Contract
የምክር አገልግሎት የኮንትራት ውል
ተዋዋዮቹ
ይህ ኮንትራት ውል በዛሬ ቀን፣ 2007 ዓ.ም
በሚካኤል ብ/ሥላሴ አማካሪ አርክቴክት (ከዚህ ቀጥሎ አማካሪ ተብለው በሚጠሩት)
አድራሻ
እና በማስ የመኖሪያ ቤት ኃ/የተ/የኅ/ሥራ ማህበር
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ 10 ቀበሌ 16/18 ብሎክ
በሆኑት ከዚህ ቀጥሎ (አሠሪ /ባለቤት ተብለው በሚጠሩት) እና/ወይም
የአሠሪው ተወካይ
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ክ/ከተማ ወረዳ የቤት ቁጥር ስልክ ቁጥር በሆኑት መካከል የተደረገ ውል ነው፡፡
ይህንንም አስመልክቶ ሁለቱ ወገኖች ከዚህ ቀጥሎ በተዘረዘረው መሠረት ስምምነት አድርገዋል፡፡
የስምምነት መሠረቶች
አማካሪውና አሠሪ /ባለቤት በአሠሪው በማስ የመኖሪያ ቤት ኃ/የተ/የኅ/ሥራ ማህበር ንብረት በሆኑ 11 የመኖሪያ ቤቶች ላይ የግንባታው ሥፍራ አድራሻ አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ 10 ቀበሌ 16/18 ብሎክ በሆነ ቦታ ላይ 11 ተጀምረው ባልተጠናቀቁ የማህበሩ ቤቶች ላይ የመሠረት ግንባታ ሥራ እና የፍሳሽ ማጠራቀሚያ ስራ በተመለከተ አማካሪው የግንባታው ስራ አስተዳዳሪ በመሆን ቀሪ የግንባታ ሥራዎችን ለመጠናቀቅ በሁለቱ ወገኖች መሃከል የተደረገ ውል ነው፡፡
የሥራ ጊዜ
የአማካሪው የአገልግሎት ጊዜ ይህ ውል ከተፈረመ የ3 ወራት ጊዜ ሲሆን ከ ቀን 2007 ዓ.ም እስከ ቀን 2007 ዓ.ም ነው፡፡
2.3 የፕሮጀክቱ ዋጋ
ይህ ውል የተገባበት የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ዋጋ ብር 1,167,000.00 / / ሲሆን
የፕሮጀክቱ ዋጋ በፕሮጀክቱ ርዕስ እንደተጠቀሰው የ11 ቤቶቹን የመሠረት ሥራዎችና የፍሳሽ መስመሮችን ግንባታ ሥራ ለማጠናቀቅና ለአማካሪው ክፍያን የሚያጠቃልል ነው፡፡
2.4 አማካሪው ለሚሰጠው ሙያዊ አገልግሎት በየምዕራፉ ተከፋይ የሚሆን አጠቃለይ ዋጋ ብር 55,000.00 / /ነው፡፡
3 አገልግሎቱ የሚያካትተው
አማካሪው ለግንባታው ስራ አስተዳዳር ስራ የቤቶቹን የመሠረት ግንባታ በተመለከተ ቀሪ የመሠረት ግንባታውን ለማጠናቀቅና የፍሳሽ መስመሮችን ለመዘርጋት የሚያከናውነው ሥራ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን
የመሠረት ድንጋይ ግንባታ ሥራ
የምርጥ አፈር ሙሌት ሥራ
የመሠረት አሳሪ አርማታ /ቢም/ መገንባታ ሥራ
የወለል አርማታ ግንባታ ሥራ
የፍሳሽ መስመሮችንና ፖሴቶችን የመዘርጋት ሥራ
ሥራዎችን የሚያካትት ነው፡፡
አማካሪው ሥራውን ለማከናወን እንዲቻለው የተሰጠው ኃላፊነት
4.1 የ11 ቤቶቹን ቀሪ ግንባታዎች ለማከናወን ባለቤቱን በመወከል የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችን ይቀጥራል፡፡
4.2 ለሥራ የሚያስፈልገውን የሠው ኃይል ስምሪት ከግንባታው የሥራ ሂደት ጋር አባሪ በማድረግ ይቆጣጠራል፡፡
4.3 ለሥራ የሚያስፈልገውን የግንባታ ዕቃዎች ባለቤቱን ወክሎ ይገዛል፣ በግንባታ ሥፍራው ላይ በመጋዘን /በጥበቃ እንዲቀመጥ ያደርጋል፡፡
4.4 ለሥራ የሚያስፈልገውን የገንዘብ ክፍያዎችን ባለቤቱን በመወከል ያካሂዳል፡፡
5 የአማካሪው ግዴታዎች
አማካሪው ሥራውን ለማከናወን
ለሥራው የሚያስፈልገውን የግንባታ ባለሙያዎች ቀጥሮ ያሰማራል፡፡
የግንባታ ሥራውን ለመምራት እንዲያስችለው ለግንባታ ባለሙያዎች አስፈላጊውን መመሪያዎችንና ዝርዝር መግለጫዎችን ይሠጣል፡፡
የአማካሪው የግንባታውን ሥፍራ ላይ በተለያየ የግንባታ ወቅቶች መሀል ጉብኝት ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም ቢያንስ በሳምንት ሁለት ጊዜ የግንባታ ሥራውን ሂደት በስፍራው በመገኘት ይቆጣጠራል፣ አስፈላጊ በሆኑ የግንባታ እርከኖች የቁፋሮ መጠናቀቅና የአርማታ ሙሌት ከመከናወኑ በፊት ጉብኝት ያደርጋል፡፡
ለግንባታ ስፍራ የሚያስፈልጉትን የግንባታ ዕቃዎችና መሣሪዎችን ይገዛል፣ ያቀርባል፣ በመጋዘን /በጥበቃ እንዲቀመጡ ያደርጋል፡፡
አማካሪው በሚያደርገው ጉብኝት ብቃታቸው እና ደረጃቸው ያልተሟላ የግንባታ ዕቃዎችን በሥራው ውስጥ እንዳይካተቱ እየተቆጣጠረ እንዲወገዱ ያደርጋል፡፡
ለአሰሪ/ባለቤቱ ተወካይ እና ለግንባታ ኃላፊዎች ለምክር አገልግሎት ለመስጠት ቢሮውን ክፍት ሆኖ እንዲገኝ ያደርጋል፡፡
የተሰሩ ሥራዎችንና እርማት የሚያስፈልጋቸው እንዲታረሙ በማድረግ የተከናወኑ ሥራዎችን ከግንባታ ባለሙያዎች ና ስራ ተቆጣጣሪ ጋር ርክክብ ያደርጋል፡፡
አማካሪው የግንባታ ሥራ ዘገባዎችን /ሪፖርቶችን በየወሩ ለአሠሪው ባለቤት አዘጋጅቶ ያቀርባል፡፡
በፕሮጀክቱ መጠናቀቅ ጊዜ ወይም በሥራው መቋረጥ ጊዜ አማካሪው ለሥራ ላይ የዋሉትን ሰነዶች አጠቃሎ ለባለቤቱ ያስረክባል፡፡
የአሠሪ ባለቤት ኃላፊነት
አሠሪ ባለቤት
6.1 የተሟላ የመሰረት (ስትራክቸራል) ፕላን፣ የፍሳሽ መስመር ፕላንና የዋጋ ዝርዝርና ተመን ሰነድ ሁለቱ ወገኖች በተስማሙበት መልኩ ሥራው ከመጀመሩ በፊት ለአማካሪው ያስረክባል፡፡
የግንባታ ሥፍራውን በተመለከተ የቦታውን ካርታ ኮፒ እና ተጓዳኝ ሰነዶችን ለአማካሪው ያስረክባል፡፡
የግንባታ ሥራውን ቁጥጥር ለማካሄድ በግንባታው ስፍራ የራሱን የስራ ተቆጣጣሪ ይመድባል፡፡
የግንባታ ሥፍራውን በተመለከተ ከአስተዳደር ለሚነሱ የፍቃድ፣ የመረጃ ፣የክፍያ ወዘተ.. ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል፡፡
የግንባታ ሥፍራውን ጥበቃ በተመለከተ አማካሪው በውሉ መሰረት በግንባታው ስራ በተሰማራበት ጊዜ ውጪ ያለውን የጥበቃ ሰራተኞች ደሞዝ ክፍያዎችን የመክፈል ሃላፊነት አለበት፡፡
በግንባታው ሥፍራ ላይ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የውሃ፣ የኤሌክትሪክ፣ የስልክ ወዘተ… መስመሮችን ግብዓት ከሚመለከተው ክፍል ጋር በመነጋገር እንዲገባ ያደርጋል፡፡
በግንባታው ሥፍራ አስፈላጊ ለሚሆኑ የግንባታ ዕቃዎች መግዢያና የሠራተኞች ክፍያ የሚሆነውን ገንዘብ በየምዕራፉ (ከዚህ ከታች እንደተመለከተው) ለአማካሪው ይሰጣል፡፡
1 |
የመሰረት ስራ 1 |
|
|
1.1 |
ለመሰረት ግንብ ስራ የአፈር ቁፋሮ ስራ |
13,316.11 |
|
1.2 |
የመሰረት ድንጋይ ግንብ ልክ የምርጥ የአፈር ሙሌት ስራ |
117,704.28 |
|
1.3 |
የድንጋይ መሰረት ግንብ ስራ |
114,543.00 |
|
|
|
245,563.39 |
245,000.00 |
3 |
የመሰረት ስራ 3 |
242,000.00 |
|
3.1 |
የመሰረት አሳሪ አርማታ (ቢም) ስራ |
294,016.87 |
|
|
የፍሳሽ ቱቦዎች የመዘርጋት ስራ |
49,500.00 |
|
|
|
343,516.87 |
345,000.00 |
2 |
የመሰረት ስራ 2 |
245,563.39 |
|
2.1 |
የፍሳሽ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ አፈር ቁፋሮ ስራ |
242,000.00 |
|
2.2 |
የፍሳሽ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ የድንጋይ ግንብ ስራ |
|
|
|
|
242,000.00 |
245,000.00 |
4 |
የመሰረት ስራ 3 |
|
|
4.1 |
የድንጋይ መስተሻታ ሙሌት ስራ |
93,537.58 |
|
4.2 |
የመሰረት የአርማታ ወለል ስራ |
221,515.95 |
332,000.00 |
|
|
|
|
|
|
315,053.53 |
1,167,000.00 |
አማካሪው ለሚሰጠው የግንባታ የአሰተዳደር ስራ አገልግሎት ከታች በክፍል 7 እነደተመለከተው በየምዕራፉ ክፍያን ያከናውናል፡፡
የግንባታው ስራ የመጀመሪያው ክፍያ እነደተከናወነ በሰባት ቀናት ውስጥ ይሆናል፡፡
አሠሪ ባለቤት በየዕምራፉ ለግንባታው ስራ አሰፈላጊ የሆነውን ክፍያ ከአማካሪው ጥያቄ በቀረበለት በአስር ቀናት ውስጥ ያስረክባል
የግንባታው ሥራው እነደተጠናቀቀ ስራውንና የግንባታውን ስፍራውን በስፍራው በመገኘት ይረከባል፡፡
7 አከፋፈል
አማካሪውን የግንባታውን ስራ በማስተዳደር ለሚሰጠው አገልግሎት አሠሪ/ባለቤት ከዚህ እንደሚከተለው ለአማካሪው ክፍያዎችን ያከናውናል፡፡
7.1 የመጀመሪያ ክፍያ ይህ የኮንትራት ውል በሚፈረምበት ቀን
ብር 17,500.00 / /
የሁለተኛ ክፍያ የሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ ስራ እንደተጠናቀቀ
ብር 12,500.00 / /
የሶስተኛ ክፍያ የሶስተኛው ምዕራፍ ግንባታ ስራ እንደተጠናቀቀ
ብር 12,500.00 / /
የአራተኛ ክፍያ የአራተኛው ምዕራፍ ግንባታ ስራ እንደተጠናቀቀ
ብር 12,500.00 / /
ይህ ክፍያ አማካሪው የሚፈለግበትን መክፈል የሚገባውን ግብር ያካተተ ነው፡፡
8 ስለሚዘገዩ ክፍያዎች
ለአማካሪው በውሉ መሠረት መከፈል የሚገባቸው ክፍያዎች ክፍያው በተጠየቀ በአምስት ቀናት ውስጥ መከፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ክፍያው ከአስር ቀናት በላይ ከዘገየ በእያንዳንዱ ተጨማሪ ቀን መከፈል የሚገባውን ገንዘብ 1/100ኛ ለአማካሪው በተጨማሪነት እንዲከፈል ይደረጋል፡፡
9 ሥራን ማስተላለፍ ማቋረጥ ወይም መሰረዝን በተመለከተ
9.1 አሰሪው ባለቤት ሥራውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የሥራውን ጊዜ ቢያሸጋግር፣ ቢያቋርጥ ወይም ቢሰርዝ አማካሪው ሥራው እስካቆመበት ጊዜ ድረስ የተሠራው ሥራ ተሰልቶ የሚገባውን ክፍያ ሊከፍለው ይገባል፡፡ በነዚህ ምክንያቶች ሥራው መቋረጥ ቢያስፈልግ ባለቤቱን ለአማካሪው የ20 ቀናት ቅድመ ማስታወቂያ ይሰጣል፡፡ በተመሳሳይም አማካሪው ሥራውን ማቋረጥ ቢኖርበት ለባሌቱ በ20 ቀናት ቅድመ ማስታወቂያ ይሰጣል ፣ የግንባታውን ስራ ለአሰሪው ያስረክባል ፡፡
9.2 የግንባታ ስራው በየምዕራፎቹ መጠናቀቅ መሃል፣ ለቀጣዩ ምዕራፍ አሰሪው ባለቤት ክፍያን ባለመልቀቅ ምክንያት ስራው ከሶስት ወር በላይ ቢቋረጥ ይህ ውል እንደተቋረጠ ይቆጠራል፡፡ ሆኖም ግን ሁለቱ ወገኖች በሚስማሙበት መሰረት ውሉ ሊታደስ ይችላል፡፡
አባሪ የተደረጉ ሰነዶች
የአሰሪ/ባለቤቱ የግንባታው ሥፍራ የፍቃድና የካርታ ኮፒ
የመሰረት ስራ ሰትራክቸራልና ፍሳሽ መስመር ፕላኖች
የአማካሪው የሙያ ፈቃድ ኮፒ ናቸው፡፡
ይህ ውል በሁለት ዋና ቅጂዎች ተዘጋጅቷል፤ እያንዳንዱ ዋና ቅጂ በሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች እጅ ይገኛል፤ ሁለቱም ቅጂዎች እኩል ሕጋዊ ዋጋ አላቸው፡፡
ይህ ውል አስመልክቶ ሁለቱ ወገኖች ውሉን ለማፅደቅ በሁለቱ ወገኖች ስምና ማህተም ፈርመው ውሉ ከዛሬ ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ሆኗል፡፡
አማካሪ አሠሪ/ ባለቤት
ስም ስም
ፊርማ ፊርማ
ቀን ቀን
እማኞች
ስም ፊርማ ስ.ቁ
1
2
3
Xxxxxxx X/S consulting Architect draft contract agreement with Mass Housing March 10, 2015 4/5 | Page