አዴራሻ፡- ቦላ ክፍሇ ከተማ ቦላ መዴኃኒዓሇም አካባቢ ሸገር ሕንጻ 7ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 706 ስሌክ፡ + 251 938 48 38 21 ኢ-ሜይሌ: info@hybriddesignsplc.com
ቀን 2013 ዓ.ም
ይህ ውሌ የኪራይ መኪና አገሌግልት ሰጪዎች የትራንስፖርት ቴክኖልጂ ተጠቃሚ እንዱሆኑ ሇማዴረግ የተዯረገ የስምምነት ውሌ ነው
`` አንቀጽ አንዴ
ስሇ ተዋዋዮች
ይህ ውሌ በውሌ ሰጪ ሃይብሪዴ ዱዛይን ኃ/የተ/የግሌ ማኅበር (ከዚህ በኋሊ ‚አቅራቢ‛ ወይም ‚ራይዴ‛ በመባሌ የሚጠራ) ዴርጅት
አዴራሻ፡- ቦላ ክፍሇ ከተማ ቦላ መዴኃኒዓሇም አካባቢ ሸገር ሕንጻ 7ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 706 ስሌክ፡ + 251 938 48 38 21 ኢ-ሜይሌ: xxxx@xxxxxxxxxxxxxxxx.xxx
አዱስ አበባ፣ ኢትዮጵያ እና
በውሌ ተቀበይ (ስም): የሰላዲ ቁጥሩ:
የጎን ቁጥሩ:
የአሽከርካሪ የመንጃ ፍቃዴ ቁጥር:
የሆነ አሽከርካሪ ወይም የኪራይ መኪና ባሇንብረት (ከዚህ በኋሊ ‚አገሌግልት ሰጪ‛ በመባሌ የሚጠራ) አዴራሻ፡- ክ/ከተማ፣ ወረዲ: _ የቤት ቁጥር:
ስሌክ፡ + 251 ኢ-ሜይሌ (ካሇ): አዱስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
አንቀጽ ሁሇት የውለ ዓሊማ
2.1. የዚህ ውሌ ዓሊማ የትራንስፖርት ቴክኖልጂ አቅራቢው፣ ከሚመሇከተው የመንግስት አካሌ ህጋዊ ፍቃዴ ተሰጥቷቸው ከሚሰሩ የኪራይ መኪና አገሌግልት አካሊት ጋር የጋራ ዯንበኞቻቸው በሚፈሌጉት መሌኩ ዓሇም አቀፍ ዯረጃውን የጠበቀ አስተማማኝ፣ ምቹ እና ቀሌጣፋ የኪራይ መኪና አገሌግልት፣ ሇተወሰነ ወይም ሊሌተወሰነ ጊዜ፣ ቦታ፣ እንዱሁም ርቀት ሊይ አገሌግልት ሇመስጠት እንዱያስችሊቸው የተፈጸመ ሲሆን፤ ዯንበኛው የትራንስፖርት ቴክኖልጂን ተጠቅሞ እንዱጓጓዝ፣ የኪራይ መኪና አገሌግልት ሰጪውም በቴክኖልጂው በመታገዝ ሇሚያገኛቸው ተጠቃሚዎች በዚህ ውሌ መሰረት የአገሌግልት ጥራት፣ ዯረጃና መመሪያዎችን አክብሮ ሇዯንበኞች አገሌግልት ሇመስጠት በመፈሇግ እና ሇሚያገኘው የቴክኖልጂ አገሌግልትም ከዚህ በታች በተመሇከተው የገንዘብ ተመን መሠረት ሇአገሌግልት አቅራቢው ክፍያ ሇመፈጸም በመስማማት ይህንን ስምምነት ተዋውሇናሌ፡፡
አንቀጽ ሶስት የአቅራቢ ግዳታዎች
3.1. ራይዴ (RIDE) የተባሇ የትራንስፖርት አገሌግልት ሰጪዎች ሇመጥራት እና ሇማስተናገዴ የሚውለ የትራንስፖርት ቴክኖልጂ መተግበሪያ ሇአገሌግልት ሰጪ ያቀርባሌ፣
3.2. በቴክኖልጂ የተዯገፈ የትራንስፖርት አገሌግልትን ሇማህበረሰቡ ማስተዋወቅ የሚያስችሌ የተሇያዩ የማስተዋወቂያ ስራዎችን ያከናውናሌ፣
3.3. አገሌግልት ሰጪው ስራውን እና አገሌግልቱን በመሌካም ስነምግባር፣ በተሳካ እና በተሳሇጠ መንገዴ እንዱሰጡ ይረዲቸው ዘንዴ አስፈሊጊውን የቴክኖልጂ አጠቃቀም፣ የስራ ስነ-ምግባር እና የዯንበኛ አያያዝ እና ተያያዥ ጉዲዮችን በዘርፉ በተመረጡ ባሇሞያዎች ስሌጠናዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ያቀርባሌ፡፡
አንቀጽ አራት የአገሌግልት ሰጪ ግዳታዎች
4.1 በአቅራቢው የትራንስፖርት መተግበሪያ ቴክኖልጂ ብቻ የሚቀርብሇትን የትራንስፖርት ጥሪ በመቀበሌ አገሌግልቱን ሇተጠቃሚዎች በፍጥነት ያቀርባሌ፣
4.2 የኪራይ መኪናውን የሚያሽከረክረው ከባሇቤቱ ውጭ በተቀጣሪ አሽከርካሪ ከሆነ ይህንን የሚያሳይ ህጋዊ የቅጥር ውሌ ያቀርባሌ፣
4.3 በተመዘገበው መኪና አገሌግልቱን ሇተጠቃሚዎች በሚሰጥበት በማናቸውም ጊዜ አሽከርካሪው የሚከተለትን ማከናወን ይጠበቅበታሌ፡-
4.3.1 ንፁህ ሸሚዝ እና በዯንብ የተተኮሰ ሱሪ መሌበስ፣
4.3.2 የኪራይ መኪናውን ውስጣዊም ሆነ ውጫዊ ጽዲትና ውበት መጠበቅ፣
4.3.3 ተሳፋሪውን በቅንነት እና ረጋ ባሇ መሌኩ የማናገር እንዱሁም ማስተናገዴ፣
4.3.4 ተሳፋሪውን ምቾት እና የጋራ ዯህንነት በጠበቀ መሌኩ በጥንቃቄ ማሽከርከር፣
4.3.5 ተሳፋሪ ወዯ ተሽከርካሪው ከመግባቱ በፊት ዯኅንነቱና ምቾቱ የሚጠበቀው ከኋሊ ወንበር ሲቀመጥ እንዯሆነ በትህትና የማሳሰብ፤ ተሳፋሪው ማሳሰቢያውን ከሰማ በኋሊ ከፊት ወንበር ሊይ ሇመቀመጥ ከመረጠ የተሳፋሪውን ምርጫ መቀበሌና፣
4.3.6 አገሌግልቱን በሚሰጥበት ማናቸውም ጊዜ ተንቀሳቃሽ ስሌኩን ተሳፋሪው በቀሊለ ሉያየው በሚችሌበት ቦታ በስሌክ ማስቀመጫ ሊይ ማስቀመጥ፣
4.3.7 የኪራይ መኪና አገሌግልት በሚሰጥበት በማናቸውም ጊዜ የግሌ ችግር ሇተሳፋሪ ያሇማጫወት፣
4.3.8 በተሳፋሪዎች መካከሌ ሌዩነት ወይም መዴል ሳያሳዴር የተሳፋሪዎቹን ሻንጣ ወይም በተሽከርካሪው ሊይ ሇመጫን የተፈቀዯሊቸውን ዕቃ ሲጭኑ በቅንነት የማገዝ፣
4.3.9 በጉዞ መስመር ሊይ ተሳፋሪው ወዯሚዯርስበት ስፍራ ሇመጓዝ ከአንዴ በሊይ አማራጭ መንገድች ካለ ጉዞውን ከመጀመሩ በፊት ተሳፈሪው በየትኛው አማራጭ ሉጓዝ እንዯሚፈሌግ የመጠየቅ እና ከአማራጭ መንገድቹ አጭሩን የጉዞ መስመር መርጦ የመጓዝ፣
4.3.10 ተሳፋሪዎቹ አረጋውያን፣ እርጉዝ ሴት፣ ታካሚዎች ወይም አካሌ ጉዲተኞች ወይም ዴጋፍ የሚሹ ማናቸውም ሰዎች ከሆኑ ሇመሳፈርም ሆነ ሇመውረዴ እንዯሚመቻቸው ተገቢውን ዴጋፍ፣ እንክብካቤና ፍቅር በመሇገስ ያሇአዴል ትብብር የመስጠት፣
4.3.11 በዝናብ ወቅት ተሳፈሪው ወዯ ተሸከርካሪው ሲገባም ሆነ ሲወርዴ ዣንጥሊ በመያዝ የማገሌገሌ፣
4.3.12 የኪራይ መኪና አገሌግልት በተጠየቀ በ10 ዯቂቃ ውስጥ ወዯ ተሳፋሪው የመዴረስ፣ ቀዴሞ ሇተያዙ ትዕዛዞች ከ10 ዯቂቃ በፊት ተሳፋሪው ወዲሇበት የመዴረስ፣ በ10 ዯቂቃ ውስጥ ወይም ቀዯም ብል ተሳፋሪው ወዲሇበት ሇመዴረስ የማያስችሌ፣ ካቅም በሊይ የሆነ እክሌ ከገጠመው ሇራይዴ የስሌክ ጥሪ ማዕከሌ የአገሌግልት ሇውጡን ቀዯም ብል ከ20 ዯቂቃ በፊት የማሳወቅ እና ወዯ ተሳፋሪው ስሌክ በመዯወሌ የማሳወቅ እና የመመካከር፣
4.3.13 የኪራይ መኪና አገሌግልት በሚሰጥበት በማናቸውም ጊዜ በጥንቃቄና በትራፊክ መቆጣጠሪያ ዯንቦች በተፈቀዯ ሕጋዊ የፍጥነት ወሰን የማሽከርከር፣
4.3.14 ዯኅነንቱና ምቾቱ የተጠበቀ የኪራይ መኪና አገሌግልት ሇመስጠት በአካሌና በመንፈስም ዝግጁ ሇመሆን ያስችሇው ዘንዴ የዴካም ስሜት በተሰማው ጊዜ በቂ እረፍት የማዴረግ፣
4.3.15 የኪራይ መኪና አገሌግልት በሚሰጥበት በማናቸውም ጊዜ የዯኅነነት ቀበቶ (ሲት ቤሌት) የማሰር እና ተሳፋሪው በፊተኛው ወንበር ሇመቀመጥ ከመረጠ የዯኅነነት ቀበቶ (ሲት ቤሌት) እንዱያሥር በትህትና የማሳሰብ፣
4.3.16 የኪራይ መኪና አገሌግልት በሚሰጥበት ማናቸውም ጊዜ በትራፊክ መጨናነቅ፣ ፀባያቸው ወይም ባህሪያቸው የማይስማማ ተሳፋሪዎች በመጫኑ ወይም በሦስተኛ ወገኖች ዴርጊት መነሻነት በተሳፋሪዬ እና በእኔ በአሽከርካሪውም መካከሌ አሇመግባባት ወይም የስሜት መጋሌ ከተከሰተ አሇምግባባቱን በሰከነ መንፈስ የመፍታት እና በጊዜው ሇጥሪ ማዕከሌ ማሳወቅ፣
4.3.17 ከአቅራቢው ሇሚመጣ ጥሪ የራይዴ ቴክኖልጂ ከሚያሰሊው የአገሌግልት ዋጋ በሊይ ተሳፋሪን ያሇመጠይቅና ያሇማስከፈሌ፣ የቴክኒካሌ ብሌሽት ካጋጠመው ወይም ከተሳፋሪ ቅሬታ ከተነሳ ከማስከፈሌ በፊት ሇጥሪ ማዕከሌ የማሳወቅ፣
4.3.18 የኪራይ መኪና አገሌግልት በሚሰጥበት ማናቸውም ጊዜ በማሽከርከር አካሊዊም ሆነ አዕምሮአዊ ብቃት ወይም በባህሪ ወይም በሁሇቱም ሊይ ተጽዕኖ ማዴርግ ከሚችለ ማናቸውም የአሌኮሌ መጠጥ፣ ጫት፣ አዯንዛዥ ዕጽ ወይም ማናቸውም ነገር ነጻ ሆኖ የመገኘት፣
4.3.19 የኪራይ መኪና አገሌግልት በሚሰጥበት በማናቸውም ጊዜ ተሳፋሪ የሚወርዯው ጨሇማ በሆነ አካባቢ ከሆነ የተሽከርካሪን ወይም ላሊ ማቸውም መብራት በማብራት ተሳፋሪ ወዯሚገባበት ስፍራ እስኪገባ ቆሞ የመጠበቅ፣
4.3.20 አገሌግልት በሚሰጥበት በማናቸውም ጊዜ ተሽከርካሪን ከማንኛውም መጥፎ ጠረን የጸዲ የማዴረግ፣
4.3.21 አገሌግልት በሚሰጥበት ማናቸውም ጊዜ ሇሚሰጠው አገሌገልት በተሸክርካሪ ውስጥም ሆነ ውጪ ከራይዴ ፈቃዴ ያሌተሰጣቸውን የቴክኖልጂ መተግበሪያዎች (አፕሉኬሽንስ) ያሇመጠቀም፣
4.3.22 ከአቅራቢው የፅሁፍ ፈቃዴ ሳያገኝ ሇሚሰጠው የትራንስፖርት ጥሪ አገሌገልት ከራይዴ በተቀበሇው ስሌክ ሊይ ምንም አይነት የቴክኖልጂ መተግበሪያዎች (አፕሉኬሽንስ) ያሇመጫን እና ከራይዴ ሥራ ውጪ ያሇመጠቀም፣
4.3.23 ከአቅራቢው የፅሁፍ ፈቃዴ ሳሊገኝ ሇሚሰጠው የትራንስፖርት ጥሪ አገሌገልት የግሌ አካውንት እንዱሁም በራይዴ የተመዘገበ ሲም ካርዴን ላሊ ሰው እንዱገሇገሌበት ያሇመስጠት፣
4.3.24 የኪራይ መኪና አገሌግልት በሚሰጥበት ማናቸውም ጊዜ የራይዴን የቴክኖልጂ መተግበሪያ (አፕሉኬሽን) መጠቀም ወይም ስሌክ መጠቀም ካስፈሇገኝ ተሸከርካሪን የማቆም፣
4.3.25 የኪራይ መኪና አገሌግልት በማሌሰጥበት ማናቸውም ጊዜ በጉዞ ወቅት የራይዴን የቴክኖልጂ መተግበሪያ (አፕሉኬሽን) ‘ከአገሌግልት ውጭ’ ‚Offline‛ ሊይ የማኖር፣
4.3.26 የኪራይ መኪና አገሌግልት በሚሰጥበት ማናቸውም ጊዜ ተሽከርካሪንም ሆነ እራሱ አሽከርካሪውን የሚመሇከቱ ማናቸውም ሕጋዊ ሰነድችን አሟቶ የመገኘት፣
4.3.27 የኪራይ መኪና አገሌግልት በሚሰጥበት ማናቸውም ጊዜ በራይዴ የሚወጡትን የሥራ መመሪያዎች የመከታተሌና የመተግበር፣
4.3.28 የሚገሇገሌበት የራይዴን የቴክኖልጂ መተግበሪያ (አፕሉኬሽን) አገሌግልት ካሰባት ቀን ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሇራይዴ የማሳወቅ፣
4.3.29 አገሌግልት የሰጠበትን ቀሪ ሒሳብ አቅራቢው በተጣሇው የጊዜ ገዯብ ውስጥ የማወራረዴ፣
4.3.30 የሚገሇገሌበት የአቅራቢ ቴክኖልጂ መተግበሪያ (አፕሉኬሽን) የተሳሳተ ወይም እሊፊ ሂሳብ ከቆጠረ ሇራይዴ ጥሪ ማዕከሌ ወዱያውኑ የማሳወቅ፣
4.3.31 የኪራይ መኪና አገሌግልት ሇመስጠት ከአቅራቢው የተቀበሊቸውን ማናቸውም የቴክኖልጂ መሣሪያ በጥንቃቄ ሇመያዝ፣ ሇመገሌገሌና በራይዴ በተጠየቅኩኝ ጊዜ የመመሇስ፣
4.3.32 ከአቅራቢው ሠራተኞች ጋር ጥሩ ግንኙነትን የፍጠርና በመግባባት መሥራት፣
4.3.33 የሚገሇገሌበትን የቴክኖልጂ መተግበሪያ (አፕሉኬሽን) ቢያንስ በወር አንዴ ጊዜ ራይዴ መሥሪያ ቤት በመዯወሌ ወይም በአካሌ በመገኘት የማሳየት እና የማስተካከሌ፣
4.3.34 የኪራይ መኪና አገሌግልት በሚሰጥበት ማናቸውም ጊዜ በአገሪቱ የሚገኙትን የተሇያዩ የወንጀሌ እና የፍታብሔር ሕግጋት፣ የራይዴን መተዲዯሪያ ዯንብን እንዱሁም ይህንን ውሌ በመጣስ ሇሚጣሌ ማንኛውም ቅጣት ኃሊፊነት የመውሰዴ፣ እና
4.3.35 የኪራይ መኪና አገሌግልት በሚሰጥበት ማናቸውም ጊዜ የሚፈጠሩ ማንኛውንም አሇመግባባቶችን በሥነ ምግባር፣ በሕግና በዯንብ መሠረት የመፍታት ግዳታ አሇበት፡፡
4.4 በአሽከርካሪው የራይዴ አፕሌኬሽን ሊይ የተመዘገበን ታርጋ ብቻ የያዘ መኪና እያሽከረከረ የራይዴ አገሌግልት ሇመስጠት፤ ታርጋ ቁጥሩ አፕሌኬሽኑ ሊይ በስህተት ከተመዘገበ ወዱያው ሇራይዴ ጥሪ ማዕከሌ ሇማሳወቅ፡፡
4.5 የተሳፋሪን አንዴ ሻንጣ ያሇ ክፍያ በነፃ የመጫን ግዳታ አሇበት፡፡ ነገር ግን የሻንጣው ብዛት ከ 1 በሊይ በሆነ ጊዜ በእያንዲንደ ሻንጣ ብር 25.00 (ሃያ አምስት ብር) በማስከፈሌ የሚጭን ይሆናሌ ፡፡
4.6 የመኪናው ዯህንነት መጠበቅ ያስችሌ ዘንዴ በየ 6 ወሩ ራይዴ በመዯበበት የቁጥጥር ጋራዥ በማቅረብ መኪናውን የማስመርመር ግዳታ አሇበት፤
4.7 አገሌግልት ሰጪው በየ3 ወር በአካሌ የራይዴ ጽ/ቤት ቀርቦ አገሌግልት የሚሰጥበትን ሞባይሌ ሇፍተሻ ማቅረብ እና ስሌክ ሊይ የተሇጠፈው ማሳሰብያ እንዱታዯስ ማዴረግ፡፡
4.8 የሚጠቀምበት የራይዴ የግሌ አካውንት የተጫነበት ስሌክ በማናቸዉ ምክንያት ቢጠፋ በራይዴ ጽ/ቤት በአካሌ ቀርቦ በ48 ሰዓት ውስጥ ማሳወቅ አሇበት ፡፡
አንቀጽ አምስት የአገሌግልት ክፍያን በተመሇከተ
5.1 የኪራይ መኪና አገሌግልት ሰጪው ሇዯንበኛ አገሌግልት በመስጠት ከሚያገኘው ገቢ ከዚህ በታች በተመሇከተው መሰረት ሇአቅራቢው ክፍያ የሚፈፅም ይሆናሌ፦
5.1.1 አሽከርካሪው በ 1 ወር ውስጥ በጠቅሊሊ ከ120 በሊይ ስራዎችን ካከናወነ በጥቅለ 12% (10.2% ኮምሽን + 1.8% ተጨማሪ እሴት ታክስ) ይከፍሊሌ፣
5.1.2 አሽከርካሪው በ 1 ወር ውስጥ በጠቅሊሊ ከ61 እስከ 119 ስራዎችን ካከናወነ በጥቅለ 15% (12.75% ኮምሽን + 2.25% ተጨማሪ እሴት ታክስ) ይከፍሊሌ፣
5.1.3 አሽከርካሪው በ 1 ወር ውስጥ በጠቅሊሊ ከ60 በታች ስራዎችን ካከናወነ በጥቅለ 17% (14.45% ኮምሽን + 2.55% ተጨማሪ እሴት ታክስ) ይከፍሊሌ፣
5.1.4 በወር በጠቅሊሊው ከ30 በታች ስራዎችን ብቻ ካከናወነ 250.00 ብር የአገሌግልት ክፍያ የሚከፍሌ ይሆናሌ::
5.1.5 ዴርጅቱ ባዘጋጀው ማንኛውም የእርዲታ ፕሮግራሞች ሊይ ሌሳተፍ ካሌሆነ አስቀዴሜ በዯብዲቤ የይሇፈኝ ማሳሰብያ ሌሰጥ
አንቀጽ ስዴስት
ውለ ስሇሚቋረጥበት ሁኔታና ስሇ ቅጣት
6.1 ይህ ውሌ በሚከተለት ምክንያቶች ሉቋረጥ ይችሊሌ፡-
6.1.1 የኪራይ መኪና አገሌግልት ሰጪው በዚህ ውሌ ውስጥ የተጣለበትን ግዳታዎች ያሇበቂ ምክንያት ሳይፈጽም ከቀረ አቅራቢው ይህን የስምምነት ውሌ ሇመሰረዝ ይችሊሌ፣
6.1.2 ተገሌጋዮች የኪራይ መኪና አገሌግልት ሰጪውን በተመሇከተ ቅሬታ ካቀረቡበት፣ ቴክኖልጂ አቅራቢው የቀረበውን አቤቱታ በማጣራት ጥፋት ነው ብል ካመነበት ያሇ ምንም ማስጠንቀቂያ በተናጥሌ ውለን ሇመሰረዝ ይችሊሌ፣
6.1.3 አቅራቢው በውለ ውስጥ የተቀመጡትን ግዳታዎች በተመሳሳይ ሁኔታ ሳይፈጽም ከቀረ የኪራይ መኪና አገሌግልት ሰጪው ጉዴሇቱ በአንዴ ወር ውስጥ እንዱስተካከሌሇት በፅሁፍ ጠይቆ ማስተካከያ ካሊገኘ ውለን ማቋረጥ ይችሊሌ፣
6.1.4 አገሌግልት ሰጭ ሇአቅራቢው ሳያሳውቅ ያሇ በቂ ምክንያት ሇአንዴ ወር ያህሌ ምንም ጥሪ ካሌተቀበሇ አቅራቢው ይህንን ውሌ በተናጥሌ መሰረዝ ይችሊሌ፣
6.1.5 ሁሇቱም ወገኖች በፅሁፍ በሚፈጽሙት ስምምነት ውለን ሇማቋረጥ ይችሊለ፡፡
6.2 የውለ ማቋረጥ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ያስከትሊሌ፡-
6.2.1 አገሌግልት ሰጪው በሲስተሙ ሊይ ቀሪ ሒሳብ ካሇዉ ተመሊሽ አይሆንም፣
6.2.2 አገሌግልት ሰጪው ውለ ከተቋረጠ በኋሊ ተመሌሶ አገሌግልት መስጠት ቢፈሌግ 2,150.00 (ሁሇት ሺ አንዴ መቶ ሀምሳ ብር) ሇውለ ማዯሻ የሚከፍሌ ይሆናሌ፡፡
6.3 ስሇ ቅጣት፡- ከዚህ በሊይ ውሌን ስሇማቋረጥ የተጠቀሰው እና በተሇያዩ የትራፊክ ዯንቦች እና ህግጋት የተጠቀሱት እርምጃዎች እንዯተጠበቁ ሆነው፡-
6.3.1 የኪራይ መኪና አገሌግልት ሰጪው የመኪናው ባሇቤትም ይሁን በእርሱ ስር ተቀጥሮ የሚሰራ አሽከርካሪ ከሆነና ከአቅራቢው የፅሁፍ ፈቃዴ ሳያገኝ ሇሚሰጠው አገሌገልት ከጥሪ አገሌግልት አቅራቢው የተሰጠውን የጥሪ አገሌገልት መጠቀሚያ የግሌ አካውንቱን እንዱሁም በራይዴ የተመዘገበ ሲም ካርዴን ሇላሊ ሰው እንዱገሇገሌበት ሰጥቶ ከተገኘ ወይም ይህንን ቴክኖልጂ የታርጋ ቁጥሩ በራይዴ ባሌተመዘገበ መኪና ሊይ ሲጠቀም ከተገኘ ሇአገሌግልት አቅራቢው የሚከተሇውን ቅጣት ሇመክፈሌ ተስማምቷሌ፡፡
6.3.1.1 አገሌግልት ሰጪው ይህንን ዴርጊት ሇመጀመሪያ ጊዜ ከፈጸመ ሇቴክኖልጂ አቅራቢው ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) የመክፈሌ ግዳታ አሇበት፤
6.3.1.2 አገሌግልት ሰጪው ይህንን ዴርጊት ሇሁሇተኛ ጊዜ ሲፈጽም ከተገኘ ሇቴክኖልጂ አቅራቢው ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) የመክፈሌ ግዳታ አሇበት፤
6.3.1.3 አገሌግልት ሰጪው ይህንን ዴርጊት ከሁሇት ግዜ በሊይ ሲፈጽም ከተገኘ ከሊይ በፊዯሌ ሇስር የተቀመጠው ቅጣት የሚከፍሌ ይሆናሌ፡፡ በተጨማሪም የቴክኖልጂ አቅራቢው ዯንበኛውን ሙለ ሇሙለ ከሲስተም በማስወጣት የሚሰርዘው ይሆናሌ፡፡
6.3.2 የኪራይ አገሌግልት ሰጪው የሚጠቀምበት የራይዴ የግሌ አካውንት የተጫነበት ስሌክ በማናቸዉ ምክንያት ቢጠፋና ሇራይዴ ጽ/ቤት በአካሌ ቀርቦ በ48 ሰዓት ውስጥ ባሇማሳወቁና ይህን አካውንት ላሊ ግሇሰብ ሲጠቀምበት ቢገኝ ሇቴክኖልጂ አቅራቢው ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) የመክፈሌ ግዳታ አሇበት፡፡
6.3.3 የኪራይ መኪና አገሌግልቱን የሚሰጠው ተቀጣሪ አሽከርካሪ ከሆነ፤ የመኪናው ባሇቤት ይህ አሽከርካሪ ከርሱ ጋር ያሇው የውሌ ግንኙነት ሲቋረጥ ውለ በተቋረጠ በሰባት ቀናት ውስጥ ሇቴክኖልጂ አቅራቢው በማሳወቅ ግሇሰቡ ቴክኖልጂውን እንዲይጠቀምበት እንዱታገግ ማዴረግ አሇበት፡፡ ነገር ግን የተሽከርካሪው ባሇቤት ይህንን ግዳታውን በተጠቀሰው ግዜ ውስጥ ሳይፈጽም እና አሽከርካሪው ቴክኖልጂውን በላሊ መኪና ሲጠቀም ከተገኘ የመኪናው ባሇቤት ሇቴክኖልጂ አቅራቢው ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ሇመክፈሌ ተስማምቷሌ፡፡
6.3.4 አገሌግልት ሰጪው የቀጠሮ ስራ ተቀብል ቦታው ሊይ በተቀጠረበት ሰዓት እና ቦታ ሳይገኝ ቢቀር የስራውን ግምት ሒሳብ ሇመክፈሌ ተስማምታሌ ፡፡
አንቀጽ ሰባት ሌዩ ዴንጋጌ
ይህ ውሌ ከተፈጸመ በኋሊ ሇጋራ ዯንበኞቻቸው የሚሰጠውን የትራንስፖርት አገሌግልትን በተመሇከተ፣ በተሊያዩ ጊዚያት ከራይዴ ሇአገሌግልት ሰጪው የሚሊኩ የተሇያዩ ዯብዲቤዎች፣ መሌዕክቶች፣ የሚሰጡ መግሇጫዎች እንዱሁም ራይዴ በሚጠራው ስብሰባ ሊይ የሚተሊሇፉ የውሳኔ ሃሳቦች፣ ራይዴ የሚያወጣው የአሰራር ፖሉሲ መመሪያ በ 8202 የሚሊክ የአጭር መሌዕክቶች እና የመሳሰለት የዚህ ውሌ አካሌ ተዯርገው እንዱቆጠሩ ተዋዋዮቹ በሙለ ፍቃዲቸው ተስማምተዋሌ፡፡
አንቀፅ ስምንት
ውለ የሚቆይበት የጊዜ ገዯብና የስምምነት ማረጋገጫ
8.1 ይህ የትራንስፖርት አገሌግልትን በትራንስፖርት ቴክኖልጂ ሇመዯገፍ የተዯረገ የስምምነት ውሌ በሁሇቱ ተዋዋይ ወገኖች መካከሌ በፍ/ሕ/ቁ/1731 መሠረት ሕግ ሆኖ ሊሌተወሰነ ጊዜ ፀንቶ ይቆያሌ፡፡
8.2 እኛ የዚህ ውሌ ተዋዋይ ወገኖች ይህንን ውሌ አንብበንና የውለን ይዘት በሚገባ ተረዴተን በሙለ ፍቃዲችን በዚህ ውሌ በተቀመጡት የስምምነት ነጥቦች ሊይ መስማማታችንን በተሇመዯው ፊርማችን እናረጋግጣሇን፡፡
የተዋዋይ ወገኖችና የምስክሮች ስምና ፊርማ
የአቅራቢው ተወካይ ፊርማ የአገሌግልት ሰጪ (ባሇንብረት) ፊርማ
ስም ስም
ፊርማ ፊርማ
ቀን ቀን
የኪራይ መኪናው አሽከርካሪ ፊርማ (መኪናው የሚሽከረከረው ከባሇቤቱ ውጪ በሆነ ግዜ ብቻ መፈረም ያሇበት)
ስም
ፊርማ ቀን
1ኛ. ምስክር 2ኛ. ምስክር
ስም ስም
ፊርማ ፊርማ
ቀን ቀን
እኛ ስማችንና ፊርማችን ከዚህ በሊይ የተጠቀሰው ምስክሮችም ተዋዋይ ወገኖች በዚህ ውሌ በተገሇጹት የስምምነት ነጥቦች ሊይ በሙለ ፈቃዲቸው መስማማታቸውን በፊርማቸው ሲያረጋግጡ የተመሇከትን መሆኑን በተሇመዯው ፊርማችን እናረጋግጣሇን፡፡
ይህ ውሌ ዛሬ ቀን ዓ.ም አዱስ አበባ _ ክ/ከተማ ሌዩ ቦታው
ተፈረመ፡፡
Technology Service Provided by
8 | P a g e