የስምምነቱ ይዘት የናሙና ክፍሎች
የስምምነቱ ይዘት. ስምምነቱ በይዘት ረገድ የስምምነቱ ዓላማ፣አሳልፎ ስለመስጠት ግዴታ፣ አሳልፎ ለመስጠት ስለሚያበቁ የወንጀል ድርጊቶች (Extraditable Offences)፣ አሳልፎ የመስጠት ጥያቄ ውድቅ ሊደረግ ስለሚችልባቸዉ ሁኔታዎች፣ የትብብር ጥቄዉ የሚላክለት አካል ፣ አሳልፎ የመስጠት ጥያቄ ስለሚስተናገድበት ሥነ-ሥርዓት እንዲሁም ሌሎች ልዩ ልዩ ድንጋጌዎችን የያዙ ሃያ አራት (24) አንቀጾች አሉት። በስምምነቱ አንቀጽ 1 የስምምነቱ ዓላማ የተገለፀ ሲሆን ስምምነቱን መሰረት በማድረግ በሁለቱ አባል ሀገራት መካከል በአሳልፎ መስጠት ዙሪያ የሚደረግ ትብብርን መሳደግን ዓላማ ያደረገ ስምምነት መሆኑ ተመላክቷል፡፡ በስምምነቱ አንቀጽ 2 መሠረት ሀገራቱ በጠያቂ ሀገር የወንጀል ድርጊት ክስ ሊቀርብበት፣ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ወይም ቅጣት እንዲፈጸምበት የሚፈለግን ግለሰብ ስምምነቱን መሰረት በማድረግ አሳልፎ ለመስጠት ግዴታ ገብተዋል። ስምምነቱ አንቀጽ 3 መሰረት አሳልፎ ለመስጠት የሚያበቃ የወንጀል ድርጊቶች ማለት አሳልፎ የመስጠት ጥያቄው በቀረበበት ጊዜ በሁለቱም አገራት ሕግ ቢያንስ በአንድ ዓመት ቀላል እስራት ሊያስቀጣ የሚችል የወንጀል ድርጊት መሆኑን አስቀምጧል። ሆኖም አሳልፎ የመስጠት ጥያቄው የቀረበው በፍርድ ቤት የተላለፈ የቅጣት ውሣኔን ለማስፈጸም በሚሆንበት ጊዜ ቀሪው የቅጣት ጊዜ ቢያንስ ስድስት ወር ሊሆን እንደሚገባ ተደንግጓል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የአሳልፎ መስጠት ጥያቄው የሚቀርብለት አካል የወንጀሉን ዓይነት ሲመረምር በጠያቂው ሀገር ሕግ አገላለፅ እና በተጠያቂው ሀገር ህግ አገላለፅ ልዩነት መኖሩ ወይም ወንጀሎቹ የሚመደቡበት ክፍል (category of offences) የተለያየ መሆኑ ልዩነት እንደማይፈጥር ያስቀምጣል፡፡ ከአንድ በላይ በሆኑ ወንጀሎች የሚፈለግ ግለሰብን በተመለከተ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ከተጠየቁት የወንጀል ጉዳዮች መካከል አንዱ ብቻ ተላልፎ ለመስጠት የሚያበቃ ወንጀል ከሆነ ሌሎቹ ባይሆኑም እንኳን አንዱ በመሆኑ ምክንያት በሁሉም ወንጀል ጉዳዮች ተላልፎ እንዲሰጠ ተደንግጓል፡፡ የስምምነቱ አንቀጽ 4 እና 5 አሳልፎ የመስጠት ጥያቄ ውድቅ ሊደረግ የሚችልባቸውን ሁኔታዎችን በዝርዝር ያስቀምጣል። በዚህ መሠረት አንቀፅ 4 የአሳልፎ መስጠት ጥያቄን አለመቀበል የሚያስችሉ አስገዳጅ ምክንያቶችን (mandatory grounds for refusal) ሲዘረዝር ከነዚህም ውስጥ፣ • ጥያቄው በቀረበለት አገር የወንጀል ድርጊቱ ፖለቲካዊ ይዘት አለው ተብሎ ሲታመን፤ • ጥያቄው የቀረበለት አገር ጥያቄው የቀረበው ግለሰቡን በዘሩ፣ በኃይማኖቱ፣ በዜግነቱ፣ በጾታው፣ በፖለቲካ አመለካከቱ ወይም በመሰል ምክንያቶች ለመክሰስ መሆኑን በሚመለከት በቂ መረጃ ሲኖረው፤ • ጥያቄ የቀረበበት የወንጀል ድርጊት በወታደራዊ ወንጀልነት ብቻ የሚያስቀጣ ከሆነ • የተጠየቀዉን ጉዳይ በተመለከተ የተጠየቀዉ ሀገር በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ፍርድ የተላለፈበት ከሆነ • የተጠየቀበት ወንጀል በቅርታ፣በምህረት ወይም በይርጋ ቀሪ ከሆነ • ተፈላጊዉ ተላልፎ ከተሰተ በኋላ የማሰቃት ተግባር ወይም ጭካኔ የተሞላበት፣ ኢሰብዓዊ የሆነ ወይም ክብሩን የሚያዋርድ አያያዝ ሊያጋጥመዉ የሚችል ከሆነ • ተፈላጊዉ ላይ የተወሰነዉ ዉሳኔ በሌለበት ተወሰነ ከሆነና ዉሳኔዉ ተፈላጊዉ ተላልፎ ከተሰጠ በኋላ እሱ ባለበት ድጋሚ ሊታይ የሚችልበት እድል ከሌለ • ተፈላጊዉ ሰዉ በተመሳሳይ ጉዳይ በሌላ ሀገር ተከሶ በነፃ የተሰናበተ፣ በይቅርታ የታለፈ ወይም ተቀጥቶ ቅጣቱን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የፈፀመ ከሆነ ናቸዉ፡፡ የፖለቲካ ወንጀልነትን የመወሰን ስልጣን የትብብር ተጠያቂ ሀገር ሲሆን በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በኩል በፕሬዝዳንቱ፣በምክትል ፕሬዝዳንቱ፣ በጠቅላይ ሚኒስቴሩ፣ በማንኛዉም የፌዴራል ጠቅላይ ምክር ቤት (Federal Suprem Council) አባል እና በቤተሰቦቻቸዉ ላይ የተሰነዘረ ጥቃት፤ በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ በማንኛዉም ሰዉ፣ በመንግስት ኃላፊዎች እና በቤተሰቦቻቸዉ በህይወታቸዉ እና በደህንነታቸዉ ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች እንደ ፖለቲካ ወንጀሎች የማይቆጠሩ ሲሆን በተጨማሪም በሌሎች ሀገሮቹ አባል በሆኑባቸዉ የባለ ብዙ ወገን ስምምነቶች መሰረት እንደ ፖለቲካ ወንጀል የማይቆጠሩ ወንጀሎች፣ የሰዉ መግደል ወንጀል፣ ሽብርተኛነት እና በነዚህ ወንጀሎች ማሴር፣ ሙከራ ማድረግ እና ወንጀለኛን በመርዳት መሳተፍ ወንጀሎች እንደ ፖለቲካ ወንጀሎች አይቆጠሩም፡፡ ፈቃጅ የሆኑ መቃወሚያ መሰረቶች (Discretionary grounds of refusal) ደግሞ በአንቀጽ 5 ተዘርዝረዋል፡፡ እነሱም፡- • ተ...