የቅሬታ አፈታት ስርዓት አስፈላጊ ሁኔታዎችና ሒደት አጠቃላይ አስፈላጊ ሁኔታዎች የናሙና ክፍሎች

የቅሬታ አፈታት ስርዓት አስፈላጊ ሁኔታዎችና ሒደት አጠቃላይ አስፈላጊ ሁኔታዎች. የቅሬታ አፈታት ስርዓት የ CFM ሰፊ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ተግባራትን የሚደግፍና የሚያጠናክር ነው፡፡ ከማህበረሰቦችና ባለድርሻ አካላት ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖር ለማስቻል ተነሳሽነቱን የሚወስድ ተሳትፎ አስፈላጊ ነው፡፡ የቅሬታ አፈታት ስርዓቱ ብቻውን መተግበር የለበትም፡፡ • ለመጀመሪያ ጊዜ ሲከሰትና በተቻለ መጠን ቅሬታ የሚፈጠርበትን ሁኔታ ለማስቀረት ሲባል፣ CFM በዓለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎች መሰረት ተነሳሽነቱን ወስዶ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ስራዎችን ያረጋግጣል፡፡ • ማንኛውም የሚመለከተው ወገን ቅሬታ መቅረብ ይችላል፡፡ ከእነርሱም መካከል በ CFM ፕሮጄክቶችና ተግባራት በቀጥታና በተዘዋዋሪ የተነኩ ማህበረሰቦች፣ የሲቪል ማህበረሰብ፣ የአካባቢና ባሕላዊ ባለስልጣናት፣ የአካባቢ ወይም ሃገራዊ መንግስት፣ የአነስተኛ ንግድ ባለቤቶች፣ ማህበራት፣ የሕክምና እና የትምህርት ባለሙያዎች፣ መያዶች እና ዓለም አቀፍ ሶስተኛ ወገኖች ይገኙበታል፡፡ • CFM ተጨባጭና ታሳቢ ተጽእኖዎችን ተቀብሎ የሚያስተናግደው በተመሳሳይ መንገድና በተመሳሳይ የጥንቃቄ ደረጃ ነው፡፡ • የቅሬታ አፈታት ስርዓት ዓላማ መደበኛም ሆኑ ኢ-መደበኛ ጥቃቅን ቅሬታዎችንም ቢሆን በመፍታት ወደ ከባድ ቅሬታነት እንዳያድጉ መከላከል ነው፡፡ • በተቻለ መጠን በፕሮጄክቱ/በወጪ አሸፋፈን ዘመን መጀመሪያ ላይ ከማህበረሰቡ ቅሬታዎችን መሰብሰቢያና ማስተላለፊያ መንገዶች ይዘረጋሉ፡፡