ባለድርሻ አካላትን ማሳወቅ የናሙና ክፍሎች

ባለድርሻ አካላትን ማሳወቅ. የተነኩ ማህበረሰቦችና ሰፊው የባለድርሻዎች አካላት የቅሬታ አፈታት ስርዓትን ዝርዝሮች እንዲያውቁት መደረግ አለባቸው፡፡ • ይህ መረጃ በየትኛውም ፕሮጄክት የቆይታ ዘመን ውስጥ በስፋትና በመደበኛነት በዋና ዋና ቦታዎች (ለምሳሌ፡ ከከተማ አዳራሽ ውጭ) በሚለጠፉ ፖስተሮች፣ በሃገር ውስጥ ጋዜጦች/ራዲዮ በሚወጡ ማስታወቂያዎች እና በቃል (ለምሳሌ፡- በባለድርሻ አካላት የተሳትፎ ተግባራት ውስጥ) አማካይነት መታተም አለበት፡፡ • መረጃው የአካባቢው ሕዝብ ሊረዳው በሚችለው ቅርጸት እና ቋንቋ (የአካባቢውን ቋንቋዎች ጨምሮ) እና/ወይም ማንበብና መጻፍ የሚችለው ሕዝብ ቁጥር አነስተኛ በሆነባቸው አካባቢዎች ደግሞ በመደበኛ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወቅት በቃል መተላለፍ አለበት፡፡