እንክብካቤ ሰጪዎች. 1. የ ProviderOne ካርድ ካልተገኘ ለጉዲፈቻ ልጆች ጊዜያዊ የፋርማሲ እና የህክመና አገልግሎቶች ደረሰኝ ለማግኘት የተመደበልዎትን የጉዳይ ሰራተኛ ያነጋግሩ፡፡ 2. ምደባው ልጁ የቀድሞው ት/ቤቱን እንዲለቅ ካደረገ ልጁን ወዲያው አዲስ ት/ቤት ያስገቡ፡፡ የተመደበውን የጉዳይ ሰራተኛን እንደልጁ አንድ አድራሻ ይጥቀሱት፡፡ ልጁን ት/ቤት ለማስገባት ችግሮች ካሉ የተመደበውን የጉዳይ ሰራተኛ ያሳውቁ፡፡ 3. ልጁ/ወጣቱ ከወላጆች፣ ወንድምና እህቶች እና/ወይም የቤተሰብ አባላት ጋር እንዲገናኝ የጉብኝት እቅድ በማዘጋጀት ይሳተፉ፤ የሚከለክል የፍርድቤት ትዕዛዝ ከሌለ በስተቀር፡፡ ለተቀጠሩ ጉብኝቶች ልጁን/ወጣቱን ያዘጋጁ፡፡ 4. ማንኛውንም ያልታቀደ የወላጅ/ልጅ/ወጣት ግንኙነት ለምሳ የስልክ ጥሪ፣ ያልተጠበቀ ጉብኝት ወዘተ ለተመደበው የጉዳይ ሰራተኛ ያሳውቁ፡፡ 5. የጋራ የማቀድ ስብሰባዎች ላይ ይሳተፉ፡፡ የጋራ የማቀድ ስብሰባ ስለልጁ ደህንነት እና ቋሚነት ግብአት እና እውቀት የሚሰጥ እድል ነው፡፡ 6. ስለልጁ/ወጣቱ ማንኛውንም ስጋት ለምሳሌ የጥቃት፣ ቸልተኝነት፣ ህክምና፣ ባህሪይ፣ እድገት ወይም የትምህርት ጉዳዮች ለተመደበው የጉዳይ ሰራተኛ ያማክሩ፡፡ 7. ከተመደበው የጉዳይ ሰራተኛ ጋር ይወያዩ እና በእርስዎ እንክብካቤ ስር ለተመደበው ልጅ/ወጣት የሚመቸውን ተገቢ የስነ-ምግባር ስልቶችን ወይም አማራጮችን ይተግብሩ፡፡ አካላዊ ቅጣት አይፈቀድም፡፡ 8. የኢንዲያ ልጅ ደህንነት ህግ መስፈርቶችን ለማሟላት ተግባራዊ መደረግ ሲኖርበት ከልጁ/ወጣቱ የተመደበ የጉዳይ ሰራተኛ የሚሰጥ ማንኛውንም መመሪያ እንዲሁም ሌላ የልጁ/ወጣቱ የባህል ፍላጎቶችን ይከተሉ፡፡ 9. ልጁ ቀጣይነት ያለው የህክምና፣ ጥርስ እና አዕምሮ የጤና አገልግሎቶች ማለትም በፌደራል ደረጃ በሚመከረው የምርመራዎች ቀጠሮ መሰረት እድሜ-ተኮር የ EPSDT ምርመራን ጨምሮ ማግኘቱን ያረጋግጡ፡፡ (በመጀመሪያው የህይወት አመት 5 ምርመራዎች፤ በ12 ወራት እና 2 አመት እድሜ መካከል 3 ምርመራዎች፣ በ3 እና 20 አመት እድሜ መካከል አመታዊ ምርመራዎች)፡፡ 10. የህክምና/የጥርስ አገልገሎት ሰጪ ለማግኘት እገዛ ከፈለጉ የ Medicaid የባለጉዳይ አገልግሎት መስመር በ0-000-000-0000 የውስጥ መስመር 15480፣ ከሰኞ እስከ አርብ ፣ ከ7:30 AM እስከ 5:00 PM (ፓስፊክ ሰአት) ያነጋግሩ ወይም የ ProviderOne ድህረ-ገጽ xxxx://xxxx.xxxx.xx.xxx/xxxxxxxxxxx/xxxxxxxxx.xxx ይጎብኙ፡፡ 11. ወደልጁ የህክምና/የጥርስ ቀጠሮዎች ለመሄድ የሚወጡ ወርሀዊ የርቀት ጉዞ ወጪዎች ይተካሉ፡፡ የእንክብካቤ ሰጪ ወርሀዊ የርቀት ጉዞ ቅጽ ከ xxxx://xxx.xxxx.xx.xxx/xx/xxxxxxxxxxxxx/xxxxx-xxxxxxxx.xxx ላይ ማውረድ ይቻላል፡፡ 12. ህክምና በሚያገኙበት ወቅት ለጤና ሰጪው የልጁን የ ProviderOne ካርድ ይስጡ፡፡ 13. የህክምና/የጥርስ እንክብካቤ ቀጠሮዎች፣ አድራሻች እና የቀጠሮዎቹን ውጤቶች/ምክሮች ለመዘገብ የህክመና ሎጎ ይጠቀሙ፡፡ የልጁ/ወጣቱን ደህንነት በይበልጥ ለማረጋገጥ እንክብካቤ ሰጪው በሚከተሉት መንገዶች ለመተባበር ተስማምቷል፡ 1. ለልጁ ቁጥጥር የማይደረግበት ተደራሽነት ያለው የ16 አመት እና ከዛ በላይ እድሜ ሰው ሁሉ ላይ የወንጀል የኋላ ታሪክ ምርመራ እንዲሁም የልጅ ጥናት እና የቸልተኛነት ምርመራ ያድርጉ፣ 2. ቤት ውስጥ የሚኖር ሰው ከተለወጠ ለተመደበው የጉዳይ ሰራተኛ ያሳውቁ እንዲሁም ሰውየው ከላይ በ#1 ላይ የተገለጸውን መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ የወንጀል የኋላ ታሪክ ምርመራ እንዲሁም የልጅ ጥናት እና የቸልተኛነት ምርመራ ያድርጉ፣ 3. ለልጁ/ወጣቱ እንክብካቤ የመስጠት ችሎታዎ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር የሚችል ማንኛውንም ጉዳይ ለተመደበው የጉዳይ ሰራተኛ ያሳውቁ፡፡ ይህ ማለት ልጁ/ወጣቱ ቤትዎ ውስጥ መቆየት እንደማይችል ካወቁ አዲስ ምደባ ለማቀድ ከተመደበው የጉዳይ ሰራተኛ ጋር በትብብር መስራትን ያካትታል፡፡ 4. ልጅ ከቤትዎ እንዲወጣ ከጠየቁ አደጋ ከሌለ በስተቀር ተገቢ የሆነ እቅድ መኖሩን ለማረጋገጥ ቢያንስ የ14 ቀናት ማስታወቂያ ለተመደበው የጉዳይ ሰራተኛ መስጠት አለብዎት፡፡ 5. ሁሉም እንክብካቤ ሰጪዎች የጣት አሻራ ምርመራ ማድረግ አለባቸው፡፡ ከላይ የተገለጸው ልጅ/ወጣት ላይ ከምደባ በፊት የ NCIC ወይም BCCU ምርመራ ማድረግ ያለባቸው የዘመድ እንክብካቤ ሰጪዎች ወይም ተመራጭ ሰዎች የጣት አሻራ ምርመራ ማድረግ እና ለተመደበው የጉዳይ ሰራተኛ መመለስ ያለባቸው የ NCIC ወይም B...