አስፈላጊነት የናሙና ክፍሎች

አስፈላጊነት. ⇒ ተሞክሮው በተገኘበት ተቋም ወይም የስራ ክፍል ተወስኖ እንዳይቀርና ለሌሎችም በሚጠቅም መልኩ በሌላ ቦታ ወይም ተቋም በተመሳሳይ ወይም በተሻለ ሁኔታ ተተግብሮ አመርቂ ውጤት ለማስገኘት እንዲቻል፣ ⇒ ተቋማትም ሆኑ ግለሰቦች ራሳቸውም ሆነ ሌሎች ያለፉባቸውን መሠናክሎች ላለመድገም፣ አሠራሮችን ይበልጥ ለማሻሻልና ለመለወጥ እንዲቻል፣ ⇒ በግብርና ኢንቨስትመንት እና በግብርና ውል (Contract Farming) ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎችን አሰራራቸውን መሰረት በማድረግ ለማወዳዳርና የተሻለ አፈጻጸም ያላቸውን በመለየት በቀጣይ ምርጥ ተሞክሯቸውን ለመቀመር የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፍጠር በማስፈለጉ፤ ⇒ በዘርፉ ተሰማርተው በሂደት የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡትን በመሸለምና በማበረታታት እንዲሁም በቀጣይ ሌሎችን የማነሳሳት አቅም በመፍጠር ዘርፉ ለኢኮኖሚውና ማህበራዊ ዕድገት የሚያበረክተውን ድርሻ ማሳደግ በማስፈለጉ፣ ⇒ ሌሎች አካላት ምርጥ ተሞክሮው ወደ ተቀመረበት ቦታ በአካል መሄድ ባይችሉ እንኳን የተቀመረውን ሰነድ በመጠቀም ብቻ ወደ ተግባር የሚገቡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እንዲቻል ግልጽና ገላጭ የሆነ ምርጥ ተሞክሮ ተደራሽ ለማድረግ ነው።