አበይት ግኝቶች የናሙና ክፍሎች

አበይት ግኝቶች. የሚከተሉትን ጉዳዮች ከግምት ውስጥ ያስገቡ፡ • መሬት ከመረከብ በፊት የቀረበ ይፋዊ መረጃና ምክክር መጠንና በመካሄድ ላይ ያለ ምክክር በቂነት • የተሰጠ ካሳ ዓይነትና የካሳው መጠን (ለምሳሌ፡ የጠፉ ንብረቶችን ለመተካት በቂ መሆን፣ የመኖሪያ ቤት ሁኔታዎች፣ ካሳ/ባለ- መብትነት፣ ገቢን ወደቀድሞ ሁኔታ መመለስና የኑሮ ዘላቂነት እርምጃዎች) • ጉዳዩ የነካቸው ሰዎች የካሳ ተመን፣ የአዲስ ሰፈራ ቦታዎችን በመለየትና የኑሮ ሁኔታን ወደ ቀድሞ ሁኔታ የመመለስ አማራጮችን የሚመለከቱ ውሳኔዎች ላይ ያላቸው የተሳትፎ ደረጃ • ከአካላዊ መዋቅር፣ ቦታ፣ የሐብቶችና አገልግሎቶች ተደራሽነት (ለምሳሌ፡ ጤና፣ ትምህርት፣ ውሃ እና ሳኒቴሽን፣ ትራንስፖርት፣ ማሕበራዊና የሕክምና ዋስትና፣ የግብርና እና የግጦሽ መሬት፣ የስራ ዕድሎች፣ የሥልጠና እና የማህበረሰብ ልማት ተነሳሽነቶች) በተመለከተ የምትክ ቤት በቂነት • የኑሮ ሁኔታን ወደ ቀድሞ የመመለሻ እርምጃዎች ውጤታማነት • ወደ አስተናጋጅ ማህበረሰቦች መዋሃድ • በባሕላዊ ንብረት ላይ የሚደርስ ተጽእኖ • ተጋላጭ ሰዎችና ቡድችን ለመከላከል የተወሰዱ እርምጃዎች • የቅሬታ አፈታት ሒደትና ውጤቶች ብቃት • የክትትልና ግምገማ ሒደትና ውጤቶች