ተመላሽ ፈንድ. ቀደም ሲሉ የነብሩ ተቋማትን እና/ወይም የንግድ እንቅስቃሴዎችን ለሚያሳትፉ እና በተመላሽ ፋይናንስ ፈንድ ፋይናንስ ለሚደረጉ ለምድብ ሀ እና ለ+ ኢንቨስትመንቶች የኢ እና ኤስ ኦዲቶች አፈጻጸም በኦፐሬሽን ሳይት(ቶች) ላይ ከፕሮጂከቱ ስጋት/ተፅእኖ ጋር ተዛማጅነት ባለው ድግምግሞሽ የሚከናወን ይሆናል። • ለዝቅተኛ ስጋት ያለባቸው ምድብ ኢንቨስትመንቶች፣ እየተከናወነ ያለው የኢ እና ኤስ ፕሮግራም አፈጻጸም በጥናት ላይ የተመረኮዘ ግምገማ ይደረግለታል፤ ሆኖም ግን ይህ ወደ ኦፐሬሽን ጣቢያ(ዎች) በሚደረጉ ጉብኝት(ቶች) ከጉዳይ ወደ ጉዳይ በመተላለፍ እንዲደገፍ ይደረጋል። • ከክውና ሳይቶች ጋር ግንኙነት ያላቸው ሁሉም ተመላሽ ፋይናንስ ተደራጊ ፈንድ ፕሮጄክቶች ለኮንስትራክሽን ድጎማ ፈንድ የተዘረዘሩትን ኪፒአይዎችን በመጠቀም ለ ሲኤፍኤም ቁጥጥር አድርገው አፈጻጸማቸውን ሪፖርት እንዲያደርጉ የሚጠየቁ ሲሆን ሪፖርት የሚደረገውም በየዓመቱ ይሆናል (ክፍል 7 (i) ይመልከቱ እና በተጨማሪ በ CO2 ልቀት እና አወጋገድ ላይ ሪፖርት ያደርጋሉ። • ሁሉም ተመላሽ ፋይናንስ ተደራጊ ፕሮጄክት ኩባንያዎች በተጨማሪ ቀጣይነት ባለው መልኩ የማናቸውንም በፕሮጄክት ክወና ቦታ (ሳይት) የተቀጠሩ ሥራ ተቋራጮችን የሥራ አፈጻጸም ይቆጣጠራሉ እንዲሁም ይገመግማሉ። እንደዚህ የመሳሰሉት እንቅስቃሴዎች ወደ ሲኤፍኤም ሪፖርት ይደረጋሉ። • በፈንዱ የሕይወት ዘመን ላይ አጠቃላዩን የ ኢ እና ኤስ አፈጻጸም ለመገምገም ሁሉም ተመላሽ ፋይናንስ ተደራጊ ፕሮጄክት ኩባንያዎች በተወሰነ ጊዜ ልዩነት በ ሲኤፍኤም በሚዘጋጀው የአስተዳደር ግምገማ ላይ እንዲሳተፉ ይጠየቃሉ። አካባቢያዊ እና ማኅበራዊ አፈጻጸም ሪፖርት አደራረግ ሲኤፍኤም ለጋሾች/ኢንቬስተሮች ኃላፊነት በሚወስድ አስተዳደር ላይ ስለ ኢ እና ኤስ ስጋቶች እና ችግሮች የሚሰጡትን ክብደት አስፈላጊነት ዕውቅና ይሰጣል። ከ ኢ እና ኤስ አፈጻጸም ጋር በተገናኘ የሚከተሉት ሪፖርት አደራረግ ደረጃዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ፦ • ሲኤፍኤም ኢ እና ኤስ ሪፖርት አደራረግ፤ • የፕሮጄክት ደረጃ ኢ እና ኤስ ሪፖርት አደራረግ፤ እና • የገጠመኞች/አደጋዎች ሪፖርት አደራረግ። የሪፖርት የሚደረገው ነገር ይዘት እና ድግምግሞሽ በሦስት የተለያዩ ፈንዶች ላይ ለፕሮጄክቶች የተለያየ ይሆናል። ይህ ክፍል በኃላፊነት የተሞላ ኢንቬስትመንት ኮድ (ክፍል 2) በዝርዝር የተቀመጡትን የሪፖርት አደራረግ መስፈርቶች መሠረት መነበብ አለበት።