ስምምነቱ የናሙና ክፍሎች

ስምምነቱ. ሁለቱም ሀገራት በሌላ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የሚያገኙትን ማንኛዉንም መብት ሆነ የተጣለባቸዉን ግዴታ ሊያስቀር የማይችል መሆኑን ሲደነግግ በአንቀጽ 19 ደግሞ በስምምነቱ አፈፃፀምም ሆነ አተረጓጎም ላይ በሁለቱም ሀገራት ማዕከላዊ ባለስልጣናት የሚነሱ አለመግባባቶች በዲፕሎማሲያዊ መስመር በሚደረግ ምክክር እንደሚፈቱ ተደንግጓል፡፡ በስምምነቱ አንቀጽ 20 ተዋዋይ ሀገራት ይህ ስምምነት ተፈፃሚ በሚሆንበት ጊዜ አንዳቸዉ ከሌላቸዉ የሚያገኙትን ማንኛዉንም መረጃ እና ማስረጃ ስምምነቱ ተግባራዊ በሚሆንበት ጊዜም ሆነ ቀሪ ከሆነ በኋላ ያለሌላኛዉ ሀገር ፈቃድ ለሶስተኛ ሀገር ያለመግለፅ እና ጥበቃ ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡ የስምምነቱ አንቀጽ 21 የመጨረሻ ድንጋጌዎችን የያዘ ሲሆን ስምምነቱ ወደ ሥራ የሚገባው በሁለቱም ሀገራት መጽደቁን በሚመለከት ሰነድ በዲፕሎማቲክ መስመር ልውውጥ በተደረገበት ቀን እንደሆነ ተደንግጓል። በተጨማሪም ሀገራቱ የ180 ቀናት የጽሑፍ ቅድመ-ማስታወቂያ በመስጠት የስምምነቱን ተፈጻሚነት ቀሪ ማድረግ እንደሚችሉ ተደንግጓል። ይህም በሚሆንበት ጊዜ ቀድሞ የተጀመሩ የትብብር ሂደቶች ላይ የሚያስከትለዉ ተጽዕኖ የሌለ መሆኑ ተደንግጓል፡፡