በግብርና ኢንቨስትመንትና በግብርና ምርት ውል (Contract Farming) የተሰማሩ ኩባንያዎች የምርጥ ተሞክሮ (Bench Mark) መቀመሪያ የአሰራር ሰነድ
የግብርና ኢንቨስትመንትና ግብዓት ዘርፍ
የግብርና ኢንቨስትመንትና ምርት ግብይት መሪ ስራ አስፈጻሚ
በግብርና ኢንቨስትመንትና በግብርና ምርት ውል (Contract Farming) የተሰማሩ ኩባንያዎች የምርጥ ተሞክሮ (Bench Mark) መቀመሪያ የአሰራር ሰነድ
ከማምረት በላይ | Beyond Production
2015 ዓ.ም.
ምስጋና
በጀርመን የልማት ትብብር ድርጅትና በግብርና ሚኒስቴር በጋራ የሚተገበረው ኃላፊነት የተሞላበት የግብርና ኢንቨስትመንት አስተዳደር ፕሮጀክት (GIZ-Responsible Governance of Investment in Land) የዚህን የምርጥ ተሞክሮ መቀመሪያ የአሰራር ሰነድ የህትመት ወጪ በመሸፈን ስላደረገልን ድጋፍ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡
የግብርና ኢንቨስትመንትና ግብዓት ዘርፍ
የግብርና ኢንቨስትመንትና ምርት ግብይት መሪ ስራ አስፈጻሚ
ማውጫ
ርዕስ ገጽ
1. መግቢያ 1
2. የምርጥ ተሞክሮ/ልምድ ትርጉም 2
3. የምርጥ ተሞክሮ ቅመራ ምንነት 2
4. አስፈላጊነት 3
5. ዓላማ 4
6. የምርጥ ተሞክሮ (ልምድ) መገለጫ ባህርያት 4
7. የምርጥ ተሞክሮ ቅመራ አቀራረብ 5
8. የምርጥ ተሞክሮ/ልምድ ቅመራ ስልትና የሚከናወኑ ተግባራት 5
9. የምዘና መስፈርቶች 6
9.1 ክፍል አንድ የእንስሳትና ዓሳ ኢንቨስትመንት 6
9.2 ክፍል ሁለት የግብርና ምርት ውል (Contract Farming) 13
9.3 ክፍል ሶስት የሆርቲካልቸር ልማት 24
9.4 ክፍል አራት የሰፋፊ እርሻ ኢንቨስትመንት 29
10. የሚወሰዱ እርምጃዎች 38
11. የአፈጻጸም አቅጣጫ 40
12. ማጠቃለያ 40
1. መግቢያ
ለስኬት የበቁ ተቋማት ለስኬታቸው መነሻ የሆኑትን አፈፃፀሞች በዝርዝር ለቅሞ ወደ ራስ በመውሰድ ከራስ ነባራዊ ሁኔታ ጋር አጣጥሞ ተግባራዊ ማድረግ ከራስ ከሚገኘው ልምድና ተሞክሮ ባሻገር ያሉ ተሞክሮዎችን በማቀናጀት ስኬታማ ከሆኑ ተቋማት የተሻለ ውጤት ማምጣት የሚቻል መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ከሌላ የሚገኝን የተሻለና የተለየ ውጤታማ አፈፃፀምን በመቀመር ሌሎች እንዲጠቀሙ በማድረግ ውጤታማ ከሆኑበት የበለጠ ውጤትና ስኬትን ለማምጣት የሚያስችል መንገድ ነው፡፡
በዚህም መሰረት በግብርና ኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎች ማለትም በእንስሳትና ዓሣ፣ በሆርቲካልቸር፣ በሰፋፊ እርሻ ኢንቨስትመንት እና በግብርና ውል (Contract Farm- ing) የተሰማሩ ኩባንያዎችን ስኬታማ የሆኑበትን አዳዲስ የአሰራር ዘዴዎችንና ቴክኖሎጅዎችን ሌሎች ኩባንያዎች ተጠቅመው ውጤታማ ለመሆን የሚያስችል ምርጥ ተሞክሮ በመቀመር በዘርፉ ለተሰማሩ ተሞክሮውን ተደራሽ በማድረግ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ያስችላል፡፡
በመሆኑም ውጤታማ የሆኑ ኩባንያዎችን አሠራር በመረጃ በመደገፍ፣ በመለየትና በመቀመር በሰነድ መልክ ተዘጋጀቶ ለሌሎች በማሰራጨት ለምርትና ምርታማነት እድገት ላቅ ያለ አስተዋ ጽኦ እንዲያበረክት የማድረግ ስራ በሚፈለገው መልኩ ስላልተሰራ ውጤታማ የሆኑ ኩባንያዎች በተሰማሩባቸው የስራ መስኮች በመስክ በመገኘት መረጃዎችን በማሰባሰብ፣ በመለየት፣ ያላቸ ውን ምርጥ ተሞክሮ በመቀመር ለሌሎች ተደራሽ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
ስለሆነም በግብርና ኢንቨስትመንትና በግብርና ምርት ውል ዘርፍ ተሰማርተው ውጤታማነትንና ቀጣይነትን ለማረጋገጥ በቢዝነስ ፕላንና በገቡት ውል መሰረት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ጥሩ አፈጻጸም ያስመዘገቡ እና ለሀገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ ድርሻ ያበረከቱ ድርጅቶችን ለስኬት ያበቋቸውን ተግባራትና ሂደቶችን በዝርዝር በመልቀም ተመሳሳይ ሥራ ላይ ለተሰማሩ ሌሎች ኩባንያዎች ከራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ተግባራዊ እንዲያደርጉት በማድረግ
ኢንቨስትመንቱ የታለመለትን ዓላማ በማሳካት ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ ሚና ስላለው ምርጥ ልምድ መቀመር ራሱን የቻለ አሰራርና ግንዛቤ የሚጠይቅ ስለሆነ ምርጥ ተሞክሮን ለመቀመር የሚያስችል ማብራሪያ የያዘ የአሰራር ስርዓት አስፈላጊ በመሆኑ ይህ የምርጥ ተሞክሮ የቅመራ ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡
2. የምርጥ ተሞክሮ/ልምድ ትርጉም
አንድ ተቋም/ድርጅት ያለውን የሥራ አፈፃፀም ከሌሎች ተቋማት ከወጪ፤ ከጥራትና ከቅልጥፍና አንጻር ያላቸውን ልምድና የላቀ አፈጻጸም በማነጻጸር ወደ ተሻለ ውጤት መድረስን የሚያረጋግጥ፤ በአነስተኛ ወጪና ጥረት የላቀ ውጤት የሚመጣበት፣ ችግሮችን ለመፍታትና ስኬትን ለማምጣት ጥቅም ላይ የሚውል፤ ተከስተው የነበሩ ስህተቶች እንዳይደገሙ ማድረግ የሚቻልበትም ስልት/ሥነ-ዘዴ ነው፡፡
በአጠቃላይ በአንድ ተቋም ያለ የላቀ ልምድና ውጤት (በአሰራሩ፤ በአደረጃጀቱ፤ ወዘተ) ተመሳሳይ በሆኑ ተቋማት በመውሰድ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር አጣጥሞ በመጠቀም ከፍተኛ ስኬት ማምጣት የሚያስችል ልምድ ነዉ፡፡
3. የምርጥ ተሞክሮ ቅመራ ምንነት
አንድን ምርጥ ተሞክሮ መቀመር ሲባል የተገኘውን ውጤትና ውጤቱን በማስገኘት ረገድ አስተዋጽዖ የነበራቸውን የአደረጃጀት፣ የአሰራርና የአመራር፤ የአመለካከትና የክህሎት፤ የግብዓት አቅርቦትና አጠቃቀም፣ የማነቆዎች አፈታት ዘዴንና የተገኘውን አጠቃላይ ትምህርት ማደራጀት ማለት ነው፡፡
ከተለየ አንድ የላቀ የዕቅድ ክንውን ውጤት በመነሳት የተሞክሮው ባለቤት የሆነው ተቋም ከዝግጅት ምዕራፍ አንስቶ አመርቂ ውጤት እስከተገኘበት ድረስ የተጠቀመባቸውን አደረጃጀት፣
አሰራርና አመራር እንዲሁም ያጋጠሙትን የአመለካከት፣ የክህሎት እና የግብዓት አቅርቦትና አጠቃቀም ማነቆዎች በመፍታት የተጠቀመበትን ስልት ለሌሎች በሚጠቅም መልኩ አደራጅቶ በማስፋት ለትግበራ ማዘጋጀት ነው፡፡
4. አስፈላጊነት
⇒ ተሞክሮው በተገኘበት ተቋም ወይም የስራ ክፍል ተወስኖ እንዳይቀርና ለሌሎችም በሚጠቅም መልኩ በሌላ ቦታ ወይም ተቋም በተመሳሳይ ወይም በተሻለ ሁኔታ ተተግብሮ አመርቂ ውጤት ለማስገኘት እንዲቻል፣
⇒ ተቋማትም ሆኑ ግለሰቦች ራሳቸውም ሆነ ሌሎች ያለፉባቸውን መሠናክሎች ላለመድገም፣ አሠራሮችን ይበልጥ ለማሻሻልና ለመለወጥ እንዲቻል፣
⇒ በግብርና ኢንቨስትመንት እና በግብርና ውል (Contract Farming) ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎችን አሰራራቸውን መሰረት በማድረግ ለማወዳዳርና የተሻለ አፈጻጸም ያላቸውን በመለየት በቀጣይ ምርጥ ተሞክሯቸውን ለመቀመር የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፍጠር በማስፈለጉ፤
⇒ በዘርፉ ተሰማርተው በሂደት የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡትን በመሸለምና በማበረታታት እንዲሁም በቀጣይ ሌሎችን የማነሳሳት አቅም በመፍጠር ዘርፉ ለኢኮኖሚውና ማህበራዊ ዕድገት የሚያበረክተውን ድርሻ ማሳደግ በማስፈለጉ፣
⇒ ሌሎች አካላት ምርጥ ተሞክሮው ወደ ተቀመረበት ቦታ በአካል መሄድ ባይችሉ እንኳን የተቀመረውን ሰነድ በመጠቀም ብቻ ወደ ተግባር የሚገቡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እንዲቻል ግልጽና ገላጭ የሆነ ምርጥ ተሞክሮ ተደራሽ ለማድረግ ነው።
5. ዓላማ
በግብርና ኢንቨስትመንት እና በግብርና ምርት ውል (Contract Farming) ዘርፍ የተሰማሩና የተሻለ አፈጻጸም ያላቸውን ኩባንያዎችን በመለየትና በማወዳደር፣ ምርጥ ልምዳቸውን በአግባቡ በመቀመርና ለሌሎች ተጠቃሚዎች እንዲደርስ በማድርግ ምርትና ምርታማነትን በመጨመር ዘርፉ ለሀገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ፋይዳው ጎልቶ እንዲወጣ ማድረግ ነው፡፡
6. የምርጥ ተሞክሮ (ልምድ) መገለጫ ባህርያት
ምርጥ ተሞክሮ የራሱ የሆነ መገለጫ ባህሪያት ያሉት ሲሆን ዋና ዋናዎቹ፡-
⇒ የስኬት ሚስጥር ነው /የሥራ ሂደት (Process) ላይ ያተኮረ ነው፡፡
⇒ ሁሉን አቀፍ (Universality) ተቀባይነት ያለው መሆኑ፤ በአንድ ቦታ ብቻ ታጥረው የሚቀሩ ሳይሆኑ ወደ ሌሎች በሰፊው ሊስፋፋ የሚችሉ (Have the potential for rep- lication) መሆናቸው፣
⇒ ከንድፈ ሀሳብ (Bussiness plan) ጀምሮ በተግባር ተፈትሸው ውጤታማ መሆናቸው የተረጋገጠላቸው፣
⇒ መሠረታዊና ሥር-ነቀል ለውጥ ያመጡ መሆኑ፣
⇒ ዘለቄታዊ ውጤት ያመጡ (have a sustainable and irreversible effect)፣
⇒ በአቅማችን/በቀላሉ ልንተገብረው የምንችለው (Affordable) እና የሚለካ መሆኑ፣
7. የምርጥ ተሞክሮ ቅመራ አቀራረብ
ምርጥ ተሞክሮ/ልምድ ተቀምሮ የሚቀርብባቸው በርካታ መንገዶች በኖሩም፤ በዋነኛነት ሁለት ዓይነት መንገዶች በሰፊው ይተገበራሉ። እነዚህም፡-
1. በትረካ (Case Study)፡- አንድን ወሳኝ ውጤት የተገኝበትን ዝርዝር ሁኔታ ቅደም ተከተሉን በጠበቀ መልኩ በትረካ መንገድ በማስቀመጥ ተሞክሮውን ለሌሎች የምናካፍልበት አቀራረብ ነው።
2. በሥዕል (በፎቶ ግራፍ እና በቪዲዮና ድምፅ)፡- አንድን ወሳኝ ውጤት የተገኝበትን ዝርዝር ሁኔታ ቅደም ተከተሉን በጠበቀ መልኩ በፎቶገራፍና በምስል ቀረጻ በማስደገፍ ተሞክሮውን ለሌሎች የምናካፍልበት አቀራረብ ነው።
ምርጥ ተሞክሮ/ልምድ አንድ ወሳኝ ውጤት የተገኘበትን ሁኔታ በትረካ መንገድ በቅደም ተከተል አስቀምጦ ሌሎች ምርጥ ልምዱን ወስደው ተግባራዊ ለሚያደርጉ በፎቶግራፍና በቪዲዮ አስደግፎ ማቅረቡ የበለጠ ለመረዳት አመቺ ሊሆን ስለሚችል ሁለቱንም አዋህዶ መጠቀሙ የተሻለ ይሆናል፡፡
8. የምርጥ ተሞክሮ/ልምድ ቅመራ ስልትና የሚከናወኑ ተግባራት የምርጥ ተሞክሮ ቅመራ ሲካሄድ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦችን ያካተተ አካሄድ መከተል ውጤታማ ያደርጋል፡-
⇒ ዘርፉን በሚደግፈው ክፍል አስተባባሪነት በግብርና ሚኒስቴር ስር ከሚገኙ የስራ ክፍሎችና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የተውጣጣ የባለሙያዎች ቡድን ማዋቀር፤
⇒ በየደረጀው ምርጥ ልምዶችን አስመልክቶ የተዘጋጁ (የተቀመሩ) ሰነዶችን መመልከት እና
የምርጥ ተሞክሮ ልምድ አዘገጃጀት የድርጊት መርሃ-ግብር ማዘጋጀት፤
⇒ ከክልል፣ ከዞንና ከወረዳ ከዘርፉ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ካላቸው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር በመሆን ስለ ስራው አላማና አፈፃፀም በመወያየት የጋራ ማድረግ፡፡
⇒ ለምርጥ ተሞክሮ ቅመራ የተለዩ ኩባንያዎች ጋር በመወያየት በሚሰሩ ስራዎች ላይ መግባባት መፍጠር፣
⇒ የምርጥ ተሞክሮ ቅመራ ለማካሄድ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች ሟሟላት፣
⇒ ምርጥ ልምድ የሚገኝባቸውን ኩባንያዎች፣ ሰራተኞች እና የኩባንያዎች ወኪሎችን በማነጋገር ውጤቱ የተገኘበትን ዝርዝር ሂደት መረጃ ለማሰባሰብ የሚያስችል ቸክ- ሊስቶችን ማዘጋጀትና ማፀደቅ እንድሁም የሚሰበሰቡ መረጃዎችን በቸክ-ሊስቱ በዝርዝር ማስቀመጥ፤
9. የምዘና መስፈርቶች
በግብርና ኢንቨስትመንትና በግብርና ምርት ውል (Contract Farming) ተሰማርተው የተሻለ አፈፃጸም ያላቸውን ኩባንያዎች ከተቋሙና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ከተውጣጡ ባለሙያዎች ጋር በቅንጅት የሚለይ ሆኖ የመመልመያው መስፈርቱም በተወሰነ መልኩ እንደየዘርፉ ልዩነት ይኖረዋል፡፡ ዝርዝር የመመልመያ መስፈርቱም የሚከተሉትን መሰረታዊ ነጥቦችን ያካተተ ይሆናል፡፡ እያንዳንዱ መመዘኛ የሚይዘው የነጥብ ክብደት ለሀገር ከሚያበረክቱት ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና አካባቢያዊ ፋይዳ አንጻር የሚታይ ይሆናል፡፡
9.1 ክፍል አንድ የእንስሳትና ዓሳ ኢንቨስትመንት
የእንስሳትና ዓሳ ኢንቨስትመንት ማለት “የኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥርን 1180/2012 መስፈርት
አሟልቶ በአገር ውስጥ ባለሀብት( Domestic Investor )፣ በውጭ ባለሀብት (Foreign In- vestor) ወይንም በአገር ውስጥና በውጭ ባለሀብት ጥምረት (Jointvencher) በወተት ከብት እርባታና ወተት ምርት፣ በዳልጋ ከብት ማድለብ፣ በእንቁላልና የስጋ ዶሮ እርባታ፣ በበግና ፍየል እርባታ/ማድለብ፣ በዓሳ እርባታ፣ በዘመናዊ ንብ ማነብ፣ በእንስሳት መኖ ማምርትና ማቀነባበር እንዲሁም በሌሎች ንዑስ ዘርፎች የሚደረግ የኢንቨስትመንት መስክ ሲሆን በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶችን ምርጥ ተሞክሮ ለመቀመር/ለማወዳደር የሚያስችል የሚከተሉትን የምዘና (የመመልመያ) መስፈርቶችና ነጥቦች የያዘ ይሆናል፡፡
i. ለግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች (Agro-processing plants) የቀረበ ምርት መጠን /የውጭ ምንዛሬ ግኝት መጠን (30%)
በእንስሳት ኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎች በገቡት ውል መሰረት ኤክስፖርት ለማድረግ ካቀዱት የምርት መጠን ውስጥ ኤክስፖርት የተደረገውን መቶኛ በመውሰድ ነጥቡ የሚሰላ ይሆናል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ድርጀቱ ለግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች ምርቱን የሚያቀርብ ከሆነ ወይንም ያመረተውን ምርት እሴት ጨምሮ በሀገር ውስጥ ጥቅም ላይ የሚያውለውን ድርሻ ከግምት ውስጥ የሚገባ ይሆናል፡፡
በዚሁ መሰረት፡-
⇒ በእቅዱ መሰረት ምርቱን ኤክስፖርት ያደረገ/እሴት ጨምሮ በአገር ውስጥ ጥቅም ላይ ማዋል ከቻለ ወይንም ምርቱን ለግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች ያቀረበ ከሆነ (30 ነጥብ)
⇒ ኤክስፖርት ለማድረግ/ እሴት ጨምሮ በአገር ውስጥ ጥቅም ላይ ለማዋል/ለግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች በግብዓትነት እንዲውል ለማቅረብ ካቀደው ከ80% - 90% ያከናወነ ከሆነ (25 ነጥብ)
⇒ ኤክስፖርት ለማድረግ/ እሴት ጨምሮ በአገር ውስጥ ጥቅም ላይ ለማዋል/ለግብርና ምርት
ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች በግብዓትነት እንዲውል ለማቅረብ ካቀደው ከ60% - 79% ያከናወነ ከሆነ (15 ነጥብ)
⇒ ኤክስፖርት ለማድረግ/ እሴት ጨምሮ በአገር ውስጥ ጥቅም ላይ ለማዋል/ለግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች በግብዓትነት እንዲውል ለማቅረብ ካቀደው መጠን ከ 40% - 59 % ያከናወነ ከሆነ (10 ነጥብ)
⇒ ኤክስፖርት ለማድረግ/ እሴት ጨምሮ በአገር ውስጥ ጥቅም ላይ ለማዋል/ለግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች በግብዓትነት እንዲውል ለማቅረብ ካቀደው መጠን 39% እና ከዚያ በታች ያስመዘገበ ከሆነ (7 ነጥብ)
⇒ ምንም ካላከናወነ (0 ነጥብ)
ii. የቴክኖሎጅና የእውቀት ሽግግር (15%)
በአገር ውስጥ ያልተለመዱና በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ተፈላጊ ሆነው ኢትዮጵያ ያስቀመጠችውን የአሰራር ሂደት ተከትሎ ቴክኖሎጂን የሚጠቀም፣ ሌሎች ኩባንያዎችን ወይንም አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ማድረግ መቻል፣ አዳዲስ አሰራሮችና ዕውቀቶች እየተለመዱ እንዲመጡ የሚያደርግ አሰራር ሲሆን፡፡ ነጥብ አሰጣጡም እንደሚከተለው ተተንትኗል፡-
⇒ በእንስሳት ኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማራና ከላይ በተጠቀሰው መልኩ መጠቀም የቻለ፣ ተሞክሮውን ለሌሎች ኩባንያዎች፣ ለአካባቢው አርሶ አደሮች በተለይም በተመሳሳይ የስራ ዘርፍ በማህበር ለተደራጁ ሴቶችና ወጣቶች የተለያዩ ድጋፎችን ማለትም ተስማሚ ቴክኖሎጂዎችን /ለአካባቢው አዲስ የሆኑና በአለም አቀፍ ደረጃ ተፈላጊ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችንና አሰራሮችን እንዲሁም ወቅታዊና ተጨባጭ ሥልጠናዎችን መስጠትና የመሳሰሉትን ድጋፎች በተሟላ መልኩ የሚያጋራ ከሆነ (15 ነጥብ)
✓ በከፊል የሚያጋራ ከሆነ (8 ነጥብ)
✓ በትንሹ የሚያሟላ ከሆነ (4 ነጥብ)
✓ ምንም የማያጋራ ከሆነ ደግሞ (0 ነጥብ)
iii. የሥራ ዕድል ፈጠራ (10%)
በእንስሳት ኢንቨስትመንትና ዓሳ ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎች አካባቢያዊና ማህበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አኳያ በቢዝነስ ፕላናቸው መሰረት ለክልሉና ለአጎራባች አካባቢዎች በቋሚነትና በጊዜያዊነት የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩ የሚጠበቅ ነው፡፡ በዚህ መመዘኛ ውስጥ እንደ አንድ መስፈርት መጠቀሙ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ሆኖም በተለያየ ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎች የሚፈጥሩት የሥራ ዕድል እንደየ ዘርፉ ነባራዊ ሁኔታ የሚለያይ እንደሚሆን ከግምት ውስጥ መግባት ይኖርበታል፡፡ ነጥብ አሰጣጡም እንደሚከተለው ይሆናል፡-
⇒ በእንስሳት ዓሣ ኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማራ ኩባንያ በቢዝነስ ፕላኑ መሰረት የፈጠረው ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ከ95% - 100% ከሆነ (10 ነጥብ)
⇒ በዕቅዱ ከተያዘው ከ80% - 94% የሥራ ዕድል የፈጠረ ከሆነ (8 ነጥብ)
⇒ በዕቅዱ ከተያዘው ከ60% - 79% የሥራ ዕድል የፈጠረ ከሆነ (6 ነጥብ)
⇒ የዕቅዱን ከ40% - 59% የሥራ ዕድል የፈጠር ከሆነ (4 ነጥብ)
⇒ ከእቅዱ 40% በታች የሥራ እድል የፈጠረ ከሆነ (2 ነጥብ)
⇒ ምንም የስራ እድል ካልፈጠረ ( 0 ነጥብ)
iv. የድርጅቱ ውስጣዊ የመሰረተ-ልማት አደረጃጀት (15%)
በዘርፉ የተሰማራ ኩባንያ በተቋሙ ውስጥ ለስራው አጋዥ የሆኑ መሰረተ-ልማት ከማሟላት አንጻርና ለሰራተኛው የሚያቀርበውን አገልግሎት ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚመዘን ይሆናል፡፡ በዚህም መሰረት፡-
⇒ ደረጃውን የጠበቀ ጽ/ቤት፣ የግብዓትና የምርት ማከማቻ መጋዘን እና የሽያጭ ማዕከላትን ያሟላ፤
⇒ እንደ ኢንቨስትመንቱ አይነት አግባብነት ያላቸው ማሽነሪዎች ማሟላት የቻለ፤
⇒ እንደ ኢንቨስትመንቱ አይነት የሰለጠነ ባለሙያ ቀጥሮ የሚያሰራ ከሆነ፤
⇒ ለሰራተኛ ምቹ የሆኑ መሰረተ ልማት (መኖሪያ ቤት፣ ሽንት ቤት፣ ሻወር ቤት፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ፣ የስራ አልባሳት፣ ህክምና መስጫ፣ መመገቢያና ማብሰያ ቦታ፣ የማሽነሪ/ትራንፖርት መጠለያ ወዘተ) ማሟላት የቻለ፣
⇒ ለሰራተኛ ድንገተኛ አደጋ መጠበቂያ ቁሳቁሶች ያሟላ ወዘተ የሚሉት መሰረታዊ የመገምገሚያ ነጥቦች ናቸው፡፡
በዚሁ መሰረት አቅርቦቱ፡-
→ የተሟላ ከሆነ (15)
→ በከፊል ያሟላ ከሆነ (10 ነጥብ)
→ በጥቂት ያሟላ (5 ነጥብ)
→ ያላሟላ ከሆነ (0 ነጥብ)
v. አካባቢያዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አንጻር (10%)
በዚህ መመዘኛ ውስጥ ሁለት ዋና ዋና ነጥቦች ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚተገበር ሲሆን እነሱም የቆሻሻ አወጋገድ፣ የአካባቢ ተፅኖ ግምገማ ሰነድ ዝግጅትና አተገባበር የሚሉት ናቸው፡፡ የነጥብ አሰጣጡም እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
1. የቆሻሻ አወጋገድ (5%)
⇒ እንደ ኢንቨስትመንቱ ዓይነት አግባብነት ያለው የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት የሚከተል መሆኑ፣
⇒ እንደ ኢንቨስትመንቱ ዓይነት አግባብነት ያለው የፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት የሚተገብር መሆኑ፣
→ በተሟላ አግባብ የተገበረ ከሆነ (5 ነጥብ)
→ ሥራውን ሰርተው ያላጠናቀቁ ግን ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ያሉ (2.5 ነጥብ)
→ በጥቂቱ ያሟላ ከሆነ (1 ነጥብ)
→ ምንም ተግባራዊ ስራ ያላከናወኑ (0 ነጥብ)
2. የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ/EIA and EMP/ ሰነድ ዝግጅትና አተገባበር (5%)
⇒ ከታወቀ አማካሪ ድርጅት የአካባቢ ተጽኖ ግምገማ ሰነድ አዘጋጅቶ ማቅረብ የቻለ፤
⇒ የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ሰነድ መሰረት እቅድ በማውጣት የተግባር ስራ የጀመረ፤
→ በተሟላ አግባብ የተገበረ ከሆነ (5 ነጥብ)
→ ስራውን ሰርተው ያላጠናቀቁ ግን ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ያሉ (2 ነጥብ)
→ ምንም አይነት የትግበራ ስራ ያልጀመረ (0 ነጥብ)
vi. ማህበራዊ ድጋፎች/Social services (10%)
የድርጅቱን ስራ ዘለቄታዊ ባለው መንገድ ማስኬድ ይቻል ዘንድ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነትን ፈጥሮ መስራት ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡ ይህም
⇒ ኢንቨስትመንት የሚካሄድበት አካባቢ ላሉ ማህበረሰቦች የተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ድጋፎች (ትምህርት ቤት፣ መንገድ፣ ጤና ጣቢያ/ክሊኒክ፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ ወዘተ) መስራት መቻሉ፤
⇒ ኩባንያው እየተጠቀማቸው ያሉትን የቴክኖሎጂ ውጤቶችና አዳዲስ አሰራሮችን ለማህበረሰቡ ማስተዋወቅና ማስረጽ መቻሉ፤
⇒ ለሰራተኞች የማትጊያ ሥርዓት ዘርግቶ የሚተገብር መሆኑ የሚሉት ነጥቦችን ከግምት ውስጥ የሚገቡ ሲሆን ነጥብ አሰጣጡም፡-
→ ከላይ ያሉትን በአግባቡ የተገበረ ከሆነ (10 ነጥብ)
→ ስራውን ሰርተው ያላጠናቀቁ ግን ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ያለ (5 ነጥብ)
→ ምንም ተግባራዊ ስራ ያላከናወነ (0 ነጥብ)
Vii የመረጃ አያያዝ፣ አደረጃጀትና ግልፀኝነት (10%)
መረጃ ለአንድ ተቋም ወሳኝ የሆነ መሳሪያ ነው፣ በመሆኑም በዚህ የምልመላ መስፈርት የመረጃ አደረጃጀትና አያያዝን እንደ አንድ የማወዳደሪያ ነጥብ የተወሰደ ሲሆን ይህም የባለሀብቱ አመታዊ እቅድ፣ የንግድ ስራ እቅድ፣ የአተገባበር እቅድ፣ በቋሚና በጊዜያዊነት የስራ እድል የፈጠረላቸው ዜጎች በፆታ (ወንድ/ሴት) የተለየ ዝርዝር መረጃ፣ የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ሰነድ፣ የኩባንያው ፕሮፋይል፣ ካመረተው ምርት መጠን እስከ ሽያጭ ድረስ ያለውን የመረጃ አያያዝ (Recording) የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ ነጥብ አሰጣጡም፡-
→ መረጃዎቹ በተሟላ መልኩ የተደራጁና አግባብነት ያለው የመንግስት አካል በሚጠይቅበት ጊዜ በግልፀኝነትና በፍቃደኝነት የሚተባበር ከሆነ (10 ነጥብ)
→ በከፊል የተሟላ ከሆነ (8 ነጥብ)
→ በጥቂት ያሟላ (5 ነጥብ)
→ ምንም ያልተሟላ ከሆነና በሚጠየቅበት ጊዜ ለበተባበር ፈቃደኛ ካልሆነ (0 ነጥብ)
9.2 ክፍል ሁለት የግብርና ምርት ውል (Contract Farming)
የግብርና ምርት ውል /Contract Farming/ ማለት በአምራቹና በአስመራቹ መካከል የሚኖር የግብርና ምርት የአመራረት ሂደትና የተመረተው ምርት ለገዥው የሚቀርብበት ስምምነት ሲሆን በሂደቱ ሁለቱም አካላት ተጠቃሚ የሚሆኑበት የአሰራር ስርዓት ነው፡፡ በሌላ አባባል በግብርና ምርት ውል ሒደት ውስጥ ምርት በአስመራች አካላትና አርሶ አደሮች መካከል የሚኖር ስምምነት ሲሆን አርሶ አደሩ የተለያዩ የግብርና ምርቶችን በመጠንና በጥራት አምርቶ ውል ለገባበት ድርጅት የሚሸጥበት ሂደት ነው፡፡ በሌላ በኩል ምርቱን ከአርሶ አደሩ የሚገዛው አስመራች
ደግሞ ለአምራቹ የምርት ጥራትና መጠንን በሚፈልገው ሁኔታ ሊጨምርለት የሚያስችል ግብዓት፣ ብድር፣ ሙያዊ ምክርና የግብይት አገልግሎቶቹን ለአርሶ አደሩ የሚያቀርብበት ሂደትን ያካትታል፡፡
አግባብነት ያለው የግብርና ምርት ውል /Contract Farming/ የትስስር ሒደት ውስጥ አራት ተዋናዮችን (አምራቹ፣ ገዥው/አስመራቹ፣ በትስስሩ አካባቢ ያሉ ማህበረሰቦችን እና መንግስትን) ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን በይበልጥ አርሶ አደሩን (አምራቹን) ተጠቃሚ ከሚያደርጉት ኩነቶች መካከል የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ (የተሻሻሉ ዝርያዎች፣ የማዳበሪያ፣ ኬሚካል ወዘተ)፣ የብድር አቅርቦት መመቻቸት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በአርሶ አደሩ ዘንድ አስቀድመው ያልተለመዱና በዓለም አቀፍ ገበያ ተፈላጊ የሆኑ የግብርና ምርቶች መለመድ መቻላቸው፣ የኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ፣ የሥልጠናና ሌሎች ልዩ ልዩ ድጋፎች ይገኙበታል፡፡ በዚህም በትስስሩ የተሳተፉ አርሶ አደሮች የኢኮኖሚ አቅማቸው እያደገ እንደሚመጣና በሂደትም ከድህነት ሊያወጣቸው እንደሚችል አመላካች ሁኔታዎች ታይቷል፡፡
በመሆኑም የግብርና ምርት ውል /Contract Farming/ ትስስር የፈጠሩ አካላትን በአግባቡ መደገፍና የትስስር አድማሱን በሁሉም ዘርፍ ማስፋት ከተቻለ ድህነትን በመቀነስ ረገድ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚችል እሙን ነው፡፡ ስለሆነም በዘርፉ የተሰማሩ አካላትን አወዳድሮ የተሻለ አፈጻጸም ያላቸውን በመለየት እና አሰራራቸውን ለሌሎች በማስፋት ዘርፉን ማጠናከር አግባብነት አለው፡፡
ከዚህ አኳያ በግብርና ምርት ውል /Contract Farming/ ተሰማርተው የተሻለ አፈፃጸም ያላቸው አካላትን ከተቋሙና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የሚለዩ ሲሆን በዘርፉ ለተሰማሩ አስመራቾች ምርጥ ተሞክሮ ለመቀመርና ለማወዳደር የሚያስችል የሚከተሉትን የመመልመያ መስፈርቶችና ነጥቦች ይይዛል። እነዚህም፦
i. ለአግሮፕሮሰሲንግ የቀረበ ምርት መጠን/ የውጭ ምንዛሬ ግኝት (10%)
በግብርና ምርት ውል /Contract Farming/ ትስስር የፈጠሩ አምራቶች ለገዥው የሚሸጡት
ምርት በገቡት ውል መሰረት ሆኖ ገዥው በሚያደርገው ሁለንተናዊ ድጋፍ መሰረት ምርቱን ከአምራቹ ሰብስቦ ኤክስፖርት ለማድረግ ካቀደው የምርት መጠን ውስጥ ኤክስፖርት የተደረገው መቶኛ በመውሰድ ነጥቡ የሚሰላ ይሆናል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ድርጀቱ አግሮፕሮሰሰር ሆኖ ከአምራቾቹ የሚሰበስበውን ምርት በሀገር ውስጥ እሴት ጨምሮ ጥቅም ላይ የሚያውለውን ድርሻ ከግምት ውስጥ የሚገባ ይሆናል፡፡
በዚሁ መሰረት፡-
→ ትስስር ከፈጠሩ አምራቾች በእቅዱ መሰረት ምርቱን በመሰብሰብ ሙሉ በሙሉ ኤክስፖርት ያደረገ/እሴት ጨምሮ በሙሉ ጥቅም ላይ ማዋል የቻለ (10 ነጥብ)
→ የተመዘገበው ምርት መጠን ከአምራቹ ለመሰብሰብ ካቀደው ከ10% - 20% ያነሰ ከሆነ (7 ነጥብ)
→ የተመዘገበው ምርት መጠን ከአርሶ አደሩ ለመሰብሰብ ካቀደው ከ21% - 40% ያነሰ ከሆነ (5 ነጥብ)
→ የተመዘገበው ምርት መጠን ከአምራቾች ለመሰብሰብ ካቀደው መጠን ከ 41% - 60 % ያህል ያነሰ ከሆነ (2.5 ነጥብ)
→ የተመዘገበው ምርት መጠን ከአምራቾች ለመሰብሰብ ካቀደው መጠን 61 % እና ከዚያ በታች ያስመዘገበ ከሆነ (0 ነጥብ)
ii. የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግር (10%)
በትስስሩ የተሳተፉ አምራቾች ትስስር ከፈጠሩባቸው ኩባንያዎች የሚያገኙትን የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግር በተመለከተ እንደ አካባቢውና እንደየዘርፉ የሚለያይ ሲሆን በዋናነት በአምራቾች ያልተለመዱና በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ተፈላጊ ሆነው ኢትዮጵያ ባስቀመጠችው ያሰራር ሂደትን ተከትሎ አምራቾችን ተጠቃሚ ያደረጉ ቴክኖሎጂዎች፣ ለአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪዎች በግብዓትነት የሚያገለግሉ ዕውቀቶች በአምራቹ ደረጃ እየተለመዱ እንዲመጡ እየተደረገ ያለውን አካሄድ/ጥረት ከግምት ውስጥ የሚያስገባ መስፈርት ሲሆን ነጥብ አሰጣጡም እንደሚከተለው ተተንትኗል፡-
→ ኩባንያው ትስስር ለፈጠረባቸው አምራቾች የተለያዩ ድጋፎች ማለትም የተስማሚ ቴክኖሎጂ፣ ወቅታዊና ተጨባጭ ሥልጠና ማመቻቸት፣ የምርጥ ዘር/የችግኝ አቅርቦት፣ ምርት ማሳደጊያ ግብአት አቅርቦት፣ የምርት መሰብሰቢያ ቁሳቁሶች አቅርቦት እና የመሳሰሉትን ድጋፎች በተሟላ መልኩ የሚያቀርብ ከሆነ (10 ነጥብ)
→ በከፊል የሚያሟላ ከሆነ (5 ነጥብ)
→ በትንሹ የሚያቀርብ ከሆነ (2 ነጥብ)
→ ምንም የማያሟላ ከሆነ ደግሞ (0 ነጥብ)
iii. የሥራ ዕድል ፈጠራ (10%)
በግብርና ምርት ውል /Contract Farming/ ትስስር የፈጠሩ አካላት በትስስሩ ምክንያት ለክልሉና ለአጎራባች አካባቢዎች በቋሚነትና በጊዜያዊነት የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩ የሚጠበቅ ነው፡፡ በዚህ መመዘኛ ውስጥ እንደ አንድ መስፈርት መጠቀሙ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ሆኖም በተለያየ ዘርፍ ተሰማርተው ትስስር የፈጠሩ ኩባንያዎች በትስስሩ ምክንያት የሚፈጥሩት የሥራ ዕድል እንደ የዘርፉ ነባራዊ ሁኔታ የሚለያይ እንደሚሆን
ከግምት ውስጥ መግባት ይኖርበታል፡፡ ነጥብ አሰጣጡም እንደሚከተለው ይሆናል፡-
→ ትስስር የፈጠረው አካል በቢዝነስ ፕላኑ መሰረት የፈጠረው ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ከ95% - 100% ከሆነ (10 ነጥብ)
→ በዕቅዱ ከተያዘው ከ80% - 94% የሥራ ዕድል የሚፈጥር ከሆነ (8 ነጥብ)
→ በዕቅዱ ከተያዘው ከ60% - 79% የሥራ ዕድል የፈጠረ ከሆነ (6 ነጥብ)
→ የዕቅዱን ከ40% - 59% የሥራ ዕድል የሚፈጥር ከሆነ (4 ነጥብ)
→ ከእቅዱ 40% በታች የሥራ እድል የፈጠረ ከሆነ (2 ነጥብ)
→ ምንም የሰራ እድል ካልፈጠረ (0 ነጥብ)
iv. በትስስሩ ተጠቃሚ የሆኑ አምራቾች በቁጥር (10%)
የዚህ መመዘኛ መስፈርት ትኩረት የሚያደርገው ትስስር የፈጠረው አካል ተጠቃሚ የሚያደርጋቸውን የአርሶ አደሮች ብዛት መሰረት ያደረገ ሲሆን በዋናነት ከቢዝነስ ፕላኑ አንጻር የሚታይ ይሆናል፡፡ በመሆኑም የነጥብ አሰጣጡ ሂደት እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
→ ትስስር የፈጠረው አምራች በቢዝነስ ፕላኑ መሰረት ተጠቃሚ የሚያደርጋቸው አስመራቾች ከ95 % - 100 % ከሆነ (10 ነጥብ)
→ ከእቅዱ ከ80% - 94% ተጠቃሚ የሚያደርግ ከሆነ (8 ነጥብ)
→ ከእቅዱ ከ60% - 79% ተጠቃሚ የሚያደርግ ከሆነ (6 ነጥብ)
→ ከእቅዱ ከ40% - 59% ተጠቃሚ የሚያደርግ ከሆነ (4 ነጥብ)
→ ከእቅዱ 40% በታች ከሆነ (2 ነጥብ)
→ ምንም ተጠቃሚ ካላደረገ (0 ነጥብ)
v. የዋጋ አተማመን ሥርዓት (10%)
በግብርና ምርት ውል /Contract Farming/ ትስስር ሂደት ውስጥ አምራቹን ተጠቃሚ ከሚያደርጉት አንዱና ዋናው ዘለቄታ ያለውና በአምራቹ አቅራቢያ የሚኖረው የገበያ ሁኔታ ነው፡፡ በመሆኑም ይህ መመዘኛ ምርጥ ተሞክሮ ለመቀመር እንደ አንድ መመልመያ መስፈርት የተቀመጠ ሲሆን የነጥብ አሰጣጡም እንደሚከተለው ተቀምጧል፡፡
→ በገበያ ዋጋ ትመና ወቅት ሁለቱም ተዋናዮች ቀድመው በስምምነት እንዲሁም በግልጽነት ዋጋን የሚወስኑ ሆኖ ወቅታዊ የዋጋ ልዩነት ከተፈጠረ በዋናነት አስመራቹ ኃላፊነት ወስዶ አምራቹን በማወያየት ሁለቱንም ተዋናዮች ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ ማስተካከያ የሚያደርግ አስመራች ከሆነ (10 ነጥብ)
→ የውል ስምምነቱ የወቅቱን ገበያ ብቻ መሰረት ያደረገ ሆኖ የምርት ዋጋ በሚጨምርበት ወቅት የማስተካከያ እርምጃ የማይወስድ ሆኖ በውሉ መሰረት ብቻ አምራቹን የሚያስተናግድ ከሆነ (5 ነጥብ)
→ የውል ስምምነት ሳይፈጥር ወቅታዊ ገበያ ብቻ መሠረት በማድረግ ሁሌም ከአምራቹ ምርት የሚሰበስብ ከሆነ (2.5 ነጥብ)
vi. የመሰረተ ልማት አደረጃጀት (10%)
በዚህ መስፈርት ትስስር የፈጠረው አስመራች የሚገመገመው ለስራው አጋዥ የሆኑ መሰረተ ልማት ከማሟላት አንጻርና ለሰራተኛው የሚያቀርበውን አገልግሎት ከግምት ውስጥ በማስገባት ይሆናል፡፡ በዚህም መሰረት፡-
⇒ ደረጃውን የጠበቀ የጽ/ቤት፣ መጋዘን (የማዳበሪያ፣ የኬሚካል፣ የምርት)፣ ለስራው አጋዥ ለሆኑ መሳሪያዎችና ማሺነሪዎች መጠለያ ያሟላ፤
⇒ እንደ ኢንቨስትመንቱ አይነት አግባብነት ያላቸው ማሽነሪዎች ማሟላት የቻለ፤
⇒ ለስራው አጋዥ የሆኑ የትራንስፖርት መገልገያ ያሟላ፤
⇒ እንደ ኢንቨስትመንቱ አይነት የመስኖ መሰረተ ልማት ያለውና ጥቅም ላይ ያዋለ፤
⇒ ለሰራተኛ ምቹ የሆኑ መሰረተ ልማት (መኖሪያ፣ ሽንት ቤት፣ ሻወር ቤት፣ ህክምና መስጭያ፣ ማብሰያ ቦታ፣ የማሽነሪ/ትራንፖርት መጠለያ ወዘተ) ማሟላት የቻለ፤
⇒ ለሰራተኛው የስራ ልብስ እንዲሁም የመመገቢያ ቦታን ያሟላ
⇒ የሰራተኛ ድንገተኛ አደጋ መጠበቂያ ቁሳቁሶች ያሟላ ወዘተ የሚሉት መሰረታዊ የመገምገሚያ ነጥቦች ናቸው፡፡
⇒ በዚሁ መሰረት አቅርቦቱ ፡-
→ ሙሉ በሙሉ የተሟላ ከሆነ (10 ነጥብ)
→ በከፊል ያሟላ ከሆነ (5 ነጥብ)
→ በጥቂቱ ያሟላ ከሆነ (1 ነጥብ)
→ ያላሟላ ከሆነ (0 ነጥብ)
vii. የኤክስቴንሽን አገልግሎት አሰጣጥ (10%)
የግብርና ምርት ውል /Contract Farming/ አሰራር የሚታቀፉ አምራቾች ከአስመራቹ ጋር በሚፈጥሩት ትስስር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በርካታ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን እንደሚያገኙ ይታወቃል፡፡ ትስስር የፈጠሩ አስመራቾች ተጠቃሚነታቸውን ማጎልበት የሚቻልበት አንዱ ስልት ትስስር የፈጠረው አካል የአምራቹን የግንዛቤ፣ የክህሎትና የአመለካከት ለውጥ ማምጣት
የሚችለው ባሉት የኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ሲሆን ይህም አምራቹን ከአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ጋር እንዲተዋወቁና የቴክኒክ ድጋፍ አገልግሎት እንዲያገኙ ወቅታዊ የስልጠና፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን፣ የመስክ ቅኝት ፕሮግራሞችን (Field trip) እና መሰል ፕሮግራሞችን በማመቻቸት አስመራቹ የሚጠብቀውን ውጤት እንዲመጣ የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወጡ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
በዚሁ መሰረት አቅርቦቱ ፡-
→ አስመራቹ ባለሙያ ቀጥሮ የተሟላ /full package/ የኤክስቴሽን አገልግሎት ድጋፍ የሚሰጥ ከሆነ (10 ነጥብ)
→ በከፊል አገልግሎት የሚሰጥ ከሆነ (5 ነጥብ)
→ በጥቂት የሚሰጥ ከሆነ (2.5 ነጥብ)
→ አገልግሎቱን የማይሰጥ ከሆነ (0 ነጥብ)
viii. አካባቢያዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አንጻር
በዚህ መመዘኛ መስፈርት ውስጥ አምስት ዋና ዋና ነጥቦች ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚተገበር ሲሆን እነሱም የቆሻሻ አወጋገድ፣ የአካባቢ ተጽኖ ግምገማ ሰነድ ዝግጅትና አተገባበር፣ የደን እንክብካቤ፣ የአፈር መከላትን መንከባከብ የሚሉት ናቸው፡፡ የነጥብ አሰጣጡም እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
1/ የተቀናጀ ደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ (3%)
⇒ እንደ ኢንቨስትመንቱ ዓይነት አግባብነት ያለው የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት የሚከተል
መሆኑ
⇒ እንደ ኢንቨስትመንቱ ዓይነት አግባብነት ያለው የፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት የሚተገብር መሆኑ
→ በተሟላ አግባብ የተገበረ (3 ነጥብ)
→ ሥራው ሰርተው ያላጠናቀቁ ግን ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ያሉ (2 ነጥብ)
→ ምንም ተግባራዊ ስራ ያላከናወኑ (0 ነጥብ)
2/ የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ/EIA and EMP/ ሰነድ ስለመኖሩና አተግበሩ( (2.5%)
⇒ ከታወቀ አማካሪ ድርጅት የአካባቢ ተጽኖ ግምገማ ሰነድ አዘጋጅቶ ማቅረብ የቻለ፤
⇒ የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ሰነድ መሰረት እቅድ በማውጣት የተግባር ስራ የጀመረ፤
→ በተሟላ አግባብ የተገበረ (2.5 ነጥብ)
→ ስራውን9ኢ ሰርተው ያላጠናቀቁ ግን ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ያሉ (1 ነጥብ)
→ ምንም አይነት የትግበራ ስራ ያልጀመረ (0 ነጥብ) 3/ የደን እንክብካቤ (2.5 %)
በዚህ መመዘኛ ሥር የሚካተቱት ተግባራት፡-
⇒ ችግኝ ጣቢያ አቋቁሞ ችግኞችን በማፍላት ለእርሻ አገልግሎት አመቺ ያልሆኑ አካባቢዎችን በደን መሸፈን እና ትስስር ለፈጠሩ አርሶ አደሮች ማሰራጨት የቻለ፣
⇒ በግብርና ምርት ውል /Contract Farming/ ትስስር የፈጠሩ አርሶ አደሮች በደን ጥቅም ላይ ተገቢ ግንዛቤ እንዲያገኙ በማድረግ ችግኞችን እንዲተክሉና እንዲንከባከቡ ማድረግ የቻለ ሲሆን ነጥብ አሰጣጡም፡-
→ ስራውን በአግባቡ የተገበረ (2.5 ነጥብ)
→ ስራው ሰርተው ያላጠናቀቁ ግን ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ያሉ (1 ነጥብ)
→ ምንም ተግባራዊ ስራ ያላከናወኑ (0 ነጥብ) 4/ የአፈር መከላትን መንከባከብ (2%)
በዚህ መመዘኛ ስር የሚካተቱት ተግባራት፡-
⇒ በይዞታው ላይ ለአፈር መሸርሸር ተጋላጭ የሆኑትን የመሬት አካል በመለየት ስነ ህይወታዊና ፊዚካል መከላከያዎችን መስራትና ትስስር ለፈጠሩ አርሶ አደሮች ተመሳሳይ ስራ እንዲሰሩ ድጋፍ ማድረግ፣
⇒ አምራቹ የእርከን ስራዎችን በራሱ ማሳ ላይ እና ትስስር በፈጠሩ አርሶ አደር ማሳ ላይ እንዲሰራ ማድረግ መቻል፣
⇒ በጣም የተጎዱ አካባቢዎችን በመከለል ቦታው እንዲለማ ማድረግ
→ ስራውን በአግባቡ የተገበሩ (2 ነጥብ)
→ ስራውን ሰርተው ያላጠናቀቁ ግን ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ያሉ (1
ነጥብ)
→ ምንም ተግባራዊ ስራ ያላከናወኑ (0 ነጥብ)
ix. ምርትና ምርታማነት ማሳደግ (10%)
በትስስሩ የተሳተፉ አምራቾችም ሆኑ ትስስር የፈጠረው አስመራች የሚያስመዘግበው ምርታማነት የሚገመገመው በቢዝነስ ፕላኑ ላይ ከተቀመጠው አንፃር ሲሆን ከአንድ የግብርና ምርት በላይ የሚያመርት ከሆነ የእያንዳንዱ የግብርና ምርታማነት ተገምግሞ አማካዩ ነጥብ የሚቀመጥለት ይሆናል፡፡ በዚሁ መሰረት፡-
→ የተመዘገበው ምርታማነት በቢዝነስ ፕላኑ 95 – 100 % መሰረትና ከዚያ በላይ ከሆነ (10 ነጥብ)
→ ምርታማነቱ ከእቅዱ ከ 85% - 94% የተመዘገበ ከሆነ (8 ነጥብ)
→ ከእቅዱ ከ75% - 84% የተመዘገበ ከሆነ (6 ነጥብ)
→ ከእቅዱ ከ55%- 75% የተመዘገበ ከሆነ (5 ነጥብ)
→ ከእቅዱ ከ 40 % - 54% የተመዘገበ ከሆነ (4 ነጥብ)
→ 40 % በታች (2 ነጥብ ይሆናል)
→ ምንም ያላስመዘገበ ከሆነ (0 ነጥብ)
x. ማህበራዊ ድጋፎች/Social services (5%)
ትስስሩን በዘላቂ መንገድ ማስኬድ ይቻል ዘንድ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነትን ፈጥሮ መስራት ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡ ይህም
⇒ ትስስሩ የሚካሄድበት አካባቢ ላሉ ማህበረሰቦች የተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ድጋፎች
(ት/ቤት፣ መንገድ፣ ጤና ጣቢያ/ክሊኒክ ወዘተ) ማድረግ መቻሉ፤
⇒ አስመራቹ እየተጠቀመባቸው ያሉትን የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለማህበረሰቡ በማስተዋወቅ ማስረጽ መቻሉ፤
⇒ ለሰራተኞች የማትጊያ ሥርዓት ዘርግቶ የሚተገብር መሆኑ የሚሉት ነጥቦችን ከግምት ውስጥ የሚገቡ ሲሆን ነጥብ አሰጣጡም፡-
→ ከላይ ያሉትን በአግባቡ የተገበረ (5 ነጥብ)
→ ስራው ሰርተው ያላጠናቀቁ ግን ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ያለ (2.5 ነጥብ)
→ ምንም ተግባራዊ ስራ ያላከናወነ (0 ነጥብ)
xi. የመረጃ አያያዝና አደረጃጀት (5%)
እንደሚታወቀው መረጃ ለአንድ ተቋም ወሳኝ የሆነ መሳሪያ ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ የምልመላ መስፈርት የመረጃ አደረጃጀትና አያያዝን እንደ አንድ የማወዳደሪያ ነጥብ የተወሰደ ሲሆን ይህም የአስመራቹ አመታዊ እቅድ፣ የንግድ ስራ እቅድ፣ የአተገባበር እቅድ፣ ትስስር የፈጠሯቸው አምራቾች ዝርዝር መረጃ፣ የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ሰነድ፣ የኩባንያው ፕሮፋይል፣ ከማሳ ዝግጅት እስከ ምርት ማሰባሰብ ድረስ ያለው የመረጃ አያያዝ (Recording)፣ የአምራቾች የምልመላ መስፈርቶች መረጃ እንዲሁም የአምራች ምዝገባና የመረጃ አያያዝ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ ነጥብ አሰጣጡም፡-
→ መረጃዎቹ በተሟላ መልኩ የተደራጁ ከሆነ (5 ነጥብ)
→ በከፊል የተሟላ ከሆነ (2.5 ነጥብ)
→ ምንም ያልተሟላ ከሆነ (0 ነጥብ)
9.3 ክፍል ሶስት የሆርቲካልቸር ልማት
የሆርቲካልቸር ኢንቨስትመንት ማለት “የኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 1180/2012 ‘ትን መስፈርት አሟልቶ በአበባ፣ በአትክልት፣ በፍራፍሬ፣ ዕፀ-ጣዕምን ጨምሮ በሌሎች የሆርቲካልቸር መዓዛማ ሰብሎችን ማምርት ላይ የሚደረግ የኢንቨስትመንት መስክ ሲሆን የሚከተሉትን የምዘና (የምልመላ) መስፈርቶችና ነጥቦች የያዘ ይሆናል። እነዚህም ፦
i. የአቅርቦት እና ኤክስፖርት ገቢ አፈጻጸም (40%)
⇒ እንደ ሀገር ካሉት በዘርፉ ከተሰማሩ ኩባንያዎች ውስጥ አንዱ ካለው የመሬት ይዞታ ጋር ተነጻጽሮ ከፍተኛ ኤክስርት ማድረግ የቻለ፤
⇒ የማይዋዥቅ እና ወጥ የሆነ የኤክስፖርት የመጠን የሚያደርግ ወይም ከአመት አመት የኤክስፖርት መጠኑ እያደገ የመጣ፤
⇒ የወጭ ምንዛሬን በወቅቱ በማስገባት እዳ ውስጥ የማይገባ፤
⇒ ኩባንያው ምርቱን ለተለያዩ የገበያ መዳረሻ ለማቅርብ ያገኘው አለም አቀፍ ሰርተፍኬት ብዛት
→ ከላይ የተቀመጡትን መስፈርቶች ያሟላ ከሆነ (40 ነጥብ)
→ በከፊል ያሟላ ከሆነ (20 ነጥብ)
→ በጥቂት የሚያገኝ (10 ነጥብ)
→ መስፈርቱን የማያሟላ ከሆነ ምንም ነጥብ አያገኝም
→ ነሀስ (10%)
ii. የአምራቾችን የአሰራር ደንብን መተግበር (15%)
→ ብር (13%)
→ ወርቅ (15%)
iii. ጥሩ የአመራረት ሂደት (Good Agricultural Practice) (15%)
⇒ የኬሚካል አጠቃቀም
→ የተፈቀደ/የተመዘገበ ኬሚካል በአግባቡ የሚጠቀም ከሆነ
→ አስፈላጊውን የኬሚካል ትጥቅ ለሰራተኞች የሚያቀርብ ከሆነ
→ ኬሚካል ርጭት ከተደረገ በኋላ ተመልሶ ስራ የሚጀምርበት ሰዓት እንደ ኬሚካሉ አቅጣጫ መሰረት በስርዓቱ የሚተገበር ከሆነ
→ አስፈላጊውን ግብአት የሚያሟላ ከሆነ (ሻወር ፤ ልብስ ማጠቢያ ቦታ ፤ የተለየ ልብስ መቀየሪያ እና ማስቀመጫ)
→ አስፈላጊውን ምርመራ በየ 3 ወሩ የሚያደርግና እንደ አስፈላጊነቱ ችግር የታየባቸውን ሰራተኞችን ከርጭት ክፍል የሚቀይር ከሆን
→ ትክክለኛ የኬሚካል እና ማዳበሪያ መጋዘን አያያዝ ካለ
→ ሴት ሰራተኞችን ከኬሚካል ጋር ተያያዥነት ባላቸው ስራዎች ላይ የማይመድብ ከሆነ (ስቶርኪፐርን ጨምሮ)
→ የኬሚካል ማስወገጃ ቦታ ካለውና በስርዓቱ የሚያስወግድ ከሆነ
→ በተቀናጀ የተባይ መከላከያ የሚጠቀም ከሆነ
⇒ የውሃ አጠቃቀም
→ የታደሰ የውሃ (የጉድጓድ ፤ የወንዝ) የመጠቀም ፍቃድ መኖሩ
⇒ የቆሻሻ አወጋገድ
→ አግባብነት ያለው የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት የሚከተል ከሆነ፤ የቆሻሻ ማቃጠያ ኢንሲሬተር የሚጠቀም ከሆነ
→ አግባብነት ያለው የፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት የሚተገብር ከሆነ
⇒ የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ/EIA and EMP/ ሰነድ ዝግጅትና አተገባበር
→ ከታወቀ አማካሪ ድርጅት የአካባቢ ተጽኖ ግምገማ ሰነድ አዘጋጅቶ ማቅረብ የቻለ፤
→ የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ሰነድ መሰረት እቅድ በማውጣት የተግባር ስራ የጀመረ፤
→ ለእርሻ ላይ የአካባቢ መኮንን ፤ የአካባቢ ኮሚቴ ስልጠና መሰጠቱ እና ሁሉም አባላት በስራ ላይ መሆናቸው
→ አመታዊ የዳሰሳ ጥናት መደረጉ ፤ እንዲሁም የመፍትሄ እርምጃዎች መወሰዳቸው
⇒ የደን እንክብካቤ
→ ችግኝ ጣቢያ አቋቁሞ ችግኞችን በማፍላት ለልማት አመቺ ያልሆኑ አካባቢዎችን በደን መሸፈን እና በአካባቢው ላሉ ማህበረሰብ ማሰራጨት የቻለ፣
⇒ የአፈር መከላትን መንከባከብ
→ በይዞታው ላይ ለአፈር መሸርሸር ተጋላጭ የሆኑትን የመሬት አካል በመለየት ስነ ህይወታዊና ፊዚካል መከላከያዎችን መስራት ከቻለ፣
→ አሰራሩን አቅርቢያ ላሉ ማህበረሰቦች በማስተማር እንሱም እንዲተገብሩት ድጋፍ ማድረግ የቻለ፣
• ከላይ የተቀመጡትን መስፈር የሚያሟላ ከሆነ (15 ነጥብ)
• በከፊል የተጠቀመ (7.5 ነጥብ)
• በጥቂት ካሟላ (3.5 ነጥብ)
• ምንም ያልተጠቀመ ዜሮ ነጥብ የሚያገኝ ይሆናል
iv. የሰራተኞች እርሻ ላይ የደህንነት አጠባበቅ (10 %)
→ ለእርሻ ላይ የደህንነት ጤንነት መኮንን፤እንዲሁም ለደህንነት ጤንነት ኮሚቴ አባላት ስልጠና መሰጠቱ እና ሁሉም አባላት በስራ ላይ መሆናቸው
→ አመታዊ የዳሰሳ ጥናት መደረጉ ፤ እንዲሁም የመፍትሄ እርምጃዎች መወሰዳቸው
→ ለተለዩ የስራ ክፍሎች አስፈላጊው ትጥቅ (እንደሰራው አይነት) ተለይቶ መሰጠቱ
→ የእርሻ ላይ አቅርቦቶች (የመጠጥ ውሃ፤ መፀዳጃ ቤት፤ ሻወር ፤ የልብስ መቀየሪያ፤ የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ፤ ምግብ መመገቢያ) በበቂ ሁኔታ መኖራቸው
⇒ የሰራተኛ አያያዝ
→ ሰራተኞች በኢትዮጵያ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 መሰረት መስራታቸው
→ ለሰራተኞች አስፈላጊው ስልጠና መሰጠቱ (የሰራ ቦታ፤ የደህንነት፤ የትጥቅ አጠቃቀም)
⬤ ሙሉ በሙሉ ማዋል ከቻለ (10 ነጥብ)
⬤ ግማሹን ያዋለ (5 ነጥብ)
⬤ በጥቂት ያሟላ (2.5 ነጥብ)
⬤ ምንም ያላሟላ (0 ነጥብ) የመሬት አጠቀቃም መስፈረት (10%)
⇒ የተረከበውን መሬት ሙሉ በሙሉ ለልማት ማዋል የቻለ
→ ሙሉ በሙሉ ማዋል ከቻለ (10 ነጥብ)
→ ግማሹን ያዋለ (5 ነጥብ)
→ በጥቂት ያሟላ (2.5 ነጥብ)
→ ምንም ያላሟላ (0 ነጥብ)
v. ማህበራዊ ኃላፊነት መስፈረት (10%)
⇒ አመታዊ የማህበራዊ ሃላፊነት እቅድ አውጥቶ መተግበሩ
⇒ ልማቱ የሚካሄድበት አካባቢ ላሉ ማህበረሰቦች የተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ድጋፎች (ት/ት፣ መንገድ፣ ጤና ጣቢያ/ክሊኒክ ወዘተ) ማድረግ መቻሉ፤
⇒ ለሰራተኞች የማትጊያ ሥርዓት ዘርግቶ የሚተገብር መሆኑ የሚሉት ነጥቦችን ከግምት ውስጥ የሚገቡ ሲሆን ነጥብ አሰጣጡም፡-
→ ከላይ ያሉትን በአግባቡ የተገበረ (10 ነጥብ)፤
→ በግማሽ ያሟላ (5 ነጥብ)
→ ስራውን ሰርተው ያላጠናቀቁ ግን ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ (2.5 ነጥብ)
→ ምንም ተግባራዊ ስራ ያላከናወነ
9.4 ክፍል አራት፡ የሰፋፊ እርሻ ኢንቨስትመንት
የሰፋፊ እርሻ ኢንቨስትመንት ማለት “የኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 1180/2012’ትን መስፈርት አሟልቶ በብዕርና በአገዳ ሰብል፣ በቅባት ህሎችና በሌሎች ንዑስ ዘርፎች ማምርት ላይ የሚደረግ የኢንቨስትመንት መስክ ሲሆን የምዘና መስፈርቱም የሚከተሉትን ነጥቦች የሚይዝ ይሆናል፡-
የሰፋፊ እርሻ ኢንቨስትመንት የልማት እንቅስቃሴ መመዘኛ መስፈርት/ነጥብ አሰጣጥይህ የፍረጃ መመዘኛ የመሬት ልማት እንቅስቃሴ መሻሻል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አስተዋጽኦ ያደርጋል የሚል ግንዛቤ ተወስዷል፡፡ በዚሁ መሰረት የለማ መሬት፣ የእርሻ መሳሪያ አቅርቦት፣ የካምፕ አደረጃጀትና የሠራተኛ አያያዝ፣ የሠራተኛ ቅጥር ለኢንቨስትመንቱ ባላቸው ወሳኝ ሚና አንፃር ታይቶ ከታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችና ነጥቦች ለፍረጃ ተወስደዋል፡፡
i. በገባው ውል መሠረት የለማ (በሰብል የተሸፈነ) መሬት መጠንና ምርታማነት (42 ነጥብ)
በሰብል የተሸፈነ መሬት መጠንና የምርታማነት ሥራዎችን ለመመዘን በሁለት መመዘኛ ቀርበዋል፣ እነሱም፡-
ሀ) የለማ (በሰብል የተሸፈነ) መሬት መጠን (30%) ፡- በዚህ ንኡስ መመዘኛ ስር የሚካተቱ ተግባራት
⇒ አንድ ኩባንያ በውሉ መሰረት ማልማት ከሚጠበቅበት የመሬት መጠን ውስጥ ያለማውን መሬት መቶኛ በመውሰድ ለዚህ መገምገሚያ መስፈርት የተሰጠውን ነጥብ ውስጥ ተሰልቶ
የሚቀመጥለት ይሆናል፡፡ በዚህም፡-
→ ሙሉ በሙሉ ማዋል ከቻለ (30 ነጥብ)
→ ግማሹን ያዋለ (15 ነጥብ)
→ በጥቂት ያሟላ (7.5 ነጥብ)
→ ምንም ያላሟላ (0 ነጥብ)
ለ) የሰብል ልማት ኩባንያው ለማልማት በገባው ውል (በቢዝነስ ፕላኑ) መሰረት ምርታማነቱ የሚታይ ይሆናል (20 ነጥብ)፡-
⇒ የኩባንያው ምርትና ምርታማነት የሚገመገመው በቢዝነስ ፕላኑ ላይ ከተቀመጠው አንፃር ሲሆን ምርታማነት ተገምግሞ አማካዩ ነጥብ የሚቀመጥለት ይሆናል፡፡ በዚሁ መሰረት፡-
→ የተመዘገበው ምርታማነት በቢዝነስ ፕላኑ 95 – 100 % መሰረትና ከዚያ በላይ ከሆነ (20 ነጥብ)
→ ምርታማነቱ ከእቅዱ ከ 85% - 94% የተመዘገበ ከሆነ (16 ነጥብ)
→ ከእቅዱ ከ75% - 84% የተመዘገበ ከሆነ (14 ነጥብ)
→ ከእቅዱ ከ55%- 75% የተመዘገበ ከሆነ (10 ነጥብ)
→ ከእቅዱ ከ 40 % - 54% የተመዘገበ ከሆነ (8 ነጥብ)
→ 40 % በታች (2 ነጥብ ይሆናል)
ii. የአከባቢ ጥበቃና አያያዝ (20 ነጥብ)
የባለሀብቶች የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ለመመዘን ሰባት መመዘኛ ቀርበዋል እነሱም፡-
ሀ) የአካባቢተፅእኖ ሰነድ ወይም የአካባቢ አያያዝ እቅድ (32 ነጥብ)፡- በዚህ ንኡስ መመዘኛ ስር የሚካተቱ ተግባራት
⇒ ኩባንያው መሬት ተረክቦ ወደ ልማት ከመግባቱ በፊት ለሚመለከተው አካል ሁለቱን ሰነዶች አዘጋጅቶ በማቅረብና በማስጸደቅ የሚተገብር መሆኑ፣
→ ሁሉንም አሟልተው ሰርተው የተገኙ 2
→ በከፊል የሰሩ 1
→ ተግባራዊ ያላደረጉ 0 ነጥብ ይሰጣቸዋል፡፡
ለ) የደን እንክብካቤ ( 3 ነጥብ)፡- በዚህ ንኡስ መመዘኛ ስር የሚካተቱት ተግባራት፡-
⇒ በመሬት ዝግጅት ወቅት የቀሩት ሀገር በቀል ዛፎችን መንከባከብ፣
⇒ አዲስ መሬት በሚዘጋጅበት ወቅት ሀገር በቀል ዛፍን በማስቀረት መንከባከብ፣
⇒ በማሳ ዝግጅት ወቅት በማሳው ላይ ምንም ዛፍ የሌለው ችግኝ በማዘጋጀት መሬቱን በውሉ መሰረት መሸፈን ሲሆኑ፡-
→ ይህን ስራ ያሟሉ 3
→ ስራውን ሰርተው ያላጠናቀቁ ግን ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ያሉ ወይም በከፊል የሰሩ 1.5
→ አካባቢውን በሚጎዳ መልኩ ያከናወኑ ወይም ምንም ተግባራዊ ስራ ያላከናወኑ 0 ነጥብ ይሰጣቸዋል፡፡
ሐ) የአፈር መከላትን መንከባከብ (3 ነጥብ)፡- በዚህ ንኡስ መመዘኛ ስር የሚካተቱት ተግባራት፡-
⇒ በመሬቱ ላይ ለአፈር መሸርሸር ተጋላጭ የሆኑትን የመሬት አካል በመለየት የመከላከያ ሥራ መስራት፤
⇒ ለመሬቱ ተስማሚ የአስተራረስ/የግብርና አስተራረስ ዘዴ መከተል፣
⇒ የእርከን ስራዎችን መስራት፤
→ ይህን ስራ በአግባቡ የሰሩ (5 ነጥብ)
→ ስራውን ሰርተው ያላጠናቀቁ ግን ተግባራዊ እንቅስቃሴ እያደረጉ ያሉ (3 ነጥብ)
→ በዝቅተኛ ደረጃ የፈፀመ (1 ነጥብ)
→ አካባቢውን በሚጎዳ መልኩ ያከናወኑ ወይም ምንም ተግባራዊ ስራ ያላከናወኑ (0 ነጥብ) ይሰጣቸዋል፡፡
መ) የአካባቢ አሀድ መቋቋምና የአካባቢና ማህበራዊ አያያዝ ስርዓት መዘርጋቱ(2)
• የአካባቢ አሃድ መቋቋሙና የሰለጠነ የሰው ሀይል መመደቡ(1)
• የአካባቢና ማህበራዊ አያያዝ ስርዓት ሥራ ላይ መዋሉ(0.5)
• ተከታታይ የአቅም ግንባታ ሥራ መሠራቱ(0.5) ሠ) የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ስለመኖሩና ስለመተግበሩ(2)
• የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ መዘጋጀቱ(1)
• የተዘጋጀው የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ በሙሉ ተግባራዊ መደረጉ(1) ረ) የሥራ ላይ ደህንነት፣ የሠራተኛ መብትና የጤና አጠባበቅ(3)
• ህጻናትን አለመቅጠር(1)
• የሥራ ላይ የደህንነት መሣሪያዎችን ማሟላት(0.5)
• የተደራጀ ክሊኒክ ማቋቋምና የሠለጠነ የጤና ባለሙያ መመደብ(1)
• የሠራተኞችን ሁለንተናዊ መብት ማክበር(0.5) ሰ) የኬሚካልና ሌሎች ግብዓቶች አያያዝና አጠቃቀም(3)
• የኬሚካልና ሌሎች ግብዓቶች የተለየ ማከማቻ ከንፋስ አቅጣጫና ከሠራተኞች መኖሪያ፣ የሥራ ቦታ እና የመመገቢያ አዳራሽ ራቅ አድርጎ ስለማዘጋጀት(1)
• የተጠቀሱትን ግብአቶች ለታለመላቸው ዓላማ ብቻ ስለማዋል(1)
• ለልማቱ ከተፈቀደውና ከሚፈለገው በላይ የኬሚካል ግብአቶን አለመያዝ/ አለማከማቸት(1)
iii. የእርሻ መሳሪያ አቅርቦት (15 ነጥብ) የኩባንያዎቹ የእርሻ መሳሪያ አቅርቦት ለመመዘን የሚከተለው ቀርቧል፤
⇒ የኩባንያዎቹ የእርሻ መሳሪያ አቅርቦት የሚመዘነው ከባህላዊ አሰተራረስ ዘዴ ውጪ በሆነ ሁኔታ በዘመናዊ እርሻ መሳሪያ አጠቃቀም ሆኖ አንድ ትራክተር ከተጨማሪ ወሳኝ ከሆኑ የእርሻ መሳሪያዎች (ማረሻ፣ መከስከሻና ዘር መዝሪያ ወዘተ) ጋር ከ250 እስከ 300 ሄ/ር መሬት ሂሳብ ሲሆን ከተያዘው የልማት እቅድ አንጻር አቅርቦቱ ታይቶ ነጥቡ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
በዚህም
→ የተሟላ ከሆነ (15 ነጥብ)፤
→ ከፊል ከሆነ (10 ነጥብ)፤
→ ዝቅተኛ/ጊዜያዊ (5 ነጥብ)፤
→ የሌለው ከሆነ (0 ነጥብ ) የሚሰጠው ይሆናል፡፡
iv. የካምፕ አደረጃጀት (15)፡- ይህ በሁለት መንገድ በመክፈል ታይቷል ሀ/ ለሰራተኛ ምቹ ሁኔታ መፍጠር (10 ነጥብ)
⇒ በዚህ መስፈርት እርሻው የሚመዘነው ለሰራተኛው በሚያቀርበው ወሳኝ አገልግሎት (የመኖሪያ ቤት፣ የመጠጥ ውኃ፣ ህክምና አገልግሎት፤ የመፀዳጃ ቤትና ሻውር ቤት፤ የመዝናኛ እና መመገቢያ አዳራሽ፣ ማብሰያ ቤት፤ የሰራተኛ የፍጆታ እቃና ምግብ አቅርቦት ሲሆኑ) እንደ አፈጻጸሙ ነጥብ የሚቀመጥላቸው ይሆናል፡፡
በዚሁ መሰረት አቅርቦቱ፡-
→ የተሟላ ከሆነ (10 ነጥብ)፤
→ ከፊል ከሆነ (5 ነጥብ)፤
→ ዝቅተኛ/ጊዜያዊ (2.5 ነጥብ)፤
→ የሌለው ከሆነ ( 0 ነጥብ ) የሚሰጠው ይሆናል፡፡ ለ/ ለስራ ምቹ ሁኔታ መፍጠር (5 ነጥብ)
⇒ በዚህ መስፈርት ወስጥ ባለሀብቱ ኢንቨስትመንቱን በአግባቡ እንዲመራና የገባውን ውል ለመፈጸም እንዲችል መሟላት የሚገባውን ምቹ የስራ ሁኔታ(የጽ/ቤት፤ የመጋዘን /
የማዳበሪያ፤ ኬሚካል፤ ምርት/ የእርሻ መሳሪያዎችና ማሽነሪዎች ጋራዥ/መጠለያ ግንባታ) ናቸው፡፡
በዚህም፡-
→ የተሟላ ከሆነ 5 ነጥብ፤
→ ከፊል ከሆነ 2.5 ነጥብ፤
→ ጊዜያዊ/ዝቅተኛ 1.25 ነጥብ፤
→ የሌለ 0 ነጥብ የሚሰጠው ይሆናል፡፡
v. የሠራተኛ ቅጥር (5 ነጥብ)
ይህ መመዘኛ ኩባንያው ስራውን አግባብነት ባላቸው ሰራተኞች እየመራ ስለመሆኑ ማረጋገጥ የሚቻልበት ሲሆን በሚሰራበት ክልል ተጨባጭ ሁኔታ በማገናዘብ አንድ እርሻ ሙሉ ነጥብ ለመስጠት ቢያንስ በሚከተሉት መስፈርቶች መሰረት የሚያስፈልገውን ሠራተኛ መቅጠር ሲችል ነው፡፡
⇒ በዚህም የመሬት ስፋቱ እየጨመረ በሚሄድበት ጊዜ ሥራው እየሰፋ ስለሚሄድ ይህንን ተከትሎ ለአነስተኛው የመሬት መጠን (ከ100 – 300 ሄ/ር) ታሳቢ ሆኖ እየጨመረ የሚሄድ 5 ሠራተኛ (አንድ ሥራ አስኪያጅ፣ አንድ የሰብል ልማት ባለሙያ፣ አንድ የሰብል ጥበቃ ባለሙያ፣ አንድ የሂሳብ ባለሙያ፣ አንድ የትራክተር ኦፕሬተር) ይሆናል የሚል ሆኖ ከክልሉ ነባራዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ፡-
⇒ ከ100 እስከ 300 ሄ/ር የተረከበ ባለሀብት ቢያንስ 3(ሶስት) ባለሙያ ቋሚ ሠራተኞች ሊኖሩት ይገባል፤
⇒ ከ301 እስከ 500ሄ/ር የተረከበ ባለሀብት ቢያንስ 5(አምስት) ቋሚ ሠራተኞች (አንድ ሥራ አስኪያጅ፣ አንድ የግብርና ባለሙያ፣ አንድ የሂሳብና የአስተዳደር ባለሙያ፣ ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ሁለት ባለሙያ) ሊኖሩት ይገባል፤
→ ከ501 እስከ 1000ሄ/ር የተረከበ ባለሀብት ቢያንስ 7(ሰባት) እና ከዛ በላይ ቋሚ
ሠራተኞች (ሥራ አስኪያጅ፣ የግብርና ባለሙያ፣ የሂሳብና የአስተዳደር ባለሙያ፣ ኦፕሬተሮች፣ ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ባለሙያዎች/ሠራተኞች) ሊኖሩት ይገባል፤
→ ከ1001 እና ከዛ በላይ ሄ/ር የተረከበ ባለሀብት አንድ ሥራ አስኪያጅ፣ አንድ ከፍተኛ የሰብል ልማት ባለሙያ፣ የሰብል ጥበቃ ባለሙያ እና 3(ሶስት) አሳሽ የሰብል ጥበቃ ባለሙያዎች፣ አስተዳደርና የሂሳብ ሠራተኛ እና ሌሎች ቋሚ ሠራተኞች(ካቦዎች፣ ጥበቃ፣ ምግብ አዘጋጅ…) በያንስ 15(አሥራምስት) ሠራተኞች ሊኖሩት ይገባል፣
በዚሁ መሰረት፡-
→ የተሟላ ባለሙያ ያለው 5 ነጥብ፤
→ በከፊል ያለው 2.5 ነጥብ፤
→ ምንም የሌለው 0 ነጥብ የሚሰጠው ይሆናል፡፡
vi. ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር ያለው የልማት ትስስርና መልካም ግኑኝነት (3 ነጥብ)
⇒ በዚህ መስፈርት ወስጥ ኩባንያው ኢንቨስትመንቱን በአግባቡ እንዲመራና የገባውን ውል ለመፈጸም እንዲችል ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር ያለው የልማት ትስስርና ማህበራዊ ግንኙነት የሚያካትት ይሆናል፡፡
በዚህም፡-
→ የተሟላ ከሆነ 3 ነጥብ፤
→ ከፊል ከሆነ 1.5 ነጥብ፤
→ ምንም ትስስር የሌለው ከሆነ 0 ነጥብ የሚሰጠው ይሆናል፡፡
10. የአፈጻጸም ደረጃ ፍረጃ
የአንድ በግብርና ኢንቨስትመንት እና ግብርና ምርት ውል ላይ የተሰማራ ኩባንያ ለማልማት ከገባው ውል አንጻር ያለውን የልማት ደረጃ ለመፈረጅ ከእያንዳንዱ መመዘኛ አንጻር የተቀመጡት ነጥቦች የሚደመሩ ሲሆን በዚሁ መሰረት አጠቃላይ ነጥቡ፡-
⇒ ከገባው ውል አንፃር ከ29% በታችና ምንም ያላሟላ ከሆነ በጣም ዝቅተኛ አፈፃፀም፣
⇒ ከገባው ውል አንፃር ከ30-39% ከሆነ ዝቅተኛ አፈፃፀም፤
⇒ ከገባው ውል አንፃር ከ40-59% ከሆነ አጥጋቢ አፈፃፀም፤
⇒ ከገባው ውል አንፃር ከ60-80% ከሆነ ከፍተኛ አፈፃፀም፤
⇒ ከገባው ውል አንፃር ከ80%› በላይ ከሆነ በጣም ከፍተኛ አፈፃፀም በሚል ይፈረጃል፡፡
11. የሚወሰዱ እርምጃዎች
በዘርፉ ያለው የልማት እንቅስቃሴ እንዳለ ሆኖ በገቡት ውል መሠረት የተሻለ አፈፃፀም ያላቸው የሚመሰገኑበት፣ የሚበረታቱበት፣ የሚደገፉበት እና አጠቃላይ አፈጻጸማቸው ተቀምሮ ለሌሎች ተደራሽ የሚሆንበት አሰራር የሚፈጠር ይሆናል፡፡
በሌላ በኩል ያለአግባብ መሬት ይዘው የተቀመጡ ወይም በገቡት ውል መሰረት ወደ ልማት ያልገቡ ኩባንያዎችን ወደ መስመር የማስገባትና በየደረጃው የማስተካከያ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ ነው፡፡
በዚሁ መሰረት ከላይ የተመለከቱትን አሰራሮች ተከትለው ከላይ በተቀመጡት መስፈርት መሰረት የተፈረጁ ባለሀብቶችን የመሬት ልማት ለማሻሻል የሚወሰዱ እርምጃዎች የተለዩ ሲሆን በዚሁ መሰረት፡-
ሀ. በጣም ከፍተኛ አፈጻጸም ያላቸው፡-
ከላይ የተመለከቱትን አሰራሮች ተከትለው በተደረገው ፍረጃ አፈፃፀማቸው በጣም ጥሩ የሆኑ ኩባንያዎች የሚበረታታና የምስጋና ደብዳቤ የሚሰጣቸው፣ እንዲሁም የተረከቡትን መሬት ሙሉ በሙሉ ያለሙ ከሆነ የማስፋፊያ መሬት ቢጠይቁ በመመሪያው መሰረት በቅድሚያ የሚሰተናገዱ ይሆናሉ፡፡ እንዲሁም አሰራራቸው ተቀምሮ ሌሎች እንዲማሩበት የሚደረግበት አግባብ የሚፈጠር ይሆናል፡፡
ለ. ከፍተኛ አፈፃፀም ያላቸው፡-
⇒ በዚህ ደረጃ የተፈረጁት በቀጣይ ይበልጥ እንዲበረታቱ ከመንግስትና ከሚመለከታቸው አካላት የቅርብ ክትትል እና ድጋፍ የሚደረግላቸው ይሆናል፡፡
ሐ. አጥጋቢ አፈጻጸም ያላቸው፡-
⇒ በአፈጻጸማቸው አጥጋቢ ውጤት ያገኙ ኩባንያዎች ጠንካራ እና ደካማ ጎናቸውን በመግለፅ በቀጣይ አሻሽለው እንዲፈፅሙ የመጀመሪያ የፅሁፍ ማሰጠንቀቂያ ደብዳቤ የሚሰጣቸው ይሆናል፡፡
⇒ በተግባር እንቅስቃሴም ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር የሚደረግባቸው ሲሆን በህግ ተጠያቂ የሚያደርግ ጉዳይ ከተገኘም በህጉ መሰረት የሚፈፀም ይሆናል፡፡
መ. ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸው፡-
⇒ በዚህ ደረጃ የተፈረጁ ኩባንያዎች የሚጠበቅባቸውን ልማት በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ እንዲያጠናቅቁ የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ የሚሰጣቸው ይሆናል፡፡
⇒ በተግባር እንቅስቃሴም ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር የሚደረግባቸው ሲሆን በህግ ተጠያቂ የሚያደርግ ጉዳይ ከተገኘም በህጉ መሰረት የሚፈፀም ይሆናል ይሆናሉ፡፡
ሠ. በጣም ዝቅተኛ አፈጻጸም ያላቸው፡-
⇒ በአፈጻጸማቸው በጣም ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸው 29 በመቶ ያመጡት ኩባንያዎች ያለሙትን መሬት ብቻ ሲቀር ያላለሙትን የሚመልሱና አዲስ ውል የሚገቡ የመጀመሪያው ውላቸው የሚቋረጥ፣ ምንም ያላለሙት ውላቸው የሚቋረጥ እና መሬትን በውሉና መመሪያ መሰረት የሚፈፀም ይሆናሉ፡፡
⇒ በተግባር እንቅስቃሴም ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር የሚደረግባቸው ሲሆን በህግ ተጠያቂ የሚያደርግ ጉዳይ ከተገኘም በህጉ መሰረት የሚፈፀም ይሆናል፡፡
12. የአፈጻጸም አቅጣጫ
ፍረጃው ከማንኛውም ነገር ነጻ ሆኖ በጥናቱ ውጤት ላይ ብቻ ተመስርቶ በጥንቃቄ ይፈጻማል፡፡ አንዳንድ ኩባንያዎች በሚሰሩበት ክልል ተጨባጭ ሁኔታ ምቹ የሥራ አካባቢ ሳይኖር በተረከቡት መሬት ላይ ማልማት ሲችሉ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት (ከፍርድ ቤት ጋር የተያያዙ ጉዳይ ያለባቸው፣ የመሬት ክርክር ያለባቸው፣ በተረከቡት መሬት ወረራና ሌላ ገብቶ መስፈርና ማረስ፣ የተፈጥሮ ሁኔታ፣ የጸጥታ ችግር ምክንያቶች ወ.ዘ.ተ ሳያለሙ ቢቀሩ ወይም እያለሙ ቢያቋርጡ ታሳቢ ተደርጎ ባለቡት ደረጃ በልዩ ሁኔታ ችግሩ እሰከ ሚፈታላቸው ድረስ ድጋፍ በሚደረግላቸው
መመዘኛ ውስጥ ይካተታሉ፡፡
13. ማጠቃለያ
ጥሩ ወጤት ያስመዘገቡ ኩባንያዎች ምርጥ ተሞክሮ በመቀመር በተመሳሳይ ስራ ላይ ለተሰማሩ ለሌሎች በማስፋት የቀጣይ አፈፃፀምን ለማሻሻል የሚያስችሉ አዳዲስ አሰራሮችን ለመቅረፅ እንደ መልካም አጋጣሚ ስለሚሆን፣ ከሌሎች ልምድ ለመማር (የሌሎችን ስህተት ላለመድገም) እንድሁም የሀገርንም ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከማሳድግ አኳያ ፈጣንና አወንታዊ የሆነ ወሳኝ ድርሻ አለው፡፡ እንደ ሀገርም የግብርና ኢንቨስትመንት እና የግብርና ምርት ውል አሰራር ከተጀመረ በርካታ አመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም ምርጥ ልምድ/ተሞክሮ ያላቸውን ኩባንያዎች አሰራር ቀምሮ ለሌሎች ተደራሽ እንዲሆን አልተደረገም፡፡ በመሆኑም ከላይ ያሉትን የምዘና መስፈርቶች በመጠቀም በእንስሳትና ዓሳ፣ በውል ምርት ውል/Contrat Farming/፣ በሰፋፊ እርሻ እና በሆርቲካልቸር ኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎችን በመገምገም የተሻለ አፈጻጸም ያላቸውን አፈጻጸማቸውን በመቀመርና ለሌሎች ተደራሽ በማድረግ ከዘርፉ የሚጠበቀውን ሁለንተናዊ ጠቀሜታ ለማስገኝት በትጋት መስራት ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከላይ በተዘረዘሩ መስፈርቶች መሰረት ድምር ነጥባቸው 80% እና ከዚያ በላይ ያመጡ ድርጅቶችን በመለየት ያላቸውን የአሰራር ልምድ (ምርጥ ተሞክሯቸውን) በመቀመር የማስፋት ስራ የሚሰራ ይሆናል፡፡