አገልግሎቱ የሚያካትተው የናሙና ክፍሎች
አገልግሎቱ የሚያካትተው. አማካሪው ለግንባታው ስራ አስተዳዳር ስራ የቤቶቹን የመሠረት ግንባታ በተመለከተ ቀሪ የመሠረት ግንባታውን ለማጠናቀቅና የፍሳሽ መስመሮችን ለመዘርጋት የሚያከናውነው ሥራ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የመሠረት ድንጋይ ግንባታ ሥራ የምርጥ አፈር ሙሌት ሥራ የመሠረት አሳሪ አርማታ /ቢም/ መገንባታ ሥራ የወለል አርማታ ግንባታ ሥራ የፍሳሽ መስመሮችንና ፖሴቶችን የመዘርጋት ሥራ ሥራዎችን የሚያካትት ነው፡፡
4.1 የ11 ቤቶቹን ቀሪ ግንባታዎች ለማከናወን ባለቤቱን በመወከል የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችን ይቀጥራል፡፡
4.2 ለሥራ የሚያስፈልገውን የሠው ኃይል ስምሪት ከግንባታው የሥራ ሂደት ጋር አባሪ በማድረግ ይቆጣጠራል፡፡
4.3 ለሥራ የሚያስፈልገውን የግንባታ ዕቃዎች ባለቤቱን ወክሎ ይገዛል፣ በግንባታ ሥፍራው ላይ በመጋዘን /በጥበቃ እንዲቀመጥ ያደርጋል፡፡
4.4 ለሥራ የሚያስፈልገውን የገንዘብ ክፍያዎችን ባለቤቱን በመወከል ያካሂዳል፡፡