ማስታወቂያ. ተዋዋይ ወገኖች ከዚህ ኤግዚቢት 2 ጋር የተያያዘውን በታቀደው የክፍል እርምጃ ማቋቋሚያ ማስታወቂያ (“ማስታወቂያ”) ላይ እንደተገለጸው ማስታወቂያ ለመስጠት ተስማምተዋል። ይህ ማስታወቂያ በፍርድ ቤት ከጸደቀ በኋላ ባሉት በአስራ አራት (14) ቀናት ውስጥ፣ ተከሳሽ DHS የሚከተሉትን ማስደረግ አለበት፡- • ማስታወቂያውን ለአርባ አምስት (45) ቀናት በእንግሊዝኛ፣ በስፓኒሽ፣ እና በአማርኛ በደንበኛ መጠበቂያ ቦታዎች በሁሉም ክፍት ቢሮዎች ላይ ወይም በአገልግሎት ማዕከላት ውስጥ ለSNAP ጥቅማጥቅሞች ማመልከቻዎች ወይም የእንደገና ማረጋገጫ ማመልከቻዎች ተቀባይ በሚሆኑበት ቦታ ላይ ይለጥፉ፣ ማስታወቂያው በእነዚህ ቦታዎች ላይ ሲለጠፍ በመጠኑ 8.5” x 11” ወይም ከዚያ በላይ የሆነ፣ የ18-ነጥብ ፊደልን በመጠቀም መሆን አለበት፤ • ማስታወቂያውን በድህረ-ገጹ ላይ ለአርባ አምስት (45) ቀናት በ https://dhs.dc.gov በእንግሊዝኛ፣ በስፓኒሽ፣ እና በአማርኛ በ18-ነጥብ ፊደል ያትሙ፤ እና • በሚጠየቁበት ጊዜ፣ ማስታወቂያውን ማንበብ ለማይችሉ ግለሰቦች የኦዲዮ ትርጉም (በእንግሊዝኛ፣ በስፓኒሽ፣ ወይም በአማርኛ) ያቅርቡ። ፍርድ ቤቱ ይህን ማስታወቂያ ካጸደቀ በኋላ ባሉት አስራ አራት (14) ቀናት ውስጥ፣ ተከሳሽ ለከሳሾች አማካሪ የማስታወቂያውን PDF በእንግሊዝኛ፣ በስፓኒሽ፣ እና በአማርኛ በ18 ነጥብ ፊደል ያቀርባል፣ ይህንም የከሳሾች አማካሪ በሚጠየቅበት ጊዜ ለክፍሉ አባላት ያቀርባል። ከዚህ ቀደም ላይ ባለው አንቀጽ የተጠቀሱት PDF እና የማስታወቂያ ግልባጮች በደረሱበት በሰባት (7) ቀናት ውስጥ፣ የብሄራዊ የህግ እና የኢኮኖሚክ ፍትህ ማዕከል እና የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ህጋዊ የእርዳታ ማህበር ለአርባ አምስት (45) ቀናት የሚከተሉትን ያደርጋል፡- • ማስታወቂያውን በራሳቸው ድህረገጽ በእንግሊዝኛ፣ በስፓኒሽ እና በአማርኛ በቅደም ተከተል በhttp://nclej.org እና https://www.legalaiddc.org ያትማል። እና • እነዚህ አካላት ማስታወቂያውን በእንግሊዝኛ፣ በስፓኒሽ እና በአማርኛ በድረ ገጻቸው ላይ እንዲለጥፉ፤ ማስታወቂያውን ለደንበኞቻቸው እንዲያሰራጩ፤ እና በሚጠየቅበት ጊዜ DHS የማስታወቂያውን የኦዲዮ ትርጉም እንደሚሰጥ ለደንበኞቻቸው እንዲያሳውቁ በመጠየቅ በኤግዚቢት 3 ላይ የተገለጹትን የአካል ጉዳተኛ መብቶች እና ህጋዊ የእርዳታ ድርጅቶችን ማስታወቂያ በፖስታ ወይም በኢሜል መላክ