34504.doc 36060.doc 36677.doc 36682.doc 38181.doc 39114.doc 41187.doc 43206.doc
34504.doc 36060.doc 36677.doc 36682.doc 38181.doc 39114.doc 41187.doc 43206.doc
ሚያዝያ 2ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልዱ
ሂሩት መለሠ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም
አመልካቾች፡- 1. ጉታ በየራ ቀርቧል፡፡
2. ተገሽ ማሞ ቀርቧል ጠበቃቸው ቀርቧል፡፡ ተጠሪ፡- ዓቃቤ ሕግ አልቀረበም፡፡
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡
ፍ ር ድ
በዚህ መዝገብ ለቀረበው አቤቱታ መሠረት የሆነው ጉዳይ ዓቃቤ ሕግ በአመልካቾች ላይ ያቀረበውን የወንጀል ክስ የሚመለከት ነው፡፡ ዓቃቤ ሕግ በአመልካቾች ላይ ክስ የመሠረተው በ1996 ዓ.ም. በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 523/1/ እና 433 የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በመተላለፍ የወንጀል ድርጊት ፈጽመዋል በማለት ነው፡፡ አመልካቾች በሰጡት መልስ ክሱን ክደው በመከራከራቸው ፍ/ቤቱ በዓቃቤ ሕግ በኩል የተቆጠሩትን ምስክሮች ከሰማ በኋላ፣ አመልካቾች ክሱን ሊከለከሉ ይገባል በማለት ብይን በመስጠቱ አመልካቾች የመከላከያ ምስክሮቻቸውን አሰምተዋል፡፡ በጨረሻም ፍ/ቤቱ አመልካቾች በተጠቀሱባቸው ሁለቱ አንቀጾች ጥፋተኞች ናቸው ብሎአል፡፡ በዚህ መሠረትም አመልካቾች በአራት ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኖአል፡፡ ይግባኝ የቀረበለት የአማራ ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤትም በሥር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ ጉድለት የለበትም በማለት ይግባኙን ሰርዞአል፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው፡፡
በበኩላችንም አመልካቾች ሐምሌ 7 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በፃፉት ማመልከቻ
ያቀረቡትን አቤቱታ መሠረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል፡፡
አቤቱታው በሰበር ችሎት እንዲታይ የተወሰነው አመልካቾች ፈጸሙት የተባለው ድርጊት እና ምስክሮች የሰጡት ቃል በተጠቀሱት ድንጋጌዎች የተዘረዘሩትን ነገሮች መፈጸማቸውን አያሳይም የሚለውን ቅሬታ ለማጣራት ነው፡፡ በዚህ መሠረትም ይህንን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መርምረናል፡፡
እንደምንመለከተው ጉዳዩ የወንጀል ክስ መሠረት ያደረገ ክርክር የሚመለከት ነው፡፡ የወንጀል ክስ የሚቀርበው ተከሣሹ በወንጀል ሕጉ የተመለከተውን ማለትም ሕገወጥነቱና አስቀጭነቱ በሕግ የተደነገገውን ድርጊት ፈጽሞአል በሚል ነው፡፡ በያዝነው ጉዳይ አመልካቾች የተከሰሱት በ1996 ዓ.ም. በወጣው የወንጀል ሕግ በአንቀጽ 523/1/ እና አንቀጽ 433 ሕገ ወጥነታቸው እና አስቀጭነታቸው የተደነገጉትን ድርጊቶች ፈጽመዋል ተብለው ነው፡፡ በመሆኑም ከሣሽ የሆነው ዓቃቤ ሕግ አመልካቾች በድንጋጌዎቹ በግልጽ የተዘረዘሩትን ድርጊቶች ስለመፈጸማቸው ያስረዳ ዘንድ ይጠበቅበታል፡፡
የዓቃቤ ሕግ ክስ እንደሚያመለክተው አመልካቾች እህልን በችርቻሮ የመነገድ ፈቃድ ያላቸው ነጋዴዎች ሲሆኑ፣ ሊከሰሱ የቻሉት የጅምላ ንግድ ፈቃድ ሳይኖራቸው ካስመዘገቡት ካፒታል በላይ እህል በመጋዘኖቻቸው ውስጥ አከማችተው ተገኝተዋል ተብለው ነው፡፡ በዓቃቤ ሕግ ምስክሮች እንደተነገረውም 1ኛ አመልካች 46 ኩንታል፣ 2ኛ አመልካች ደግሞ 96 ኩንታል በመጋዘናቸው ውስጥ ተገኝቶአል፡፡ በምስክሮቹ የተነገረው እና የተረጋገጠው ፍሬ ነገርም ይኸው ብቻ ነው፡፡ አመልካቾች በወ/ል ሕግ አንቀጽ 623/1/ እና 433 የሚያስቀጡ ድርጊቶች የተባሉትን ፈጽመዋል ወይስ አልፈጸሙም የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ በምስክሮች የተነገረውን ቃል ከድንጋጌዎቹ ይዘት ጋር ማገናዘብ የግድ ይሆናል፡፡
የወ/ል ሕግ አንቀጽ 523 ርእስ “ችግር ወይም ረሃብ እንዲደርስ ማድረግ” የሚል ነው፡፡ በመልካቾች ላይ የተጠቀሰው ንዑስ አንቀጽ /1/ ይዘትም፡-
- ማንም ሰው አስቦ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ በተለይም በመደበቅ፣ ያለአግባብ በማከማቸት፣ በማጥፋት ወይም ለሰው ወይም ለቤት እንስሳት ሕይወት ወይም ጤና አስፈላጊ የሆኑትን የእሕልን፣ የምግብን፣ የቀለብን፣ የመድኃኒትን ወይም አስፈላጊ የሆኑትን ሌሎች ነገሮች ማመላለስን ወይም ማከፋፈልን በመከልከል በአገር ውስጥ ከባድ መከራ፣ እጦት፣ ረሃብ፣ ተላላፊ በሽታ፣ የእንስሳት በሽታ ወይም ችግር እንዲደርስ ያደረገ እንደሆነ፣ የሚል ነው፡፡ የወ/ል ሕግ እንቀጽ 433 “ም” “ያለፈቃድ ወይም ከተሰጠው ፈቃድ ውጪ መሥራት” የሚል ርእስ የተሰጠው ሆኖ ማንኛውም ሰው በሕግ ወይም በደንብ መሠረት ፈቃድ ሊሰጥበት የሚባውን ማናቸውም ሥራ ያለፈቃድ ወይም ከተሰጠው ፈቃድ ውጭ የሠራ እንደሆነ እንደሚቀጣ ይደነግጋል፡፡
ከፍ ሲል እንዳመለከትነው አመልካቾች እህልን በችርቻሮ ለመነገድ ይችሉ ዘንድ በዚህ የንግድ ዘርፍ የንግድ ፈቃድ አላቸው በመጋዘናቸው የተገኘው 46 ኩንታል እና 96 ኩንታልም መጠኑ የበዛ ቢሆንም ይኸው የሚቸረቸረው እህል ነው፡፡ በመሆኑም ያለፈቃድ ወይም ከተሰጣቸው ፈቃድ ውጭ ሲሰሩ የተገኙበት ሁኔታ የለም፡፡ በወ/ል ሕግ አንቀጽ 523/1/ በዝርዝር እና በግልጽ እንደተመለተው በአካባቢው ሕብረተሰብ እና እንስሳት ላይ ችግር ወይም ረሃብ እንዲደርስ በማሰብ የፈጸሙት ድርጊት አለ ለማለትም በፍጹም የሚቻል አይደለም፡፡ በተሰጣቸው የንግድ ፈቃድ መሠረት የእህል ችርቻሮ ንግድ መስራት የሚችሉት እህሉን ገዝተው በመጋዘን በማስቀመጥ ነው፡፡ በምስክሮች ተነገረ የተባለውም ይኸው ብቻ ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ዓቃቤ ሕግ የወንጀል ሕጉ ሕገወጥና አስቀጪ ነው
በማለት የደነገገውን ድርጊት በአመልካቾች ስለመፈጸሙ ሊያስረዳ አልቻለም ማለት ነው፡፡ ይልቁንም አመልካቾች ባወጡት ንግድ ፈቃድ መሠረት ሲሠሩ ሰለመገኘታቸው ነው በፍሬ ነገር ረገድ የተረጋገጠው፡፡ ሲጠቃለል አመልካቾች ፈጸሙት ተብሎ በዓቃቤ ሕግ የተገለጸው ድርጊት እና ምስክሮቹ የሰጡት ቃል በተጠቀሱት ድንጋጌዎች የተዘረዘሩትን የወ/ል ድርጊቶች መፈጸማቸውን አያሳይም፡፡ በመሆኑም በመልካቾች ላይ የተላለፈው የጥፋተኛነነት እና የቅጣት ውሣኔ በሕግ ወንጀል ነው ተብሎ ባልተነገረው ድርጊት ላይ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በሕግ አተረጓጎም እና አተገባበር ረገድ እንደመሠረታዊ ስህተት ሆኖ የሚቆጠር
ነው፡፡
ው ሣ ኔ
1. አቤቱታ የቀረበበት በአማራ ብ/ክ/መ/ የሰሜን ሸዋ መስተዳድር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 19ዐዐዐ ግንቦት 15 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የተሰጠው ፍርድ እና የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 6771 ሰኔ 18 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝ በወ/መ/ሕግ/ሥ/ሥ/ቁ. 195/2/ለ/1/ መሠረት ተሰርዘዋል፡፡
2. አመልካቾች የፈጸሙት ወንጀል ስለሌለ በነፃ ይለቀቁ ብለናል፡፡ መዝገቡ ይመለስ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡
ነ/ዓ
ሚያዝያ 6 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አብዱልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልዱ
ሒሩት መለሠ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም
አመልካች፡- አቶ አበባው የሺድንበር አልቀረቡም፡፡
ተጠሪ፡- አቶ ካሣ በቀለ ቀረቡ፡፡
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡
ፍ ር ድ
የጉዳዩ መነሻ የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ፍ/ቤት መስከረም 22 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በዋለው ችሎት ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 14/95 በሆነው በ1ዐ/7/99 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የሰጠው እግድ ትዕዛዝ ስላልተነሳ በመዝገቡ ላይ ክርክር መቀጠል አልተቻለም ሲል መዝገቡን ዘግቷል፡፡ ይግባኝ የቀረበለት ከፍተኛ ፍ/ቤትም በመ/ቁጥር 16552 በሆነው ጥቅምት 11 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በዋለው ችሎት ብይኑን አጽንቶታል፡፡ እንደገና በይግባኝ የመረመረው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 44/2ዐዐዐ በሆነው መዝገብ ኀዳር 13 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በዋለው ችሎት መልስ ሰጭ የሆነውን የአሁኑን አመልካችን ሳይጠራውና ሳያከራክር “ምንም እንኳ ሥነ ሥርዓት ሕጉ ባይፈቅድም” በማለት ተጠሪ ጣልቃ ገብቶ እንዲከራከር የተሠጠ ውሣኔ የሌለ በመሆኑ የመጀመሪያ ክስ ቢዘጋለትም እንደ ገና እንዲንቀሳቀስለት በተወሰነው መሠረት ክርክሩ
እንዲቀጥል የተፈጠረው ስህተት ተስተካክሏል በማለት ውሣኔውን በመለወጡ የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው፡፡
አመልካች ታህሣሥ 17 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ጽፎ ያቀረበው ቅሬታ ለተጠሪ ደርሶት ጥር 28 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. የተፃፈ መልስ አቅርቧል፡፡ አመልካችም የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል፡፡
እኛም የግራ ቀኙን ክርክር በሕግ ረገድ በአጭሩ እንደሚከተለው መርምረናል፡፡ በመሠረቱ በፍ/ቤቶች የተከራካሪ ወገኖች ማንኛቸም አቤቱታና ቅሬታ ዳኝነት
ሊታይ የሚችለው በሕግ በተመለከቱ ሥርዓቶች ብቻ ነው፡፡ በተያዘው ጉዳይ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ምንም እንኳ የሥነ-ሥርዓት ሕጉ ባይፈቅድም በማለት በበታች ፍ/ቤቶች የተፈጠረውን ስህተት ለማረም የአሁኑን አመልካች ሳይጠራውና ሳያከራክረው የአንደኛውን ወገን ቅሬታና ክርክር ብቻ በመስማት ውሣኔ ላይ መድረሱ የአንደኛውን ወገን የመስማት መበት የተጋፋና ከሥነ - ሥርዓት ሕግ ውጪ ነው፡፡ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ ቁጥር 338/1/ ሥር በግልጽ እንደተመለከተው ይግባኝ የቀረበለት ፍ/ቤት ይግባኙን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሠረት ያልሠረዘ እንደሆነ ይግባኙ የሚሰማበትን ቀነ ቀጠሮ ወስኖ መልስ ሰጭው ቀርቦ እንዲከራከር መደረግ እንዳለበት ተደንግግል፡፡ ይህን በሕግ የተመለከተውን የመስማት /the right to be heard/ ሕገ መንግሥታዊ መብት ባልጠበቀ መልኩ የተሰጠው ውሣኔ በየትኛውም መመዘኛ ፍትሐዊና የሕግ መሠረት አለው ለማለት የሚችልበት አግባብ የሌለ በመሆኑ አንደኛውን ወገን ሳይጠራ ሳያከራክር የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል፡፡
ው ሣ ኔ
1. የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 44/2ዐዐዐ በ13/3/2ዐዐዐ ዓ.ም. በዋለው ችሎት የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሠረት ተሽሯል፡፡ ይፃፍ፡፡
2. በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ ቁጥር 338/1/ መሠረት ግራ ቀኙን አከራክሮ ተገቢውን እንዲወስን ጉዳዩ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት እንዲመለስ ብለናል፡፡ ይፃፍ፡፡
3. ወጪና ኪሣራ የዚህ ፍ/ቤትን ግራ ቀኙ ይቻቻሉ ብለናል፡፡
4. የውሣኔው ግልባጭ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይተላለፍ ብለን መዝገቡን ዘግተናል፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡
ነ/ዓ
የሰበር መ/ቁ. 36ዐ6ዐ ሚያዝያ 29 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም
ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ
በላቸው አንሽሶ አልማው ወሌ ዓሊ መሐመድ
አመልካች፡-የወ/ሮ ብሬ አያና ወራሾች /እነ አሰገደች በቀለ/ አራት ሰዎች ቀረቡ ተጠሪዎች፡- እነ ዓለማየሁ አየለ / 6 ሰዎች/ ቀረቡ
መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነበር፡፡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡
ፍ ር ድ
ች
ጉዳዩ የቀረበው አመልካ የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር
ች
ዐ1457 ህዳር 27 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የከፍተኛው ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 4352ዐ ጥር 8 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት
ስላለበት በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልካ በተፃፈ አቤቱታ ስለጠየቁ ነው፡፡
የካቲት 27 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም
ች
የክርክሩ መሠረታዊ ጉዳይ ተጠሪዎች በከሣሽነት ቀርበው እናታችን ወ/ሮ ሣህለማርያም ደርስህ ስማቸው ከተራ ቁጥር 3 እስከ 6 ከተጠቀሰው ከሣሾች ወላጅ አባት ከሆነው አቶ በቀለ ገብረእየሱስ በትዳር አብረው በሚኖሩበት ጊዜ ከአርባ ዓመት በፊት በወረዳ 18 ቀበሌ ዐ6 ቁጥር 437 የሆነ ስድስት ክፍሎች ያሉትና ግምቱ ብር 3ዐ,ዐዐዐ /ሰላሣ ሺ ብር/ ሠርተዋል፡፡ ይህንን ቤት ተከሣሽ ማለትም የአመልካ
አውራሽ ወ/ሮ ብሬ አያና ያያሱ በመሆኑ አባታችን ከሞተበት ታህሣሥ 22 ቀን 1993 ዓ.ም ጀምሮ በብር 42ዐ /አራት መቶ ሃያ ብር/ ኪራይ እያከራየች ስለተጠቀመች ቤቱንና የቤት ዕቃ የአቶ በቀለ ድርሻ ለዘጠኝ ወራሾቹ የሚከፈል ሆኖ የእናታችንን ድርሻ እንድንካፈል ይወሰንልን በማለት ክስ አቅረበዋል፡፡
ች
የአመልካ አውራሽ የሆኑት ወ/ሮ ብሬ አያና በበኩላቸው ቀርበው ቤቱን
ከመጋቢት 4 ቀን 197ዐ ዓ.ም ጀምሮ እኔ ከሟች በቀለ ገብረእየሱስ ጋር ሕጋዊ ጋብቻ ፈጽሜ በዚያ አምስት ዓመት ያለምንም ተቀናቃኝ ስጠቀምበት ቆይቻለሁ፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ የከሣሾች /ተጠሪዎች/ አውራሽ በእኔና በሟች አቶ በቀለ ገብረእየሱስ መካከል የነበረውን ጋብቻ አልተቃወሙም፡፡ የንብረት ልካፈል ጥያቄም አቅርበው አያውቁም፡፡ ስለዚህ የከሣሾች ጥያቄ በይርጋ ቀሪ ይሆናል የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን ለፍሬ ጉዳዩ በሰጡት መልስ፣ ቤቱ የጋራ ንብረት እንዲሆን ሟች አቶ በቀለ ገብረእየሱስ መጋቢት 4 ቀን 197ዐ ዓ.ም ከእኔ ጋር ባደረጉት የጋብቻ ውል የተስማሙ በመሆኑ የጋራ ንብረቴ ነው፡፡ ከሣሾች /ተጠሪዎች/ በሟች እናታቸው ወ/ሮ ሣህለማርያም ደርስህ እና አቶ በቀለ ገብረእየሱስ መካከል ጋብቻ የነበረ መሆኑን አላስረዱም የቤት ዕቃም የለም ስለዚህ ክሱ ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክረዋል፡፡ የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመዘነ በኋላ በወረዳ 18 ቀበሌ 6
ች
ቁጥሩ 427 የሆነው ቤት የአመልካ አውራሽ ወ/ሮ ብሬ አያናና አቶ በቀለ
ገብረየሱስና እና የወ/ሮ ሣህለማሪያም የጋራ ንብረት ነው፡፡ በ197ዐ ዓ.ም ወ/ሮ ብሬ አያና እና አቶ በቀለ ገብረእየሱስ ያደረጉት የጋብቻ ውል "ካብትሽ በካብቴ" የሚል ቢሆንም የጋብቻ ውሉ ሟች አቶ በቀለ ገብረእየሱስ ቤቱን ከወ/ሮ ብሬ አያና ጋራ የጋራ ንብረት ለማድረግ የተስማሙ መሆናቸውን አያሣዩም፡፡ ስለዚህ ቤቱ ለሁለት ተከፍሎ
ግማሹ ለወ/ሮ ሣህለማሪያም ወራሾች ግማሹ ደግሞ ለሟች አቶ በቀለ ገብየሱስ ወራሾች እንዲካፈሉ በማለት ወስኗል፡፡
ች
የአመል አውራሽ ወ/ሮ ብሬ አያኔ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ
ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ያቀረቡ ቢሆንም የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሥር ፍርድ ቤት
ች
የሰጠውን ውሣኔ ሙሉ በሙሉ አጽንቶታል፡፡ የአመልካ ለዚህ ችሎት በጽሑፍ
ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት አለበት፡፡ ምክንያቱም ቤቱ የሟች አቶ በቀለና ወ/ሮ ሣህለማሪያም የጋራ ሀብት ስለመሆኑ የቀረበ ማስረጃ የለም፡፡ በሌላ በኩል ቤቱ የተጠሪዎች አውራሽ ወ/ሮ ሣህለማሪያም ነው ቢባል እንኳን አውራሻቸው 197ዐ ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ሀያ አምስት ዓመታት የጋራ ሀብቴን ያካፍሉኝ በማለት ያልጠየቁ በመሆኑ በይርጋ ይታገዳል በማለት ያቀረበውን ክርክር አግባብ ውድቅ አድርጎብኛል፡፡ በእኛ አውራሽና በሟች አቶ በቀለ ገብየሱስ መካከል የተደረገውን ግልጽ የጋብቻ ውል የሥር ፍርድ ቤት ከውሉ ይዘትና መንፈስ ውጭ የሆነ ትርጉም በመስጠት ውድቅ ማድረጉ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ እንዲሻርልን በማለት አመልክተዋል፡፡
ተጠሪዎች በበኩላቸው ሚያዚያ 28 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም ባቀረቡት መልስ
ች
አመልካ ያቀረቡት የይርጋ ክርክር የእኛን የወራሽነት መብት የሚገድብ ስላልሆነ
ተቀባይነት የለውም፡፡ ቤቱ እናታችን ወ/ሮ ሣህለማሪያም የጋራ ንብረት ለመሆኑ በበቂ ሁኔታ አስረድተናል፡፡ ይህንንም የሚያስረዳ የጽሑፍ ማስረጃ አቅርበናል፡፡ ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤቶች ውሣኔ የሕግ ስህተት የሌለበት በመሆኑ እንዲፀናልን በማለት
ች
ች
የተከራከሩ ሲሆን አመልካ አመጣጥ እና በሰበር አመልካ
በጽሑፍ የመልስ መልስ አቅርበዋል፡፡ ከሥር የክርክሩ እና ተጠሪዎች ያቀረቡት የጽሑፍ ክርክር ከላይ
የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል፡፡ ጉዳዩን እንደመረመርነው ፡
ች
1ኛ/ የሥር ፍርድ ቤቶች አመልካ ተጠሪዎች የሟች ወ/ሮ ሣህለማሪያም
የጋራ ንብረት እንዲያካፍሉን በማለት ያቀረቡት ክስ በይርጋ ይታገዳል በማለት ያቀረቡትን የመጀመሪያ የክስ መቃወሚያ ያለፉት በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም?
ች
2ኛ/ የሥር ፍርድ ቤቶች በአመል አውራሽ ወ/ሮ ብሬ አያኔና አቶ በቀለ
ገብረእየሱስ መካከል መጋቢት 4 ቀን 197ዐ ዓ.ም ያደረጉት የጋብቻ ውል ክርክር የተነሣበትን ቤት የጋራ ሀብት ለማድረግ፣ የሚችል አይደለም በማለት የሰጡት ውሣኔ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚሉትን ጭብጦች መፍታት አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ በተጠሪዎች አውራሽ ሟች ወ/ሮ ሣህለማርያም ደርስህና ሟች አቶ በቀለ ገብረእየሱስ መካከል በመዝገብ ቁጥር 2344/67 የባልና የሚስት ክርክር የነበረ መሆኑን በማገናዘብ በሟች ወ/ሮ ሣህለማሪያም ደርስህና በሟች አቶ በቀለ ገብረእየሱስ መካከል ጋብቻ የነበረ መሆኑንና ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤትም በጋብቻ በነበሩበት ጊዜ ያፈሩት የጋራ ንብረት መሆኑን ከሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ለመረዳት ይቻላል፡፡ ሟች አቶ በቀለ ገብረእየሱስ እና ሟች ወ/ሮ ሣህለማሪያም ከዚህ በኋላ አብረው የማይኖሩና በተቃራኒው አቶ በቀለ ገ/እየሱስ 197ዐ ዓ.ም የአመልካ ችን አውራሽ ወ/ሮ ብሬ አያና አግብተውና ትዳር መሥርተው ክርክር ያስነሣውን ቤት ሙሉ በሙሉ ይዘው ይኖሩ የነበረ መሆኑ ከሥር ፍርድ ቤት ተረጋግጧል፡፡ ስለሆነም ወ/ሮ ሣህለማሪያም ደርስህ /የተጠሪዎች አውራሽ/ በህይወት በነበሩበት ጊዜ አቶ በቀለ ገብረእየሱስ የጋራ ሀብታቸውን እንዲያካፍሏቸው ሣይጠይቁ ወይም ክስ ሣያቀርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ መሆናቸውን ለመረዳት ይቻላል፡፡ ሟች አቶ በቀለ ገብረእየሱስ ከአመልካ ች እናት ወ/ሮ ብሬ አያኔ ጋር ጋብቻ ከመሠረቱበት
197ዐ ዓ.ም ጀምሮ ሟች ወ/ሮ ሣህለማሪያም ደርስህ በሞት እስከተለዩበት ድረስ ያለው
ጊዜ ስታብ አስራ አራት ዓመት ያህል የተጠሪዎች አውራሽ አቶ በቀለ ገብረእየሱስና
ች
የአመልካ አውራሽ የጋራ ንብረታቸውን እንዲከፍሏቸው ጥያቄ /ክስ/ ሣያቀርቡ የቆዩ
ች
መሆኑን እና ተጠሪዎች የሟች ወ/ሮ ሣህለማሪያም ደርስህ ወራሾች መሆናቸውን በመዝገብ ቁጥር 17ዐ/85 ታህሣሥ 21 ቀን 1985 ዓ.ም ያረጋገጡ መሆኑን ከዚያም በኋላ የእናታችንን የጋራ ሀብት ያካፍለን የሚል ጥያቄ እስከሚያዝያ 15 ቀን 1994 ዓ.ም ድረስ ያላቀረቡ መሆኑን ከሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ተገንዝበናል፡፡ የተጠሪዎች እናትና ተጠሪዎች የጋራ ንብረት ክፍያ ጥያቄ ሣያቀርቡ ከሀያ አራት ዓመት በላይ ያለፈ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ ከዚህ አንፃር ስናየው ባልና ሚስት ጋብቻቸው ከፈረሰ በኋላ ገደብ በሌለው ሁኔታ የጋራ ንብረት ክፍፍል ጥያቄ እንዲያቀርቡ የማይፈቀድ በመሆኑና ይልቁንም በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1677 ንዑስ አንቀጽ 1 እና በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1845 ድንጋጌ መሠረት በአስር ዓመት ጊዜ ውስጥ ክስ ካላቀረቡ ጥያቄው በይርጋ ቀሪ እንደሚሆን ከዚህ በፊት የሰበር ችሎት የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡ ከዚህ አንፃር ስናየው የተጠሪዎች አውራሽ ወ/ሮ ሣህለማሪያም ደርስህ ከሟች አቶ በቀለ ገብረእየሱስ ጋር የነበራቸው ትዳር ከፈረሰ በኋላ በአስር አመት ጊዜ ውስጥ በጋብቻ በነበርኩበት ጊዜ አፍርቸዋለሁ የሚሉትን የጋራ ሐብት ሟች አቱ በቀለ ገ/እየሱስ እና የአመልካ እናት ወ/ሮ ብሬ አያኔ እንዲያካፍሏቸው ወይም እንዲሰጧቸው ያልጠየቁ በመሆኑ የጋራ ንብረት ለመካፈል ያቀረበው ክስ በአስር ዓመት የይርጋ የጊዜ ገደብ ቀሪ የሚሆን ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
አንድ ሰው ሲሞት ለወራሾቹ የሚተላለፈው መብትና ግዴታ ሟች በሕይወት ቢኖር ኖሮ ሊጠይቀውና ሊሠራበት የሚችለው መብት ብቻ እንደሆነ ከፍትሐብሔር ሕግ
ች
ቁጥር 826 ንዑስ አንቀጽ 2 ይደነግጋል፡፡ የአመልካ አውራሽ ወ/ሮ ብሬ አያኔ
የተጠሪዎች አውራሽ ወ/ሮ ሣህለማሪያም ደርስህ በህይወት እያሉ የጋራ ንብረት
ለመካፈል ክስ አቅርበው ቢሆን ኖሮ በክሱ ላይ ሊያቀርቡ የሚችሉትን የይርጋ ጊዜ ገደብ መቃወሚያ ተጠሪዎች እናታችን በጋብቻ ያፈራችው የጋራ ንብረት ተከፍሎ ይሰጠን በማለት ያቀረቡትን ክስ አቅርባለች፡፡ ተጠሪዎች የጋራ ንብረቱ ተካፍሎ እንዲሰጣቸው የሚያቀርቡት ጥያቄ የሚመነጨው ከአውራሻቸው ወ/ሮ ሣህለማሪያም ደርስህ መብት ነው፡፡ የተጠሪዎች አውራሽ ከሟች በቀለ ገብረእየሱስ ጋር ያላቸው የጋራ ሀብት ለመካፈል /ክስ/ ያቀረቡ ከአስራ አራት ዓመት በላይ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ ተጠሪዎች ደግሞ እናታቸው በሞት ከተለዩ ከአስር ዓመት በኋላ የጋራ ንብረት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ የተጠሪዎች አውራሽ ወ/ሮ ሣህለማሪያም ደርስህ የጋራ ንብረት የመካፈል ክስ የማቅረብ መብታቸው በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1677 ንዑስ አንቀጽ 1 እና በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1845 በአስር ዓመት የይርጋ ጊዜ የሚቋረጥ በመሆኑ ተጠሪዎች አውራሻቸው ከሞቱ ከአስር ዓመት በኋላ በአጠቃላይ በአውራሻቸው ወ/ሮ ሣህለማሪያም ደርስህ እና በሟች በቀለ ገብረእየሱስ መካከል ያለው ጋብቻ ከፈረሰ ከሀያ አራት ዓመት በኋላ ያቀረቡት ክስ በይርጋ ቀሪ ይሆናል፡፡ ተጠሪዎች አውራሻቸው የሌላቸውንና በይርጋ ቀሪ የሆነ የጋራ ንብረት ክፍያ ጥያቄ የማቅረብ መብት እነርሡ
ች
ሊኖራቸው አይችልም፡፡ ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤቶች የአመልካ አውራሽ የሆኑት
ወ/ሮ ብሬ አያኔ ክሱ በይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት ያቀረቡትን መቃወሚያ ማለፋቸው መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
ች
2. በሁለተኛ ደረጃ መታየት ያለበት ጭብጥ በአመልካ አውራሽ የሆኑት
ወ/ሮ ብሬ አያናና ሟች አቶ በቀለ ገብረእየሱስ መጋቢት 4 ቀን 197ዐ ዓ.ም ያደረጉት የጋብቻ ውል ክርክር የተነሣበትን ቤት የጋራ ንብረት የሚያደርግ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነው፡፡ ይህንን ጭብጥ እልባት ለመስጠት በሁለቱ መካከል የተደረገውን ውል ይዘት መመርምር አስፈላጊ ነው፡፡ የጋብቻ ውሉ " እኔ አቶ በቀለ ገብረእየሱስና ወ/ሮ
ብሬ አያና በሰማኒያ ትዳር መሥርተን አብረን ለመኖር ባደረግነው ስምምነት መሠረት በሁለታችንም በኩል ጥረን የምናገኘው ሁሉ ልጅ ከወለድን ለልጆቻችን ማሣደጊያ ለኑሯችን ማስፋፊያ እያደረግን አብሮ በመኖር ካብትሽ በካብቴ ሆኖ ያለውን 1 ቤት አራት ክፍል ከነሙሉ የቤት ዕቃዎች ቆጥሬላት በሰማኒያ አግብቻታለሁ፡፡ እኔ ወ/ሮ ብሬ አያኔ አቶ በቀለ ገብረእየሱስን በሰማኒያ ሣገባ ከዚህ በላይ የተዘረዘረውን ቤትና ዕቃ ቆጥረውልኝ በሰማኒያ ማግባቴን በፊርማዬ አረጋግጣለሁ" የሚል ነው፡፡
ከላይ ሙሉ ይዘቱን የፃፍነው የጋብቻ ውል ሁለት መሠረታዊ ክፍሎች አሉ፡፡ የመጀመሪያው ሟች አቶ በቀለና ወ/ሮ ብሬ አያና ከተጋቡ በኋላ የሚያገኙትን ሀብት የሚመለከት ሲሆን ይኸም ንብረት ልጆች ከተወለዱ ለልጆች ማሣደጊያና ለኑሮ ማስፋፊያ እያደረጉ አብረው ለመኖርና "ካብትሽ በካብቴ" እንዲሆን የተስማሙ መሆኑን፣ የሚገልፀው ነው፡፡ ክርክር የተነሣበት ቤት ከጋብቻ በፊት የተሠራ በመሆኑ በዚህ በመጀመሪያው የጋብቻ ውል ክፍልና ሀይለቃል የሚጠቃለል አይደለም፡፡
ሁለተኛው ክፍል አቶ በቀለ ገብረእየሱስ ያለውን ቤት ከነሙሉ ዕቃዎች ቆጥሬላት በሰማኒያ አግብቻታለሁ በማለት የገለፁትና ሟች ወ/ሮ ብሬ አያናም ከላይ የዘረዘረውን ቤትና ዕቃ ቆጥረውልኝ በሰማኒያ ማግባቴን በፊርማዬ አረጋግጣለሁ በማለት የገለፁት የጋብቻ ውሉ ክፍል ነው፡፡ ከዚህም የምንረዳው " ካብትሽ በካብቴ" የሚለው ቃልና አገላለፅ ከተጋቡ በኋላ ለሚያፈሩት ንብረት ተፈፃሚ የሚሆንና ከጋብቻ በፊት የነበረውን ቤት እና የቤት ዕቃ አስመልክቶ ሟች አቶ በቀለ ገብእየሱስ "ቆጥሬላት" የሚል ቃልና አገላለፅ የተጠቀሙና ሟች ወ/ሮ ብሬ አያናም ቆጥረውልኝ የሚል ቃልና አገላለጽ የተጠቀ መሆኑን ነው፡፡ ስለሆነም "ቆጥሬላትና" ቆጥረውልኝ" የሚለው አባባል ግልፅነት የጎደለውና ሟች አቶ በቀለ ገብረእየሱስ ከጋብቻ በፊት ያሠሩት ቤት የወ/ሮ ብሬ አያና የጋራ ንብረት እንዲሆን፣ የተስማሙ መሆናቸውን በግልፅ የሚያሣይ ነው፡፡
የጋብቻ ውሉ ከጋብቻ በፊት የነበረው ንብረት በግልፅ የጋራ ንብረት እንዲሆን ተጋቢዎች የተስማሙ መሆኑን በማያሣይበትና ትርጉሙን ከልማድም ሆነ ከመዝገበ ቃላት ለመረዳት በማይቻልበት ሁኔታ ንብረቱን የጋራ ለማድረግ ተጋቢዎቹ ተስማምተዋል ብሎ ለመደምደም አይቻልም፡፡ ስለሆነም ሟች በቀለ ገብረእየሱስና ሟች ብሬ አያና መጋቢት 4 ቀን 197ዐ ያደረጉት የጋብቻ ውል "ቆጥሬላት" እና "ቆጥረውልኝ" የሚል ቃልና አገላለፅ የተጠቀሙ ቢሆንም ይኸ ቃል ሟች አቶ በቀለ ገብረእየሱስ ወ/ሮ ብሬ አያና ከማግባታቸው በፊት ያፈሩት ቤትና የቤት ዕቃ የጋራ ንብረት እንዲሆን የተስማሙ መሆናቸውን በግልጽ የማያሣይ በመሆኑ፣ የሥር ፍርድ ቤቶች ክርክር የተነሣበት ቤት የሟች ወ/ሮ ብሬ አያና የጋራ ንብረት አይደለም በማለት የሰጡት ውሣኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የሌለውና ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤቶች ክርክር የተነሣበት ቤት የሟች የወ/ሮ ብሬ አያኔ የጋራ ንብረት አይደለም በማለት የሰጡት ውሣኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የሌለበት
ች
ሲሆን የአመልካ አውራሽ ያቀረቡትን የይርጋ መቃወሚያ ውድቅ ማድረጋቸው
መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበትና መሻሻል የሚገባው ነው በማለት ወስነናል፡፡
ው ሣ ኔ
1. የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር ዐ1457 ህዳር 27 ቀን 1998 የሰጠው ውሣኔና የከፍተኛው ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 4352ዐ ጥር 8 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በከፊል ተሻሽሏል፡፡ ይፃፍ፡፡
2. ተጠሪዎች የእናታችን የወ/ሮ ሣህለማሪያም ደርስህ ድርሻ ይሰጠን በማለት ያቀረቡት ክስ በይርጋ ቀሪ ይሆናል ብለናል፡፡
ች
3. አመልካ ክርክር የተነሣበት ቤት የእናታችን የወ/ሮ ብሬ አያና
የጋራ ንብረት ነው በማለት ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የሌለው ነው ብለናል፡፡
4. የክርክሩ መነሻ የሆነውና በአዲስ አበባ ከተማ በቀድሞው ወረዳ 18 ቀበሌ ዐ6 ቁጥሩ 437 የሆነው ቤት የሟች በቀለ ገብረእየሱስ የግል ንብረት ነው፡፡ ስለሆነም የሟች በቀለ ገብረእየሱስ ወራሽ ለሆኑት ከወ/ሮ ሣህለማሪያም ደርስህና ከሟች ብሬ አያና የወለዳቸው ልጆቹ ብቻ እኩል ሊካፈሉት ይገባል በማለት ወስነናል፡፡ ይፃፍ፡፡
5. በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኛቸው ራሣቸውን ይቻሉ ይኸ ፍርድ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ሚያዚያ 29 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በሙሉ ድምፅ ተሰጠ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ተ.ወ
ዳኞች፡- አብዱልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ
ፀጋዬ አስማማው አልማው ወሌ ዓሊ መሐመድ
የሰ/መ/ቁ. 36677 ሚያዝያ 3ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
አመልካች፡- ወ/ሮ ሻምሺ ዩኑስ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ኑሪያ ማሚ
መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነበር፡፡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ
ሰጥተናል፡፡
ፍ ር ድ
ጉዳዩ የቀረበው የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሸሪዓ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 16/99 የካቲት 27 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት መጋቢት 19 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ስለጠየቁ ነው፡፡
ክርክሩ የተጀመረው፣ በድሬዳዋ ናኢባ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በድሬደዋ ናኢባ ፍርድ ቤት ተጠሪ በከሳሽነት ቀርባ ሟች አባቴ በድሬደዋ ከተማ ቀበሌ ዐ8 በአምስት መቶ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ቦታውን እንድትለቅ ስትጠየቅ ለመልቀቅ ትንሽ ቤት ሠርታ ትኖር ነበር፡፡ ቦታው ያገባችው የዛሬ ሰባት ዓመት ሲሆን ወላጅ አባቴ ከሞተ በኋላ በቦታው ላይ ግንቦታ ለማካሄድ ቦታውን እንድትለቅልኝ ስጠይቃት እንቢ ስላለችኝ ቦታውን እንድትለቅ እንዲወሰንልኝ በማለት ክስ ያቀረበች ሲሆን የአሁን አመልካች በተጠሪነት ቀርባ፣ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን የማየት ስልጣን የለውም በአዋጅ ቁጥር 25/1988 መሠረት የመደበኛ ፍርድ ቤት ሥልጣን ነው በማለት የመጀመሪያ ደረጃ የይግባኝ መቃወሚያ አቅርበዋል፡፡
አመልካች በፍሬ ጉዳይ እረገድ ቦታው በአዋጅ ቁጥር 47/1967 የተወረሰ ነው የሚሉና ሌሎች ክርክሮችን አቅርበዋል፡፡ የናኢባ ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረበችውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ለማለፍ የፍሬ ጉዳይ ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኋላ፣ አመልካች ይዞታውን ለተጠሪ እንድትለቅ በማለት ወስኗል፡፡ አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ የድሬደዋ ፌዴራል ከፍተኛ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበው ከተከራከሩ በኋላ የከፍተኛ ሸሪዓ ፍ/ቤቱ የሥረ ነገር ሥልጣንን በተመለከተ የቀረበውን የይግባኝ ቅሬታ በማለፍ በፍሬ ጉዳይ በኩል አጣርቶ እንዲወስን ጉዳዩን በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 343 መሠረት መልስ ልኮለታል፡፡ ሆኖም በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ተጠሪ ይግባኝ ለፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት አቅርባ ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤቱ የናኢባ ፍርድ ቤት ከፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የማያንስ ስልጣን አለው ካለ በኋላ በፍሬ ጉዳይ ረገድ፣ የድሬደዋ ፌዴራል ከፍተኛ ሸሪዓ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር የናኢባ ወረዳ ፍርድ ቤት ውሣኔ በማጽደቅ ውሣኔ ሰጥቷል፡፡
አመልካች ይህ የጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት አለበት፡፡ ተጠሪ ያቀረባቸው ክስ የወላጅ አባቴን ይዞታ ታስረክበኝ የሚል ሲሆን እኔ ደግሞ 1982 ዓ.ም. ጀምሮ በቦታው ላይ ማንናቸውም የጋብቻ የፍች የቀለብ አወሳሰን፣ አካለ መጠን ያልደረሱ ሕፃናት ሞግዚትነት እና የቤተሰብ ተዛምዶ ላይ የሚነሱ ጉዳዮችን አስመልክቶ ጥያቄ ያስከተለው ጋብቻ በእስልምና ሀይማኖት ሥርዓት መሠረት የተፈፀመ የሆነ እንደሆነ ወይም ባለጉዳዮቹ በእስልምና ሀይማኖት ሥርዓት ለመዳኘት አቅደው እንደሆነ
- የእውቅና ስጦታ /ሂባ/ ውርስ ወይም ኑዛዜ ጉዳዮችን በተመለከተ አውራሹ ወይም ስጦታ አድራጊ ወይም ተናዛዥ ሙስሊም የሆነ እንደሆነ ወይም ሟች በሞተበት ሰዓት ሙስሊም ሆኖ የሞተ እንደሆነ
- ከላይ በተገለጹት ጉዳዮች ላይ የሚቀርቡ ክሶችን ኪሣራ የሚመለከት ሲሆን እንደሆነ ከአዋጅ ቁጥር 188/1992 አንቀጽ 4 ንዑስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ ለመረዳት እንችላለን፡፡
ከዚህ ውጪ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የናኢባ ፍርድ ቤት የከፍተኛው ሸሪዓ ፍርድ ቤትም ሆነ የጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ክርክር የመስማትና ውሣኔ የመስጠት ሥልጣን የላቸውም፡፡ የያዝነው ጉዳይ፣ የይዞታ ክርክር ጉዳይ ነው፡፡ አመልካችና ተጠሪ የአንድ ሰው ወራሾች በመሆናቸው ምክንያት የቀረበ የውርስ ንብረት ክፍያ ጥያቄ አይደለም፡፡ ስለሆነም ቦታው የማን ይዞታ ነው የሚለውን ጉዳይ አከራክረው የመወሰን የዳኝነት ሥልጣን ያላቸው በአዋጅ ቁጥር 25/1988 መሠረት መደበኛ ፍርድ ቤቶች ናቸው፡፡ ከዚህ አንፃር ስናየው የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት የድሬደዋ ናኢባ ፍርድ ቤት የቦታውንና ቦታውን አስመልክቶ፣ ከፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያላነሰ ሥልጣን አለው በማለት መወሰኑ የፌዴራል ሸሪዓ ፍርድ ቤቶችን አቋም በማጠናከር የወጣ አዋጅ ቁጥር 188/92 አንቀጽ 4 ንዑስ አንቀጽ
1 የተመለከቱትን መሠረታዊ ድንጋጌዎች ባለማገናዘብ የተሰጠ ሆኖ ስላገኘነው መሠረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት ወስነናል፡፡ ቤት ሰርቼ እየኖርኩ ያለሁ መሆኔን ገልጬ የናኢባ ፍርድ ቤት ይዞታን አስመልክቶ የሚነሳ ክርክር የማየት ሥልጣን የለውም በማለት ያቀረበኩት መቃወሚያ አላግባብ አልፎና በይዞታ ጉዳይ አከራክሮ ወስኗል፡፡ ስለዚህ ያለበቂ ማስረጃ አከራክሮ ውሣኔ የሰጠ በመሆኑም የጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤትም የተፈፀመውን የሕግ ስህተት ያላረመ በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት የሰበር አቤቱታ አቅርቧል፡፡
ተጠሪ በበኩሏ ክርክሩ በሸሪዓ ፍርድ ቤት የተደረገው በአመልካች ፈቃደኝነት ነው፡፡ ስለዚህ የሸሪዓ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ የሚነቀፍበት መሠረታዊ የሕግ ስህተት የለም የሚል ክርክር አቅርበዋል፡፡ አመልካች በጽሁፍ የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታዋን የሚያጠናክር ክርክር አቅርባለች፡፡
ከሥር የክርክሩ አመጣጥ ከላይ በአጭሩ የተገለፀው ሲሆን፣ እኛም መዝገቡን መርምረናል፡፡ መዝገቡን እንደመረመርነው የሸሪዓ ፍርድ ቤት በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተፈጠረውን የይዞታ መብት ጥያቄ አይቶ የመወሰን የሥረ ነገር ስልጣን አለው? ወይስ የለውም? የሚለውን ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
ከድሬደዋ ናኢባ ፍርድ ቤት ከከፍተኛ ሸረዓ ፍርድ ቤትና ከጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት የውሣኔ ግልባጭ ለመረዳት እንደቻልነው ይዞታ ክርክር ነው፡፡ ተጠሪ ቤቱ የሟች ወላጅ አባቷ መሆኑንና አመልካች ቤት የሰራችው በአባቷ ፈቃድ ልቀቂ ስትባል ለመልቀቅ ተስማምታ መሆኑን በመግለጽ የምንከራከር ሲሆን አመልካች በበኩሉ 1982 ዓ.ም. ጀምሮ ይዞታው የእሷ መሆኑን በመግልጽ የይዞታ ክርክር የናኢባ ፍርድ ቤት ማየት የለበትም የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርባለች፡፡ የፌዴራል ሸሪዓ ፍርድ ቤት የወል የዳኝነት ሰልጣን በምን ጉዳዮች ላይ እንደሆነ በአዋጅ ቁጥር 188/1992 በአንቀጽ 4 ተደንግጓል፡፡ በዚህ የሕግ ድንጋጌ መሠረት በፌዴራል በማናቸውም ደረጃ የሚገኙ የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ጉዳዩን አይተው
የመወሰን የዳኝነት ሥልጣን የሚኖራቸው፡፡
ው ሣ ኔ
1. የፌዴራል ሸሪዓ ፍርድ ቤት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የድሬደዋ ናኢባ ፍርድ ቤት የይዞታ ጉዳይ አከራክረው የመወሰን የዳኝነት ስልጣን የሌላቸው በመሆኑ ውሣኔያቸው ሙሉ በሙሉ ሽሯል፡፡
2. ይህ ውሣኔ ተጠሪ ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ክስ አቅርባ ከመጠየቅ የሚገድባት አይደለም ብለናል፡፡
3. በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻሉ፡፡
ይህ ፍርድ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ሚያዝያ 3ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
በሙሉ ድምጽ ተሰጠ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡
ነ/ዓ
ጥቅምት 25 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም.
ዳኞች፡- አብዱልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልዱ
ሒሩት መለሠ ተሻገር ገ/ሥላሴ ሱልጣን አባተማም
አመልካች፡- አቶ መለሠ ሲማ - ጠበቃ አቶ ካሣሁን አሰፋ ቀረቡ፡፡
መልስ ሰጪ፡- ወ/ሮ ምስራቅ ኃይሉ ጠበቃ ኮሌኔል ካሣሁን በላቸው ቀረቡ፡፡ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን፤ መርምረን ፍርድ ሰጥተናል፡፡
ፍ ር ድ
ለዚህ የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ.
32ዐ91 ታህሣሥ 24 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በዋለው ችሎት የሰጠው ትዕዛዝ ነው፡፡
የጉዳዩም አመጣጥ ባጭሩ እንደሚከተለው ነው፡፡ የአሁን መልስ ሰጭ ወ/ሮ ምስራቅ ኃይሉ ባቀረቡት የፍቺ ውሣኔ እና የንብረት ክፍፍል ጥያቄ መነሻ የአሁን አመልካች የበኩላቸውን ክርክር ካቀረቡ በኋላ የፍቺ እና የንብረት ክፍፍል ጥያቄ የቀረበለት ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ተመልክቶ ሐምሌ 23 ቀን 1996 ዓ.ም. ውሣኔ ሰጥቷል፡፡
በዚህ ውሣኔ ከተሸፈነው አንዱ የአመልካች በሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተከሣሽ የአቶ መለስ ሲማ የመከራከሪያ ነጥብ የጋራ ንብረት እንደሆነ ተቆጥሮ የቀረበው የመኖሪያ ቤት እና መጋዘን ከጋብቻ በፊት የነበረኝን የግል ንብረቶች ሸጨ የተሰራ ስለሆነ በጋራ ሀብትነት ሊያዝ አይገባም የሚለው ነው፡፡
የመጀመሪያው ደረጃ ፍ/ቤትም ይህንኑ ነጥብ በሚመለከት በፍ/ብ/መ/ቁ. 942
ሐምሌ 23 ቀን 1996 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ውሣኔ ካሣረፈባቸው ፍሬ ጉዳዮች አንዱ ሲሆን የሰጠውም ዳኝነት በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 58 መሠረት በግል ሀብት
ለውጥ የተገኘ ንብረት የግል ሀብት የሚሆነው የግል ነው ይባልልኝ ብሎ ለፍ/ቤት ቀርቦ መጽደቁ ሲታወቅ ነው፡፡ በዚህ አኳኋን የግል ንብረታቸው መሆኑ በፍ/ቤት ቀርቦ የፀደቀ ለመሆኑ ማስረጃ አላቀረቡም፡፡ ስለሆነም ይኸው ቦታና መጋዘን የጋራ ሀበት ነው ሲል ወስኗል፡፡
እንዲሁም ክርክር የቀረበበትን የኪራይ አላባ የአሁን አመልካች በተከሳሽነታቸው በግልጽ ክደው ስላልተከራከሩ እንዳመኑ ይቆጠራል፤ በማለት እንደድርሻቸው እንዲከፋፈሉና የአሁን አመልካች የዕቁብ የጋራ ዕዳ ስላለብን ግማሹን ልትከፍል ይገባል በማለት ያቀረቡትም ክርክር ዕዳ አለባቸው ብሎ 3ኛው ወገን የሚያቀርበው ክርክር እንጂ አመልካችን የሚመለከት አይደለም በማለት በሌሎች ነጥቦችም ላይ ውሣኔ አሳርፎበታል፡፡
ይህ ከላይ የተመለከተው የመጀመሪያ ደረጃ ውሣኔ ከመሰጠቱ በፊት የአሁን አመልካች የግል ንብረቴን ሸጨ ያገኘሁት ንብረት የግል ሆኖ ይጽደቅልኝ በማለት በሌላ ፍ/ቤት አቤቱታ በማቅረቡ ይኸው አቤቱታ የቀረበለት ፍ/ቤት ይህን ጉዳይ ከፍቺ ውሣኔ ጋር በተያያዘ የፍቺውን ጉዳይና የንብረት ክፍፍሉን እያየ ባለው ፍ/ቤት ቀርቦ እየታየ የሚገኝ መሆኑን ገልፆ መዝገቡን በመዝጋቱ የተነሣ የአሁን አመልካች በእነዚህ የተለያዩ ሁለት ጉዳዮች ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በየፊናቸው ሁለት የይግባኝ አቤቱታ አቅርቧል፡፡
የይግባኝ አቤቱታውም የቀረበለት ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛው ፍ/ቤት ሁለቱም መዝገቦች ተጣምረው ሊታዩ የሚገባቸው መሆኑን ገልፆ አጣምሮ በማየት በኮ/ቁ. 32ዐ91 ሚያዝያ 2ዐ ቀን 1998 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የግል ንብረት በፍ/ቤት ይረጋገጥልኝ የሚልን አቤቱታ የፍቺና የጋራ ሀብት ክፍፍል ክርክር ሊያግደው የሚችል አይደለም፡፡ አለበለዚያ የግል ንብረት አለኝ የሚለውን ወገን መብት የሚያጣብብና ሕጉ የግል ሀብቱን እንዲያስከብር የሰጠውን መብት መንፈግ ይሆናል የሚለውን ምክንያት
አስደግፎ የግል ንብረቴ ይጽደቅልኝ ጥያቄ አስፈላጊው ማጣሪያ ተደርጎበት በመጀመሪያ ውሣኔ እንዲሰጥበት በመቀጠልም በመ/ቁ. 942 የቀረበው የንብረት ክፍፍል ክርክር እልባት እንዲያገኝ በማለት ወስኗል፡፡ ይህን ሲወስን አስቀድሞ በጭብጥነት ይዟቸው የነበረውን
1ኛ/ የጋራ ንብረትን በተመለከተ የሥር ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ ማስረጃዎችን ያገናዘበ ነው ወይስ አይደለም?
2ኛ/ የጋራ ዕዳ የተባለውስ ነጥብ በሥር ፍ/ቤት በሚገባ ተመርምሯል ወይስ አልተመረመረም? የሚሉት ነጥቦች በሥር ፍ/ቤት በጭብነት ተይዘው ሊሰሩ የሚገባ መሆኑን ጠቅሶ መመርመር ሳያስፈልግ ጉዳዩ ወደ ሥር ፍ/ቤት ተመልሷል፡፡ በሚል አልፏቸዋል፡፡
በዚህ የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ውሣኔ የአሁን መልስ ሰጭ ቅር ተሰኝተው የይግባኝ አቤቱታ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በማቅረባቸው ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ በፍ/ብ/ይ/መ/ቁ. 26813 ሰኔ 27 ቀን 1989 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 58 መሠረት የሚቀርብ አቤቱታ ተጋቢዎች ጋብቻቸው ፀንቶ ባለበት ጊዜ እንጂ ጋብቻ ፈርሶ የንብረት ክፍፍል እየተደረገ ባለበት ጊዜ ለማስረጃ ፍለጋነት በሚያገለግል መልኩ ተፈፃሚነት የሌለው በመሆኑ በዚህ ረገድ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል፡፡ ነገር ግን የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የንብረት ክፍፍሉን በማስመልከት በሰጠው ውሣኔ ላይ የቀረበለትን የይግባኝ ክርክር ሊሰማ ይገባል፡፡ ስለመሆነም የንብረት ክፍፍሉን በማስመልከት በተሰጠው ውሣኔ ላይ የአሁን አመልካች በይግባኝ ባይነቱ ያቀረበውን ይግባኝ ለብቻው መርምሮ የመሰለውን ውሣኔ ይስጥበት በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/መ/ቁ. 341/1/ መሠረት መዝገቡን በመመለስ ወስኗል፡፡ ሆኖም መዝገቡ የተመለሰለት የይግባኝ ሰሚው ከፍተኛው ፍ/ቤት መዝገቡን ካንቀሣቀሰ በኋላ ታህሣሥ 24 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በዋለው ችሎት በይግባኝ ደረጃ ክርክር
ሊደረግ የቻለው በግብይት የተገኘው ንብረት የግሌ ይሁንልኝ የሚለው ጥያቄው በሚመለከት ሲሆን፤ በዚህም ጉዳይ ላይ ጠቅላይ ፍ/ቤት ውሣኔ ስለሰጠበት ለፍቺ ውጤቱ የተሰጠውን ውሣኔ ለመለወጥ የሚያስችል ምክንያት አላገኘሁበትም በማለት በትዕዛዝ መዝገቡን ዘግቶታል፡፡
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ የይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍ/ቤት በሰጠው ትዕዛዝ ላይ ነው፡፡
የአሁን አመልካች የሰበር አቤቱታ በሁለት ነጥቦች ላይ ያተኮረ ነው፡፡ 1ኛው የተሻሻለውን የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 58ን ድንጋጌ አስመልክቶ ይግባኝ ሰሚው ጠ/ፍ/ቤት የሰጠው ትርጓሜ ትክክል አይደለም፡፡
2ኛ የጠ/ፍ/ቤቱ በይግባኝ ተመልክቶ በሰጠው ውሣኔ መሠረት የከ/ፍ/ቤት ሌሎች የመከራከሪያ ነጥቦች ሳይመረምር በደፈናው መዝገቡን መዝጋቱ አግባብ አይደለም የሚሉት ናቸው፡፡ በእነዚህም ነጥቦች ላይ የአሁን መልስ ሰጭ የበኩላቸውን ክርክር አቅርበዋል፡፡
እኛም ጉዳዩን ለክርክር አቀራረብና አመራር ሥርዓት ጋር አገናዝበን መርምረናል፡፡ እንደመረመርነውም የተሻሻለውን የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 58 በሚመለከት የጠቅላይ ፍ/ቤት በይግባኝ ሰሚነቱ ሥልጣን የሰጠው ውሣኔ ሰኔ 27 ቀን 1989 ዓ.ም. ሲሆን በዚህ ነጥብ ላይ ደግሞ ይኸው ቅሬታ ከሌላው የመከራከሪያ ነጥብ ጋር ተቀላቅሎ የቀረበው ደግሞ መጋቢት 19 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. እንደሆነ የሰበር መዝገቡ ያስረዳል፡፡
ይህንኑ የመከራከሪያ ነጥብ አስመልክቶ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠው የሕግ ትርጉም ስሀተት አለበት እንኳ ቢባል የሰበር አቤቱታ ማቅርቢያ ጊዜው ካለፈ በኋላ ከሌሎች ነጥቦች ጋር ተቀላቅሎ የቀረበ በመሆኑ በዚህ ደረጃ ሊታይ የሚችል የሰበር ቅሬታ ነጥብ ሆኖ አላገኘነውም፡፡
ሁለተኛውን ነጥብ በሚመለከት ግን ቀደም ሲል በዚህ የፍርድ ሐተታ እንደተጠቀሰው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በግብይት የተገኙ የግል ንብረቶች ናቸው ወይስ አይደሉም ከተባሉት ንብረቶች ውጭ ያለውን የጋራ ንብረት ክፍፍል በሚመለከት በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ ማስረጃዎችን ያገናዘበ ነው? ወይስ አይደለም? የጋራ ዕዳ ነው የተባለን ዕቁብ አስመልክቶ የቀረበው ክርክር በአግባቡ ታይቷል ወይስ አልታየም? የሚሉት ነጥቦች በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ምላሽ ሊሰጥባቸው የሚገቡ ጉዳዮች መሆናቸውን አምኖ በጭብጥነት ከያዛቸው በኋላ የእነዚህ ነጥቦች ምላሸ አስቀድሞ በተያዘው ጭብጥ ላይ የተመረኮዘ መሆኑን በመጥቀስ እንደገና በሥር ፍ/ቤት ሊታዩ የሚችሉ ናቸው በማለትመዝገቡን መመለሱን የእራሱ የውሣኔ ግልባጭ እያስረዳ፤ እንዲሁም የጠ/ፍ/ቤቱም ለሁሉም ጭብጦች መሠረት ሆኖ የተያዘው የግል ንብረቴ ተሸጦ የተገኙ ንብረቶች ናቸው የሚለው ክርክር በተገቢው ጊዜና ሥርዓት ያልቀረበ መሆኑን በማስገንዘብ በዚህ ረገድ የከፍተኛው ፍ/ቤት ውሣኔ ተሽሯል፡፡ ተከትሎት እንደነበረው አካሄድ በሌሎች በተያዙት ነጥቦች ላይ የመሰለውን ውሣኔ ይሰጥበት በማለት ለትርጉም በሚያሻማ ሁኔታ ወስኖ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 341/1/ መሠረት መመለሱ እየታወቀ የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. 32ዐ91 ታህሣሥ 24 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በዋለው ችሎት “ይህ ፍ/ቤት የፍቺ ውጤቱን ይግባኝ ለማጣራት ያስቀርባል ያለው ንብረት የግል ይባልልኝ የሚለውን ክርክር መነሻን ታሳቢ በማድረግ ነው፡፡ ይሁንና ይህ ጭብጥ ደግሞ በፌ/ጠ/ፍ/ቤቱ የመጨረሻ ውሣኔ ተሰጥቶበታል፡፡ በመሆኑም በፍቺ ውጤቱ የተሰጠው ውሣኔ የሚለወጥበትን ምክንያት አስቀርቶታል፡፡” በማለት መዝገቡን መዝጋቱ በበላይ ፍ/ቤቱ የተሰጠውን ውሣኔ ያልተከተለ ከመሆኑም በላይ ቀደም ሲል እራሱ በዚያው መዝገብ ሚያዝያ 2ዐ ቀን 1998 ዓ.ም. ከሰጠው ፍርድ ጋር የሚጣረስ በመሆኑ በክርክሩ አካሄድ የተከተሉት ሥርዓት ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም፡፡
ው ሣ ኔ
1. የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. 32ዐ91 ታህሣሥ 24 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሠረት ተሽሯል፡፡
2. የአሁን አመልካች የግል የነበሩ ንብረቶቼ ተለውጠው የተገኙ ሀብቶች በመሆናቸው እንደ ጋራ ሀብት ሊቆጠሩ አይገባም በማለት ከጠቀሳቸው ንብረቶች በስተቀር ሌላው የጋራ ንብረት ክፍፍል በሚመለከትና የጋራ ዕዳ ስለተባለው ጉዳይ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ በአግባቡ ስለመሆኑና አለመሆኑ በአሁን አመልካች የይግባኝ ቅሬታ መነሻነት ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ጉዳዩን መርምሮ የመሰለውን ውሣኔ ሊሰጥበት ይገባል በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 347/1/ መሠረት መዝገቡን መልሰናል፡፡
ሐምሌ 3ዐ ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡
ነ/ዓ
ግንቦት ዐ4/2ዐዐ1
ዳኞች፡- 1. አብዱልቃድር መሐመድ
2. ሐጎስ ወልዱ
3. ሒሩት መለሠ
4. በላቸው አንሺሶ
5. ሱልጣን አባተማም
አመልካች፡- የኢት/መንገዶች ባለሥልጣን - ነ/ፈጅ ጌታቸው አካሣ ቀረቡ፡፡ ተጠሪዎች፡- 1. ወ/ሮ ትዕግሥት ወንድይፍራው - ጠ/ላቀ ቀረቡ፡፡
2. አቶ ባህሩ አህመድ - በሌሉበት
ፍ ር ድ
በዚህ መዝገብ የተያዘው ጉዳይ ክስ በሚሠማበት ቀጠሮ የከሣሽ /የይግባኝ ባይ/ አለመቅረብ የሚያስከትለውን ውጤት የሚመለከት ነው፡፡
ጉዳዩ የተጀመረው በፌ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን አመልካች ከሣሽ ሲሆን ተጠራዎች ደግሞ ተከሣሾች ነበሩ፡፡ በክሱም የ1ኛ ተጠሪ ንብረት የሆነውን መኪና 2ኛ ተጠሪ ሲያሽከረክሩ በግልገል ግቤ ወንዝ ላይ የተሠራው ድልድይ ላይ ጉዳት በማድረሣቸው ተጠሪዎች በደሰረው ጉዳት ካሣ እንዲከፍሉ ጠይቋል ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን አከራክሮ የከሣሽን ክስ ውድቅ በማድረግ ወስኗል፡፡ በዚህ ውሣኔ ላይ አመልካች በፌ/ከፍተኛ ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታውን ያቀረበ ሲሆን የይግባኝ ቅሬታው መልስ ሰጪዎች ባሉበት የሚጣራ ነጥብ በማግኘቱ ይግባኙን ለመስማት ቀጠሮ ሠጥቷል፡፡
ይግባኙ በሚሠማበት ዕለትም አመልካች ባለመቅረቡና የ1ኛ ተጠሪ ጠበቃም መዝገቡ እንዲዘጋላቸው ስለጠየቁ ፍ/ቤት መዝገቡን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 መሠረት መዝገቡን ዘግቷል፡፡ አመልካች የተዘጋው መዝገብ እንዲፈቀድ አመልክቶ ፍ/ቤቱ በቂ ምክንያት አልቀረበም በሚል ጥያቄውን ሣይቀበለው ቀርቷል፡፡
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው፡፡ በቅሬታውም 1ኛ ተጠሪ የተከሠሠበትን ነገር ሣይክድ መዝገቡ እንዲዘጋ በመጠየቁ ብቻ መዝጋቱ ስህተት ነው ለ2ኛ ተጠሪ መጥሪያ መስጠት እንዳልተቻለ በፍ/ቤቱ ተገልፆ የክሣቸው ጥሪ ጉዳይ በእንጥልጥል ላይ እያለ ጉዳዩን ለመስማት የሚያስችል ሁኔታ ሣይኖርና 2ኛ ተጠሪ በምትክ መጥሪያ ሣይጠሩ መዝገቡ መዘጋቱ ስህተት ነው በቀጠሮው እለት ያልቀረብንበት በቂ ምክንያት እያለ መታለፉ ስህተት ነው በማለት የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ ተሽሮ መዝገቡ ተከፍቶ እንዲታይ አመልክቷል፡፡
ይህ ችሎትም መዝገቡ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 መሠረት የመዘጋቱን አግባብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችሎት ያስቀርባል በማለቱ ተጠሪዎች እንዲቀርቡ ታዘው 2ኛ ተጠሪ አልቀረቡም፡፡ 1ኛ ተጠሪ ቀርበው የግራ ቀኙ የቃል ክርክር ተሠምቷል፡፡ ከፍ ሲል የተገለፀው የግራ ቀኙ ክርክር ሲሆን ችሎቱም መዝገቡን እንደሚከተለው መርምሯል፡፡ በዚህ ጉዳይም ሊመለስ የሚገባው የይግባኝ ቅሬታው በሚሰማበት ቀን ይግባኝ ባይ /የአሁን አመልካች/ ያልቀረቡ ቢሆንም 1ኛ ተጠሪ የይግባኝ ቅሬታውን ክደው ሣይከራከሩ መዝገቡ መዘጋቱ በአግባቡ ነው አይደለም? የሚለው ነጥብ ነው፡፡
ስለ ባለጉዳዮች ፍ/ቤት መቅረብና ሣይቀርቡ መቅረት በሚናገረው ምዕራፍ ውስጥ የሚገኘው የፍ/ሥ/ሥ/ሕጉ ቁጥር 73 ባንድ ነገር ክስ ያቀረበ ሰው ክርክሩ እንዲሰማ በተወሰነው ቀነ ቀጠሮ ሣይቀርብ የቀረ እንደሆነ ተከሣሹ ቀርቦ የተከሠሠበትን ነገር በሙሉ ወይም በከፊል ያመነ እንዲሆነ ከሣሹ በሌለበትም ቢሆን ፍ/ቤቱ ተከሣሽ ላመነው ጉዳይ ውሣኔ መስጠት እንደሚችል ተከሳሹ የካደ እንደሆነ ግን መዝገቡን እንደሚዘጋውና ተከሣሹን እንደማያሠናብት ይደግጋል፡፡ በእርግጥ ይህ ድንጋጌ ከሣሽና ተከሣሽ እያለ የሚናገር ይሁን እንጂ የፍ/ሥ/ሥ/ሕጉ በይግባኝ የሚቀርቡትንም ክርክሮች አጠቃሎ ስለሚይዝ እንደነገሩ አግባብ ከሣሽ የሚለው ቃል ይግባኝ ባይን ተከሣሽ
የሚለው ደግሞ መ/ሰጪን የሚተካ መሆኑ በዚሁ ሕግ ቁጥር 32/2/ ሥር ተመልክቷል፡፡ በመሆኑም የይግባኝ ቅሬታው በሚሠማበት ቀነ ቀጠሮ ይግባኝ ባይ ካልቀረበ ተፈፃሚነት ያለው ይኸው የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 ነው፡፡ በዚህ የሥነ ሥርዓቱ ድንጋጌ ደግሞ ይግባኙ በሚሠማበት ቀነ ቀጠሮ ይግባኝ ባይ ያልቀረበ ከሆነ መ/ሰጪው ይግባኝ የቀረበበትን ነጥብ በከፊል ወይም በሙሉ ካመነ በእምነቱ መሠረት ፍ/ቤቱ ውሣኔ የሚሠጥ መሆኑን ነገር ግን ይግባኙን ክዶ የተከራከረ ከሆነ መዝገቡን መዝጋት እንዳለበት ተመልክቷል፡፡ በዚህም መሠረት የይግባኙ መዝገብ መዘጋት የሚወሰነው መ/ሰጪው ለቀረበበት የይግባኝ ቅሬታ ከሚሠጠው መልስ አኳያ ታይቶ ነው ማለት ነው፡፡ በመሆኑም መ/ሰጪ የቀረበውን የይግባኝ ቅሬታ መካድ ማመኑ ሣይረጋገጥ መዝገቡ እንዲዘጋ በመጠየቁ ብቻ መዝገቡ ሊዘጋ የሚችልበትን ሁኔታ ድንጌጋው አያመለክትም፡፡ በመሆኑም የይግባኝ ሠሚው ፍ/ቤት የ1ኛ መልስ ሰጪን መልስ ሣይመለከት መዝገቡን መዝጋቱ ስህተት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
በሌላ በኩል ከአመልካች አቤቱታ እንደተመለከትነው 2ኛ ተጠሪ በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት እንዲቀርብ የተላከላቸውን መጥሪያ መ/ሰጪውን አግኝቶ መስጠት አለመቻሉ ለፍ/ቤቱ ተገልፆለት 2ኛ ተጠሪ እንዲቀርቡ ምትክ መጥሪያ ሳይላክ በእንጥልጥል ላይ የነበረ መሆኑን ተረድተናል፡፡ ሁለተኛ ተጠሪም በዚህ ፍ/ቤት ተጠርተው ያልቀረቡ በመሆኑ በዚህ ነጥብ ላይ የቀረበ ማስተባበያ የለም፡፡ በመሆኑም 2ኛ ተጠሪ በምትክ መጥሪያ እንዲጠሩ ፍ/ቤት ትዕዛዝ ሣይሠጥ አመልካች ይግባኝ በሚሠማበት ቀን አልቀረበም በማለት በ2ኛ ተጠሪ ላይ የቀረበው ይግባኝም አብሮ መዘጋቱ አግባብ ሆኖ አላገኘነውም፡፡
በአጠቃላይ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 መሠረት መዝገቡ የሚዘጋው ይግባኝ ባዩ የይግባኝ ቅሬታውን ክዶ ከተከራከረ በመሆኑ የ1ኛ ይግባኝ ባይ መልስ ተጠይቆ ሳይረጋገጥ መዝገቡ መዘጋቱም ሆነ ለ2ኛ ተጠሪ መድረስ አለመቻሉ ተገልፆ በምትክ
መጥሪያ እንዲቀርብ ሣይታዘዝ መዝገቡ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 መሠረት መዘጋቱ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
ው ሣ ኔ
1. የፌ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 33199 ግንቦት 5/2ዐዐዐ ዓ.ም. እንዲሁም በዚህ መዝገብ ግንቦት 14/2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል፡፡
2. የተዘጋው መዝገብ ተከፍቶ ነገሩ እንዲቀጥል ብለናል፡፡
3. ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻሉ፡፡ መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ ለመዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡
ነ/ዓ
ሚያዝያ 2ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልዱ
ሂሩት መለሠ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም
አመልካቾች፡- 1. ጉታ በየራ ቀርቧል፡፡
2. ተገሽ ማሞ ተጠሪ፡- ዓቃቤ ሕግ አልቀረበም፡፡
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡
ፍ ር ድ
በዚህ መዝገብ ለቀረበው አቤቱታ መሠረት የሆነው ጉዳይ ዓቃቤ ሕግ በአመልካቾች ላይ ያቀረበውን የወንጀል ክስ የሚመለከት ነው፡፡ ዓቃቤ ሕግ በአመልካቾች ላይ ክስ የመሠረተው በ1996 ዓ.ም. በወጣው የወንጀል ሕግ በንቀጽ 523/1/ እና 433 የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በመተላለፍ የወንጀል ድርጊት ፈጽመዋል በማለት ነው፡፡ አመልካቾች በሰጡት መልስ ክሱን ክደው በመከራከራቸው ፍ/ቤቱ በዓቃቤ ሕግ በኩል የተቆጠሩትን ምስክሮች ከሰማ በኋላ፣ አመልካቾች ክሱን ሊከለከሉ ይገባል በማለት ብይን በመስጠቱ አመልካቾች የመከላከያ ምስክሮቻቸውን አሰምተዋል፡፡ በጨረሻም ፍ/ቤቱ አመልካቾች በተጠቀሱባቸው ሁለቱ አንቀጾች ጥፋተኞች ናቸው ብሎአል፡፡ በዚህ መሠረትም አመልካቾች በአራት ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኖአል፡፡ ይግባኝ የቀረበለት የአማራ ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤትም በሥር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ ጉድለት የለበትም በማለት ይግባኙን ሰርዞአል፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው፡፡
በበኩላችንም አመልካቾች ሐምሌ 7 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በፃፉት ማመልከቻ ያቀረቡትን አቤቱታ መሠረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል፡፡ አቤቱታው በሰበር ችሎት እንዲታይ የተወሰነው አመልካቾች ፈጸሙት የተባለው ድርጊት እና ምስክሮች ያሰሙት ቃል በተጠቀሱት ድንጋጌዎች የተዘረዘሩትን ነገሮች መፈጸማቸውን አያሳይም የሚለውን ቅሬታ ለማጣሪት ነው፡፡ በዚህ መሠረትም ይህንን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መርምረናል፡፡
ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ
ፀጋየ አስማማው አልማው ወሌ ዓሊ መሐመድ
አመልካች፡- አቶ ገብረሃና አባዲ - አልቀረቡም ተጠሪ፡- አቶ አረጋዊ ገ/ኪዳን - ቀረቡ
መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡
ፍ ር ድ
ይህ ጉዳይ የሥራ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ተጠሪ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ በግለሰቦች አገናኝነት የተከሳሽ ንብረት በሆነው የሠ.ቁ 3-8723 ኤኒትሬ መኪና ላይ በወር ብር 1500 ደመወዝ ተቀጥሬ ለመሥራት ከተከሳሽ ጋር በቃል ተስማምተን ጥር 22 ቀን 1999 ዓ.ም ኤፍ.ኤም በተባለ ጋራዥ የመኪናውን ቀኝ እግር ጐማ በማጥበቅ ላይ እንዳለሁ በድንገት መስቀለኛው የጐማ ማሰሪያ አዳልጦ ግራ ዓይኔን በመምታት ጉዳት አድርሶብኛል፡፡ በጉዳቱ ምክንያት ዳግማዊ ምንሊክ ሆስፒታል ሕክምና ስከታተል ቆይቼ ስወጣ ተከሳሽ የጉዳቱ ካሳ እንዲከፈለኝ ብጠይቅ ለመክፈል ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ጉዳቱ ሲደርስብኝ ዕድሜዬ 50 ዓመት የነበረ ሲሆን እስከ 60 ዓመት ድረስ በወር ብር 1500 አገኝ ነበር፡፡
ስለሆነም የ10 ዓመት ብር 90,000 ከወለድ ጋር ተከሳሽ እንዲከፍል ይወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል፡፡
ተከሳሹም በሰጡት መልስ በከሳሽ ላይ ጉዳት መድረሱን አምነው ነገር ግን በመካከላችን የተቋቋመ የሥራ ውል የሌለ ስለሆነ በክስ የተጠየቀውን ካሳ ለመክፈል አልገደድም በማለት ተከራክረዋል፡፡
የፌዴራል መ/ደ/ፍ/ቤትም ከሳሽ ከተከሳሽ ጋር የሥራ ውል መደረጉን ያውቁልኛል ያሏቸውን ምስክሮች ሰምቶ ምስክሮች ከሳሽና ተከሳሽን ማገናኘታቸውን ከመግለጽ በስተቀር ተከሳሽ ከሳሽን ስለመቅጠሩ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ የመሰከሩ በመሆኑ የከሳሽ ክስ የማስረጃ ድጋፍ የሌለው ነው በማለት ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡
ከሳሽ በዚሁ ውሳኔ ቅሬታ አድሮባቸው የይግባኝ ቅሬታ ለፌዴራል ከ/ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱም በበኩሉ ግራ ቀኙን አከራክሮ የሥራ ውል መኖሩን ለማስረዳት ይግባኝ ባይ በሥር ፍ/ቤት ያቀረቧቸው ምስክሮች ይግባኝ ባይና መ/ሰጭ በደመወዝ ጉዳይ ሲስማሙ አለማየታቸውን ወይንም አለማወቃቸውን ቢመሰክሩም ነገር ግን መ/ሰጭ ሹፌር ለመቅጠር ፍላጎት ስለነበራቸው ከይግባኝ ባይ ጋር ያገኛቸው መሆኑን መ/ሰጭም ሊገዙት የነበረው መኪና ጋራዥ ቆሞ እንዳለ ይ/ባይ ይህንኑ መኪና ሲፈትሽ ጉዳት እንዳደረሰበት የተረጋገጠ ስለሆነ ይህ ሁኔታ በደመወዝና በሥራ ሁኔታ ግራ ቀኙ ተስማምተው እንደነበር የሚያረጋግጥ በመሆኑ የሥር ፍ/ቤት የሥራ ውል የለም ያለው በአግባቡ አይደለም በማለት በመሻር በመካከላቸው የሥራ ውል ያለ ስለሆነ የተጠየቀው የጉዳት ካሳ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 111 እና 112 መሠረት በወር ብር 1500 ሂሳብ ተሳስቶ መ/ሰጭ በይ/ባይ ሊከፍሉ ይገባል በማለት ውሳኔ ሠጥቷል፡፡
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህም ችሎት አቤቱታውን መርምሮ በግራ ቀኙ መካከል የሥራ ውል ስለመኖሩ ለሰበር ቀርቦ ሊመረመር እንደሚገባው በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን አከራክሯል፡፡
በአጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከፍ ብሎ የተጠቀሰው ሲሆን የዚህን ችሎት ምላሽ ማግኘት ያለበት የጉዳዩ ጭብጥ በግራ ቀኙ መካከል በሕግ አግባብነት የተቋቋመ የሥራ ውል አለ? ወይንስ የለም? የሚለው ነው፡፡
አንድ ግዴታ ይፈጸምልኝ በማለት ጥያቄ የሚያቀርብ ወገን ግዴታው ስለመኖሩ ማስረዳት እንደሚጠበቅበት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2001(1) ላይ ተመልክቷል፡፡
በተያዘውም ጉዳይ ግዴታ ይፈጸምልኝ በማለት ጥያቄ ያቀረቡት የሥር ከሳሽ የአሁን ተጠሪ እንደመሆናቸው መጠን የግዴታውን መኖር ማስረዳት ይጠበቅባቸዋል ማለት ነው፡፡
በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ክርክር ሲደረግ የግዴታውን መኖር ማለትም በአመልካችና በተጠሪ መካከል የሥራ ውል የተቋቋመ መሆኑን ለማስረዳት ከሳሽ/አመልካች/ ምስክሮችን አቅርበው አሰምተዋል፡፡ የእነዚህ ምስክሮች አመሰካከር ሲታይም አመልካች ሹፌር ለመቅጠር ፍላጎት ስለነበራቸው ከተጠሪ ጋር ማገናኘታቸውን መስክረው ነገር ግን ደመወዝና ሌሎችንም የሥራ ሁኔታዎች በተመለከተ ሲዋዋሉ አለማየታቸውን መስክረዋል፡፡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በግራ ቀኙ መካከል የሥራ ውል ተቋቁሟል ወደሚል መደምደሚያ ሊደርስ የቻለው ምስክሮቹ ሁለቱን ወገኖች ማገናኘታቸው ከተረጋገጠና ተጠሪም አመልካች ለመግዛት ያሰቡትን መኪና ሲፈትሽ መገኘቱ በደመወዝና በሥራ ሁኔታ ላይ በመስማማት የሥራ ውሉ እንደተደረገ ስለሚያሳይ በመካከላቸው የሥራ ውል በማለት ነው፡፡
የሥራ ውል ይዘት ምን መምሰል እንዳለበት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 4 ሥር የተመለከተ ሲሆን ከነዚህም መካከል ማንኛውም የሥራ ውል የሥራውን ዓይነትና ቦታ፣ ለሥራው የሚከፈለውን የደመወዝ መጠን፣ የስሌቱን ዘዴ፣ የአከፋፈሉን ሁኔታና ጊዜ እና ውሉ ጸንቶ የሚቆይበትን ጊዜ መያዝ እንዳለበት በዚሁ አንቀጽ 4 በንዑስ
አንቀጽ /3/ ሥር ተመልክቷል፡፡
ነገር ግን የተጠሪ ምስክሮች ከፍ ብሎ እንደተጠቀሰው ተጠሪና አመልካችን ማገናኘታቸውን ከማስረዳት በስተቀር በሕጉ ላይ እንደተመለከተው ግራ ቀኙ ወገኖች በዝርዝር የሥራ ሁኔታዎች ላይ ስለመስማማታቸው አልመሰከሩም፡፡
የሥር ከሳሽ የአሁን ተጠሪ በሕግ አግባብነት የሥራ ውሉ የተቋቋመ መሆኑን ካላስረዱ ደግሞ የግዴታውን መኖር እንዳላስረዱ ስለሚቆጠር በዚህ ሁኔታ ያቀረቡት የጉዳት ካሳ ክፍያ ጥያቄ ተቀባይነት ያለው አይሆንም፡፡
ስለሆነም የፌዴራል መ/ደ/ፍ/ቤት በግራ ቀኙ መካከል የሥራ ውል ስለመኖሩ ከሳሽ አላስረዱም በማለት የሰጠው ውሳኔ አግባብነት ያለው ሆኖ ሳለ የፌዴራል ከ/ፍ/ቤት ይህንኑ ውሳኔ በመሻር በመካከላቸው የሥራ ውል አለ በማለት አመልካች ካሳ ሊከፍሉ ይገባል ሲል የሰጠው ውሳኔ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 4 ላይ የተመለከተውን ያላገናዘበና መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል፡፡
ው ሳ ኔ
1. የፌዴራል ከ/ፍ/ቤት በመ.ቁ. 67107 በ22/11/2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 348/4/ መሠረት ተሽሯል፡፡
2. የፌዴራል መ/ፍ/ቤት በመ.ቁ 26847 በ9/8/2000 ዓ.ም በአመልካችና በተጠሪ መካከል የሥራ ውል ስለመኖሩ ተጠሪ አላስረዱም በማለት የሰጠው ውሳኔ በአግባቡ ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 348/1/ መሠረት አጽንተነዋል፡፡
3. ግራ ቀኙ ወጭና ኪሳራ ይቻቻሉ፡፡
4. መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ራ/ታ
ሚያዝያ 20 ቀን 2001 ዓ.ም
ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ሐጐስ ወልዱ
ሂሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም
አመልካቾች፡- እነ ወ/ሮ ሐረገወይን ደነቀ (8ሰዎች) ጠበቃቻው አቶ ተማም አባቡልጉ ቀረቡ፡፡
ተጠሪዎች፡- 1. ባላምባራስ ባሹ ቀረቡ
2. xx xxx xx ቀረቡ
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡
ው ሳ ኔ
የአመልካቾች ጠበቃ መጋቢት 11 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ በ9/7/2001 ዓ.ም ለነበረው ቀጠሮ አመልካቾች አልቀረቡም በሚል መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ ነገር ግን በእለቱ ከሰዓት በነበረው ችሎት የአመልካቾች ጠበቃ ቀርቤ ችሎቱ እስኪያልቅ ድረስ ባለመጠራቴ አመልካች በፀሐፊዎች በኩል በጧቱ ቀጠሮ መዘጋቱን ለማወቅ ችያለሁ፡፡ ቀደም ሲልም ቀጠሮው ከሰዓት በኋላ ተብሎ ነው የተነገረን በመረጃም/touch screen/ ላይም ከሰአት በኋላ እንደሆነ ይገልፃል፡፡ ስለዚህ ይህ ግምት ውስጥ ገብቶ የተዘጋው መዝገብ ተከፍቶ ጉዳዩ እንዲቀጥል ሲል ጠይቋል፡፡
ይህ አቤቱታ ለተጠሪዎች ደርሶአቸው በሰጡት መልስ፡-በ9/7/2001 ዓ.ም በዋለው ችሎት መዝገቡ የተዘጋው ጠበቃው እንዳሉት በጧቱ ቀጠሮ ሳይሆን ከሰአት በኋላ ነው፡፡ በጧቱ ችሎት ቀርበን ክርክራችንን ካዳመጠ በኋላ በመዝገቡ ላይ ትእዛዝ ለመስጠት
ከሰአት በኋላ ተቀጥሮ ከ8፡30 ጀምሮ ባለጉዳይ ማረፊያ አዳራሽ ስንጠባበቅ ቆይተን ከቀኑ
10፡30 ሰአት በኋላ ተጠርተን ቀርበን ለ2ኛ ጊዜ አመልካቾች ባለመቅረባቸው መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ የአመልካቾች ጠበቃ እንዳሉት ጉዳዩን ከሰአት በኋላ እየተከታተሉ ቢሆን ኖሮ ስንጠራ ወደ ችሎቱ ይቀርቡ ነበር፡፡ እንዲያውም ከመጀመሪያ ጀምሮ ጉዳዩን በአግባቡ አልተከታተሉም ፍ/ቤቱ ያስቀርባል ብሎ ትእዛዝ የሰጠው የካቲት 24 ቀን 2001 ዓ.ም ነው፡፡ የቃል ክርክር ለመስማት የተቀጠረው ለመጋቢት 9 ቀን 2001 ዓ.ም ነው፡፡ እኛ ለቃል ክርክር መቀጠሩን የሰማነው ከፍ/ቤቱ መረጃ ክፍል ነው፡፡ አመልካቾች ሌላ ቀርቶ መጥሪያውንም አላወጡም፡፡ በመጥሪያው ላይ ቀጠሮው ጧት መሆኑ ተገልፆአል፡፡ ጠበቃው በእለቱ ቀርበው ቢሆን በእለቱ አቤቱታውን ያቀርቡ ነበር፤ አቤቱታው ይህ የሚያሳየው ፍ/ቤቱን እንዳልረገጡ ነው በማለት ለተጉላሉበት ወጪና ኪሳራ አስከፍሎ መዝገቡ እንዲዘጋ ተከራክረዋል፡፡
የአመልካቾች ጠበቃ በመልስ መልስ ክርክራቸው መዝገቡን ያስከፈቱት ደንበኞቼ ናቸው ክሱን መርቼ መጥተው አስከፍተው ሄዱ ያስቀርባል መባሉንም አላወቅንም በማለት በአቤቱታው የጠቀሱትን ነጥቦች በመድገም ተከራክረዋል፡፡
እኛም የግራ ቀኙን ክርክር ከዚህ በታች እንደተመለከተው መርምረናል፡፡
ለክርክሩ መነሻ የሆነው ጉዳይ በ29/5/2001 ዓ.ም ፋይል ተከፍቶ ለ24/6/2001 ዓ.ም ለምርመራ ቀጠሮ ተሰጥቶ በዚሁ ቀጠሮ ቀን ያስቀርባል ተብሎ መጥሪያ ለተጠሪዎች ደርሶአቸው መጋቢት 9 ቀን 2001 ዓ.ም ከጧቱ በ2፡30 ለቃል ክርክር ተዘጋጅተው እንዲቀርቡ ስለመታዘዙ መዝገቡ ያስረዳል፡፡ በዚህ ትእዛዝ መሰረት ፋይሉን አስከፈቱ የተባሉ አመልካቾችም ሆኑ ጠበቃቸው መጥሪያውን አልወሰዱም፡፡ ይህ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 70/መ/ አኳያ በአመልካቾች ወይም በጠበቃቸውም በኩል ግልጽ የሆነ ቸልተኛነት እንዳለባቸው የሚያመለክት ቢሆንም በእለቱ በችሎቱ የተገኙት ተጠሪዎች ክደው ተከራክረዋል፡፡ ከዚህ በኋላ በመዝገቡ ላይ ትእዛዝ ለመስጠት ከሰአት ብኋላ መቀጠሩን መዝገቡ ያስረዳል፡፡
ከመነሻው አመልካቾች ወይም ጠበቃቸው መጥሪያውን ከፍ/ቤቱ አውጥተው ባልወሰዱበት የቀጠሮው ቀን ጧት ይሁን ከሰአት በኋላ እንደሆነ እንዴት ሊያውቁት ቻሉ? የሚለው አጠራጣሪ ነው፡፡ እንዲያውም ያስቀርባል መባሉንም አላወቅኩም ቅሬታውን አዘጋጅቼ ለደንበኞቼ ሰጥቼ ነው መዝገቡን ያስከፈቱት ብለው እየተከራከሩ በሌላ በኩል ደግም ቀጠሮው ከሰዓት በኋላ ነው በማለት እርስ በርሱ የሚጋጭ ክርክር ማቅረባቸው አቤቱታቸውን ይበልጥ ተአማኒነት የሚያሳጣ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ የአመልካቾች ጠበቃ ጉዳያቸውን በዳተኝነት ትተውት አልተከታተሉም ወይንስ በቂ ሆኖ በሚገመት እክል ምክንያት ነው ያልቀረቡት የሚለውን ሲመረመር፡-
1. መጥሪያ አለመውሰዳቸው፣
2. እርግጠኛና ወጥነት ያለውን ምክንያት አለማቅረባቸው፣
3. ያስቀርባል መባሉንም አለማወቃቸው፣
4. ቀጠሮው ከሰዓት በኋላ ሆኖ መዝገቡ የተዘጋው በጧቱ ችሎት ነው ማለታቸውና እንዲሁም መዝገቡ የተዘጋው በጧቱ ችሎት ሳይሆን ከሰአት በኋላ በነበረው ችሎት በመሆኑ ይህ ሁሉ ተዳምሮ ሲታይ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 74/2/ መሰረት በቂ ሆኖ በሚገመት እክል ምክንያት ሳይሆን ገልጽ በሆነ ቸልተኛነት በመሆኑ የተዘጋው መዝገብ እንደገና ተከፍቶ ክርክሩ ሊቀጥል የሚችልበት የሕግ አግባብ የለም በማለት
ቤ/ኃ
መዝገቡን ዘግተናል፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት