀሜታ ሰኔ ላይ ያለውን የግዥ ሩጫ ሙሉ በሙሉ ዝግ ያደርጋል። ለምሳሌ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዚህ ሩብ ዓመት ብቻ የበጀት ዓመቱን ግዥ 92 በመቶ ደርሷል። ይህም ተቋሙ ማቀዱን፤ በበጀት ዓመቱ ምን እንደሚገዛ ማወቁን የሚገልጽ አፈጻጸም ነው። ስለዚህ ሦስተኛና አራተኛ ሩብ ዓመት ላይ ምንም ግዥ ላይኖረው ይችላል።
አዲስ ዘመን፡- የኤሌክትሮኒክስ የግዥ ሥርዓት አቅዶ ከመግዛት አንጻር ምን ፋይዳ ይኖራል?
አቶ ሐጂ፡- ድሮ የተቋማት ውድቀት ለገዥ ዕቅድ አለማቀድ ነው። የሰኔና የግንቦት የግዥ ሩጫ የሚያሳየውም ግዥ ያለ ዕቅድ የሚሠራ በመሆኑ ነው። እንዲሁ በዘፈቀደ የመንግሥትን በጀት ላለመመለስ ትዝ ሲል ሶፋ መግዛት፤ ቢሮ ይታደስ፤ አጥር አጥራለሁና መሰል ያለ ዕቅድ የሚሠሩ ሥራዎች ብዙ ነበሩ። የኤሌክትሮኒክስ ግዥ የሚመልሰው ያለ ዕቅድ የሚገዛ የተቋም ንብረት እንዳይኖር ማድረግ ነው።
ማንኛውም ተቋም ወደደም ጠላም ግዥ ፈላጊ ከሆነ ዕቅድ ማቀድ ግዴታው ነው። አንድ ተቋም ውሃ እገዛለሁ ቢል ከመጀመሪያው ዕቅዱ ውስጥ ካልተካተተ ሲስተሙ እቅድህ አይደለም ብሎ ይዘጋል። ዕቅድ ውስጥ ሳይገባ ግዥ አይፈጽምም። በመሆኑም 163ቱም የፌዴራል ተቋም የግዥ ዕቅድ አላቸው። ቀሪዎቹ ተቋማትም በማንዋል ዕቅዱ ስላላቸው ኔትወርኩ ሲስተካከል ወደ ሲስተም ይለወጣል። አቀዱ ማለት መቼ ነው የሚገዛው፤ ምንድን ነው የሚገዛው፤ ከየት ነው የሚገዛው፤ የዕቅዱ ዝርዝር በለቀማ፣ በውስን ጨረታ፣ በሀገር አቀፍ ጨረታ ነው፤ ወይም በዓለም አቀፍ ጨረታ ነው የሚለው አብሮ የሚታይ ነው።
በፊት አንድ ሊትር ነዳጅ 80 ብር እየተገዛ መቶና ሁለት መቶ መኪና በየሱቁና በየሆቴሉ እየዞረ የሚያባክንበት ሁኔታ ነበር። ፕሮፎርማ ለመሰብሰብ ሁለት ቀን ሲዞር ይውላል፤ በሦስተኛ ቀን ሂዶ ይለቅማል። አሁን ላይ በፌዴራል ተቋማት ደረጃ
አንድም መኪና ፕሮፎርማ ለመሰብሰብ በየሱቁ አይዞርም። በኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓት ግን ሁሉም በኦንላይን በመሆኑ የሚባክን ነዳጅ፤ ጉልበትና ጊዜ የለም። በዚህም አሠራሩ መንግሥትና ሕዝብን አቀራረበ ለማለት ያስችላል።
አዲስ ዘመን፡- ተቋማት በዚህ መልኩ ዕቅድ የሚያቅዱት ኃላፊነት ስላለባቸው፣ ወይንስ በእናንተና በአሠራሩ ጫና ምክንያት ነው?
አቶ ሐጂ፡- በተቋማቱ ዕቅድ እንዲታቀድ ማድረግ የየተቋማቱ ኃላፊዎች ሥራ ነው። የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ለአብነት እንዲነሳ ያደረገውም የተቋሙ ኃላፊዎች ተግባራዊ ስላደረጉና ለሥራው ቁርጠኛ ስለሆኑ ነው። የመጀመሪያ ፍርድ ቤት 12 የሚሆኑ ቅርንጫፎቹን ጨምሮ ወደ ሲስተሙ ገብተዋል።
መንግሥት ከሕዝቡ ሰብስቦ ነው በጀት የሚበጅተው። ስለዚህ እያንዳንዱ ተቋም አመራር ዕቅድ ማቀድ አለበት። አንድ የመንግሥት ሠራተኛ በደሞዙ ያቅዳል። ስለዚህ እንደ አቅም ለመኖር ዕቅድ አስፈላጊ ነው። ይህም ያለዕቅድ የሚባክነውን በጀት ለማስቀረት ከፍተኛ ሚና አለው።
አሁን ላይ እንደ ሀገር ለመጀመሪያ ጊዜ በሚባል ደረጃ ሁሉም የፌዴራል ተቋም የግዥ ዕቅድ አላቸው። ሁሉም ፌዴራል ተቋም በሚባል ደረጃ በኤሌክትሮኒክስ ግዥ እየገዙ ነው። በዚህም የመጨረሻ ሩብ ዓመት ግዥ እንደማይፈጸም እቅዳቸው ላይ ማስቀመጥ አለባቸው። ባለሥልጣኑም ከሚያዝያ 30 በኋላ ግዥ የሚባል ሙሉ በሙሉ ያቆማል። ይህ ማለት ግን ጥቃቅን ግዥዎች ይቆማሉ ማለት አይደለም።
አዲስ ዘመን፡- ጥቃቅን ግዥዎች ሲባል ምን ማለት ነው?
አቶ ሐጂ፡- ጥቃቅን ግዥ ማለት ለምሳሌ፣ አንድ ኃላፊ መንገድ እየሄደ ጎማው ቢፈነዳበት ሰኔ ላይ አይገዛም ተብሎ አይመለስም። እስከ ሰኔ 28 ሊገዛ የሚችልበት
ወደ ገጽ 7 ዞሯል
አዲስ ዘመን ረቡዕ ኅዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም ገጽ 7
ተጠየቅ
«የኤሌክትሮኒክስ የግዥ ሥርዓት አድሎና ...
ከገጽ 6 የዞረ
አግባብ ይኖራል። ነገር ግን መሠረታዊ ግዥ የሚባሉት በሙሉ በዕቅድ ብቻ መገዛት አለባቸው። የፕሮጀክትም ቢሆን ሰኔ ላይ አይደለም እገዛለሁ የሚባለው፤ የአዲስ በጀት መጀመሪያ ወሩ ሐምሌ ላይ ሊታቀድ ይገባል። በዚህ ዓመት ከፌዴራል ውጪ ባሉ ተቋማት ላይ አዲስ አበባ ተጀምሯል።
አዲስ ዘመን፡- ለፌዴራል ተቋማት ተጠሪ የሆኑ ተቋማት ቁጥር ከፍተኛ ነው፤ በዚህ ደግሞ በማንዋል ግዥ የሚባክነው በጀት ቀላል አይደለም፤ እነዚህን ወደ ግዥ ሥርዓቱ ማስገባት ያልተቻለበት ምክንያት ምንድን ነው?
አቶ ሐጂ፡- ይህ የሆነበት ዋናው ምክንያት የባለሥልጣኑ አቅም ውስንነት ነው። ለሁሉም ፌዴራል ተቋማት ባለሙያ ተመድቦ ሥራ እያገዘ ነው። ለሁሉም በአንድ ጊዜ መድረስ አይቻልም። ምክንያቱም ያለው የሰው ኃይል ውስንነት ነው። በ163 ተቋማት ለአንድ ወር የሚሆን ሥልጠና ተሰጥቷል። ከእቅድ ጀምሮ እስከ ውል አስተዳደር ድረስ ለአንድ ወር ሰልጥኖ ወደ ሥራ ተገብቷል።
በመሆኑም ተጠሪ ተቋማትን ጨምሮ ለማስገባት ከሰው ኃይል አንጻር አይቻልም። ሳይደገፉ ወደሥራ ቢገቡ ደግሞ የሚጎድሉ ነገሮች አሉ። ለምሳሌ፣ ገቢዎች ሚኒስቴር ከአምስት በላይ ቅርንጫፍ አለው። ማዕከላዊ ስታስቲክስ ከ27 በላይ ቅርንጫፍ አለው። ስለዚህ የሁሉንም ተቋማት ተጠሪ ይግቡ ከተባለ ከአቅም በላይ ይሆናል። ሆኖም በሂደት አቅም እየተፈጠረ እስከ ቀበሌ ድረስ ያለው የግዥ ሥርዓት ተግባራዊ ሲሆን አለአግባብ የሚባክን የመንግሥት በጀት ማዳን ያስችላል።
አዲስ ዘመን፡- ዓለም አቀፍ ጨረታዎች ላይ መጓተቶች ይታያሉ፤ ይህም በፕሮጀክቶች አፈጻጸም ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እየፈጠረ መሆኑ ይነገራል፤ በዚህ ላይ እርሶ ምን ይላሉ? ለዚህ ችግር መቃለልስ የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ምን ያግዛል?
አቶ ሐጂ፡- የኤሌክትሮኒክስ የግዥ ሥርዓት ዓለም ላይ ባመጣው ለውጥ ምክንያት ነው ኢትዮጵያም እንደ ሀገር የገባችበት። ይህም ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዳይጠናቀቁ አንዱ ማነቆ የሚሆነው የግዥ ሥርዓቱ አለመዘመኑ ነው። ስለዚህ ይህ ሥርዓት የግዥ ጊዜን የሚያሳጥር ነው፤ ሌብነትን በከፍተኛ ሁኔታ ይከላከላል። ለምሳሌ፣ በቀደመው ግዥ ‹‹ፕሮፎርማ›› የሚባል የግዥ አሠራር አለ፤ ከሦስት ሱቅ ፕሮፎርማ ማምጣትና እንዴት እንደተመረጠም ሳይታወቅ በተጭበረበረ መንገድና በጥቅም ትስስር ግዥ የሚፈጸምበት ሂደት ነበር። ይህም በጥቅም ኔትወርክ የተመሠረተ ነበር። ሦስቱም ሱቅ በተለያየ ማለትም በእናት በአባት በልጅ የተለያየ ማህተም አላቸው። የሚሰጠው ፕሮፎርማ ግን ከአንድ ሱቅ ነው። አሁን ላይ ይህ አሠራር እየተቀየረ
ነው።
በዚህ ዓመት ድል የተነሳና በልበ ሙሉነት መናገር የሚቻለው ይህን ዓይነት መሰል ስርቆት መቅረፍ መቻሉ ነው። በፊት ዓለም አቀፍ ጨረታ ከሦስት እስከ አራት ወር ነበር። አሁን ላይ ከሁለት ወር በታች ባለ ጊዜ ግዥ ይፈጸማል።
አዲስ ዘመን፡- ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በዓለም አቀፍ ጨረታዎች ላይ የሚታይ ውስንንት የለም ማለት ይቻላል?
አቶ ሐጂ፡- ውስንነት የለም ማለት ሳይሆን፤ ደላላ ከመሃል ይጠፋል። ዓለም አቀፍ ጨረታ ቢወጣ በቀድሞ አሠራር ደላላ ይገዛና ለቻይና፤ ለአሜሪካ፤ ለቱርክና መሰል ሀገሮች ላይ ሆነው ለሚጫረቱ ድርጅቶች ይልካል። ከአራት ወር በላይ የሚቆየው በማንዋል ከዚህ ተገዝቶ በፖስታ ቱርክ ላይ ለሚወዳደረው ዓለም አቀፍ ተጫራች አድርሶ ሞልቶ እስኪመለስ ያለው ጊዜ ነው። አሁን ላይ ግን በአንድ ጊዜ ዓለም ላይ ላለ የንግዱ ማኅበረሰብ ጨረታው በእጅ ስልኩ ስለሚደርሰው ወዲውኑ ሞልቶ መጫረት የሚችልበት አውድ ተፈጥሯል። ለዚህም ጊዜው አጭር እንዲሆን አደርጓል።
ስለዚህ እንደ ድሮው በር ተዘጋብኝ የሚባል ነገር የለም፤ ሰነዱን የሚሸጠው አካል ዛሬ አልገባም፤ ለሥራ ወጥቷል አይባልም፤ ሰነድ ለመግዛት ከክፍለ ሀገር አዲስ አበባ መምጣት አይጠበቅም። በኤሌክትሮኒክስ የግዥ ሥርዓት አድሎ፤ ማጭበርበር የሚባል ነገር የለም፤
ሮ የዓመቱን ግብር ሳይከፍል
ድ
የሚወዳደር ነበር። አሁን ላይ ግን ግብር መገበሩን አለመገበሩን የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር ሲገባ ይለየዋል። ካልገበረ ከውድድር ውጪ ይሆናል
ለተጫራቾች እኩል ዕድል የሚሰጥ ነው። ለማንም ነጋዴ አያዳላም።
ለአብነት፣ በኮንስትራክሽን ዘርፍ አራት ሺህ 18 ተወዳዳሪዎች አሉ። ድሮ መርጦ ለሦስቱ አሊያም ለሁለቱ የሚሰጥበት ዕድል ነበር። አሁን ግን፣ ለሁሉም ጨረታው ስለሚደርስ በሥርዓቱ ተወዳደረ አልተወዳደረ የእያንዳንዱ ተጫራች መብት ነው። ምክንያቱም አሁን ላይ ፕሮፎርማ ጨረታና ውስን ጨረታ ከሌብነት ወጥቷል። ስለዚህ ዓለም አቀፍ ጨረታው ላይ ምንም ውስንነት የለም።
የሜጋ ፕሮጀክቶች ግዥ የሚፈጸምው በዓለም አቀፍ ጨረታ ነው። ዓለም አቀፍ ጨረታ የሚወጣው ሁልጊዜም ለግዙፍ ፕሮጀክቶች ግንባታ ነው። ስለዚህ የሀገር ውስጥ ተጫራችም አቅሙ ያለው ሁሉ በመስፈርቱ ይወዳደራል። ውድድሩ ጠንካራ ነው። ኤሌክትሮኒክስ ግዥ ፉክክር ካለ ወደ ትክክለኛው ዋጋ የመጠጋት ዕድል አለ። የውሸት ዋጋዎችን ማስወገድ ያስችላል።
አዲስ ዘመን፡- አልፎ አልፎ በጨበጣ ውስጥ ገብተው በዓለም አቀፍ ጨረታ የሚሳተፉ ተቋማት እንዳሉ ይነገራል፤ ለጨረታው ያላቸው አቅም በምን ይገመገማል?
አቶ ሐጂ፡- ምን አልባት ንግድ ሚኒስቴር ካልተሳሳተ ጨበጣም ሆነ ቆረጣ የሚባል የለም። ለምሳሌ፣ አበበ የሚል ስም የተመዘገበ የግብር መክፈያ ቁጥር ‹‹ቲን ነምበር›› ሲገባ ከንግድ ሚኒስቴር ጋር ይገናኛል። ስለዚህ አበበ ንግድ ፈቃድ አለው ወይ ይልና ያለው የችርቻሮ ከሆነ ኮንስትራክሽን ጨረታ ከተመዘገበ እሱ የችርቻሮ ነው፤ ኮንስትራክስን ላይ ገብቶ መወዳደር አይችልም ብሎ ሲስተሙ ይጥለዋል። ስለዚህ በትክክለኛ ፈቃዱ ብቻ ነጋዴው ይወዳደራል።
የኮምፒዩተር ፈቃድ ያለው ሰው በራሱ ብቻ እንጂ የመኪና ጨረታ ላይ ሊወዳደር አይችልም። ስለዚህ ንግድ ሚኒስቴር ፈቃድ ሲሰጥ በትክክለኛ መንገድ ካልሰጠና በጨበጣ መዝግቦ አልፎ ካልሆነ በስተቀር ባለሥልጣኑ የሚወስደው መረጃ ከንግድ ሚኒስቴር ነው። ድሮ የሚያስቸግረው አንዱ መጥቶ ክስ ያቀርባል። አሁን ላይ ግን አስር ፈቃድ ካለው አንድ ሰው አስሩንም ይዘረዝራል። ድሮ የዓመቱን ግብር ሳይከፍል የሚወዳደር ነበር። አሁን ላይ ግን ግብር መገበሩን አለመገበሩን የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር ሲገባ ይለየዋል። ካልገበረ ከውድድር ውጪ ይሆናል።
ስለዚህ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል። በተጨማሪም ገንዘብ መኖሩንና አለመኖሩን ከባንኮች ጋር ያገናኛል። ፡ የመንግሥት ከሆነ ከኢፍ ሚስ ጋር ያገናኘዋል። ስለዚህ ቀድሞ የነበረውን የሰነድ ማጭበርበር ቀንሷል። ይህም የኦዲት ሥራን አቅሏል። አሁን ላይ እያንዳንዱ ኦዲተር በኦንላይ የሚለቀቀውን ጨረታ የመከታተል ዕድል ተፈጥሮለታል።
አዲስ ዘመን፡- የኤሌክትሮኒክስ የግዥ ሥርዓት ንብረት ባግባቡ ሳይቆጠር ባለው ንብረት ላይ አላስፈላጊ ግዥን በማስቀረት ረገድ አስተዋጽኦው ምን ያህል ነው?
አቶ ሐጂ፡- ውሸት መናገር ጥሩ አይደለም። ንብረት ላይ አሁንም ብዙ ችግር አለ፤ ምክንያቱም ብዙ ነው። በእርግጥ አሁን ላይ እየተገዙ ያሉ ዕቃዎች ወደ ኮምፒዩተር ስለሚሰፍሩ ግዥ ከማውጣት በፊት የተመዘገቡት ንብረቶች የማየት ዕድል ተፈጥሯል። ነገር ግን የቆዩ ንብረቶችም አሉ። ለምሳሌ፣ በኃይለሥላሴ፤ በደርግ የተገዙ ንብረቶች አሉ። መቼ እንኳን እንደተገዙ መለየት አቅቶን መከራ የምናይባቸው መኪናዎች አሉ። የመኪናዎቹ ታሪከ ባለመመዝገቡ የዛሬ 30 አመት የተገዛ መኪና እንሽጥ ሲባል እንዲሁ ተነስቶ የሚሸጥ አይደለም።
መቼ እንደተገዛ፤ በመንግሥት ገንዘብ ነው የተገዛው ወይስ በእርዳታ መልክ የሚለውን መለየት አይቻልም። ዕዳ እንዳለበት፤ በመኪናው ወንጀል መሠራቱን አለመሠራቱን ተጣርቶ ነው የሚሸጠው። ነገር ግን አሁን ላይ የመኪናው ታሪካዊ ዳራ ተመዝግቦ ባለመኖሩ በርካታ ተሽከርካሪዎች መሸጥ ተስኖናል። ነገር ግን እንደ አንደ መፍትሔ ታሪክ የሌላቸውን ተሽከርካሪዎች በአንድ ተሰብስቦ ለመንግሥት ቀርቧል። ከተፈቀደ ይሸጣል። ከዚያ ውጪ ግን ለቆዩ ዕቃዎች ለመሸጥም ለማስወገድም መነሻ የሚሆን ሰነድ የለም።
እንደ ኬሚካል ያሉትን በሀገር ደረጃ ማስወገድ
የማንችላቸው የተቀመጡ አሉ። እነዚህን የማስወገጃ መፍትሔ እየተጠና ነው። ወደፊት አንድ ኬሚካል ከመጣ በኋላ እንዴት ይወገዳል? መቼ ይወገዳል? የሚለው የሚረጋገጠው ኬሚካል ካስገቡ በኋላ አይደለም። ሲገባ ለስንት ዓመት እንደሚያገለግል ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
ለምሳሌ፣ ከአንድ ዓመት በኋላ የአገልግሎት ጊዜው የሚያልፍ ኬሚካል በእርዳታ መልኩ ወደ ሀገር ውስጥ ይገባል። ዕቃው ከገባ በኋላ ጥቅም ላይ ሳይውል የአገልግሎት ጊዜው ያልፋል። ከዚያ በኋላ ለማስወገድ ከገባበት ዋጋ በላይ ይጠይቃል። ስለዚህ እያንዳንዱ ተቋም ኬሚካል ከማስገባቱ በፊት የዕቃውን ዕድሜ የአካባቢ ብክለት ተፅዕኖ አለመኖሩን አረጋግጠው ማስገባት አለባቸው። ማንኛውም ኬሚካል ወደ ሀገር ውስጥ ሲገባ የረጅም ጊዜ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ካልሆነ ግን ወደ ሀገር ውስጥ ሳይገባ ወደ መጣበት ሀገር መመለስ፤ እና እያጣሩ ማስገባት እንደሚገባ በአዋጅ ላይ ተቀምጧል።
አዲስ ዘመን፡- የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸው ንብረቶችን ተቋማት በአግባቡ ማስወገድ ሳይችሉ ሲቀሩ ባለሥልጣኑ የሚወስደው እርምጃ አለ?
አቶ ሐጂ፡- አይ፣ አንወስድም፤ ወስደንም አናውቅም። ከዚህ በፊት የነበረው አዋጅ ይህን ሥልጣን አልሰጠንም። በንብረት ላይ ተጠያቂነት የሚባል ጉዳይ የለም። በዚህ ምክንያት ሰው ንብረትን መንካት ይፈራል። አመራር በአንድ ተቋም ሲሾም በርካታ መኪኖች ቆመው ቢያገኝ ሳይነካ ይነሳል። በአዲሱ አዋጅ ላይ ግን ተጠያቂነት እንዲኖር ተደርጓል። ኃላፊ ተሹሞ በገባበት ተቋም ውስጥ ንብረትን በእንክብካቤ የመያዝ፤ መወገድ ያለበትን በወቅቱ ማስወገድ፤ መሸጥ ያለበትንም በወቅቱ መሸጥ እንደሚገባው ተቀምጠዋል። ይህን ባለማድረግ ተጠያቂነት እንዳለበት በአዋጅ ተቀምጧል። እስካሁን ንብረትን በማባከን የተጠየቀ አካል የለም አልጠየቅንም። ወደፊት ግን ተጠያቂነት ይኖራል።
አዲስ ዘመን፡- በ2015 በጀት አመት የነበረው አፈጻጸምን እንዴት ይገልጹታል?
አቶ ሐጂ፡- ባለፈው ዓመት እስከ ዓመቱ መጨረሻ 27 የሚሆኑ የፌዴራል ተቋማት ዕቅድ የላቸውም ነበር። ነገር ግን ግዥ ይፈጽማሉ። በዚህም የባለሥልጣኑ ኃላፊነት የነበረው ለገንዘብ ሚኒስቴር ሪፖርት ማድረግና ለፓርላማ ማሳወቅ ነው። የእኛ ሥራ የግዥ አፈጻጸምን ከእነ ጉድለቱ ዝርዝር ባለመልኩ ለገንዘብ ሚኒስቴር ማሳወቅ ሲሆን፤ እርጃ የመውሰድ ሥልጣን የገንዘብ ሚኒስቴር ነው። በዋናነት እንደ ሀገር ለመጀመሪያ ጊዜ ሁሉም የፌዴራል ተቋም የግዥ ዕቅድ እንዲኖራቸው ተሠርቷል።
ስለዚህ የ2015 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸሙ የፌዴራል ተቋማት በኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓት እንዲገቡ ማድረግ ነው። ለምሳሌ ኢፍ ሚስ ከጀመረ 15 ዓመቱ ሲሆን ያለው አንድ መቶ (15 ተቋም) ብቻ ነው። የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓት ግን በሦስት ዓመት ውስጥ 169 ተቋማት እንዲገቡ ተደርጓል። የግዥ ሥርዓቱ ሙሉ በሙሉ እንደ ሀገር ተግባራዊ ሲደረግ ፋይናንሻል ኦዲተርን ይተካል። ማጭበርበር፤ መደራደር አይቻልም። ምን ያክል በጀት ከብክነት መታደግ እንደተቻለ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እያጠና ነው። ከግለሰብ እስከ መንግሥት ምን ያህል ገንዘብ ማዳን እንደተቻለ ጥናቱ ሲጠናቀቅ ይፋ ይደረጋል።
አዲስ ዘመን፡- በ2016 በጀት አመት እንደ ግብ ምን ተይዟል? ምንስ ለማሳካት ታስቧል?
አቶ ሐጂ፡- የዚህ ዓመት እቅዳችን፣ በ2016 በጀት አመት መጨረሻ ሁሉም የፌዴራል ተቋም ከእነ ተጠሪዎቻቸው በግዥ ሥርዓቱ ውስጥ እንዲገቡ ማድረግ ነው። ይህ ሲሆን ሌብነትንና ማጭበርበርን በብዙ መልኩ እንደተዋጋን እንቆጥረዋል። ይህ ሲሆን የጥቅም ኔትወርክ እና አድሎ ጠፍቶ መልካም አስተዳደርና ፍትሐዊነት ይሰፍናል። አሁን እንኳን የንግዱ ማኅበረሰብ እንኳን እኩል መወዳደር የሚችልበት ሁኔታ ተፈጠረ የሚል ምላሽ እየሰጡ ነው። ለዚህ ሥራ እንዲያግዘንም ከደረጃዎች ኤጀንሲ ጋር በመነጋገር 328 ዕቃዎች ላይ ደረጃ ወጥቷል።
አዲስ ዘመን፡- ስለነበረን ቆይታ እናመሰግናለን።
አቶ ሐጂ፡- እኔም አመሰግናለሁ።
አዲስ ዘመን
ረቡዕ ኅዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም
ፖለቲካ እና ልዩ ልዩ
ከእኛ አልፈን ለልጆቻችን ተስፋ የምትሆን ሀገር እንስራ !
ነፃ ሃሳብ
በ
ታሪኩ ዘለቀ
ኢትዮጵያ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ጉዞ ብዙ ታሪካዊ ሁነቶች ተስተናግደዋል። እነዚህ ታሪካዊ ሁነቶች በክፉም
በደጉም ሊነሱ የሚችሉ ናቸው። ይህ ደግሞ ትናንት የተገነቡባቸው ሁነቶች/ታሪኮች ባህሪ ነው። ይህንን እውነታ በበቂ ሁኔታ ለትውልዶች ማስገንዘብ ባለመቻላችን በብዙ ፈተናዎች እየተፈተንን ነው።
በእርግጥም የሀገራችን አብዛኛው የታሪክ ትርክት በጦርነት ላይ የተመሠረተ ነው። ይህም በመሆኑ ለከፋ ድህነትና ኋላ ቀርነት ተዳርገናል። እንኳን ከእኩዮቻችን ከታናናሾቿም አንሳ ዘመናት አስቆጥረናል። በየዘመኑም ከዚህ የችግር አዙሪት የምንወጣባቸውን የተለያዩ ዕድል እና መልካም አጋጣሚዎችን መጠቀም ሳንችል ቀርተን አሳልፈናል።
ከ1953 ዓ.ም መፈንቅለ መንግሥት ጀምሮ የ1966ቱ አብዮት፣ የ1983ቱ የኢህአዴግ ድል፣ የ1997ቱ ምርጫ፣ የ2010 ለውጥ እንደመልካም አጋጣሚ ሊቆጠሩ የሚችሉ ናቸው። እስከ 1997 ድረስ ያሉትን ላንመልሳቸው ያባከንናቸው መልካም አጋጣሚዎች ነበሩ፤ የአሁንም ቢሆን በብዙ ፈተናዎች እየተናጠ ነው።
የ1966 ሶሻሊዝም፣ የ1983 የብሔር ፌዴራሊዝም ሕዝብ ሳይመክርበትና ሳያስብበት በጊዜው በነበሩ መንግሥታት የተጫኑ ርዕዮቶች ናቸው። ሀገርና ሕዝብን ያልተገቡ ብዙ ዋጋዎችን ከማስከፈል ባለፈ፤ ዘላቂ ሀገራዊ ሰላምና ልማትን በማስቀጠል ሕዝባችንን ከሚፈልገው የብልጽግና ጎዳና ሊወስዱት አልቻሉም። በአንድ ወቅት ዮሴፍ ወርቁ ደግፌ የተባለ ጸሐፊ
«ቤት በጥበብ ይሠራል በማስተዋልም ይጸናል» በሚል ርዕስ በፃፈው መጣጥፍ፤ «ኢትዮጵያውያን በትንሹም ይሁን በትልቁ በማንኛውም ሀገራዊ ጉዳዮቻችን ላይ ዘወትር በከፋ የአለመግባባት ልዩነት (ቅራኔ) ውስጥ ስለምንገባ፤ በኅብረት (በአንድነት) ለመሥራት ፈፅሞ አለመቻላችን ከመጥፎ ሰብእና (ባህርይ ችግር) ወደ መጥፎ ፖለቲካ ባህልነት እየተቀየረ መጥቷል» ይላል።
«የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሺህ አመታት የዘለቁ ታላላቅ ቀደምት ሃይማኖቶች ተከታይ እንደመሆኑ፤ ከእኛ በላይ በጥሩ ሥነ ምግባር የታነጸና ደግሞም ባለታሪክ ሕዝብ በዓለም ላይ የሚገኝ አይመስለንም።
«ነገር ግን እንደታሪካችን ጥንታዊነትና የቆየ ሃይማኖተኛነታችን ሳይሆን፤ ትናንት ነፃነታቸውን ካገኙ ሀገሮች ጋር ስንወዳደር እንኳን ያለማደጋችን ምስጢር የእኛን የባህርይ ችግር የሚያጋልጥ ነው።
«ነፃነታቸውን ካገኙ ሃምሳ አመት ያልሞላቸው ሀገሮች ከሞላ ጎደል በአጭር ጊዜያት ውስጥ ሠርተው ለውጥ ሲያመጡ፣ እኛ ሺ አመታት ቀደምት ብንሆንም ተስማምተን በጋራ ለመሥራት ባለመቻላችን ብቻ፣ በሚጠበቅብን ደረጃ ማደግ እንዳልቻልን» አትቷል።
በርግጥ በቀደምት ሀገራዊ ትርክቶች ላይ አለመግባባቶች የመኖራችን ያህል እንደ ሀገር ለሺ አመታት አብረን እንድንዘልቅ ያደረጉን፤ የጋራ ፖለቲካዊ ፤ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እሴቶች እንዳሉን መካድ የሚቻል አይደለም። ባህላዊና መንፈሳዊ እሴቶች እንደምንጋራም አፍን ሞልቶ ለመናገር የሚከብድ አይደለም።
በአብዛኛውን የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት አሁን አሁን እየተፈጠሩ ያሉ አለመግባባቶች፤ ሥራዬ ተብለው በሚከወኑ የተዛቡ ትርክቶች የመዋጣቸው እውነታ እንደ ሀገር ለሀገረ መንግሥቱ ሆነ ለብሔራዊ አንድነታችን ስጋት እየሆነ ከመጣ ውሎ አድሯል። ይህ በአብዛኛው በፖለቲካ ኢሌቱ፤ በአክቲቪስቱና በምሁሩ እየተቀነቀነ ያለው ልዩነቶችን አጉልቶ መስበክ፤ የጋራ በምንላቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባገኙ ብሔራዊ ማንነቶቻችን ዙሪያ ሳይቀር ልዩነቶች እንዲሰፉ የሚያስችል ክፍተት እየፈጠረ ነው።
ይህን ዓይነት ችግር የብሔራዊ አንድነት እና የሀገረ መንግሥት ስጋት በሚሆንበት ወቅት፣ ችግሩን ቁጭ ብሎ በሰላማዊ መንገድ በውይይት መፍታት
የሃይማኖት አባቶችም ለሀገር ብቻ ሳይሆን ለግለሰብ ሰላም ለመንፈሳዊ fhይወቱ ካለው ሁለንተናዊ ፋይዳ አንጻር፤ የሰላምን አስፈላጊነት አበክረው ሊሰብኩ፤ ለዚህ ደግሞ ችግሮችን በንግግር በውይይት መፍታት ዋነኛ አቅም ስለመሆኑ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ
ሊያስተምሩ ያስፈልጋል፤
ዘላቂ መፍትሔ እንደሚሆን ይታመናል። ለዚህም እንደ ሀገር ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አቋቁመን ወደ ሥራ መግባታችን በብዙ መልኩ የሚበረታታ እና እውቅና ሊሰጠው የሚገባ ነው።
ምክክርና ውይይት በቦሲንያ ተፈጥሮ ለነበረው የእርስ በርስ ግጭት ዘላቂ መፍትሔ ለማስገኘት፣ በካምቦዲያና በቱኒዝያም ፤ ከሁሉም የከፋ የዘር ፍጅት ባስተናገደችው በሩዋንዳ ስኬታማ ውጤት አስገኝቷል። ‹‹እኔ ርዋንዳ ነኝ›› የሚለው ሕዝባዊ መፈክር ከርዋንዳ ጭፍጨፋ በኋላ የተፈጠረ ቢሆንም፣ መፈክሩ ዛሬም በርዋንዳውያን ልብ ውስጥ ፀንቶ ይገኛል።
ሀገራችን የዛሬዎቹን ሆነ ያደሩ ችግሯቿ ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት ያቋቋመችው ኮሚሽን አሁን ላይ የልዩነት አጀንዳዎችን ወደ ምክክር በማምጣት የጋራ ሀገራዊ እሴቶችን መፍጠር ዋነኛ ግቡ አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ነው። ለግጭትና አለመረጋጋት ምክንያት በመሆን የፖለቲካ ሥርዓት ለውጦች ማምጣት ያስቻሉ ቅራኔዎችን በሠለጠነው የሃሳብ ውይይት ብቻ እንዲፈቱ እየሠራ ይገኛል።
ሀገራዊ የምክክር መድረኩ ችግሮቻችንን ለዘለቄታው ለመፍታት ትልቅ አቅም እና ዕድል ነው። በከፍተኛ ሁኔታ ሕዝብን በማሳተፍ ቀዳሚ ሊሆን የሚችል እንደሆነም እየተነገረ ነው። ከ16 በላይ ተቋማት በንቃት የሚሳተፉበት ከመሆኑ አንፃር ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በአንድም በሌላም የማሳተፍ ዕድሉ ከፍተኛ ነው።
በተለይ አሁን ላይ በኃይል ሃሳብን በሌላው ላይ መጫን እንደ ሀገር ያለንን አቅም ከማዳከም ውጪ የሚያተርፈው ነገር አይኖርም። ከዚህ ይልቅ ልዩነቶችን በውይይት፣ በንግግር መፍታት እንደሀገር ሕዝባችን የሚሻውን ልማት እውን ለማድረግ ያለን አንድ አማራጭ እንደሆነ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ መረዳት የቻልንበት ነው ።
የኢትዮጵያ ሀገር ምስረታ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች የተለየ ነው። ሌሎች ሀገራት አሁን ያላቸው ይዘትና ቅርፅ የያዙት በቀኝ ገዢዎች ነው። የእኛ የሀገረ መንግሥት ምስረታ ታሪክ ረጅም ዘመን ያስቆጠረና የየዘመኑን ዐሻራ የተሸከመ ነው። በዚህ የረጅም ዘመን ሀገረ መንግሥት ታሪክ ውስጥ በእውቀትም ያለ እውቀትም ሊነሱ የሚችሉ ጥያቄዎች ይኖራሉ። ጥሩም መጥፎም ሊባሉ የሚችሉ የታሪክ ክስተቶች ይኖራሉ። እነዚህን ታሪካዊ እውነታዎች አስታርቆ መሄድ ዛሬዎቻችንን ብቻ ሳይሆን ነገዎቻችንን ብሩህ ለማድረግ ወሳኝ እንደሚሆን ይታመናል፣ የኮሚሽኑ አስፈላጊነት ሆነ ተልዕኮ የሚመነጨው ከዚህ ተጨባጭ እውነታ ነው። ትናንቶቻችንን ጎራ ለይተን ለማውገዝና ለመመረቅ ሳይሆን አውቀናቸው ከነሱ
ለመማር ነው ።
የቀደሙት ታሪኮቻችን፤ «ብርሃማ ሆኑ ጨለማማ» ገፆቻችን ፤ የምንጋጭባቸው፣ የምንጣላባቸው፣ ዛሬዎቻችንን የምናባክንባቸው ሳይሆኑ፤ የምንማርባቸው ፣ የመማሪያ መጻሕፍቶቻችን ሊሆኑ ይገባል።
እዚህ ላይ /በብሔራዊ ውይይቶቻችን ወቅት / ትኩረት ልንሰጣቸው የሚገቡ መሠረታዊ ጉዳዮች አሉ። የመጀመሪያው ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽኑ በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ሁሉም ጥያቄዎች ወደ የውይይት መድረኩ እንዲመጡ ዕድል መስጠት አለበት። ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል አለኝ የሚለውን ጥያቄ ይዞ እንዲቀርብ ማስቻል ይተበቅበታል። በዚህ ሂደት አይነኬ የሚባል ጥያቄ ሊኖር አይገባም።
የሌሎች ሀገራት ተሞክሮ ለዚህ እውነታ ትኩረት የሰጠ ነው። የምክክር ሂደቶቹ ከፍተኛ እልቂት ለፈጠሩ አለመግባባቶች ሳይቀር መፍትሔ ማበጀት አስችሏል። በዚህም የታሪክ ሆነ የታሪክ ትርክት ለውጥ መፍጠር ችለዋል። የደቡብ አፍሪካን ተሞክሮ ማንሳት ይቻላል፤ ለብሔራዊ እርቅ የምክክርና የእርቅ ኮሚሽን አቋቁመው ሀገራቸውን ከፍ ካለ ጥፋት መታደግ ችለዋል። በትናንቱ ላይ ተወያይተው ነገዎቻቸውን ብሩህ በሚያደርጉ ዕድሎች ላይ ተወያይተው ወደፊት
መራመድ ችለዋል።
በሀገራችንም በሥራ ላይ የሚገኘው ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ትውልዱን በመንታ መንገድ ላይ ያቆሙ፤ እስከ ዛሬም በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በተጨባጭ ዘላቂ መፍትሔ ማፈላለግ የሚያስችል አስቻይ ሁኔታ ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል። የኮሚሽኑን ተልዕኮ በውጤት ለመደምደም ማኅበረሰቡ ተነጋግሮ ለመግባባት የተከፈተ አእምሮና ለይቅርታ የተከፈተ ልብ ያስፈልጋል።
የምክክር ኮሚሽኑ ሥራ እንዲሳካ የተለያዩ አካላት ኃላፊነት አለባቸው። ከእነዚህ አካላት መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው የመገናኛ ብዙሃን ናቸው። የመገናኛ ብዙሃን የመገንባትም ሆነ የማፍረስ ኃይላቸው ከፍ ያለ ነው። በተለይ አሁን ባለንበት 21ኛው መቶ ክፍለዘመን የኢንፎርሜሽን (የመረጃ ዘመን) በመሆኑ፤ ሕዝቡን ከተሳሳቱና ከተዛቡ መረጃዎች መታደግ ይጠበቅባቸዋል።
የምክከር ኮሚሽኑ ዓላማና ተልዕኮ ለሕዝብ ከማስረዳት ባለፈ፤ የምክክር ምንነትን አስፈላጊነትን በማስረዳት፣ ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት ያለውን ሁለንተናዊ ፋይዳ በማስገንዘብ ሙያዊ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል።
መገናኛ ብዙሃኑ የማኅበረሰብ መሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶችን፣ ምሁራንን በማነጋገር፣ የተለያዩ የኅብረተሰብ አካላትን በማሳተፍ፣ ጉዳዩ በማኅበረሰቡ ውስጥ ትኩረት እንዲያገኝ ማድረግ፤ ሀገሪቱ ያላት ተስፋ ተነጋግራ ችግሮችን መፍታት እንጂ ጦርነት ግጭት አለመሆኑን ማስተማር ይኖርባቸዋል ።
ሀገራዊ ምክክር የአዲስ ባህል ግንባታ አካል ተደርጎ የሚወሰድ፤ እንደሀገር መቀጠል ከፈለግን መነጋገርን፤ መመካከርን ባህል ማድረግ እንዳለብን የሚያመላክት ተጨባጭ ተሞክሮ ሊሆን የሚችል ነው። የምሁራን እና የምርምር ተቋማት ተሳጥፎም ወሳኝ ነው።
የሃይማኖት አባቶችም ለሀገር ብቻ ሳይሆን ለግለሰብ ሰላም ለመንፈሳዊ ሕይወቱ ካለው ሁለንተናዊ ፋይዳ አንጻር፤ የሰላምን አስፈላጊነት አበክረው ሊሰብኩ፤ ለዚህ ደግሞ ችግሮችን በንግግር በውይይት መፍታት ዋነኛ አቅም ስለመሆኑ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሊያስተምሩ ያስፈልጋል፤ ይህ የሃይማኖታዊ ኃላፊነታቸው አካል ስለመሆንም በአግባቡ ተገንዝበው ሊንቀሳቀሱ ይገባል። አስፈላጊ ከሆነም አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ሃይማኖተኛ ከመሆኑ አንጻር በሀገራዊ አለመግባባቶች ዙሪያ ፀሎት እና ምልጃዎችን ማካሄድ፤ባለጉዳዮችን መምከርና መገሰፅ ይጠበቅባቸዋል።
በአጠቃላይ ለምክክር ኮሚሽኑ ስኬት ሁላችንም (ዜጎች) በጋራ ልንታገል ይገባል። በንቃት በመሳተፍ ዓላማውንም በመደገፍ ቁርሾአችንን በይቅርታ፤ ልዩነታችንን በሰጥቶ መቀበል መርህ ልንፈታ ታሪክም፣ ሕግም፣ ህልውናም ግድ የሚሉን ዘመን ላይ እንገኛለን። ይህንን ዕድል ካልተጠቀምን እንደሀገርም እንደሕዝብም የምንከፍለው መስዋዕትነት ከባድና ምናልባትም ከህልውናችን ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል።
ሀገራችን ያለችበትን የፖለቲካ ትኩሳት በመረዳት፣ ካለፉት የጎደፈ ፖለቲካ ታሪካችን በመማር፣ የዓለም አቀፍ ተጨባጭ ሁኔታን ታሳቢ በማድረግ፣ የልዩነት ትርክቶችቻንን በማጥበብ፤ አሰባሳቢ ትርክቶች ላይ ትኩረት በማድረግ እንደ ትውልድ ተሻጋሪ ታሪክ ለመሥራት ራሳችንን ልናዘጋጅ ይገባል፤ ልዩነቶቻችንን ወደ ጠረጴዛ በማምጣት ተወያይተን ሀገራዊ እድገትን በጋራ የሚያራምድ የጋራ ብሔራዊ አጀንዳ ለመቅረፅ እንዘጋጅ።
የኮሚሽኑ ተልዕኮ ጥንታዊቷ ስመ ገናና ሀገራችንን ከጥፋት ከመታደግ ባለፈ፤ ወደ ቀደመ የታሪክ ከፍታዋ የመመለስ ተልዕኮ አካል በመሆኑ በሙሉ አቅማችን ተነጋግረን እና ተስማምተን ልንንቀሳቀስ ያስፈልጋል። በዚህም ከእኛ አልፈን ለልጆቻችን ተስፋ የምትሆን ሀገር እንስራ ።
አዲስ ዘመን ረቡዕ ኅዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም
ኢኮኖሚ
ንግድና ግብይት
በገበያ ትስስርና የገጽታ ግንባታ አላማውን ያሳካው ጉባኤ
ፍሬfhይወት አወቀ
የኢትዮጵያ ጥራጥሬ፣ ቅባት እህሎችና ቅመማ ቅመም አዘጋጅቶ ላኪዎች ማሕበር ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በቅርቡ ለ12ኛ ጊዜ ዓለም አቀፍ የጥራጥሬና የቅባት እህሎች ጉባኤ አካሂዷል። ጉባኤው በርካታ የዘርፉ ተዋናዮች ተሳትፈዋል። ጉባኤው ዘርፉን ለማሳደግ፣ የገበያ ትስስር ለመፍጠር፣ ምርቶቹን ለማስተዋወቅና የገጽታ ግንባታ ለመፍጠር በእጅጉ እንደሚያግዝ አስቀድሞም እንደታመነበት ሁሉ፣ ስኬታማ መሆኑን የኢትዮጵያ ጥራጥሬ፣ ቅባት እህሎችና ቅመማ ቅመም አዘጋጅቶ ላኪዎች ማሕበር ጉባኤው ገልጿል።
“ኢትዮጵያ ለግብርና ምርት ፍላጎት አስተማማኝ ምንጭ” በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደው ይህ ጉባኤ አገሪቱ ለወጪ ንግዱ ያላትን እምቅ ሀብት ለዓለም በማስተዋወቅ የውጭ ምንዛሪ ግኝቷን ማሳደግ እንድትችልና ባለሀብቶችንም በመሳብ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ተገልጿል። ከዚህ ባለፈም ዘርፉ የሚጠበቅበትን እንዲወጣና በመንግሥት የተያዘው የወጪ ንግድ እቅድ እንዲሳካ ለማድረግና የጥራጥሬ፣ ቅባት እህሎች እና ቅመማቅመም አዘጋጅቶ ላኪዎች ማሕበርም በዘርፉ እያበረከተ ያለውን የሥራ እንቅስቃሴ ለማስተዋወቅ ጉባኤው የላቀ ድርሻ ማበርከቱም ተጠቁሟል።
12ኛው ዓለም አቀፍ የጥራጥሬና የቅባት እህሎች ጉባኤ በኢትዮጵያ መካሄዱ በዘርፉ ያለውን የገበያ ትስስር
በጉባኤው ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና በጥራጥሬና ቅባት እህሎች ዘርፍ የሚሰሩ በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል
መፈረም እንደቻሉ የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፤ ይህ ከገዥ አገራት ጋር የተደረገ ስምምነት ውጤታማ እንደነበርም አስታውቀዋል። በተጨማሪም የዓለም አቀፍ ምርት ፍላጎት መጠን እና የዋጋ አዝማሚያ መረጃዎችን ማግኘት
በአሁኑ ወቅት ያለው ሁኔታ ምርት ለማንቀሳቀስ ምቹ መሆኑን አቶ ሲሳይ ጠቅሰው፣ የሰላሙ ሁኔታ በዚሁ ከቀጠለ ይህ ዓመት ከፍተኛ መጠን ያለው ምርት ማግኘት እንደሚቻልም ተናግረዋል።
ለውጭ ገበያ በሚቀርቡ ምርቶች ላይ እሴት ከመጨመር ጋር ተያይዞ ማሕበሩ የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ መቆየቱን ያነሱት ፕሬዚዳንቱ፤ ለእዚህም ከአኩሪ አተርና ከመሳሰሉት ዘይት ለማምረት የተደረጉ ሙከራዎች መኖራቸውንም በአብነት ጠቅሰዋል። በአገሪቱ ከምርት አቅርቦት ጋር በተያያዘ ፋብሪካዎች በሚፈለገው መጠን ጥሬ ዕቃዎችን እያገኙ እንዳልሆነም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።
ማሕበሩ ምርቶቹን በጥሬው ብቻ ለውጭ ገበያ ከማቅረብ ይልቅ እሴት ጨምሮ ለመላክ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ያጋጠሙ ችግሮችን አንድ በአንድ በጥናት በመለየት ለሚመለከተው አካል በማቅረብ መፍትሔ የማምጣት ሥራ እየተሰራ ነውም ብለዋል። ለአብነትም ከችግሮቹ መካከል ተጠቃሽ የሆነውን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ሰፊ መሬት የሌላቸው አርሶ አደሮች በኮንትራት እርሻ በስፋት እንዲያመርቱ የማድረግ ሥራ መሰራቱን አስታውቀዋል። በቀጣይም ይህ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠው፣ አገሪቷ ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን የውጭ ምንዛሪ ማግኘት እንድትችል እንደሚሠራ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።
እሳቸው እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚመረቱት
ለማጠናከርና የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ ለማስተዋወቅ ማስቻሉን የጥራጥሬ፣ ቅባት እህሎች እና ቅመማቅመም አዘጋጅቶ ላኪዎች ማሕበር ገልጿል፤ ማሕበሩ ዓላማውን ማሳካት የቻለ ጉባኤም ብሎታል። በጉባኤው በአገሪቱ የሚገኙ ላኪዎች፣ ግብዓት አቅራቢዎች፣ አገልግሎት ሰጭዎችና ገዥዎችን በአንድ መድረክ ማገናኘት መቻሉን ማሕበሩ ጠቅሶ፣ እነዚህ አካላት የንግድ ግንኙነታቸውን ማጠናከር በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል ብሏል። በተለይም በጉባኤው የተገኙ አምራቾች፣ ላኪዎችና አቅራቢዎች አዳዲስ የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ ማስቻሉንም አስታውቋል።
ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትልካቸው የግብርና ምርቶች መካከል የጥራጥሬና ቅባት እህሎች በውጭ ምንዛሪ ግኝት ከፍተኛ አቅም እንዳላቸው የጠቀሱት የማኅበሩ ፕሬዚዳንት አቶ ሲሳይ አስማረ፣ ለውጭ ምንዛሪ ግኝት ጉልህ አበርክቶ ያላቸውን እነዚህን ምርቶች በጥራት አምርቶ ለገበያ ማቅረብ ተገቢ መሆኑንም አመልክተዋል። ለዚህም ለዘርፉ ዕድገት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን መፍታት ቀዳሚው ሥራ ሊሆን ይገባል ብለዋል።
‹‹ለዘርፉ ዕድገት ማነቆ ከሆኑ ችግሮች መካከል የፀጥታ እጦት፣ የኮንትሮባንድ ንግድና የምርት ጥራት ችግር ተጠቃሽ ናቸው›› ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ችግሩን ለመፍታት ከመንግሥትና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሠራ እንደሆነም ተናግረዋል። በቀጣይም ዘርፉን በማሳደግ አገሪቱ በሚፈለገው ደረጃ የውጭ ምንዛሬ እንድታገኝ ለማድረግ የምርት ጥራትን በማሻሻልና የገበያ መዳረሻ ሀገራትን በማስፋፋት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
ፕሬዚዳንቱ እንዳሉት፤ በወጪ ንግድ ሰፊ ድርሻ ካላቸውና ለአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ከሚያስገኙ የግብርና ምርቶች መካከል የላቀ ድርሻ ያላቸው የቅባትና ጥራጥሬ ሰብሎች በዓለም አቀፍ ገበያ ውስጥ ገብተው ተወዳደሪ መሆን እንዲችሉ በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ ናቸው። ከሥራዎቹ መካከልም በየዓመቱ የሚዘጋጁ ጉባኤዎች ይጠቀሳሉ። በቅርቡ የተካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤም የግብይት ሰንሰለትን የሚዳስሱ፣ የአቅርቦትና የገበያ ሁኔታን የሚመለከቱ፣ የዓለም ገበያው ያለበትን ሁኔታ ለሀገር ውስጥ ላኪዎች ሊያስረዱ የሚችሉ ከ14 በላይ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበውበታል።
ከዚህ ቀደም ከተካሄዱት ጉባኤዎች ይልቅ በቅርቡ የተካሄደው 12ኛው ዓለም አቀፍ የጥራጥሬ እና ቅባት እህሎች ጉባኤ በርካታ ተሳታፊዎችን ማስተናገድ የቻለ ሲሆን፤ በዚህም ጥሩና አበረታች ውጤት ተመዝግቧል። በቀረቡት ጽሁፎች ዙሪያ ጥያቄዎች ቀርበው ተገቢ ምላሾች ከመድረኩ ተሰጥቶባቸዋል።
በጉባኤው ላይ የአገር ውስጥ እንዲሁም የተለያዩ አገራት እንግዶች ተገኝተዋል፤ ከእነሱም መካከል ላኪዎች፣ ገዥዎች፣ የእርሻ ግብዓት አቅራቢዎች፣ የእርሻ ማሽን
በዓለም አቀፍ የጥራጥሬና የቅባት እህሎች ጉባኤው የግብይት ሰንሰለትን የሚዳስሱ፣ የአቅርቦትና የገበያ ሁኔታን የሚመለከቱ፣ ዓለም ገበያው ያለበትን ሁኔታ ለሀገር ውስጥ ላኪዎች ሊያስረዱ የሚችሉ ከ14 በላይ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበውበታል
አቅራቢዎች፣ ተጋባዥ እንግዶች ከተለያዩ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ ኤምባሲዎች፣ የልማት አጋር ድርጅቶች እና መገናኛ ብዙሃን ተጠቃሾች ናቸው።
በጉባኤው የተገኙት አጠቃላይ ተሳታፊዎች 482 ሲሆኑ፤ ከእነዚህ መካከልም የአገር ውስጥ ተሳታፊዎች 292 ናቸው። ከ19 የተለያዩ አገራት የመጡ የውጭ አገር ተሳታፊዎች ደግሞ 70 ይደርሳሉ። በጉባኤው ከተሳተፉ ሀገሮች መካከል ቤልጂየም፣ ቡርኪናፋሶ፣ ቻይና፣ ግብጽ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፣ ሕንድ፣ እስራኤል፣ ጃፓን፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ናይጄሪያ፣ ፓኪስታን፣ ሳውዲአረቢያ፣ ታንዛንያ፣ ሱዳን፣ ቱርክ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ዩክሬንና ሲንጋፖር ይገኙበታል።
ከኤምባሲዎች የተገኙት ተጋባዥ እንግዶች፣ ከመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ ከግሉ ዘርፍ፣ ከልማትና አጋር ድርጅቶች እንዲሁም የሚዲያ ባለሙያዎች በአጠቃላይ 120 እንደሚደርሱም ማህበሩ ጠቅሷል። ከተሳታፊዎች መካከል በተለይም አምራችና ላኪዎች ከገዢ አገራት ጋር ስኬታማ የሆነ የንግድ ለንግድ የአቻ ውይይቶችን ማካሄድ ችለዋል።
በተፈጠረው የገበያ ትስስር የንግድ ለንግድ አቻ ውይይትም 20 በመቶ የሚሆኑ ላኪዎች በቀጣይ ምርቶቻቸውን መላክ የሚያስችላቸውን ስምምነት
መቻሉንም ገልጸዋል። ይህንንም ከተሳታፊዎቹ ባገኙት ግብረመልስም ማረጋገጥ እንደቻሉ ተናግረዋል።
በጉባኤው የሽልማት ፕሮግራም እንደተካሄደም የጠቀሱት ፕሬዚዳንቱ፣ በጥራጥሬ እና ቅባት እህሎች ዘርፍ ከፍተኛ አፈጻጸም ላሳዩ ስድስት ድርጅቶች የዋንጫ እና የምስክር ወረቀት መሰጠቱን ገልጸዋል። በተለይም በጥራጥሬ እና በቅባት እህሎች ዘርፍ ከፍተኛ ዕውቅና ባገኙ 12 ባለሙያዎች ጠቃሚና ተገቢ መረጃ መቅረቡንም አመላክተዋል። ከ12ቱ ባለሙያዎች ሁለቱ የአገር ውስጥ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ አስሩ ደግሞ የውጭ አገር መሆናቸውን አመልክተዋል። የዘርፉ ባለሙያዎች ያቀረቧቸው ጥናታዊ ጽሁፎች፤ የገበያ መረጃዎች፣ የምርት አቅርቦት እና የዋጋ አዝማሚያዎች ትንተናዎች እና ትንበያዎችን ያካተቱ ጽሁፎች እንደነበሩም ጠቁመዋል።
12ኛው ዓለም አቀፍ የጥራጥሬና የቅባት እህሎች ጉባኤ ዋና ዓላማ አድርጎ የተነሳው አባላት ወይም የኢትዮጵያ ላኪዎች ከገዢዎች ጋር ግንኙነት ማድረግ እንዲችሉ መሆኑን የጠቀሱት ፕሬዚዳንቱ፣ ሌላው የጉባኤው ዓላማ በዚሁ አጋጣሚ የአገሪቱን መልካም ገጽታ ማስተዋወቅ እንደሆነና ይህንንም ማሳካት እንደተቻለ ነው ያመላከቱት።
እሳቸው እንዳሉት፤ ከዚህ ቀደም የተካሄዱ ዓለም አቀፍ የጥራጥሬና የቅባት እህሎች ጉባኤ ኢትዮጵያ በቅባት እህሎችና በጥራጥሬ ምርት አቅርቦት ቀዳሚውን ስፍራ እንድትይዝ አድርገዋል። በመሆኑም በአሁን ወቅት ኢትዮጵያ በጥራጥሬና የቅባት እህል አቅራቢዎች ሰሌዳ ላይ የተቀመጠች አገር መሆን ችላለች። በተለይም ጥራት ያላቸውና ስም ያላቸው ምርቶች ማለትም እንደ ሁመራ ሰሊጥ የመሰለ ምርት ኢትዮጵያ በዓለም ስሟ እንዲጠራ አድርጓል። ለዚህም ላኪዎችና ማሕበሩ ትልቅ ድርሻ የነበራቸው መሆኑን ነው የጠቀሱት።
በቀጣይም ኢትዮጵያ በግብርና ምርት ያላትን እምቅ ሃብት ተጠቅማ ኢኮኖሚዋን ማሳደግ እንድትችል እንዲህ አይነት ጉባኤዎች ወሳኝ ናቸው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ የግብርና ምርት ለኢትዮጵያውያን እንጀራ በመሆኑ በዘርፉ ሰፊ የሆነ የእሴት ሰንሰለት ስለመኖሩ አስረድተው ምርቱን በሌሎች ዓለማት የማስተዋወቅ ሥራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አመላክተዋል።
12ኛው ዓለም አቀፍ የጥራጥሬና የቅባት እህሎች ጉባኤ የተካሄደበት ወቅት አዳዲስ ምርቶች ወደ ገበያ እየገቡ ያሉበት መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ጠቅሰው፣ ገዢዎች ወደ አገሪቷ መጥተው ፋብሪካዎችን መጎብኘት መቻላቸው ውጤታማ አድርጎናል ነው ያሉት። በዚህ ረገድም ሰፊ ሥራ እየተሰራ እንደሆነ አመላክተው፣ ላኪዎች እስከታች ወርደው አርሶ አደሩ ምርቱን እንዲያወጣ በማድረግ በተለይም ኢትዮጵያ የምትታወቅበትን የሰሊጥ ምርት በጥራት ሰብስቦ ወደ ገበያ ለማቅረብ ሰፊ ሥራ እየተሰራ ነው ብለዋል።
የጥራጥሬና የቅባት እህሎች በዓለም ላይ እጅግ ተወዳዳሪና ተፈላጊ ናቸው። የአገሪቷ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ለብዙ የዓለም አገራት ቅርብ እና አመቺ መሆን ለእዚህ አንዱ ምክንያት ተደርጎ ይወሰዳል። ይህንኑ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ምርቱን በጥራት በማምረት በተቀላጠፈ መንገድ ለዓለም ገበያ ማቅረብና ኢኮኖሚያዊ አበርክቶውን ከፍ ለማድረግ ማሕበሩ ትልቅ ድርሻ አለው።
ለእዚህም ምርቶቹን በጥራት ለዓለም ገበያ ለማቅረብ የማስተዋወቅ ሥራ መሥራት አንዱና ዋነኛው ሥራ መሆኑንም አስታውቀዋል። በአፍሪካ ኢትዮጵያን የሚያህል ሰፊ መሬት ያለውና በግብርና ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚ ያለው አገር የለም ሲሉ ጠቅሰው፣ ይህን በተቻለ መጠን ወደ ማዕከል አምጥቶ ለዓለም ገበያ ለማስተዋወቅ የቅንጅት ሥራ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። በእዚህ በኩል ማሕበሩ ከመንግሥት ጋር እየሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ በአብዛኛው ምርቶቿን ወደ ኤዥያ፣ መካከለኛው ምስራቅ፣ አሜሪካና አውሮፓ ስትልክ መቆየቷን የጠቀሱት ፕሬዚዳንቱ፤ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ምርቶቹ ለአፍሪካ አገራት በተለይም ጎረቤት ከሆኑ አገራት ጋር የገበያ ትስስር በመፍጠር ወደ ኬንያ፣ ጅቡቲ፣ ሶማሊያ እየተላኩ መሆናቸውን አመልክተዋል።
እሳቸው እንዳሉት፤ ይህም ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገራት ጋር ያላትን የንግድ ቁርኝት በማጠናከር በኩል ያለው አበርክቶ ጉልህ ነው። በጉባኤው ላይም የጉባኤው ተሳታፊ በርካታ ገዢዎች ከአምራችና ላኪዎች ጋር የተዋወቁበትና አዳዲስ የገበያ ዕድሎችም የተገኙበት ሁኔታ ታይቷል።
በ2015 በጀት ዓመት 147 ሺህ 205 ቶን የሚደርሱ የቅባት እህሎች ለውጭ ገበያ ቀርበው 253 ሚሊዮን 344 ሺህ 754 የአሜሪካ ዶላር ገቢ ተገኝቷል። ለውጭ ገበያ ከተላኩ 377 ሺህ 261 ቶን የጥራጥሬ ምርቶችም እንዲሁ 310 ሚሊዮን 568 ሺህ 278 የአሜሪካ ዶላር ገቢ ተገኝቷል።
በ2016 በጀት ዓመት ከቅባት እህሎችና ከጥራጥሬ ሰብሎች ወጪ ንግድ 593 ሚሊዮን 300 ሺህ ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ እየተሠራ ሲሆን፤ በሩብ ዓመቱም ከ117 ሚሊዮን 769 ሺህ ዶላር በላይ ተገኝቷል።
በጉባኤው የተገኙ የተለያዩ የውጭ ዜጎች ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን እምቅ ሃብት የመረዳት ዕድል ያገኙ ሲሆን፤ ለንግድ አመቺ መሆኗን ጭምር መገንዘብ ችለዋል። ደንበኞች በጉባኤው የገቡት ውል ተፈጻሚ እንደሚሆንም አስታውቀዋል፤ የውል መቋረጥም ሆነ የጭነት መስተጓጎል ሊገጥማቸው እንደማይችል ፕሬዚዳንቱ አረጋግጠዋል። በአጠቃላይ ጉባኤው የንግድ ልውውጥና የገበያ ማስፋት ሥራ የተሠራበት ብቻ ሳይሆን አገራዊ የገጽታ ግንባታ መፍጠር የተቻለበትና ስኬታማ መሆን የቻለ እንደነበር አስታውቀዋል።
አዲስ ዘመን ረቡዕ ኅዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም
መዝናኛ
50 ሜትር ፈቀቅ …
ማረፊያ/ትዝብት
ሰሚራ በርሀ
በአንድ ትልቅ የኪነጥበብ ምሽት ላይ ነው። ብዙ ወጣት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ በምሽቱ የተገኙ የጥበብ ወዳጆችና በእንድግነት የተጋበዙ አንጋፋ ባለሙያዎች በቦታው አሉ። በመድረኩ ስራቸውን እንዲያቀርቡ አንድ እንግዳ ተጋበዙ። በእድሜ ገፋ ያሉ፣ አንገታቸው ላይ ስካርፍና ክብ ባርኔጣ ያደረጉ ሰው ወደ መድረኩ ቀረቡ።
ሰውዬው ወግ አዋቂ ናቸው። ካሳለፉት ሕይወት የሚሉት አላቸው። ወጋቸው በቁም ነገር የተከበበ ነው። ልክ ልጅ ለአባቱ የሚሰጠው ትህትናና ቅንነት የሚታይበት ምክር አይነት። በጨዋታ እያዋዙ ጥሩ ይናገራሉ። ታዳሚው በንግግራቸው መሀል በሳቅና በጭብጨባ ይከተላቸዋል።
ምክሮቻቸው በገጠመኞች የተዋዙ ናቸው። የዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎች ስነ-ምግባር በጎደላቸው መመህራን ስለሚገጥማቸው የጾታ ትንኮሳ አንስተው እነዚህ መምህራን ከዚህ ተግባራቸው እንዲታቀቡ በቀልድ አዋዝተው ገሰጽ አደረጉ።
ቀጠል አደረጉ እና ይህ ችግር እሳቸው ዩኒቨርሲቲ በሚማሩ ጊዜ የነበረ እና አሁንም ያለ ስለመሆኑ አስታውሰው ችግሩ መቼም የማይፈታና የማይለቅ በሽታ ነው አሉ። በታዳሚዎቹ መሀል አሁንም ሳቅ ሆነ። ጨዋታ አዋቂው ሰው ቀጥለው ለወንዶች ተማሪዎች እንዲህ አሉ ‹‹ አስተማሪ አይኑን ከጣለባት ተማሪ
50 ሜትር ራቅ በሉ ወይንም በፍጹም እንዳታስቡት
›› ወጥወድ ውስጥ ናችሁ አይነት ማስጠንቀቂያ ጣል አደረጉ።
ንግግሮቻቸው በሙሉ ሳቅን ያዘሉ በመሆናቸው አለመሳቅ አይቻልም። እኔ ግን በዚህ ጨዋታ እንኳን ለመሳቅ ጥርሴ አልፈገገም። የዩኒቨርሲቲ
ተማሪ በነበርኩበት ወቅት በዚህ መንገድ የተፈተኑ ሴት ተማሪዎች መኖራቸውን ስለ ማውቅ ይሁን ሴት ስለሆንኩ አላውቅም ከሳቅ ይልቅ ወደ አዕምሮዬ የመጣው ጥያቄ ሆነ።
ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ ለግቢው ማሕበረሰብ አዲስ ስለሆኑ፣ የተለያየ ሀሳብ እና ልምድ ካላቸው ተማሪዎች ጋር ስለሚተዋወቁና በአፍላ ዕድሜያቸው ላይ ስለሚገኙ ቦታው ስብዕናቸውን የሚገነቡበት ይሆናል።
ይህ አካባቢ አዲስ ቦታ፣ አዲስ የመማሪያ ስፍራ፣ አዲስ ጓደኛ፣ አዲስ የመማር ማስተማር ሂደት በእኩል የሚገናኙበት ነው። ተማሪዎቹ በነዚህ ሁሉ አዳዲስ ነገሮች ይፈተናሉ። ወግ አዋቂው እንደተናገሩትም ለወጣት ወንድ ተማሪዎች ሁነኛ መፍትሄው ከጉዳዩ መራቅ ነው።
ለሴት ተማሪዎች ግን መፍትሄው ምን እንደሆነ አልጠቀሱም። አንድ ሰው ራሱን በስነ ምግባር ከማረቅ በዘለለ ምን ማድረግ እንደሚሻል ጠቅሰውም ይህ ነው አላሉም። ምናልባት የመፍትሄ አካል ናቸው የሚባሉት የነገሩ ተባባሪ ሆነው ይሆናል።
ለኔም ጥያቄ የሆነብኝ ነገር ለምን የማይፈታ ነገር ችግር ሆነ የሚለው ነው። ወግ አዋቂው በንግግራቸው መሀል ባነሱት ገጠመኝ አንዲት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ወደ እርሳቸው ጠጋ ብላ በትምህርት ቤት ውስጥ በሁለት ምክንያት መቸገሯን ታጫውታቸዋለች። ጉዳዩ በሁለት ስነ ምግባራቸውን ባልጠበቁ ‹‹ወደድኩሽ›› ባዮች መካከል ያለ እውነታ ነው።
አንደኛው ‹‹ወደድኩሽ›› ባይ ተማሪ ‹‹የፍቅር ጥያቄዬን ተቀበይኝ አለዚያ ግን ጉልበት አለኝ›› የሚላት ሲሆን ሌላኛው ጠያቂ ደግሞ በጊዜው አገላለጽ ‹‹እሺ በይኝ ካልሆነ ውጤት አለኝ ብለሽ እንዳታስቢ›› የሚል የመምህርነትን ካባ የለበሰ ነው።
የወግ አዋቂው ሀቅ የሁሉም ችግር መፍትሄው ራስን ማነጽ እና በስነ ምግባር መገንባት መሆኑ ግልጽ ነበር። ይሁን እንጂ ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች በብልሹ ስነ-ምግበር ውስጥ ወድቀው ይገኛሉ። ይህ የስነምግባር ግድፈት ደግሞ ሌሎች ሰላማዊ ሰዎችንም ሲያውክ ይታያል። የሕግ አስፈላጊነትም ለዚህ ይመስለኛል።
ሴት ተማሪዎች ታዲያ የዚህ ሰለባ ላለመሆን የሚጠቀሙበት አንዱ መንገድ ውጤታቸው በማያውቁት መንገድ ቢበላሽ በምንም አይነት ሁኔታ ወደ መምህሩ ቢሮ አለመሄድን ነው። ቆፍጠን ያሉ ጎበዝ ሴት ተማሪዎችም ቢሆኑ ትክክለኛ ውጤታቸውን ለመጠየቅ ቢፈልጉ መጀመሪያ የአስተማሪውን ጀርባ ማጥናታቸው አይቀሬ ይሆናል።
በዚህ ጉዳይ ብዙ ችግር የደረሰባቸው፣ ከሚመለከተው አካል መፍትሄ ማግኘት ያልቻሉ የሚገባቸውን ውጤት የተነፈጉና ግፋ ሲልም ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎች አሉ።
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ መግባት ለወላጆችም ሆነ ለተማሪዎች ትልቅ ቦታ አለው። ወላጆች
‹‹ልጄ ትማርልኛለች፣ ትልቅ ደረጃ ትደርስልኛለች›› ብለው ልጆቻቸውን ከጉያቸው ሲለዩ በቆይታዋ የሚገጥማትን ፈተና እንዴት እንደምታልፈው ነግረው፣ መክረው፣ እና አስጠንቅቀው ይልካሉ።
ይህን መሰሉን ከአንዳንድ አስተማሪዎች የሚደርስባትን ትንኮሳ ግን እንዴት ታልፈው ይሆን ሲሉ የሚያስቡት አይመስልም። እንዲያው ይህን መሰል መፍትሄ ያጣ ጉዳይ በዩኒቨርሲቲ ስለመኖሩ ቢያውቁ ምን ይሉ ይሆን ? ተማሪዋ ደግሞ ‹‹ይበጀኛል›› የምትለውን የትምህርት ዘርፍ መርጣ ‹‹እደርስበታለው›› ያለችውን አቅዳ ስትመጣ ይህ ጉዳይ ከገጠማት ህልሟን እውን ስለማድረጓ ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ
ስጋት ነው።
ይህ ጉዳይ በዩኒቨርሲቲ ሕይወት ተንሰራፍቶ እንደ ልማድ መቆጠሩ አዲስ አለመሆኑ በራሱ የሚያሳፍር ጉዳይ ነው። ችግሩን ለመፍታት ወግ አዋቂው እንዳሉት
‹‹ራስን በስነ ምግባር ማነጽ›› ትልቅ ነገር ቢሆንም ሁሉም አንድ አይነት አይሆንምና ችግሩ ከዩኒቨርሲቲው ሳይወጣ መፈታት የሚችልበት ብዙ መፍትሄ ይኖራል።
ከነዚህ መፍትሄዎች አንዱ የትምህርት ክፍሉ ኃላፊዎች ይህ መሰሉ ጥቆማ ሲደርሳቸው የሚወስዱት እርምጃ ነው። እንዲህ መደረጉ ነገሩን ከጅምር አስቀርቶ የመማር ማስተማር ሂደቱን ሰላማዊ ያደርጋል። ሌላው በግቢው ከሚቋቋሙት ዘርፎች አንዱ ሴት ተማሪዎችን የሚደግፈው የስርዓተ-ጾታ ጉዳዮች ክፍል ሚና ነው። በእኔ እሳቤ ይህ ክፍል ስለዚህ ጉዳይ ‹‹ጆሮ ዳባ ልበስ›› ብሎ መቀመጥ አይገባውም። ተማሪዎችን ከወላጆቻቸው በአደራ ተቀብለው በዚህ ረገድ ግን ኃላፊነታቸውን መወጣት ያልቻሉ ኃላፊዎችም ሊጠየቁ ይገባል። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚመጡ እንደመሆናቸው
ትንሿ ኢትዮጵያን ይወክላሉ።
ችግሩ በትምህርት ገበታ ላይ ብቻ ታይቶ የሚቋጭ አይደለም። በተመሳሳይ ይህ መሰሉ ፈተና በስራ ዓለም ጭምር የሚያጋጥም እውነታ ነው። በትንሿ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ እየታየ የቆየው ችግር ወደሌላኛው ትውልድ እንዳይቀጥል ያስፈልጋል።
ችግሩ መኖሩ ሲታወቅ የሚመለከታቸውና ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን መወጣት ቢችሉ ይህ ማሕበረሰባዊ ጠንቅ ዕድሜው ባጠረ ነበር። ወግ አዋቂው በቦታው ተገኝተው ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያስተላለፉት መልዕክት ግን ከዓመታት በኋላ ባለውለታ አድርጎ እንደሚያስቆጥራቸው ጥርጥር የለውም። አበቃሁ!
ዓለም አቀፍ
ሴኡል ምስሎቹ በይፋ ስላልተለቀቁ የስለላ ሳተላይቷን አቅም መገምገም ይከብዳል ብላለች
የሰሜን ኮሪያ የስለላ ሳተላይት “ዋና ዋና ኢላማዎችን” ፎቶ አንስታ መላክ ጀመረች
የተራዘመው የተኩስ አቁም ጊዜ በቂ አይደለም-ተመድ
በጋዜጣው ሪፖርተር
ሰሜን ኮሪያ በቅርቡ ያመጠቀቻት የስለላ ሳተላይት ምስሎችን መላክ መጀመሯ ተነግሯል።
የስለላ ሳተላይቷ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት መቀመጫ ዋይትሃውስን እና የመከላከያ ሚኒስቴሩን ቢሮ (ፔንታጎን) የሚያሳዩ ምስሎች መላኳ ነው የተገለጸው።
የሀገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ ኡንም ምስሎቹን መመልከታቸውን የሰሜን ኮሪያ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ (ኬሲኤንኤ) ዘግቧል። ፒዮንግያንግ የአሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለመቃኘት ታገለግላለች የተባለች የስለላ ሳተላይት
ባለፈው ሳምንት በተሳካ ሁኔታ ማስወንጨፏ ይታወሳል። ሳተላይቷ “ወሳኝ የኢላማ ክልሎች”ን ምስል እየላከች ነው
ያለው ኬሲኤንኤ፥ የደቡብ ኮሪያ መዲና ሴኡል እና የአሜሪካ ወታደራዊ ጣቢያዎችን ምስል መላኳንም አመላክቷል።
ኪም ጆንግ ኡን በአሜሪካ የሚገኘውን የአንደርሰን አየር ኃይል ጣቢያ እና ኖርፎልክ በተሰኘው አካባቢ የሚገኘውን
የአሜሪካ ባሕር ኃይል እንቅስቃሴ የሚያሳዩ በሳተላይቷ የተላኩ ምስሎች መመልከታቸው ተገልጿል።
በእነዚህ ወታደራዊ ጣቢያዎች አሜሪካ አራት በኒዩክሌር የሚሰሩ ግዙፍ መርከቦችን ጨምሮ በርካታ የጦር መሳሪያዎች ማከማቸቷንም ነው የሰሜን ኮሪያ ቴሌቪዥን ጣቢያ የዘገበው። አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ሰሜን ኮሪያ ለሶስተኛ ጊዜ ያደረገችውን የስለላ ሳተላይት ሙከራ የመንግስታቱ ድርጅትን ክልከላ ይቃረናል በሚል መቃወማቸውን ሬውተርስ
አስታውሷል።
ፒዮንግያንግ ግን አሳሳቢ የሆነውን የዋሽንግተን እና ሴኡል ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለመቃኘት ሳተላይቷ ወሳኝ ድርሻ እንዳላት ስትገልጽ ቆይታለች።
አሜሪካ ስለሳተላይቷ ምስሎች እስካሁን ምንም አስተያየት አልሰጠችም።
ደቡብ ኮሪያ ግን በሳተላይቷ ተነሱ የተባሉት ምስሎች በይፋ ስላልተለቀቁ የስለላ ሳተላይቷን አቅም ለመገምገም አዳጋች ነው ብላለች።
በጋዜጣው ሪፖርተር
ተመድ በጋዛ የተራዘመው የተኩስ አቁም ጊዜ በቂ አለመሆኑን ገልጿል።
የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በእስራኤል እና ሀማስ መካከል የተራዘመው ተኩስ አቁም ተስፋ ሰጭ ቢሆንም በጋዛ ያለውን የእርዳታ ፍላጎት ለማሟላት በቂ አይደለም ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
አደራዳሪዋ ኳታር የአራቱ ቀን የተኩስ አቁም ስምምነቱ በሁለት ቀናት የተራዘመው ሁለቱም ኃይሎች ፍላጎት በማሳየታቸው ነው ብላለች።
በእስራኤል እና ሀማስ መካከል ለሰባት ሳምንታት የቆየው ጦርነት ጋብ ያለው በጋዛ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ነው።
ዘላቂ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ ቢደረግም፣ ሀማስን አጠፋለሁ የምትለው እስራኤል ግን እንደማትቀበለው ስትገልጽ ቆይታለች።
የተኩስ አቁሙ መራዘም በጋዛ እርዳታ ለሚፈልጉ
ሰዎች የሚደረገውን እርዳታ መጠን ለመጨመር የሚያስችል መሆኑን የገለጹት ዋና ጸኃፊው ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ሕዝብ ለመድረስ ግን የሚበቃ አይደለም ብለዋል።
ተመድ እስካሁን እርዳታ እያደረሰ ያለው በግብጽ በኩል ያለውን የራፋ ድንበርን በመጠቀም ነው። ተመድ እርዳታ ለማድረስ በእስራኤል ቁጥጥር ስር ያለውን ከረም ሻሎም ሟቋረጫን ለመጠቀም ፍላጎት አለው።
አንቶኒዮ ጉተሬዝ ይህ እንዲሆን እስራኤል ትፈቅዳለች ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
የጉተሬዝ ቃል አቀባይ ስቴፋኒ ዱጃሪክ ጊዚያዊ ተኩስ አቁሙን ወደ ዘላቂ ተኩስ አቁም ለመቀየር ድርድሮች መቀጠል አለባቸው ብለዋል።
ሰባት ሳምንታት ያስቆጠረውን ጦርነት ያስቆመውን ጊዚያዊ ተኩስ አቁም፣ በሀማስ እጅ የነበሩ በርካታ የእስራኤል ታጋቾች እንዲለቀቁ እና በእስር ላይ የነበሩ ፍልስጤማውያን እንዲለቀቁ አስችሏል።
አዲስ ዘመን ረቡዕ ኅዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም
ሰሚራ በርሀ
ባለውለታዎቻችን
ማህበራዊ
የሀገር ፍቅርን በስራቸው የገለጹት የቴሌኮሙ ሰው
በዓለማችን ላይ በአሁን ሰዓት የምናስተውላቸውን ለውጦች አዲስ የፈጠራ ሀሳብ ባመጡ የፈጠራ ባለቤቶች ብቻ ሳይሆን እነዚህን የፈጠራ ውጤቶች ደፍረው ለመጀመሪያ ጊዜ የሞከሯቸውና እውቅና የሰጧቸው ሰዎች ለዓለም መቀየር ትልቁን ድርሻ ይወስዳሉ። ነገር ግን የለውጥ ሂደት መነሻው ሀሳብ በመሆኑ ከተለመደው አስተሳሰብና አኗኗር ለየት ብለው ለምን ብለው የጠየቁ ሰዎችን መርሳት አይገባም ።
መጋቢት ሁለት 1928 ዓ.ም በጥንታዊቷ አንኮበር ከተማ አፈርባይኔ በተባለች መንደር ተወለዱ። የተወለዱበት ወቅት ጣልያን ኢትዮጵያን የወረረበትና ወደ አንኮበር የተጠጋበት ጊዜ ነበር። የሚኒልክ ቤተመንግስት የሚገኘው ደግሞ በዚሁ በአንኮበር ሲሆን በዚያ የነበሩ አርበኞችም ቤተመንግስቱን እየጠበቁ ይዋጉ ነበር። የጣልያን ጦር ወደ ከተማዋ ተጠግቶ የመሳሪያ ድምፅ ሲሰማ የአጼ ሚኒልክን ቤተመንግስት እንዳልነበር ሲያደርገው በስፍራው የነበሩ ጎጆ ቤቶችም ሲቃጠሉ በአካባቢው የነበሩ ነዋሪዎችም ራሳቸውን ለማዳን ከቦታው መሸሽ ጀመሩ። ወይዘሮ አስካለ ማርያም የአራስ ቤት ልጃቸውን ይዘው ከቦታው ሸሹ። በማግስቱ ነገሩ ሲረጋጋ የተረፈውም ሰው ወደቀዬው ሲመለስ ሕጻኑና ወይዘሮ አስካለ የደረሱበት አልታወቀም። ሞተዋል ተብሎ ለቅሶ ይጀመራል። ባለቤታቸው እምሩ ራስወርቅም ወዲያና ወዲህ እያሉ ፈልጉልኝ በማለት ተጨንቀዋል። ሰዓቱ ረፈድፈድ ሲል ሁሉም ወደ ነበረበት ተመልሶ ሁካታው ጋብ ሲል እናት አራስ ልጃቸውን በጉያቸው አቅፈው ወደመንደራቸው ተመለሱ። በሕይወት በመገኘታቸውም እልልታ ሆነ። መምህር ራስወርቅም ልጄ ተረፈልኝ ብለው እግዚአብሔርን አመስግነው የልጃቸውን ስም ተረፈ ብለው ሰየሙት።
የተረፈ አባት በሙያቸው የተለያዩ መጽሀፍትን ይጽፉ የነበረ፣ በቤተክህነት ውስጥ የሚያገለግሉ ሰው ነበሩ። ከዚህም ሌላ አባታቸው ራስወርቅ የተለያዩ መጽሀፎችን የማሸግ ስራ የሚሰሩ ሲሆን ከጣልያን ወረራ በኋላ ትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤትን አቋቁመዋል። በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤትም የመጀመሪያው መምህር ነበሩ።
ጣልያን በኢትዮጵያ ላይ ያደረገው ወረራ ተረፈን ገና ከልጅነት ጊዜያቸው ጀምሮ ሲፈትናቸው፤ አባታቸውም ሆኑ ወንድሞቻቸውም ለሀገራቸውም ትልቅ መስዋዕትነትን የከፈሉ ናቸው። ጣልያን በኢትዮጵያ ለአምስት ዓመት ሲቆይ የተረፈ አባት ሚናቸው ሁለት ነበር። አንድም የቤተክርስትያን አገልጋይ አንድም ደግሞ በአንኮበር የነበሩ አርበኞችን በድብቅ ማገዝ። በዚህ ስራቸው ያግዟቸው የነበሩት የተረፈ ታላቅ ወንድም ጥሩነህ ራስወርቅ ናቸው። እሳቸው በተፈሪ መኮንን ት/ቤት ሳሉ የፈረንሳይኛ ቋንቋን ለምደው ነበርና ወደ አንኮበር ተጉዘው በዚያ ሰፍሮ የነበረውን ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጣልያን ጦር በመጠጋት የታቀደውን እና የተደረገውን ለአባታቸው በመናገር እንደ ውስጥ አርበኛ ሆነው አገልግለዋል።
ሌላኛው ወንድማቸው ሜጄር ዮሀንስ ራስወርቅ ሲሆኑ በጊዜው ጣልያን ኢትዮጵያ ላይ የምታደርሰውን ግፍ ለመቃወም ንጉሰነገስቱ ወደ ጄኔቭ ሲያመሩ ዮሀንስና አጋሮቻቸው በሀገር ውስጥ ትልቅ ተጋድሎ ፈጽመዋል። በአንድ አጋጣሚም ሜጄር ዮሃንስ ከሌሎች አለቆች ጋር ጦራቸውን ለማጠናከር ሲሰባሰቡ በድንገት በጣልያን ጦር ከበባ ስር ወደቁ። ወደ አዲስ አበባ አምጥተዋቸውም እንዲተባበሯቸው ጠየቋቸው የቁም እስረኛ አድርገውም አስቀመጧቸው። በዚያን ወቅትም በየካቲት 12 1934 ዓ.ም ግራዚያኒ ላይ በተደረገው የግድያ ሙከራ በኢትዮጵያውያን ላይ በደረሰው ግፍ ውስጥ እጃቸው አለበት በሚል ሜጀር ዮሀንስ ላይ ሞት ፈረዱባቸው።
ኢንጂኒየር ተረፈ ከካህንና መምህር አባት እንደመገኘታቸው በልጅነታቸው ከአባታቸው እግር ስር ፊደልን ቆጥረዋል። በ1933 ዓ.ም ቤተሰቦቻቸው ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ በቄስ ትምህርት ቤት ገብቶ ዳዊትን ደግመዋል። በዳግማዊ ሚኒልክ ትምህርት ቤት ቀጥሎም ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት በመግባት ትምህርታቸውን ቀጥለዋል። ተፈሪ መኮንን በዘመኑ በሀገሪቱ ትልቅ ከሚባሉት ትምህርት ቤቶች ውስጥ አንዱ ነበር። ከአንድ ሺህ በላይ ተማሪዎች የሚማሩበት ሲሆን የንጉሠ ነገሥቱ ቤተ መንግሥት ቅርብ ስለነበር ጃንሆይ በየጊዜው ትምህርትቤቱን ይጎበኙ ነበር። ይህም ዘወትራዊ ጉብኝት ተማሪዎቹንና መምህራኑን ያስደስታቸውና ያበረታታቸው
ኢንጂነር ተረፈ ራስወርቅ
ነበር።
በሕይወት ዘመናቸው ለነበራቸው በጎ ስብዕናና የቀናነት መንፈስ በትምህርትቤታቸው ውስጥ የነበረው የስካውት ቡድን መርህ በእጅጉ እንደረዳቸውና ሕይወታቸውን ሙሉ ሲከተሉት እንደነበር በነበራቸው ቃለመጠይቅ ተናግረዋል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ከጨረሱ በኋላ በቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ቻሉ። በመጀመሪያው የትምህርት ዓመትም የነበራቸው ውጤት በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ ሲሆን ለወጣቱ ተረፈ ደግሞ በእችላለሁ መንፈስ በላቀ ውጤት እንዲቀጥሉ አድርጓቸዋል። ከትምህርት ባሻገርም በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በርካታ ስራዎች ላይ መሳተፋቸውን ቀጠሉ። በተሳትፏቸውም ከንጉሰነገስቱ ሙገሳን አግኝተዋል።
በ1950 ዓ.ም ለተሻለ ትምህርት ከተመረጡ ሌሎች ተማሪዎች ጋር ወደ ኒውዮርክ አሜሪካ አቀኑ። ኢንጂኒየር ተረፈ የመረጡት የትምህርት ክፍል የኤሌክትሪክ ምህንድስና ነበር። በሚማሩበት ትምህርትቤት ውስጥ ጥቂት ጥቁሮች ብቻ ሲኖሩ በመረጡት ትምህርት ክፍል ውስጥ ከጓደኛቸው ማህዲ መሀመድ በቀር ሌላ ጥቁር አልነበረም። ተረፈና ጓደኛው በክፍሉ ውስጥ በጊዜ ተገኝተው ሲቀመጡ ከነሱ በኋላ የሚመጡት ነጭ ተማሪዎች በፍፁም በአጠገባቸው አይቀመጡም ነበር። ሁለቱ ተማሪዎች ለዚህ መፍትሄ ያደረጉት ተማሪዎች ገብተው ካለቁ በኋላ መሄድን ነበር። ይህ ከትምህርቱ በላይ በጣም ከባድ ነበር። የኢንጂኒየሩ ጓደኛ ማህዲ ወደ ጂኦሎጂ የትምህርት ክፍል ሲቀይር ኢንጂኒየር ተረፈ ብቻቸውን ሆኑ። መምህሩ በክፍሉ ውስጥ የሚሰጡትን የቡድን ስራ አብሯቸው ለመስራት የሚፈልግ ነጭ አልነበረም። ሌሎች በቀኝ ግዛት ተይዘው የነበሩ ሀገራት በእንደዚህ አይነት ጫና ውስጥ ሲወድቁ አንገታቸውን ይደፋሉ። ወጣቱ ግን ይህ ታሪክ በዘመናቸው አልነበረምና ለመቀበል ፍቃደኛ አልነበሩም። ታሪካቸውን ማንነታቸውን ማወቃቸውም የመንፈስ ጥንካሬ አሳድሮባቸዋል። በመሆኑም በገፏቸው ቁጥር ጠንክረው በመማር በትምህርታቸው ውጤታማ ለመሆን ችለዋል።
ኢንጂኒየር ተረፈ ትምህርታቸውን እንደጨረሱ በተማሩበት ሀገር በትልልቅ ኩባንያዎች ውስጥ የመስራት እድል ጠቀም ካለ ክፍያ ጋር ቀርቦላቸው ነበር። ነገር ግን ኢንጂኒየሩ ፍቃደኛ አልነበሩም ምክንያታቸው ደግሞ ለውጭ ሀገር የትምህርት እድል ተመርጠው የስንብት ፕሮግራም ሲደረግላቸው ጃንሆይ ያሏቸው በልባቸው ቀርቶ ነበር። ‹‹ የተማረ የሰው ኃይል ያስፈልገናል እናንተ ውጪ ሀገር የምትሄዱት ትምህርት ቀስማችሁ ሀገራችሁን እንድታገለግሉ ነው። ሀገራችሁ ትጠብቃችኋለች እንደጨረሳችሁ ተመልሳችሁ ኑ ›› የሚል ንግግር ነበር። በዚያ የወጣትነት እድሜ ላይ ከንጉሰ ነገስቱ አንደበት
ለሀገር ትጠቅማላችሁ መባል ትልቅ ነገር በመሆኑ በጊዜው ወደ ውጭ ሀገር የሄዱ ተማሪዎችም ትምህርታቸውን እንደጨረሱ ወደ ሀገራቸው መመለስን ነበር የሚያስቡት። ትምህርታቸውን ጨርሰው ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ስራቸውን የጀመሩት በቴሌኮሙኒኬሽን ቦርድ ውስጥ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ የተመደቡበት የትራንስሚሽንና የረጅም ርቀት ስርጭት ክፍል ነበር። በጊዜው ገና የ25 ዓመት ወጣት ቢሆኑም የእድሜ ማነስ ሳይገድባቸው
ስራቸውን በጥልቅ ማስተዋል ሰርተዋል።
በወቅቱ የፋክስ ግንኙነት ባለመኖሩ የመልዕክት ልውውጥ የሚደረገው በቴሌግራፍ ነበር። ይህ የቴሌግራፍ የመልዕክት ልውውጥ የሚደረገው በላቲን ፊደላት ነበር። በዓለም ላይ የራሳቸው ፊደላት ያላቸው ሀገራት ውስን ሲሆኑ ከአፍሪካ ደግሞ ኢትዮጵያ የራሷ ፊደል ያላት ብቸኛዋ ሀገር ናት። ነገር ግን ለመልዕክት ልውውጥ የምትጠቀመው የላቲን ፊደልን ነበር። ይህ ለሀገር ወዳዱ ኢንጂኒየር በቀላሉ የሚታለፍ አልሆነም የራሳችንን ፊደል ለምን አንጠቀምም ሲሉ ጠየቁ የተሰጣቸውን ምክንያትም በቂ ሆኖ አላገኙትም። የመከራከሪያ ነጥቡ የነበረው የኢትዮጵያ ፊደላት ቁጥር ከላቲን ፊደላት ቁጥር መብለጡ ቴሌፕሪንተሮቹ የተፈጠሩት ለላቲን ፊደላት ነው የሚል ነበር። ኢንጂኒየሩም የኢትዮጵያ ፊደላትን እንዴት ቴሌፕሪንተር ውስጥ ማስገባት እንደሚቻል በሆሄያቱ ላይ ልዩ ጥናት አደረጉ።
ጥናታቸውን ሲጨርሱም በወረቀት የሰፈረው ንድፈ ሀሳብ ሲመንስ ለተባለ የጀርመን ኩባንያ ተላከ። ኢንጂኒየር ተረፈም ወደ ጀርመን ሄደው በቴሌፕሪንተሩ ላይ የፊደላቱን አቀማመጥ ልክ መሆኑን ካረጋገጡ በኋላ በኢትዮጵያዊው ወጣት የተሰራ የመጀመሪያው ቴሌፕሪንተር ይፋ ሆነ። ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴም ቴሌፕሪንተሩን መርቀው በከፈቱበት እለት አንዱ ቴሌፕሪንተር በአሥመራ ቤተ- መንግስት አንደኛው አዲስ አበባ ተቀመጠ። በወቅቱ የኤርትራው ገዢ የነበሩት ራስ አስራተ ካሳ በአዲሱ ቴሌፕሪንተር መልዕክታቸውን በአማርኛ ፊደላት ሲልኩ ግርማዊነታቸው መልዕክቱን አይተው የደስታ ስሜታቸውን መደበቅ አልተቻላቸውም ነበር።
ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ኢንጂኒየሩ ለሰሩት ስራ በጊዜው የነበሩትን ስራ አስኪያጅ ምን አድርጋችሁለታል ሲሉ ቢጠይቁም ‹‹ አስፈላጊው ተደርጎለታል ›› ሲሉ መለሱ፤ ነገር ግን ወጣቱ ኢንጂኒየር ተረፈ ራስወርቅ ምንም ጥቅም አላገኙም ነበር። ኢንጂኒየሩም ስለዚህ ጉዳይ አንስተው ለመጠየቅ ፍላጎት አልነበራቸውም። ነገር ግን በአእምሮኣዊ ንብረት የባለቤትነት መብታቸው እንዲጠበቅ አድርገዋል። ኢንጂኒየር ተረፈ ራስወርቅ ይህንን የኢትዮጵያ ፊደል የያዘ ቴሌፕሪንተር ለመስራት ባደረጉት ጥናት ሀሁ በቀላሉ የሚል ፊደላትን በቀላሉ ለመማር የሚያስችል መማሪያ መጽሀፍም አዘጋጅተዋል።
የዓለም አቀፍ የቴሌኮምኒኬሽን አንድነት በ1865 ዓ.ም ተቋቁሞ መቀመጫውን ጄኔቭ ያደረገ ትልቅ ድርጅት ነው። ይህን ድርጅት ኢንጂኒየሩ በተቀላቀሉበት ዘመን ሕብረቱ የአፍሪካ ክፍልን የሚመራ ባለሙያ በመፈለግ ለአባል ሀገራቱ ክፍት ቦታ መኖሩን አሳወቀ። ኢንጂኒየር ተረፈም ከተወዳዳሪዎቹ አንዱ ሆነው የትምህርት ሁኔታቸውና የሰሩት ስራ ሁሉ በሚገባ ታይቶ የሕብረቱ ባልደረባ ለመሆን ቻሉ። ከዚያም በዓለም አቀፍ የቴሌኮምኒኬሽን ሕብረት የአፍሪካ ጉዳይ ክፍል ውስጥ ስራቸውን ጀመሩ። የተመደቡበት ክፍል ስራ አፍሪካ በቴሌኮም ዘርፍ እድገት እንድታመጣ ማስቻል ነው። በሕብረቱ ውስጥ የአፍሪካ ጉዳዮች ኃላፊ ሆነው በሰሩባቸው ዓመታት የአፍሪካን የቴሌኮም ዕድገት እውን ለማድረግ ልክ እንደሁልግዜው
መስራት ጀመሩ። የመጀመሪያው የሕብረቱ ቀዳሚ ተግባር የቴሌኮምኒኬሽን ማሰልጠኛዎችን በየሀገሩ መመስረት ነበር።
ኢንጂኒየር ተረፈ ራስወርቅ አንዳንድ የአፍሪካ አገራት ነፃነታቸውን ካገኙ በኋላም የስልክ መገናኛ መስመራቸው ከድሮ ቀኝ ገዢ ሀገራት ጋር ስለነበረ መስመሩን የሚያስተላልፉት በብራስልስ፣ በፓሪስ፣ በለንደንና በሮም በኩል በመሆኑ ቀኝ ገዢዎቹ መረጃውንም ይጠቀሙበት ነበር። የኢንጂኒየር ተረፈ ራስወርቅ ትልቁ ስኬት የነበረው የቀኝ ግዛት መስመርን መስበር መቻላቸው ነበር።
በመስሪያቤቱ በነበራቸው ቆይታ የበርካታ ሀገራትን የቴሌኮም የእድገት ደረጃ ለመለየት ችለዋል። በእርሳቸው የስራ ዘመን የቻይና ቴሌኮምኒኬሽን ከኢትዮጵያም ያነሰ በመሆኑ ቻይና እና ጃፓን አሁን ላሉበት የቴሌኮሙኒኬሽን ኢንደስትሪ ትልቅ አስተዋፅኦ ካደረጉ የሕብረቱ ሰዎች ውስጥ ይጠቀሳሉ። በኢትዮጵያ ውስጥ በቴሌው ዘርፍ ብዙ መሠራቱን ያምኑበታል። በዓለም አቀፍ የቴሌኮም ዘርፍ ባለሙያዎች ዘንድ ትልቅ ከበሬታን አግኝተዋል። ኑሯቸውንም ስራቸውንም በጄኔቭ አንድ ብለው የጀመሩት የስራ ዘመንም ለ40 ዓመታት ያህል ዘልቋል።
ኢንጂኒየር ተረፈ ራስወርቅ ትዳር የመሰረቱት በ1954 ዓ.ም ሲሆን ከወይዘሮ ብርሀኔ አስፋው ጋር ከ50 ዓመታት በዘለቀ ትዳራቸው መተሳሰብ መደጋገፍና ፍቅር የሚታይበት ነበር። በትዳራቸው ሶስት ልጆችን አፍርተዋል። ኢንጂኒየር ተረፈ ራስወርቅ አብዛኛውን የስራ ሕይወታቸውን ከሀገራቸው ውጪ ስላሳለፉ ልጆቻቸውም የተወለዱት ከሀገር ርቀው ነበር። በዚህም ስለ ሀገራቸው ያላቸው ቦታ እና እይታ እንዳይቀንስ ኃላፊነት የሚሰማቸው ሀገራቸውንና ማንነታቸውን እንዲያውቁ አድርገው አሳድገዋቸዋል። ልጆቻቸውም በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ሀገራቸውን በበጎ ለማገልገል እየሰሩ ሲሆን በስማቸው የተሰየመ ፋውንዴሽንና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሽልማትን መስርተው ሳይንስና ቴክኖሎጂ ነክ ፈጠራዎች በኢትዮጵያ እንዲበረታቱ ያደርጋሉ። በተጨማሪም የኢንጂኒየር ተረፈ ፈጠራ የሆነውን የመጀመሪያውን ቴሌፕሪንተር የሀገር ሀብት ነው በማለት ለኢትዮጵያ ቅርስና ጥበቃ ባለስልጣን አበርክተዋል። በርክክቡ ወቅትም ቴሌፕሪንተሩ በሙዚዬም ውስጥ ከሚገኙ ውስን የኢትዮጵያን የቴክኖሊጂ ጉዞ የሚያሳይ ቅርስ መሆኑ ተጠቅሷል።
ኢንጂኒየር ተረፈ ራስወርቅ የስራ ጊዜያቸውን ጨርሰው ጡረታ በወጡበት ጊዜም ልረፍ ብለው ሳይቀመጡ ወደ ተወለዱባት አንኮበር ከተማ ተመልሰው ታሪካዊነቱን በሚመጥን መልኩ ከእህታቸው ልጅ ኃይለ ገብርኤል ዳኜ (ዶ/ር) ጋር በመሆን አምባ ኤኮቱሪዝም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በማቋቋም ፋሺሽት ጣሊያን ኢትዮጵያን በ1928 ዓ.ም. በወረረ ጊዜ በጦር አውሮፕላን ያወደመውን የአፄ ምኒልክ ሕንፃ በባሕላዊ መንገድ እንደገና ከማሠራታቸውም ባሻገር በዙሪያው የነበሩትን የሹማምንቱን መኖሪያ ቤቶችን በጥንቱ አሠራር እንደገና በመገንባት የእንግዶች መኝታ ቤቶች በተለየ መልኩ ሎጅ በመስራት አንኮበር በድጋሚ ለቱሪስቶች ምቹ እንድትሆን አድርገዋል። የስራ ጉዟቸውን ሕይወታቸውን የሚዳስስ
‹‹የአንኮበሩ ሰው በጄኔቫ›› የሚል መጽሀፍም አሳትመዋል። ላመኑበት ጉዳይ እስከመጨረሻው ቆመው ያሰቡትን የሚያሳኩ፤ ለሀገራቸው የነበራቸውን ፍቅር በሕይወት ዘመናቸው በስራዎቻቸው ውስጥ የገለጡት እኚህ የሀገር ባለውለታ በተወለዱ በ86 ዓመታቸው ሚያዝያ 30 ቀን 2014 ዓ.ም አጥተናቸዋል። ስማቸውም በሰሩት ስራ ሁል
ጊዜ ሲወሳ ይኖራል።
ስፖርት
አዲስ ዘመን
ረቡዕ ኅዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ዋንጫ ሶስተኛውን ዙር የተቀላቀሉ ክለቦች ተለይተዋል
አለማየሁ ግዛው
ከሶስት ዓመታት መቋረጥ በኋላ ሂደቱን በመቀየር ወደ ውድድር የተመለሰው የኢትዮጵያ ዋንጫ ወደ ሶስተኛው ዙር ያለፉ ክለቦች ተለይተው ታውቀዋል፡፡ በሁለተኛው ዙር 32 ክለቦችን እርስ በእርስ በማፋለም ቀጣዩን ዙር የተቀላቀሉ 16 ቡድኖችን በመለየት የቀጣይ መረሃ ግብሮች ይፋ ተደርገዋል፡፡
በታሪካዊው የኢትዮጵያ ዋንጫ የሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች ላለፉት ሶስት ቀናት ማለትም ቅዳሜ፣ እሁድ እና ሰኞ የተካሄዱ ሲሆን፤ በዚህም ወደ ሶስተኛ ዙር ያለፉ ክለቦች ተለይተዋል፡፡ ጨዋታዎቹ በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ፣ በሀዋሳ አርቴፊሻል ሜዳና በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ስታዲየም በማካሄድ ቀጣዩን ዙር የተቀላቀሉት ክለቦች ታውቀዋል፡፡ ዘንድሮ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የፕሪምየር ሊጉን ክለቦችና የታችኛውን እርከን ክለቦች በአንድ በማፋለም ላይ የሚገኘው ውድድሩ ጠንካራና ያልተጠበቁ ውጤቶችንም በማስመልከት ላይ ይገኛል፡፡ ከነዚህም መካካል ለረጅም ዓመታት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲወዳደር የነበረው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ተሸንፎ ከውድድር መውጣቱ ተጠቃሽ ነው፡፡ በተጨማሪም እርስ በርስ የተገናኙት የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ከወዲሁ ከውድድሩ አንዲወጡ ግድ ሆኖባቸዋል፡፡
በዚህም በመጀመሪያ ቀን በተካሄዱ ውድድሮች ኢትዮጵያ መድን፣ ኮልፌ ቀራኒዮ እና ደብረ ብርሃን ከተማ ሶስተኛውን ዙር የተቀላቀሉ ክለቦች ሆነዋል፡
፡ ኢትዮጵያ መድን ድሬደዋ ከተማን በመግጠም
አዲስ አበባ አስተዳደር
በጠባብ ውጤት አሸንፎ ቀጣዩን ዙር የተቀላቀለ ሲሆን፤ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን አስተናግዶ 1ለ0 በማሸነፍ
በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል፡፡ ደብረብርሃን ከተማ ከጋሞ ጨንቻ ያደረጉት ጨዋታ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ያለ ግብ ተጠናቆ በመለያ ምት ደብረብርሃን ከተማን
5ለ4 አሸንፎ እሱም በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ሩብ ፍጻሜውን መቀላቀል ችሏል፡፡
በተመሳሳይ ቀን በተካሄዱ ሌሎች ጨዋታዎች ወደ ቀጣይ ዙር ያለፉ ክለቦች የተለዩ ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈው ወደ ቀጣይ ዙር ገብተዋል፡
፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ አዲስ አዳጊውን ሀምበሪቾ ዱራሜን ገጥሞ 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ አጼዎቹ በበኩላቸው ነቀምቴ ከተማን አስተናግደው 3ለ0 በማሸነፍ
ቀጣዩን ዙር ሲቀላቀሉ፣ ወላይታ ድቻ ደሴ ከተማን 3ለ1 በሆነ ውጤት በመርታት ማለፉን አረጋግጧል፡፡
እሁድ ዕለት ሌሎች ቀጣዩን ዙር የተቀላቀሉ ክለቦች የተለዩባቸው ጨዋታዎች የተደረጉ ሲሆን በነዚህም የተለያዩ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡ ሁለቱን የሊጉን ክለቦች ያፋለመው የመቻል እና የወልቂጤ ከተማ ጨዋታ በመቻል 2 ለምንም አሸናፊነት
ሊጠናቀቅ ችሏል፡፡ ኦሮሚያ ፖሊስን ከ አርባ ምንጭ ከተማ ያገናኘው ጨዋታ ደግሞ በመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 1ለ1 ተጠናቆ በመለያ ምቶች አዞዎቹ 10 ለ9 አሸንፈው ቀጣዩን ዙር ተቀላቅለዋል፡፡ ሻሸመኔ ከተማ ከከፋ ቡና ያደረጉት ጨዋታ በመለያ ምት በሻሸመኔ
ከተማ 5ለ4 አሸናፊነት ተጠናቆ ሻሸመኔ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅሏል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና ወልዲያ ከተማን 4ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፎ ቀጣዩን ዙር የተቀላቀለ ሌላኛው ክለብ ሲሆን ባህርዳር ከተማ እንደ አዲስ የተመሰረተውን ሸገር ከተማን ገጥሞ 1ለ0 በማሸነፍ ወደ ቀጣይ ዙር አልፏል፡፡ አዳማ
ከተማ ሲዳማ ቡናን ገጥሞ በአስገራሚ ሁኔታ 4ለ0 በሆነ ውጤት ረቶ ማለፍ ችሏል፡፡ ከትላንት በስቲያ በተካሄዱ የመጨረሻ ቀን ጨዋታዎች ነገሌ አርሲ ስልጤ ወራቤን፣ ሀዲያ ሆሳዕና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን፣ ሀዋሳ ከተማ ቤንች ማጂ ቡናን እና ቢሾፍቱ ከተማ ሀላባ ከተማን በማሸነፍ ቀጣዩን ዙር የተቀላቀሉ ክለቦች መሆን ችለዋል፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሶስተኛው ዙር የሚገናኙትን ክለቦች ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ ጨዋታዎቹ ከታህሳስ 12-14 ባለው ጊዜ ወደ ፊት በሚገለጽ ቦታ፣ ቀንና ሰዓት
የሙያ ምዝገባና ፈቃድ መጥፋት ማስታወቂያ
አቶ ባህሩ ደመቀ ሸዋረጋ የተባሉ በሲኒየር ፋርማሲ ሙያ በጤና ሚኒስቴር የተመዘገቡ ሲሆን የሙያ ፈቃድ ሰርተፊኬት ጠፋብኝ ብለው በቀን 11/03/2016ዓ.ም ከፖሊስ በተጻፈ ማስረጃ አመልክተዋል፡፡ ስለሆነም የተጠቀሰውን የሙያ ፈቃድ ሰርተፊኬት ወድቆ ያገኘ ወይንም በእዳ ይዤዋለሁ የሚል በአንድ ወር ጊዜ ካላመለከተ ተለዋጭ የሙያ ፈቃድ ሰርተፊኬት የሚሰጥ
መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድኃኒት አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን
እንደሚካሄዱ ገልጿል፡፡ በዚህም መሰረት 16 ክለቦች ሩብ ፍጻሜውን ለመቀላቀል ጠንከር ያለ ፉክክርን እንደሚያስተናግዱ ይጠበቃል፡፡ ይፋ በሆነው መረሃ ግብር መሰረት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሻሸመኔ ከተማ፣ ሀዲያ ሆሳዕና ከወላይታ ድቻ፣ ቢሾፍቱ ከተማ ከአዳማ ከተማ፣ ነገሌ አርሲ ከኢትዮጵያ መድን፣ ባህርዳር ከተማ ከአርባ ምንጭ ከተማ፣ ሀዋሳ ከተማ ከ መቻል፣ ደብረብርሃን ከተማ ከፋሲል ከነማ እና ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ይጫወታሉ፡፡
የባለንብረት ስም ሄኖክ አስራት ተገኔ የሰሌዳ ቁጥር አአ 02-01-C20632 የተሽከርካሪው አይነት
አውቶሞቢል የሻንሲ ቁጥር MBHZF6C11NG235562 ሞዴል ZF6C1 የሞተር ቁጥር K12MP4321135 የሊብሬ ቁጥር 479396 ከላይ የተጠቀሰው የተሽከርካሪ ባለንብረት የተሽከርካሪ ሰሌዳ ጠፋብኝ ብለው 11/3/2016 አመልክተዋል፡፡ ሠሌዳው ወድቆ፣ ተሠርቆ ወይም በሌላ ተሽከርካሪ ላይ ተለጥፎ ያገኘ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀን ውስጥ የፍ/ቤት ማሳገጃ ትዕዛዝ እንዲያቀርቡ እያስታወቅን ፣ ይህ ባይሆን ግን ለአመልካች ተለዋጭ ሠሌዳ የምንሰጥ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ
ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅ/ጽ/ቤት
አመልካች ወ/ሮ ሰብለ አድነው
ተጠሪ አቶ ዘውዱ ማስረሻ
መካከል ስላለው የቤተሰብ ክርክር ጉዳይ ፍ/ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ ተከሣሽ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ቂርቆስ ምድብ 1ኛ ቤተሰብ ችሎት እየታየ መሆኑን በዚህ የጋዜጣ ማስታወቂያ አውቀው መልስዎን በጽሁፍ ለ02/04/2016 ዓ.ም. በ3፡30 ሰዓት እንዲያቀርቡ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
የሙያ ምዝገባና ፈቃድ መጥፋት ማስታወቂያ
ማርታ ተፈሪ ታደሰ በ “Junior Level 4 Nurse ሙያ በአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት አስተዳደር እና ቁጥጥር ባለስልጣን የተመዘገቡ ሲሆን የሙያ ፈቃድ ሰርተፊኬት ጠፋብኝ ብለው በቀን 07/03/2016ዓ.ም ከፖሊስ በተጻፈ ማስረጃ አመልክተዋል፡፡ ስለሆነም የተጠቀሰውን የሙያ ፈቃድ ሰርተፊኬት ወድቆ ያገኘ ወይንም በእዳ ይዤዋለሁ የሚል በአንድ ወር ጊዜ ካላመለከተ ተለዋጭ የሙያ ፈቃድ ሰርተፊኬት
የሚሰጥ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድኃኒት አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን
ደረሰኝ መጥፋት ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ወረዳ 12 የቤት ቁጥር አዲስ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) 0016948439 ቢኮ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋም ኃላ/የተ/የግ/ማኀበር በግብር/ታክስ ከፋይነት ከተመዘገብኩበት በገቢዎች ሚ/ር ምዕራብ አዲስ አበባ ቁጥር 2 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ፅ/ቤት የህትመት ፍቃድ በማግኘት ካሳተምኩት የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ የእጅ በእጅ ሽያጭ ደረሰኝ ከቁጥር 1451 እስከ 1469 የተሰራበት እና ከቁጥር 1470 እስከ 1450 ያልተሰራበት ስለጠፋብኝ በማንኛውም አካል እጅ ውስጥ ገብቶ ወንጀል እንዳይሰራባቸው እና የጠፋ መሆኑን የ3ኛ ወገን እንዲያውቀው ይህ ማስታወቂያ እንዲተላለፍ ተደርጓል፡፡ነገር ግን ከደረሰኙ ውስጥ ተሰርቶበት ያገኘ ወይም ከድርጅቱ ግዥ በማከናወን ክፍያ በመፈፀም በማስረጃነት የተቀበለ ማንኛውም ሰው ከላይ ለተጠቀሰው በግብር/ታክስ ከፋይነት ለተመዘገብኩበት በገቢዎች ሚ/ር ምዕራብ አዲስ አበባ ቁጥር 2 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ፅ/ ቤት ወይም በአቅራቢያ ለሚገኝ ገቢ ሰብሳቢ መ/ቤት በማሳወቅ በግብር/ታክስ አሰባሰብ ላይ ትብብር እንዲያደርግ አስታውቃለሁ፡፡
የግብር ከፋይ ስም ቢኮ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋም ኃላ/የተ/የግ/ማኀበር
ደረሰኝ መጥፋት ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክ/ከ ወረዳ 05 የቤት ቁጥር 754 ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) 0002192755 ኢማጅ መፍቱ መሐመድ በግብር/ታክስ ከፋይነት ከተመዘገብኩበት በገቢዎች ሚ/ር ልደታ ክ/ከ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ፅ/ቤት የህትመት ፍቃድ በማግኘት ካሳተምኩት የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ የእጅ በእጅ ሽያጭ ደረሰኝ ከቁጥር 01 እስከ 1400 የተሰራበት ስለጠፋብኝ በማንኛውም አካል እጅ ውስጥ ገብቶ ወንጀል እንዳይሰራባቸው እና የጠፋ መሆኑን የ3ኛ ወገን እንዲያውቀው ይህ ማስታወቂያ እንዲተላለፍ ተደርጓል፡፡ነገር ግን ከደረሰኙ ውስጥ ተሰርቶበት ያገኘ ወይም ከድርጅቱ ግዥ በማከናወን ክፍያ በመፈፀም በማስረጃነት የተቀበለ ማንኛውም ሰው ከላይ ለተጠቀሰው በግብር/ ታክስ ከፋይነት ለተመዘገብኩበት በገቢዎች ሚ/ር ልደታ ክ/ከ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ፅ/ቤት ወይም በአቅራቢያ ለሚገኝ ገቢ ሰብሳቢ መ/ቤት በማሳወቅ በግብር/ታክስ አሰባሰብ ላይ ትብብር እንዲያደርግ አስታውቃለሁ፡፡
የግብር ከፋይ ስም ኢማጅ መፍቱ መሐመድ