ስነዳ እና የሪኮርድ ቁጥጥር. ሁሉም ሰነዶች እና ሪኮርዶች በ ISO 9001 (የጥራት ቁጥጥር ሥርዓት) እና/ወይም እንደ ተገቢነቱ በሌሎች ዓለም አቀፍ የደረጃ መለኪያ መስፈርቶች (ለምሳሌ፦ ISO 14001 እና OHSAS 18001 (ወደፊት ISO 45001 ተብሎ የሚጠራ)) መሠረት የሚያዙ ይሆ።ናሉ። ሁሉም ፕሮጄክት ኩባንያዎች በዚህ ሰነድ ላይ በተቀመጡት ሁሉም መስፈርቶች መሠረት ተገዢ መሆናቸውን በሚያሳይ መልኩ ተገቢ ደረጃቸውን በመጠበቅ የስነዳ (የሰነድ አያያዝ) ተግባርን ያከናውናሉ። ሲኤፍኤም የፕሮጄክቱን ኢ እና ኤስ ስነዳ ማናቸውም ክፍል ተገቢነት ባለው የጊዜ ቅጽር ውስጥ መገምገም እንዲችል ለሁሉም የኢ እና ኤስ ስነዳ በሁሉም ፕሮጄክት ኩባንያዎች ክፍት የሆነ የፋይል አያያዝ ፖሊሲ ተፈጻሚ ይሆናል። የኢ እና ኤስ መረጃን መገምገም፣ ማጽደቅ፣ ማዘመን፣ የሕትመት ቁጥጥር፣ ምሥጢራዊነት፣ ስርጭት፣ አከመቻቸት፣ አያያዝ እና አወጋገድ በተመለከተ ተፈጻሚነት የሚኖራቸው የአፈጻጸም አካሄዶች ተፈጻሚ ይሆናሉ።