ብቁ ያልሆኑ ቅሬታዎች የናሙና ክፍሎች

ብቁ ያልሆኑ ቅሬታዎች. ከ CFM ወይም ከኮንትራክተሮቹ ፕሮጄክቶች ጋር ግልጽ የሆነ ግንኙነት የሌላቸው፣ ጉዳያቸው ከዚህ የቅሬታ አፈታት ስርዓት ወሰን ውጭ የሆኑ ወይም ቅሬታውን ለመፍታት ሌሎች የ CFM ወይም የማሕበረሰብ አሰራሮች ይበልጥ አግባብነት ያላቸው የሆኑትን ሊያካትት ይችላል፡፡ ክስተት - ጉዳት፣ ሕመም፣ የሐብት መጥፋት ወይም በግንኙነቶች ወይም መልካም ስም ላይ ታሳቢ ወይም ተጨባጭ ጉዳት ያስከተለ ወይም ሊያስከትል ይችል የነበረ ክስተት ወይም የክስተቶች ትስስር፡፡ የሚመለከተው ወገን - በ CFM ወይም በስራዎቹ ባይነኩም በ CFM እና በስራዎቹ ላይ ጥቅም ወይም ተጽእኖ ያላቸው ግለሰቦች ወይም ቡድኖች፡፡ በእነዚህም ውስጥ የእርዳታ ድርጅቶች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የአካባቢ ንግድ ተቋማትና የፖለቲካ ቡድኖችን ሊያካትት ይችላል፡፡ መያድ - መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የተግባቦት/የምክክር መዛግብት - የተግባቦት/የምክክር መዛግብት ውስጥ ዋነኛ ኢሜሎች፣ ደብዳቤዎች፣ ዜና መዋዕሎች፣ የውስጥ መጻጻፊያዎች፣ ቅሬታዎች፣ የመሻሻል ዕድሎች፣ የስርጭት/የአቴንዳንስ መዛግብት፣ የመደበኛና የኢ-መደበኛ ስብሰባዎች መዛግብትና የቁርጠኝነቶች መዛግብት ሊካተቱ ይችላሉ፡፡ ባለ ድርሻ አካል - ፕሮጄክቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚነካቸውና በአንድ ፕሮጄክት ላይ ጥቅሞች እና/ወይም ውጤቱ ላይ አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተጽእኖ የማሳደር ችሎታ ሊኖራቸው የሚችሉ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች፡፡ እነዚህም ወገኖች ባለድርሻ አካላት፣ አበዳሪዎች፣ ሠራተኞች፣ ማህበረሰቦች፣ ኢንዱስትሪ፣ መንግስታት እና ዓለም አቀፍ ሶስተኛ ወገኖች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የባለ ድርሻ አካላት ተሳትፎ - በፕሮጄክቱ የቆይታ ዘመን ውስጥ ግልጽ፣ ተጠያቂ፣ አዎንታዊና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚፈጥሩ የስራ ግንኙነቶችን