የምርጥ ተሞክሮ/ልምድ ትርጉም. አንድ ተቋም/ድርጅት ያለውን የሥራ አፈፃፀም ከሌሎች ተቋማት ከወጪ፤ ከጥራትና ከቅልጥፍና አንጻር ያላቸውን ልምድና የላቀ አፈጻጸም በማነጻጸር ወደ ተሻለ ውጤት መድረስን የሚያረጋግጥ፤ በአነስተኛ ወጪና ጥረት የላቀ ውጤት የሚመጣበት፣ ችግሮችን ለመፍታትና ስኬትን ለማምጣት ጥቅም ላይ የሚውል፤ ተከስተው የነበሩ ስህተቶች እንዳይደገሙ ማድረግ የሚቻልበትም ስልት/ሥነ-ዘዴ ነው፡፡ በአጠቃላይ በአንድ ተቋም ያለ የላቀ ልምድና ውጤት (በአሰራሩ፤ በአደረጃጀቱ፤ ወዘተ) ተመሳሳይ በሆኑ ተቋማት በመውሰድ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር አጣጥሞ በመጠቀም ከፍተኛ ስኬት ማምጣት የሚያስችል ልምድ ነዉ፡፡