በዚህ ፍርድ ቤት የናሙና ክፍሎች
በዚህ ፍርድ ቤት. ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻሉ፡፡ ይህ ፍርድ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ሚያዝያ 3ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በሙሉ ድምጽ ተሰጠ፡፡ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡ ነ/ዓ ሒሩት መለሠ ተሻገር ገ/ሥላሴ ሱልጣን አባተማም 32ዐ91 ታህሣሥ 24 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በዋለው ችሎት የሰጠው ትዕዛዝ ነው፡፡ የጉዳዩም አመጣጥ ባጭሩ እንደሚከተለው ነው፡፡ የአሁን መልስ ሰጭ ወ/ሮ ምስራቅ ኃይሉ ባቀረቡት የፍቺ ውሣኔ እና የንብረት ክፍፍል ጥያቄ መነሻ የአሁን አመልካች የበኩላቸውን ክርክር ካቀረቡ በኋላ የፍቺ እና የንብረት ክፍፍል ጥያቄ የቀረበለት ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ተመልክቶ ሐምሌ 23 ቀን 1996 ዓ.ም. ውሣኔ ሰጥቷል፡፡ በዚህ ውሣኔ ከተሸፈነው አንዱ የአመልካች በሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተከሣሽ የአቶ መለስ ሲማ የመከራከሪያ ነጥብ የጋራ ንብረት እንደሆነ ተቆጥሮ የቀረበው የመኖሪያ ቤት እና መጋዘን ከጋብቻ በፊት የነበረኝን የግል ንብረቶች ሸጨ የተሰራ ስለሆነ በጋራ ሀብትነት ሊያዝ አይገባም የሚለው ነው፡፡ ለውጥ የተገኘ ንብረት የግል ሀብት የሚሆነው የግል ነው ይባልልኝ ብሎ ለፍ/ቤት ቀርቦ መጽደቁ ሲታወቅ ነው፡፡ በዚህ አኳኋን የግል ንብረታቸው መሆኑ በፍ/ቤት ቀርቦ የፀደቀ ለመሆኑ ማስረጃ አላቀረቡም፡፡ ስለሆነም ይኸው ቦታና መጋዘን የጋራ ሀበት ነው ሲል ወስኗል፡፡ እንዲሁም ክርክር የቀረበበትን የኪራይ አላባ የአሁን አመልካች በተከሳሽነታቸው በግልጽ ክደው ስላልተከራከሩ እንዳመኑ ይቆጠራል፤ በማለት እንደድርሻቸው እንዲከፋፈሉና የአሁን አመልካች የዕቁብ የጋራ ዕዳ ስላለብን ግማሹን ልትከፍል ይገባል በማለት ያቀረቡትም ክርክር ዕዳ አለባቸው ብሎ 3ኛው ወገን የሚያቀርበው ክርክር እንጂ አመልካችን የሚመለከት አይደለም በማለት በሌሎች ነጥቦችም ላይ ውሣኔ አሳርፎበታል፡፡ ይህ ከላይ የተመለከተው የመጀመሪያ ደረጃ ውሣኔ ከመሰጠቱ በፊት የአሁን አመልካች የግል ንብረቴን ሸጨ ያገኘሁት ንብረት የግል ሆኖ ይጽደቅልኝ በማለት በሌላ ፍ/ቤት አቤቱታ በማቅረቡ ይኸው አቤቱታ የቀረበለት ፍ/ቤት ይህን ጉዳይ ከፍቺ ውሣኔ ጋር በተያያዘ የፍቺውን ጉዳይና የንብረት ክፍፍሉን እያየ ባለው ፍ/ቤት ቀርቦ እየታየ የሚገኝ መሆኑን ገልፆ መዝገቡን በመዝጋቱ የተነሣ የአሁን አመልካች በእነዚህ የተለያዩ ሁለት ጉዳዮች ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በየፊናቸው ሁለት የይግባኝ አቤቱታ አቅርቧል፡፡ የይግባኝ አቤቱታውም የቀረበለት ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛው ፍ/ቤት ሁለቱም መዝገቦች ተጣምረው ሊታዩ የሚገባቸው መሆኑን ገልፆ አጣምሮ በማየት በኮ/ቁ. 32ዐ91 ሚያዝያ 2ዐ ቀን 1998 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የግል ንብረት በፍ/ቤት ይረጋገጥልኝ የሚልን አቤቱታ የፍቺና የጋራ ሀብት ክፍፍል ክርክር ሊያግደው የሚችል አይደለም፡፡ አለበለዚያ የግል ንብረት አለኝ የሚለውን ወገን መብት የሚያጣብብና ሕጉ የግል ሀብቱን እንዲያስከብር የሰጠውን መብት መንፈግ ይሆናል የሚለውን ምክንያት አስደግፎ የግል ንብረቴ ይጽደቅልኝ ጥያቄ አስፈላጊው ማጣሪያ ተደርጎበት በመጀመሪያ ውሣኔ እንዲሰጥበት በመቀጠልም በመ/ቁ. 942 የቀረበው የንብረት ክፍፍል ክርክር እልባት እንዲያገኝ በማለት ወስኗል፡፡ ይህን ሲወስን አስቀድሞ በጭብጥነት ይዟቸው የነበረውን 1ኛ/ የጋራ ንብረትን በተመለከተ የሥር ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ ማስረጃዎችን ያገናዘበ ነው ወይስ አይደለም? 2ኛ/ የጋራ ዕዳ የተባለውስ ነጥብ በሥር ፍ/ቤት በሚገባ ተመርምሯል ወይስ አልተመረመረም? የሚሉት ነጥቦች በሥር ፍ/ቤት በጭብነት ተይዘው ሊሰሩ የሚገባ መሆኑን ጠቅሶ መመርመር ሳያስፈልግ ጉዳዩ ወደ ሥር ፍ/ቤት ተመልሷል፡፡ በሚል አልፏቸዋል፡፡ በዚህ የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ውሣኔ የአሁን መልስ ሰጭ ቅር ተሰኝተው የይግባኝ አቤቱታ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በማቅረባቸው ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ በፍ/ብ/ይ/መ/ቁ. 26813 ሰኔ 27 ቀን 1989 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 58 መሠረት የሚቀርብ አቤቱታ ተጋቢዎች ጋብቻቸው ፀንቶ ባለበት ጊዜ እንጂ ጋብቻ ፈርሶ የንብረት ክፍፍል እየተደረገ ባለበት ጊዜ ለማስረጃ ፍለጋነት በሚያገለግል መልኩ ተፈፃሚነት የሌለው በመሆኑ በዚህ ረገድ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል፡፡ ነገር ግን የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የንብረት ክፍፍሉን በማስመልከት በሰጠው ውሣኔ ላይ የቀረበለትን የይግባኝ ክርክር ሊሰማ ይገባል፡፡ ስለመሆነም የንብረት ክፍፍሉን በማስመልከት በተሰጠው ውሣኔ ላይ የአሁን አመልካች በይግባኝ ባ...