ማኅበራዊ ቁጥጥር የናሙና ክፍሎች

ማኅበራዊ ቁጥጥር. ሲኤፍኤም ሁሉም የፕሮጄክት ኩባንያዎች በሕጋዊ መስፈርቶች እና በአይኤፍሲ ፒኤስ 4፣ 5፣ 6 እና 8 መሠረት ገንዘቡን ኢንቬስት የሚያደርግባቸው የፕሮጄክቶቹ እና የእሴቶቹ ማኅበራዊ ተፅእኖዎችን ማስተዳደር የሚያስችሉ የተዘጋጁ እርምትና ቁጥጥር አሠራር ዘዴዎች እንዲኖራቸው ይጠይቃል። በፕሮጄክቱ ወይም በእሴት ራሱን የቻለ ልዩ ነገር አገባብ ላይ የሚወሰን ሆኖ የጥንቃቄና የቁጥጥር አሠራር ዘዴዎች የሚከተሉትን በሚያሟሉ መልኩ ተፈጻሚ መሆን አለባቸው፦ • የባለድርሻ ተሳትፎ እና መልእክት ልውውጥ ወይም ተግባቦት ዘዴ (ከዚህ በታች ያለውን ክፍል xi ይመልከቱ)፤ • ሰብአዊ መብቶችን በሚያከብር መልኩ እሴቶችን እና ሠራተኞችን መጠበቅ እንዲሁም በአይኤፍሲ ፒኤስ4 መስፈርቶች መሠረት (ከዚህ በታች ያለውን ክፍል xii ይመልከቱ) የማኅበረሰብ ጤና እና ደኅንነት ላይ ተፅእኖ ባረፈባቸው ማኅበረሰቦች ላይ ስጋትን የማያስከትል፤ • በአይኤፍሲ ፒኤስ5 መስፈርቶች መሠረት (ከዚህ በታች ያለውን ክፍል xiii ይመልከቱ) እስከሚቻል ድረስ የሰፈራ አስተዳደርን በመቆጣጠር ላይ አካላዊ እና/ወይም ኢኮኖሚያዊ መፈናቀል እንዳይኖር ማድረግ፤ • በአይኤፍሲ ፒኤስ7 መስፈርቶች መሠረት (ከዚህ በታች ያለውን ክፍል xiv ይመልከቱ) ለአካባቢ ተወላጅ ሰዎች ጥበቃ ማድረግ እና ሰብአዊ መብታቸውን ማክብር፤ • የአይኤፍሲ ፒኤስ8 መስፈርቶች መሠረት ለሚዳሰሱ እና ለማይዳሰሱ ባሕላዊ ቅርሶች ጥበቃ ማድረግ፤ • ለአስተናጋጅ ማኅበረሰቦች አዎንታዊ የልማት ጥቅሞችን ለማስገኘት ኃላፊነት የተሞላ የሥራ ቅጥር አፈጻጸም፣ ግዢ ማከናወን ኣና ማኅበራዊ ኢንቨስትመንትን ማድረግ (በሲኤፍኤም መልካም አድርግ ፕሮግራም በኩል)። የባለድርሻ አካል ተሳትፎ እና መልእክት ልውውጥ ወይም ተግባብቶት ዘዴ ውጤታማ የሆነ የማኅበረሰብ ተሳትፎ መኖር በፕሮጄክቱ ተፅእኖ የሚያርፍባቸው ማኅበርሰቦች ላይ ስጋቶችን እና ተፅእኖዎችን በተሳካ ሁኔታ መቆጣጠር ላይ እና የላቁ የማኅበረሰብ ጥቅሞችን ማስገኘት ላይ ቁልፍ ሚናን ይጫወታል። በገንዘብ ምደባ ደረጃ ላይ፣ ሲኤፍኤም በባለድርሻ አካላት የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ምላሽ መስጠት እና መቆጣጠር ላይ የአቤቱታ ቁጥጥር ዘዴን ተፈጻሚ ያደርጋል። ይህ በዚህ ኢኤስኤምኤስ አባሪ 11 ላይ ቀርቧል። ይህ በመልካም ዓለም አቀፍ የኢንዱስትሪ አሠራር ልማዶች መሠረት ተዘጋጅቶ ተፈጻሚ ሆኗል። ሲኤፍኤም ገንዘብ ኢንቬስት የሚያደግባቸው ሁሉም ፕሮጄክት ኩባንያዎች በአይኤፍሲ ፒሲ መሠረት የተዘጋጀ ኤስኢፒ እንደሚያዘጋጁ እና ተፈጻሚ እንደሚያደርጉ የሚያረጋግጥ ሲሆን ይኸውም የሚከተሉትን አባለ ነገራት በውስጡ የያዘ ይሆናል፦ • ምርጥ የባለ ድርሻ አካላት ተሳትፎን ለማረጋገጥ ዓለም አቀፋዊ እና ብሔራዊ መመሪያዎችን እና ምርጥ አሠራሮችን ለይቶ ማወቅ፤ • ከፕሮጄክቱ ጋር ዝምድና ያላቸውን ባለድርሻ አካላት ለይቶ ማወቅ እና ትንታኔ መስጠት፤ • በግንባታው ሂደት ላይ የአፈጻጸም ዘዴ እና የተሳትፎ እንቅስቃሴዎች ፕሮግራምን ማዘጋጀት፤ • በመልካም የዓለም አቀፍ የኢንዱስትሪ አሠራር ልማዶች መሠረት የአቤቱታ አቀራረብን ዘዴ መመሥረት፤ እና • የቁጥጥር እና የሪፖርት አደራረግ ውጤታማ አሠራር ዘዴዎችን ማዘጋጀት። ለአንድ ፕሮጄክት የሚያስፈገው የባለ ድርሻ አካላት ተሳትፎ ደረጃ በፕሮጄክቱ በኢ እና ኤስ የስጋት ምደባ (እንዲሁም አግባብነት ባላቸው ሕጋዊ መስፈርቶች መሠረት) መሠረት የሚወሰን ይሆናል። የተለያዩት ደረጃዎች ከዚህ በታች በሠንጠረዥ 6.1 ላይ ተጠቅሰዋል። በፕሮጄክቱ አማካይነት እነዚህን መስፈርቶች ማሟላት ለሁሉም ሊፈጸሙ የሚችሉ ኢንቨስትመንቶች የግድ አስፈላጊ ነው። ሲኤፍኤም ከሲአይኦ የሚመደብ ገንዘብ እና አሴቶቹ ጋር ግንኙነት ላላቸው ሁሉም ውጫዊ ተሳትፎዎች የመጨረሻውን ኃላፊነት ይወስዳል። ሠንጠረዥ 6.1 በኢ እና ኤስ ተፅእኖ እና ስጋት ደረጃ መሠረት የሚያስፈልግ የባለ ድርሻ አካላት ተሳትፎ ደረጃ ስጋት/ተፅእኖ ደረጃ ለበጣም ተገቢነት ያላቸው ፕሮጄክቶች ተፅእኖ የሚያርፍባቸው ባለድርሻ አካላት የደንበኛ ኃላፊነቶች የሲአይኦ ኃላፊነቶች በክፍል 5 በተገለጸው መሠረት በጣም ከፍተኛ ኢ እና ኤስ ስጋት ፕሮጄክቶች አይፒዎች በእነዚህ ሁኔታዎች ሥር፦1) በመሬት/ተፈጥሮ ሀብቶች ላይ ተፅእኖ፤ 2) የአይፒዎች ዳግም ሰፈራ፤ 3) ባሕላዊ ቅርሶችን ለንግድ ጥቅም ማዋልን ጨምሮ አደገኛ ባሕላዊ ቅርሶች ያላቸው ተፅእኖ (ኤፍፒአይሲ መቼ እንደሚያስፈልግ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት አይኤፍሲ ፒኤስ7፣ ጂኤን27 ን ይመልከቱ)። ነጻ፣ በቅድሚያ ተሰጪ እና በቅድሚያ በመረዳት ስምምነትን መግለጽ...