ኃላፊነት የተሞላ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ የናሙና ክፍሎች

ኃላፊነት የተሞላ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ. ኃላፊነት ያለው የኢንቨስትመንት ፖሊስ ("ፖሊሲው") (የመጨረሻውን ማስታወሻ 1 ይመልከቱ) የCFM ግዴታዎችን ኃላፊነት ላለው ኢንቨስትመንት ከE&S አደጋ ቁጥጥር እና ጥቅማ ጥቅም ፈጠራዎች ጋር ለተያያዘው ይቆማል። ይህም በCFM CEO የተፈረመ እና እንደ አጠቃላይ የአመራሪ የምልከታ ሂደት ክፍል በየዓመቱ የሚታይ ይሆናል። እንደ አስፈላጊነቱም ከፕሮጄክቱ ባሕርይ እና መጠን ጋር ተገቢ በሆነ ሁኔታ ሊሄድ መቻሉን እና የአጋር ቀራጮች/የገንዘብ ድጋፍ ሰጪዎች የሥራው ዓላማውች መሄዱን ለማረጋገጥ ይታያል። ሁሉም ኮንትራት የገቡት እና ከፊል ኮንትራት ገብተው የሚሰሩት፣ ወይም በገንዘብ ድጋፍ ሰጪ አስተዳደር እና CIO የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግላቸው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች ፈንታ ፖሊሲውን በቀጥታ ለመውሰድ፣ ወይም ከራዕዩ፣ ከዓላማው እና በፖሊሲው ውስት የተቀመጡትን አነስተኛውን ግዴታዎችን ጋር የሚሄዱትን ፖሊስውን ለመመስረት እና ለማቆየት ይገዙለታል። ለሁሉም የCFM ሠራተኞች እንደ ሥልጠናቸው አካል ተደርጎ የሚተላለፊላቸው ሲሆን ፍላጎት ላላቸው አካላት በጥያቄ መሰረት ይቀርብላቸዋል።
ኃላፊነት የተሞላ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ. ሲኤፍኤም አዎንታዊ ቀጣይ የልማት ውጤቶችን በኢንቨስትመንቶቹ ለማግኘት ጥረት የሚያደርግ ሲሆን ለሚከተሉት ቁርጠኛ አቋም አለው፦ • በአካባቢ ማኅበረሰቦች ላይ ኢንቨስትመንቶች የሚኖራቸውን ተፅእኖ ማስወገድ ካልተቻለም በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ፤ • አካባቢን መጠበቅ እና ቀጣይነትን ባረጋገጠ መልኩ የተፈጥሮ ሀብቶችን መጠቀም፤ • በአካባቢ አየር ለውጥ ላይ የሲኤፍኤም አስተዋጽኦን በራሱ ኢንቨስትመንቶች የታዳሽ ኃይል ዘርፍን በመጠቀም መቀነስ፤ • ሲኤፍኤም ኢንቨስት የሚያደርግባቸው ፕሮጄክቶች ላይ የሚሠሩ ሁሉንም ሰዎች ጤና እና ደኅንነት መጠበቅ፤ እና • ለአዎንታዊ እና ማኅበራዊ ጥቅሞች ተፈጻሚነት መልካም ዕድሎችን መፍጠርና ቊጥራቸውን ከፍ ማድረግ። እነዚህ ቁርጠኝነት የሚጠይቁ ግቦችን ለማሳካት፣ ሲኤፍኤም ለሁሉም ኢንቨስትመንቶች በሁሉም ሕጎች እና አግባብነት ባላቸው የአካባቢ እና ማኅበራዊ መስፈርቶች ተገዢ ለመሆን ቁርጠኛ አቋም አለው። መልካም ዓለም አቀፍ የኢንዱስትሪ አሠራር ልማዶች እና የአካባቢ እና ማኅበራዊ አስተዳደር1 መስፈርቶች የአስተዳደር ቅጽርን ለማዘጋጀት እንደ ተገቢነታቸው ጥቅም ላይ ይውላሉ። የሁሉም ተጽእኖዎች እና ስጋቶች ጠቅለል ያለ ግምገማ ከሁሉም የኢንቨስትመንት ውሳኔዎች በፊት ይደረጋል። ሁሉም ተጽእኖዎች እና ስጋቶች በሲኤፍኤም ውስጣዊ የስጋት ቁጥጥር ሂደት መሠረት የሚስተናጋዱ ሲሆን ለእያንዳንዱ ፈንድ የሥርዓተ ክወና ሂደት እንዲጠቃለሉ ይደረጋሉ። ሲኤፍኤም ዲዛይን ሊደረጉ፣ ሊገነቡ፣ ሊሠሩ እና ሊጠገኑ ሲሉ ብቻ በፕሮጄክቶች ላይ ኢንቬስት ያደርጋል እንዲሁም ተገቢነት ባላቸው የአካባቢ እና ማኅበራዊ መስፈርቶች መሠረት እንዲነብሩ እንዲደረጉ ይጥራል። የኢንቨስትመንት ውሳኔ በሚሰጥበት ጊዜ ተቀባይነት በሌለው የአካባቢ እና ማኅበራዊ ቁጥጥር አሠራር ልማድ ምክንያት ለፈንዱ ወይም ለኢንቬስተሮቹ መልካም ስም ስጋትን ሊያስከትል የሚችል ሆኖ ከተገኘ ፕሮጄክቱ ውድቅ ይደረጋል። አካባቢያዊ እና ማኅበራዊ ፋይዳዎችን የሚያበረታቱ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ይበረታታሉ። ሁሉንም አካባቢያዊ እና ማኅበራዊ መስፈርቶች በስኬታማ መንገድ ለማስተዳደር እና ተፈጻሚ ለማድረግ እንዲቻል ሲኤፍኤም ሁሉም ፕሮጄክቶች በቂ ሠራተኛ፣ የአስተዳደር ዕቅድ፣ እና ሀበት እንዲኖራቸው ይፈልጋል። የሲኤፍኤም ቦርድ፣ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና የኢንቨስትመንት ሠራተኞች ሁሉም ኢንቨስትመንቶች ተገቢነት ባለው፣ ተጠያቂነትን በጠበቀ እና በግልጽነት የተሞላ አካሄድ መፈጸማቸውን ለማረጋገጥ ተገቢነት ባላቸው ደረጃዎች ላይ ሁሉ እንደ መመሪያ የሚያገለግሉ መሪ ሐሳቦችን እያቀረቡ ይጠቀሙባቸዋልም። ተሳትፎ እና ምክክር በ ሲኤፍኤም ከባለ ድርሻ አካላቱ ጋር የሚከናወን ሲሆን በአካባቢያዊ እና ማኅበራዊ አስተዳደር ጉዳዮች ላይ በሁሉም ኢንቨስትመንቶቹ ላይ በግልጽነት መልእክትን ያስተላልፋል። ሁሉም የኢንቨስትመንት ሠራተኛ በሁሉም ከአካባቢ እና ማኅበራዊ ስጋት አስተዳደር ጋር የተገናኙ ሁሉንም እንቅስቃሴዎች አስቀድሞ ለመከላከል ወደ ሲኤፍኤም ሪፖርት ያደርጋል። ሲኤፍኤም ከአካባቢ እና ማኅበራዊ አፈጻጸም ጋር የተገናኘ መረጃን በመደበኛ ሁኔታ ይገልጻል። ቀጣይ መሻሽል እንዲኖር ከሚደረግ ጥረት አንጻር፣ እና ኢ እና ኤስ ስጋቶችን ማስተዳደር በሁሉም የኢንቨስትመንቱ የሕይወት ዘመን ላይ ተፈጻሚ መሆኑን ለማረጋገጥ ሁሉም የኢንቨስትመንት ሠራተኛ የአፈጻጸም ዕቅዶችን እንዲወጥን እና ለመቆጣጠር ዒላማ ለማድረግ እና ይህንንም ለሲኤፍኤም በእነርሱ የኢ እና ኤስ አፈጻጸም ላይ ሪፖርት እንዲያደርግ ይጠይቃል። ይህ ፖሊሲ ተፈጻሚ መሆኑን ማረጋገጥ የሲኤፍኤም ቦርድ ኃላፊነት ነው። ይህ ፖሊሲ ለሁሉም የ ሲኤፍኤም ሠራተኛ መልእክቱ የሚተላለፍ ይሆናል። ፊርማ፦ ሚና፦ << [ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሹም] >> ቀን፦ 1 የምድር ወገብ መርሆዎች [Equator Principles III]፤ ዓለም አቀፍ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) በአካባቢያዊ እና ማኅበራዊ ቀጣይነት አቅም የአፈጻጸም መስፈርቶች 2012፤ ILO አብይ ኮንቬንሽን፣ ILO መሠረታዊ የሥራ ቅጥር ደንቦች እና ሁኔታዎች፤ የተባበሩት መንግሥታት መመሪያ መርሆዎች አባሪ 2 ለአዳዲስ ፕሮጄክቶች የአካባቢ እና የማኅበራዊ መጠይቅ – የድርድር ፍተሻ ማረጋገጫ ዝርዝር ይህ ማረጋገጫ ዝርዝር በሁሉም ሊያጋጥሙ በሚችሉ የ ኢ እና ኤስ ችግሮች ላይ እንደ የመጀመሪያ የስጋት ፍተሻ መልመጃ ጥቅም ላይ መዋል አለባቸው። የስጋት ፍተሻ መልመጃው ምህዳር እና ጥልቀት በፕሮጄክቶቹ ባሕሪያት፣ ሴክተር እና መገኛ አካባቢ ላይ በመመርኮዝ ሊለያዩ ይችላሉ፤ ሆኖም ግ...